søndag 27. juli 2014

በርገር የወያኔ አሎሎ – ከሄኖክ የሺጥላ

ከኢትዮጵያ ውጭ በምንኖር ስለ ኢትዮጵያ ዝም ማለት ያቃተንን ኢትዮጵያውያኖች ወያኔ እንደ አሎሎ የሚጠቀምበት በርገርን ነው።ስለ- መብታችን ስንናገር በርገር እየበላህ ነው ፣ ስለ ግፍ ስናወራ በርገር እየበላህ ነው ፣ ስለ አፈና እና ግድያ ስናወራ በርገር እየበላህ ነው ፣ እስክንድር ለምን ታሰረ ፣ ርዮት ትፈታ ፣ የበቀለ ገርባ እስር ኢ’ፍታዊ ነው ፣ እነ አንዱዓለም አራጌ ስለነጻነት፣ ስለ ፍትሕ እና ርትዕ ምክንያታዊ ጥያቄ ነው ያነሱት ማለት ፣ ህውሃትን የጥያቄውን ስር እንዲመለከት ሳይሆን ይልቁንም በተጣመመ አስተሳሰብ ፣ ነገሩን በመጠምዘዝ ” በርገር እየበላህ” ወደሚል ክርክር እና አግቦ መሰል ፍሬ ከርስኪ ወሬ እንዲምዘገዘጉ አድርጎዋቸዋል ።
andargachew Tsege
ለምሳሌ እኔ አማሪካ ነው የምኖረው ፣ የምኖርበት ሀገር ደሞ የራሱ የሆነ የአመጋገብ ባህል አለው ፣ ከዚያ የአመጋገብ ባህል ውጭ ራስን ሙሉ ለሙሉ ነጻ ማውጣት አይቻልም ፣ የዚያ የምኖርበት ሀገር የ ምጣኔ ሀብት ጥንካሬ ፣ የአስተሳሰብ ሆኔታ ፣ ያ የአስተሳሰብ ሁኔታ ያፈለቃቸው መሳሪያዎች ብሎም እነዚህ መሳሪያዎች የሚያመርቱዋቸው ምርቶች ሁሉ ተጠቃሚ መሆን ብርቅ አይደለም ። ለምሳሌ የእጅ ስልኬ በ አፕል የሚሰራው (አይ ፎን) የተባለው ነው፣ ከቤቴ ፊት ለፊት የመዋኛ ገንዳ አለ፣ ሁለት አዳዲስ ሞዴል መኪኖች አሉኝ ፣ በአሜሪካ የኑሮ ደረጃ የመካከለኛ ገቢ እርከን ላይ ካሉት ውስጥ ልመደብ እችላለሁ ፣ ለልጄ በዓመት ለሞግዚት የምከፍለው በአሁኑ የኢትዮጵያ ብር ሲሰላ ከ ሁለት መቶ ሺ ብር በላይ ነው ፣ ማቀዝቀዣዬ ውስጥ ( ለጌጥም ቢሆን እንኩዋ ) ብዙ አይነት መጠጦች፣ ፍራፍሬዎች አሉ ፣ ቅዳሜ ቅዳሜ በል ካለኝ የመርከብ ላይ ጉብኝት አደርጋለሁ ፣ ከፈለኩ የፈለኩትን ጸሐፊ መጽሐፍ ከአማዞን ላይ ገዝቼ ማንበብ እችላልሁ፣ በርገር ብቻ ሳይሆን ፣ ላዛኛ ፣ ሱሺ ፣ ሚት ቦል፣ ስቴክ ፣ ቺክን ክባብ ወዘተ ወዘተ እበላለሁ ። እንግዲህ ይሄ የምኖርበት ሀገር ራስን ለመርሳት የተመቸ ፣ እጅግ በጣም ልብ የሚሰልብ ፣ ቀልብ የሚስብ ፣ በሕልቅ ውበት የተሞላ መንደር ነው ማለት ነው ። ግን ያም ሆኖ ስለ ኢትዮጵያ እጮካለው ፣ ስለ ሀገሬ ዝም አላልኩም ፣ የመጨረሻውን መስዋትነትም ልከፍል መንገዴን ሀ ብዬ ጀምሬያለሁ ።
አንተ ግን እስከ አሁን ከተናገርኩት ፣ እስከ ዛሬም ይሄን ሁሉ ምቾት ጥሶ ፣ ከዚህ ሁሉ ሙቀተ ሕይወት ገዝፎ ስለተናገርኩት ማንነት ፣ ሃገሬ ስለምላት ሀገሬ ስላወራሁት እውነት ሳይሆን በርገር መብላቴ ያስቆጨህ ይመስላል ፣ ያሳዝናል ። ባታውቀው ነው እንጂ እኮ አንተ ያለህበት ሀገር ጨጨብሳ ፣ ስልጆ፣ ክትፎ፣ ዶሮ፣ ሃምባሻ፣ ሕብስቲ፣ ጠላ፣ ጠጅ፣ ቁርጥ ፣ ሸክላ ጥብስ ፣ ተጋቢኖ ፣ አረ ስንቱ ስንቱ አለ መሰለህ ፣ ግን እሱን እንኩዋ እየበላህ አይደለም ። ቢገባህ በርገር እየበሉ ነው የሚሉህ አለቆችህ ፣ እነሱም ከላይ የጠቀስኩትን ምግብ እየበሉ ነው አንተን ወታደር ፣ ድንጋይ ፈላጭ ፣ ህገ መንግሱትን ጠባቂ ፣ ልማታዊ ፣ ሕዳሴያዊ ፣ ገለመኔ ገለመኔ ሁን የሚሉህ። ደሞ በርገር እኮ ምንም የተለየ ነገር አይደለም ፣ በ ዘይት የተጠበሰ ሙዳ ስጋ ነው ፣ ታዲያ ሙዳ ስጋ ኢትዮጵያ የለም? አለ ! አንተ ግን አይተኸው ታውቃለህ ? አታውቅም ፣ ምክንያቱም በርገር እየበሉ የሚሉህ አለቆች ወጥ አርገው እየበሉት ስለሆነ አንተን አይታይህም። አየህ በርገር በ ቀይ ወጥ መልክ እየበሉ ፣ በርገር በክትፎ መልክ እየበሉ ፣ በርገር በጥብስ መልክ እየበሉ ፣ አንተን ድንጋይ እያስፈለጡ ፣ ወታደር አርገው ጸሓይ እያሥቀጠቀጡ ፣ በርገር እየበሉ ይሉሃል ። እኔ ዝም ብል ምን የማጣ ይመስልሃል ( እንደው ቁም ነገሩ ለራስ መሆን፣ ለራስ መኖር ከሆነ )፣ ምን እንዳይጎልብኝ ነው ስላንተ የምጮኸው? ምን እንዳላጣ ። ከገባህ ነጻነት የምግብ ጥያቄ አይደለም ፣ ግን የምግብ ጥያቄ ነጻነት በሌለው ስርዓት ውስጥ የሚጠየቅ ጥያቄ እንጂ። አየህ እኔ በርገር እየበላሁ ዝም ብዬ መተኛት አልቻልኩም ፣ ያንተ ቁርጥ አለመብላት አሳስቦኛል ማለት ነው ፣ የሀገሬ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አስጨንቆኛል ማለት ነው ፣ መናቅ አብሽቆኛል ማለት ነው ።
እስኪ ማን ይሙት ስለ ሀገር መጮህን በርገር ከመብላት ጋ ምን አገናኘው ? ወይስ ባዶ ሆዳችሁን ተቃወሙን እያሉ ነው ያሉት ? አልገቡኝም ፣ አይገቡኝም ። ጉራ ፈርዳ ላይ ስለተፈናቀሉት ዘመዶቼ መናገር በርገር ከመብላት ጋ ምን ያገናኘዋል ፣ የኦሮሞ ገበሬን መሬት በግፍ መቀማት አግባብ አለመሆኑን ማጋለጥ ከበርገር ጋ ምን ያገናኘዋል ፣ እስክንድር ነጋ እኮ የታሰረው ማክዶናልድ ዘይት ሰርቆ አይደለም፣ የአንዱዋለም ጥያቄ ጃክ እን ዘ ቦክስ ወይም ኬ-ኤፍ-ሲ አስቀጥሩን የሚል አልነበረም፣ ርዮት አለሙ እኮ የታሰረችው ፣ ቀኑ ያለፈበት ምግብ ( በርገር ) ስትሸጥ አይደለም ፣የሕዝበ ሙስሊሙ የመጅልስ ጥያቄ ከበርገር ጋ ምን አገናኘው ? አቡበከር የጣልያን ባሬስታ ልሁን እኮ አላለም፣ የጣልያን እንቁላል አዙዋሪ ልሁን አላለም ! ብሎዋል እንዴ? ማወቅ ከፈለክ ይህንን ጽሑፍ ስጽፍም ፒዛ እየበላሁ ነሁ ( ፒዛ ማለት ምን ማለት መሰለህ ፣ ጨጨብሳ ታውቃለህ ፣ ወይም ፈታ አዋ በቃ እሱ ነው )፣ እመነኝ እንጀራ ስበላ ግን ወያኔን ውሃ ውሃ የሚያስብል ግጥም ነው የምጽፈው ! ደሞ ተጋዳላይ ለመሆን የግድ አንበጣ መብላት ፣ ድንጋይን እንደ ግብር ውሃ መጠቀም ፣ ሰውነቴ ላይ ቅማል መፍላት አለበት ብለህ አታስብ ፣ መሆን ሲኖርበት ደሞ እናደርገዋለን ፣ እመነኝ ቅማል ብርቄ አይደለም ፣ ከቅማላሞች ጋ 20 ዓመት ኖረያለሁ ! ታዲያ ምንደን ነው ይሄ በርገር እየበሉ ፣ በርገር እየበሉ ።
ይቺ ” በርገር እየበሉ ” የወያኔ አሎሎ ናት ፣ ግን ወንጭፍ የሆንከው አንተ ነህ ፣ እስቲ ረጋ ብለህ አስበው ፣ እኔ ለምን እጮኸለው ? ታማኝ ለምን ይጮሃል ፣ እያሱ አለማየሁ ለምን ይጮሃል? ብርሃኑ ነጋ ለምን ይጮሃል ? ሲሳይ አጌና ለምን ይጮሃል ? መሳይ መኮንን ለምን ይጮሃል ? ተክሌ የሻው ለምን ይጮሃል ? ቡልቻ ደመቅሳ ለምን ይጮሃል ? አበበ ገላው ለምን ይጮሃል ? ( ልዩነታችን እንዳለ ሁኖ፣ ሲገባኝ ይሄ ሁሉ ሰው ግን የሚጮኸው የሚቀጥለው ወር የበርገር አገልግሎት እንዳይቁዋረጥ ብሎ አይመስለኝም

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar