fredag 22. november 2013

ዲፕሎማቱ በትዕዛዝ ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች ወዳልታወቀ ስፍራ ሰደዱ 12ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ 200 ስደተኞች የደረሱበት አልታወቀም


saudi ethio11
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ይገኙ የነበሩ 12 ነፍሰ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 በላይ ስደተኞች በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ወዳልታወቀ ስፈራ ተወሰዱ ።
በሪያድ ልዩ ስሙ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰሞኑንን የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ አያሌ ወግኖቻችን መገደላቸው እና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችን ህይወት አስከፊ ገጽታ ላይ ባለበት ሁኔታ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ከአንድ አመት በላይ ተጠልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው እነዚህ ወገኖች ወዳልታወቀ ስፈራ መወሰዳቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል።
አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል ራሳቸውን ለመታደግ ቀደም ብለው ወደ ኮሚኒቲው ግቢ እንደመጡ የሚነገርላቸው እኚህ ወግኖች፤ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ጉዳዩቻቸውን ተከታትለው ሊያስፈጽሙላቸው ባለመቻሉ በተጠቀሰው የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በሚገኝ አንድ ኮንቴነር ውስጥ ሲሰቃዩ መኖራቸውን የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል። ከ12 በላይ ነፍሰጡሮች እና የአእምሮ በሽተኞችን ጨምሮ ከ200 በላይ ስደተኞች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ያለምንም የህክምና እርዳታ ሲሰቃዩ ከከረሙት እህቶቻችን ውስጥ 3ቱ በሞት መለየታቸውንና 5ቱ ለአእምሮ ጭንቅት መዳረጋቸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ልብ የማይጠፋ መሪር ሃዘን መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሰሞኑንን መንፉሃ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንደ ገባ ለሚነገርለት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልኡካን ቡድን ገበናችንን ያጋልጣሉ በሚል ስጋት ዲፕሎማቱ እነዚህን ወገኖቻችንን ወደ አልታወቀ ስፍራ በአውቶብስ ጭነው መውሰዳቸው ታውቆል።
ስደተኞቹ ያሉበት ሁኔታ እስካሁን በውል እንደማይታወቅ የሚናገሩት የሪያድ ምንጮች ምናልባት ወደ አገራቸው ለመግባት ለፖሊስ እጅ ሰጥተው በየጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ከሚሰቃዩ ወገኖቻችን ጋር ቀላቅሎዋቸው ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ያጠናክራሉ። ዲፕሎማቱ የሚፈሩት ነገር ከሌለ በቀር እነዚህ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ኮኔትንር ውስጥ ላለፉት ወራት ያሳለፉትን የችግር እና የመከራ ጊዜያቶች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዳዩቻቸውን ባሉበት በማስፈጸም ወደ ሃገር በመላኩ ረገድ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ። ዲፕሎማቱ የፈጸሙት ድርጊት ወገናዊነት የጎደለው መሆኑን የሚገልጹ ምንጮች የተጠቀሱት እህቶቻችን ኮሚኒቲው መጠለያ ግቢ ውስጥ በነበሩባቸው ጊዜያቶች አንዳንድ እህቶቻችን ተመርጠው በዲፕሎማቱ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል ሽፋን ማታ ማታ ከማደሪያ ኮንቴነር ክፍላቸው እየተጠሩ እዛው ኮሚኒት ግቢ ውስጥ በሚገኝ አንድ ጽ/ቤት ውስጥ ለሰአታት ቆይተው ይወጡ እንደነበር በማስታወስ በእህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት ሳይፈጸምባቸው እንደማይቀር ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ።
እንዲህ አይነት አስጸያፊ ድርጊት አልፎ አልፎ የሚሰማ መሆኑንን የሚገልጹ ወገኖች በሪያድ አንዲት ኢትዮጵያዊት ወጣት ላይ መከስቱን ተከትሎ ኮሚኒቲው አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ወጀለኛውን ፍ/ቤት በማቆም 60 ሺህ ሪያል ካሳ እንዲከፍል ማስወሰናቸውን የሚያወሱ አንድ አባት፤ ጉዳዩን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከታትሎ እንዲያሰፈጽም አደራ ቢሰጡም ሃላፊነቱን በብቃት ሳይወጣ በመቅረቱ ወንጀለኛው ከእስርቤት ተለቆ ተበዳይ እህት ሰሞኑንን ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር ወዳልታወቀ ስፍራ እስከተወስደችበት ጊዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቴ ግቢ ውስጥ በህመም ስትሰቃይ እንደነበር እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በሚገኙ እህቶቻችን ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መሞከሩን የሚናገሩ የአካባቢው ምንጮች አንዲት ወጣት በቆንስላው ጽ/ቤት ዘበኛ ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባት ጉዳዩ ፍ/ቤት ደርሶ እንደነበርና በቆንስላው የመንግስት ባለስልጣኖች ተድበስበሶ መቅረቱ የሚያስታውሱ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ጊቢ ይኖሩ ከነበሩ ስደተኞች ውስጥ የ12ቱ ነፍሰ ጡር እህቶቻችን ጉዳይ ሳይጣራ ሰሞኑንን በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ ከኮሚኒቲው ግቢ ባስቸኳይ እንዲለቁ መደረጉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጥርጣሬ የበለጠ ያጠናክረዋል ብለዋል።
Ethiopian Hagere በፌስቡክ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከጅዳ በዋዲ የላኩት

ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ


የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ
obang-o-metho-hearing
በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡
ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
“አልዘገዩም” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “አኢጋን ችግር በተከሰተ ቁጥር የሚቋቋምና የሚፈርስ የዕቁብ ይዘት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ወይም እሣት ሲነሳ ድምጽ እያሰማ እንደሚከንፍ የእሣት አደጋ መኪና የሚመሰል ድርጅት አይደለም” በማለት የጋራ ንቅናቄውን የተጠና አካሄድ በመጠቆም የመለሱት አቶ ኦባንግ ይህ ችግር እንደሚከሰት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
ችግሩ አስቀድሞ እንደሚከሰት ቢታወቅም ምላሽ የሚሰጥ ብቃት ያለው አካል ባለመኖሩ አንገት የሚያስደፋና ኃፍረት የሚላብስ፤ “አገር አለኝ ወይ?” የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ኃፍረት ሊደርስብን ችሏል፡፡ “ይሁን እንጂ” አሉ ኦባንግ “ይህ መራር ዜና ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የጋራ ንቅናቄው የበኩሉን” ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡
“ከተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ አግባብ ካላቸው መንግሥታዊ አካላትና በተለያየ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረናል” በማለት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ ለዓብነት ያህልም የሳዑዲ ም/ጠ/ሚ/ር እና የመከላከያ ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፍትሕ ሚ/ር እና ሌሎች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የመንግሥት መ/ቤቶችን ጨምሮ በአውሮጳና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን የሳዑዲ ኤምባሲዎችን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርን፣ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ACHPR)፣ ወዘተ ማነጋገራቸውንና በየደረጃውም ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል፡፡
በመላው የመካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዕረፍት የሚሰጥ እንዳልሆነ የጠቆሙት “ጥቁሩ ሰው” ሳዑዲ ካላትና ከምትከተለው “የበርህን ዝጋ ፖሊሲ” አንጻር በአካል በቦታው ላይ ከመገኘት ይልቅ አቅም ካላቸው ዓለምአቀፋዊ አካላት ጋር በአፋጣኝና በቅርበት መሥራቱ ድርጅታቸው የወሰደው አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሎጂስቲክሱ ጉዳይ መስመር ሲይዝም የጋራ ንቅናቄው ከዚህ በፊት በየአገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ሲያስፈጽምበት የነበረውንና በውጤታማነቱ የሚታወቀውን አማራጭ እንደሚተገብር ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ኢህአዴግ አገርን እንደሚያስተዳድር ድርጅት በዜጎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን አስነዋሪ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ አለመመከቱ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ወገኖቻችንን ድንበር በማሻገርና ኤጀንሲ ከፍተው ወደ አረብ አገራት ሲልኩ የነበሩት ሁሉ ሕግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የተለያዩ ተግባራት” እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
alamudi-ሼክ መሐመድ አላሙዲ የሠራተኛ ኃይል ወደ ሳዑዲ እንዲላክ ከኢህአዴግ ጋር በይፋ ስምምነት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ከሚፈልጉበት ክልል መሬት ለመውሰድ፣ ከሚፈልጉበት ባንክ ኮሪደር ገንዘብ ለመበደር ገደብ የሌላቸውና በሞቀበት ሁሉ ባለመጥፋት በጀት መድበው በሚያስተዳድሯቸው ሚዲያዎች እንዲሁም አንደበታቸውን በሙስና ላሰሯቸው ባለሥልጣናት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” እያሉ በተገኙበት ቦታ ሁሉ ለሚዲያ ፍጆታ የሚደሰኩሩትና ግጥም የሚያስደረድሩት ሼክ መሐመድ አላሙዲ፣ “ወገኔ” የሚሉት ሕዝብ በአባታቸው አገር ወሮበሎች ሲያልቅና ሲጨፈጨፍ ዝም ማለታቸው ኢንቨስትመንቶቻቸውን ጥያቄ ውስጥ ከትቷል፡፡
አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ አሰቃቂ ድርጊት መስመር ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት የሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን ከርስ እንዲሞላ በኢትዮጵያ የተቋቋመው ሳዑዲ ስታር ኩባንያ በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ እንደሚችል መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ ሳዑዲ ስታር በኪሣራ ወደ መዘጋት መድረሱ የኩባንያው “ባለቤት የሆኑትን ሼክ ሙሐመድ አል አሙዲንና የሳዑዲ ዓረቢያን ስም የሚያጎድፍ ከመሆኑም ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪታክት የተወራለት ይህ ፕሮጀክት መና መቅረቱ ሁለቱን አካላት በሕዝቡ ዘንድ ለከፍተኛ ትችትና ወቀሳ እንደሚያጋልጣቸውም” ጠቁሞ ነበር፡፡
mohammed bin nayef
ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ
በአሁኑ ጊዜ “ሕገወጥ ናችሁ” በሚል ሰብዓዊነት የጎደው እርምጃ እየተወሰደባቸው ያለው የበርካታ አገራት ዜጎች በተለይም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመውን ሰቅጣጭ ተግባር ሕገወጦችን የማባረር “ዘመቻ” በማለት ያቃለሉት የሳዑዲው አገር ውስጥ ሚ/ር ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ ወንጀለኛ ሬንጀር ለባሾችን፣ ፖሊሶችንና ወሮበሎቹን ሸባቦች አደፋፍረዋል፡፡ “ዘመቻው ይቀጥላል … በተወሰነ ጊዜ የተገደበ አይደለም” በማለት “እስክንጨርስ እንጨርሳችኋለን” የሚመስል የማፊያ መሪ መሰል መልዕክት ለአንጋቾቻቸው አስተላልፈዋል፡፡
አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በሕጋዊነት የሚኖሩትም ጭምር በሳዑዲ ያለው ሁኔታ አሳሳቢነት ወደፊት ችግር ውስጥ ሊከትታቸው እንደሚችል በመገመት ወደ አገራቸው መመለስ ይፈልጋሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ሰቆቃ የተጋለጡት ኢትዮጵያውያን “ቤት አለን ቤታችን መልሱ” እያሉ የሰቆቃና የድረሱልን ጥሪ በሚያስተላልፉበት ወቅት ሰብዓዊነት የጎደላቸው የኢህአዴግ መሪዎች ይህ ነው የሚባል አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለመቻላቸው “በእርግጥ ኢትዮጵያውያን አገር አላቸው?” ብሎ የሚያስጠይቅ እንደሆነ በርካታዎች የሚጋሩት ነው፡፡
አቶ ኦባንግ በበኩላቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአንድ ሳምንት ሥራውን አቋርጦ እንኳን ቢሆን ስደተኞቹን ባፋጣኝ የማመላለስ ተግባር መፈጸም ይገባው ነበር በማለት ቁጭታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ህይወታቸው እየተቀጠፈ “3ሺህ ዛሬ ገቡ … ድምሩ 10ሺህ ሆኗል …” የሚል የሞላ ጎደለ ቁማር ዓይነት ጨዋታ በትዊተር መጫወት የቴድሮስ አድሃኖምን ዘመነኛነት ሳይሆን ለሰውልጅ ህይወት ያላቸውን ደንታቢስነት የሚያሳይ መሆኑን ሁኔታው ያስቆጣቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ኦባንግም “ቤቴ መልሱኝ” ብሎ ለሚለምን አንድ ዜጋ የተከፈለው ተከፍሎ ትራንፖርት በማቅረብ ክቡር ህይወትን በአስቸኳይ ለመታደግ አለመቻል ለትውልድ የሚተላለፍ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡

torsdag 21. november 2013

በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጐሜዝ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው


Photo: © Europen Parliament/P.Naj-Olearipietro.naj-oleari@europarl.europa.eu
በ1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫና ምርጫውን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው የፖለቲካ ውዝግብ አካል የነበሩት የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ አና ጐሜዝ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በ1997 ዓ.ም. ተካሂዶ የነበረውን ምርጫ በአውሮፓ ኅብረት ተወክለው ምርጫውን በዋና ታዛቢነት የመሩትና የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባል የሆኑት አና ጐሜዝ፣ ምርጫውን አስመልክቶ ባወጡት ሪፖርት ኢሕአዴግ ከሚመራው መንግሥት ጋር ጥልቅ የሆነ ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡
አና ጐሜዝ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በምርጫው ሳቢያ ውዝግብ ከገቡበት ጊዜ አንስቶ የኢሕአዴግን ፖለቲካ በተለይም የሰብዓዊ መብት አያያዙን ከመተቸት ተቆጥበው አያውቁም፡፡ ይሁን እንጂ ከምርጫው በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አያውቁም፡፡
በሚቀጥለው ሳምንት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ፣ የካረቢያንና የአውሮፓ ኅብረት አገሮች የጋራ የፓርላማ አባላት ጉባዔ ላይ ለመገኘት በአገሮቹ ከተወከሉ ግለሰቦች መካከል አና ጐሜዝ እንዳሉበት በኢትዮጵያ በኩል anaየጉባዔው አስተባባሪ ከሆነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምንጮቻችን ለመረዳት ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ለፖርቹጋላዊቷ የፓርላማ ተወካይ አና ጐሜዝ ቪዛ ሰጥቶ ይሁን ከልክሎ ለማወቅ ያደግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ ግለሰቧ በቲዊተር ገጻቸው ላይ በአዲስ አበባው ጉባዔ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል፡፡ አና ጐሜዝ በ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ምርጫ ትዝብት ሪፖርታቸው፣ ምርጫው ነፃና ፍትኃዊ እንዳልነበር ሪፖርት በማድረጋቸው ሪፖርቱ የውዝግቡ ምንጭ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሪፖርቱን ከማጣጣል አልፈው ግለሰቧን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ መዝለፋቸው ይታወሳል፡፡
አና ጐሜዝ በበኩላቸው እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የዕርዳታ ማዕቀብ እንዲጣልበት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ‹‹ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ በተለይም የእንግሊዝና የአሜሪካ መንግሥታት በኢትዮጵያ ዜጎች ላይ መንግሥት የሚፈጽመውን በደል እያዩ እንዳላዩ፤ እየሰሙ እንዳልሰሙ ችላ ብለዋል፤›› በማለት ከዓመት በፊት የሰላ ትችት በመሰንዘር የአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያ የሚደረገውን ዕርዳታ እንዲያቆም ተከራክረዋል፡፡ (ሪፖርተር)

Ethiopians protest in Aotea Square


November 21, 2013
The New Zeland Herald
New Zealand outside the Saudi Arabian Consulate in Auckland
Teklay Zinaw protests alongside fellow Ethiopians in New Zealand outside the Saudi Arabian Consulate in Auckland denouncing Saudi Arabian crimes against their people. Photo / Richard Robinson
About 100 Ethiopians gathered in Auckland’s Aotea Square this afternoon for a lunchtime rally to protest against Saudi Arabian “crimes” against Ethiopians.
Saudi authorities last week began a clampdown on illegal migrant workers which led to clashes in its capital, Riyadh, where at least five people have been killed.
“Ethiopians in Auckland hereby demand the immediate halt of the barbaric act in general, the killings, the gang-rape and mistreatment,” a statement distributed at the protest said.
“We are shocked by the atrocities, cruelty, killings, rape and beatings of Ethiopian immigrants by Saudi security forces and police-backed thugs called shebab.”
Ethiopia’s Foreign Affairs Minister Tedros Adhanom said he had information that three Ethiopian citizens had been killed in the clashes.
But Saudi authorities said three Saudis were among the dead, along with two foreign nationals.
The Auckland protest was part of rallies held worldwide against the attacks, with demonstrations in Switzerland, the UK, Norway and the US.

tirsdag 19. november 2013

ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ ምክንያትና መፍትሄዎች ዶ/ር ያቆብ ኃ/ማሪያም


Image
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :- ባለፈው እሁድ ህዳር 8 ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ለመቃወም ያወጣውን መርሃ ግብር መዝጊያ ላይ እውቁ የዓለም አቀፍ ህግ ምሁር ዶክተር ያቆም ኃ/ማሪያም በታጋባዥ እንግዳነት ተገኝተው ነበር፡፡ በወቅቱ ዶ/ክተሩ ያደረጉትን ንግግርም በስነ ስርዓቱ ላልተገኙት ይደርስ ዘንድ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡ ምንም እንኳ ያለፉት 20 አመታት የሰቆቃና የውርደት አመታት ቢሆኑም ሳውዲ ውስጥ በሚገኙት ወገኖቻቸን የደረሰው ግን በ1977 በኢትዮጵያውያን ላይ ከደረሰው ርሃብና ውርደት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡(ምንሊክ ሳልሳዊ)በዚህ ችግር ሳውዲ አረቢያ ያሉት ብቻ ሳይሆን አገር ውስጥም ሆነ በሌላው አለም ያለነው ኢትዮጵያውያን ተደፍረናል፡፡

አገራችንም ቢሆን ተደፍራለች፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ባሉት ዘመናት ከውርደት የታደጓት ትውልዶችን አይታለች፡፡ ይህ በተለይ ለዘመኑ የኢትዮጵያ ትውልድ አሳፋሪ ውርደት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ሳውዲ ስላለው የምናወራው ግልጽ ሆኖ ስለወጣ እንጅ ውርደቱ እጅግ መጠነ ሰፊ ነው፡፡ ለአብነት ያህል 23 እስረኞች በዛምቢያ እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ በታንዛኒያ 50፣ በማላዊ ደግሞ 25 ኢትዮጵያውያን ህዝብ፣ መሪና አገር እንደሌላቸው በእስራት እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ አገሪቱ በገጠማት ችግር ምክንያት በስደት ላይ እያለ በርሃብ የሞተውን፣ ውሃ ውስጥ የቀረውን፣ በአውሬ የተበላውንና በሌላም ችግር ነፍሱን ያጣውንና የተሰቃየውን ደግሞ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ በሌሎች አገራት እንዲህ አይነት ችግር ታይቶ ወይንም ተስምቶ አይታወቅም፡፡ ለምን የኬንያና የታንዛኒያ ህዝቦች እንዲህ አይነት ችግርና ውርደት አይገጥማቸውም? ኢትዮጵያ ከሌሎች አገራት የተሻለ ሀብትና ህዝብ አላት፡፡

ሰፋፊ መሬቶች አሉን፡፡ ወንዞች አሉን፡፡ እንዲያውም የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ተብላ ትጠራለች፡፡ የምስራቅ አፍሪካም ሆነ የአህጉሩ የውሃ ማማ ትባላለች፡፡ ህዝቡን ከሌላው አገር ህዝብ ጋር ሲነጻጸር ትሁት ቢሆን እንጅ ሰነፍ አይደለም፡፡ ከአፍሪካዋ ደቡብ አፍሪካ ጀምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሰርተው የማይጠግቡ ናቸው፡፡ እንዲያውም በደቡብ አፍሪካና በእነዚህ አገራት ኢትዮጵያውያን የትላልቅ ህንጻዎች፣ የንግድ ድርጅቶችና የሌሎች ሀብቶች ባለቤቶች ናቸው፡፡ አገር ውስጥ ምቹ ስርዓት ባለመኖሩ ምክንያት ግን ህዝቦች አገራቸው ላይ ሰርተው ከመኖር ይልቅ ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያልተማሩት ብቻ ሳይሆኑ የተማሩትም በከፍተኛ ደረጃ እየተሰደዱ ነው፡፡ በምሁራን ፍልሰት ኢትዮጵያ ቀዳሚ አገር ሆናለች፡፡ ስለሆነም አገር ውስጥም አላሰራ ያለው፣ ለስደቱም ምክንያትና በስደተኞቻችንም ሆነ በአገራችን ላይ እየደረሰ ለሚገኘው ስቃይ ዋነኛው ምክንያት ስርዓቱ ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራቸው ‹‹የዚህ ብሄር አባል አይደለህም ውጣ›› ተብለው ከተባረሩ አገራችን ብለው ከመኖር ይልቅ ስደትን ይመርጣሉ፡፡ ለበርካታ አመታት ተምሮ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀ ወጣት የፓርቲ አባል ስላልሆነ ብቻ ስራ አታገኝም ከተባለ እጣ ፈንታው ስደት ነው የሚሆነው፡፡ እትብቱ የተቀበረበትን መሬት በሲጋራ ዋጋ አሁን ህዝቦቻችንን ለሚያሰቃዩት ሳውዲዎች አሳልፎ ሲሰጥበት ህዝብ ከስደት ውጭ ምን አማራጭ ይሆረዋል?

መንግስት የሌለው ህዝብ ሳውዲዎች በህዝቦቻችን ላይ የፈጸሙት በደል በተጎጅ ወገኖቻችን፣ በቀሪው ህዝብና በአገራችን ላይ የተቃጣ ብቻ አይደለም፡፡ የአገሬው ሰው ‹‹ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ›› እንዲሁ መንግስት ነኝ ብሎ የተቀመጠውን አካልም እንደ መንግስት ስለማይቆጥሩትና ስለሚንቁት የፈጸሙት ተግባር ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ኢህአዴግ እንደ መንግስት ለኢትዮጰያ ህዝብ እንደማይጨነቅም ህዝብ ሲበደል ምንም ደንታ እንደሌለው አሳምረው ያውቃሉ፡፡ የሌሎች አገራት መንግስታት ግን ለዜጎቻቸው ከፍተኛ ጥበቃና ለሚደርስባቸው ችግርም ተገቢውን ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል በአንድ ወቅት አንድ ፓኪስታናዊ ቦሌ አገር ማረፊያ ሲገባ ኢትዮጵያዊው ልጅ ስለያዝኩ ደብተር ያዝልኝ ይለዋል፡፡ ፓኪስታናዊውም ይተባበረዋል፡፡ ይሁንና ደብተሩ ውስር 90 የሚሆኑ ሲም ካርዶች ነበሩት፡፡ ፖሊሶቹም ይህን ፓኪስታናዊ ያስሩታል፡፡ ፓኪታናዊያንም ዜጋቸው መታሰሩን በመግለጽ እንዳስፈታላቸው ይጠይቃሉ፡፡ ከፓኪስታን ኤምባሲ ጋርም መረጃ ተለዋውጠናል፡፡ ይህ ፓኪስታናውይ ተፈትቶ አገሩ ከገባ በኋላ ሳይቀር ኤምባሲው እየደወለ ጉዳዩ ምን ላይ እንደደረሰ ይጠይቀኝ ነበር፡፡ በቡሽ አስተደደር ዘመን ወደ ሰሜን ኮሪያ ዘመዶቿን ልትጠይቅ የሄደች አሜሪካውይት ሰላይ ነሽ ተብላ ትታሰራለች፡፡ ለዚህ አሜሪካው መፈታት እንዳለባት ፕሬዝደንት ክሊንተን ተነሳሽነቱን ይወስድና ለቡሽ አስተዳደር ያቀርብለታል፡፡ በስተመጨረሻ ፕሬዝደንት ክሊንተን ይችን አሜሪካውይንት ሰሜን ኮሪያ ድረስ ሄዶ አስፈትቷታል፡፡ በ1960ዎቹ ፍልስጤማውያን በርካታ አውሮፕላኖችን የሚጠፍፉበት ወቅት ነበር፡፡ ከዚህ መካከል አንዱ ዩጋንዳ ውስጥ የተደረገው ጠለፋ ነው፡፡ የኢንተቤው ክስተት በሚባለው በዚህ ጠለፋ ፍልስጤማውያን ከጠለፉት አውሮፕላን ውስጥ አንዲት እስራኤላዊ አሮጊት ነበሩበት፡፡ ለዜጎቹ የሚጨነቀው የእስራኤል መንግስትም አስራ ሁለት አውሮፕላን ይህችን አሮጊት የሚያስለቅቅ ቡድን ላከ፡፡ ይህ ቡድን በስተመጨረሻ ጠላፊዎቹን ገድሎ አሮጊቷን አድኗል፡፡ ይህን ‹‹ኦፕሬሽን›› የመሩት የአሁኑ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሆ ናቸው፡፡ የጓትማላ ሁለት ዜጎች ወደ ችሊ ባቀኑበት ወቅት ይሞታሉ፡፡ እነዚህን ዜጎች የደረሰውን ችግር ተከትሎም የጓትማላው ፕሬዝደንት ችሊ ድረስ አቅንተው የሁለቱን ዜጎች አስከሬን ይዘው በመምጣት አገራቸው ውስጥ እንዲቀበሩ አድርገዋል፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ ይህን ያህል ሰቆቃ ሲደርስ ግን ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ምንም አላሉም፡፡ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ተደርጎ እንዲውለበለብ አልተደረገም፡፡ የሀዘን ቀን እንዲኖር አልተደረገም፡፡ ይልቁንስ በወገኖቻቸው ላይ የደረሰውን ችግር ለማጋለጥ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡትን ኢትዮጵያውያን በጨካኝነት ደብድበዋል፤ አስፈዋል፡፡ ኢህአዴግ ለምን ይህን አደረገ? አስራኤሎች አንዲት አዛውንት ላይ የደረሰን ችግር አስራ ሁለት አውሮፕላን በማሰለፍ ለህዝበባቸው ምን ያህል እንደሚጨነቁ አሳይተዋል፡፡ የጓትማላው ፕሬዝዳንት የሁለቱን ዜጎቹን አስክሬን እራሱ በማስመጣት አገራቸው ውስጥ እንዲቀበሩ አድርጓል፡፡ ቢል ክሊንተን ሰሜን ኮሪያ ድረስ በማቅናት እንድትፈታ አድርጓል፡፡ ሳውዲ አረቢያ የእኛዎቹን ዜጎች እየገደለችና፣ እያሰቃየች ግን ኢህአዴግ ምንም እርምጃ አልወሰደም፡፡ እንዲያውም በራሳቸው ተነሳሽነት ለዜጎቻቸው አለኝታ ለመሆን የተነሱት ላይ እርምጃ በመውሰድ ለኢትዮጵያውያን ያለውን ንቀትና ጥላቻ አሳይቷል፡፡ ይህ ለምን ሆነ? በአገራችን ዴሞክራሲያዊና የህዝብ ምርጫ የለም፡፡ ይህም ማለት ህዝብ መንግስትን የማውረድና ስልጣን ላይ የማውጣት ስልጣን የለውም ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ኢህአዴግ ይህ የማይጨነቅለት ህዝብ በምንም መልኩ ከስልጣኑ ሊያወርደው እንደማይችል ስለሚያውቅ ምንም አይነት በደልና ሰቆቃ ቢደርስበትም ደንታ ቢስ መሆንን መርጧል፡፡ ከምርጫ ባሻገር ነጻ ፍርድ ቤትም አለመኖሩ ኢህአዴግ ራሱ በሚያስቀምጣቸው አካላትና በአባላቱ በሚመራው ፍርድ ቤት ምክንያት ምንም እንደማይደርስበት ያውቃል፡፡ ነጻ ፍርድ ቤት ቢኖር ኖሮ ኢህአዴግ ህዝብ በሚደርስበት ማንኛውም ጉዳይ በቀዳሚነት መቆም እየነበረበት ቸልተኛ በመሆኑ ሊያስቀጣው ይችል ነበር፡፡ ይህ ባለመኖሩ ምንም ችግር እንደማይደርስበት ያውቃል፡፡ በአገራችን ነጻ ሚዲያ አለመኖሩም ሌላኛው ምክንያት ነው፡፡ ነጻ ሚዲያ መንግስታት መንግስታት በህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በድል፣ መውሰድ ያለባቸውን እርምጃና ሌሎች መረጃዎችን በመስጠት ህዝብን ያነቃል፡፡ ኢህአዴግ ይህን ቸልተኝነቱን ለህዝብና ለዓለም ማህበረሰብ የሚያጋልጥ አማራጭ ሚዲያ ባለመኖሩ የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ ምንም ሊመስለው አይቻለም፡፡ ኢህአዴግ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያውያን ላይ ይህን ያህል ከፍተኛ በደልና ሰቆቃ እየደረሰ፣ አገራችን እየተዋረደች እንቅልፍ ሊወስደው አይችልም ነበር፡፡ በመሆኑም የአንድ አገር ህዝብ የሚቨነቅለትና የሚቆምለት መንግስት ሊያገኝ የሚችለው ዴሞክራሲን ከገነባና መንግስቱን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለስልጣን ካበቃ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ለኢትዮጵያውያን ሰቆቃ መሰረታዊ መፍትሄው ዴሞክራሲን ማስፈን ብቻ ነው፡፡ ሳውዲ ውስጥ እየተደረገ ያለውን ሰቆቃ በመቃወም የወጡት ኢትዮጵያውያን ላይ መንግስት የወሰደው እርምጃ አሳፋሪ ነው፡፡ ዜጎቹ ያነሱት ጥያቄ ኢህአዴግ ከሚፈራቸው ፖለቲካውይም ሆነ ሌሎች ጥያቄዎች የተለዩ ናቸው፡፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ አንግበው የወጡት የሀይማኖት ጥያቄ ይከበር የሚል አልነበረም፡፡ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱም አላሉም፡፡ ጋዜጠኞች ይፈቱ የሚል ጥያቄ ያነሳም አልነበረም፡፡ ይሁንና ከኢህአዴግ ስልጣን ጋር የማይገናኝና ጥያቄን ያነሱትን ዜጎች ሳውዲ ላይ እንደደረሰው የሰቆቃው ሰለባ ሆነዋል፡፡ ምን ይደረግ? ሳውዲ አረቢያ አባል ከሆነችባቸው ትቂት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል ዓለም አቀፍ የሰላተኞች ድርጅት (ILO) አባል ነች፡፡ በዚህ ድርጅት መርህ መሰረት ሰራተኞችመብት መከበር ይኖርበታል፡፡ በተለይ ለሴቶች፣ ለህጻናትና ከአገራቸው ርቀው ለሚገኙ ሰራተኞች ትልቅ ጥበቃ ይሰጣል፡፡ አንድ አባል አገር እነዚህን መብቶች ከጣሰና በሰራተኞች ላይ ችግር ከደረሰ በተቋሙ በኩል መክሰስ ይቻላል፡፡ ምንም እንኳ ሳውዲ አረቢያን ማስቀጣት ባይቻልም ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ማሳጣትና ማሳፈር እንዲሁም በሚቀጥሉት ጊዜያት ተመሳሳይ እርምጃ እንዳይወስዱ ማድረግ ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ አገራችን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን የፈረመችው እ.ኤ.አ በ1948 ነው፡፡ ከሀይቲ ውጭ ሌላ የጥቁር ህዝቦች መኖሪያ አገር ይህን ህግ በወቅቱ አልፈረመም፡፡ ሌሎች ህጎችን በመፈረምም ኢትዮጵያ ቀዳሚ አገር ነች፡፡ ባለፉት 20 አመታት ግን ህግን በመጣስና ከዓለም አቀፍ ተቋማት በመራቅ ከሚገኙት አገራት መካከል ቀዳሚዎቹ ጋር ተመድባለች፡፡ ዜጎቻችን እያሰቃየች የምትገኘው ሳውዲ በንጉሳዊ ስርዓት የምትመራ በህግ በኩል ኋላ ቀር አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ልክ እንደ ሳውዲ አረቢያ ሁሉ የጦር ወንጀለኞችን ፍርድ ቤት አባል ያካልሆኑ ጥቂት አገራት መካከል አንዷ ነች፡፡ ሳውዲ አረቢያ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባል ባለመሆኗ ክሱ ሊቀርብ የሚችለው በአገሯ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሳውዲ አረቢያ መንግስት ላይ የሚደረገው ክስ ጊዜ ከመፍጀት ውጭ ምንም ውጤት አይኖረውም፡፡ ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ባልተናነሰ ስርዓቱን ለማስጠበቅ የቆሙ ናቸው፡፡ ከሳውዲ አረቢያ በተጨማሪ ኢህአዴግ ላሳየው ነቀትና ቸለተኝነትም በአለም ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መክሰስ ይቻል ነበር፡፡ ሆኖም የፍርድ ቤቱ አባል ባለመሆናችን እንክሰስ ካልን ክሱ የሚሆነው አገር ውስጥ ባለው ፍርድ ቤት ነው፡፡ ይህም ቢሆን ከሳውዲ አረቢያ የተለየ ውጤት አይኖረውም፡፡ አኬልዳማ በሚል የተሰራው ዶክመንተሪና በሌሎች ጉዳዮች ክስ አቅርበናል፡፡ ሆኖም ምንም ውጤት ሊያመጡ አልቻሉም፡፡ በአገራቸው እየተፈናቀሉ ያሉት ኢትዮጰያውያንን አስመልክተንም ክስ ብናቀርብም ፍርድ ቤቱ እንደማያስከስስ ውድቅ አድርጎታል፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን መክሰስ ክፋት የለውም፡፡ እንደ አንድ ትግል ስልትና ለህዝብ እንደማሳወቂያ መውሰድ ይቻላል፡፡ በደሉ የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ኢህአዴግ ላሳየው ቸልተኝነትና ንቀት ክስ ማቅረብ መብት አላቸው፡፡ ውጤቱ ግን በቀላሉ መገመት የሚቻል ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ኢትዮጵያውያን ተበታትነው ከመታገል ይልቅ ህብረት በመፍጠር በስርዓቱ ላይ ጫና ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን እራሳችን አጠናክረንና አደራጅተን ስለ መብታችን ካልታገልን በስተቀር ከውጭ አገራትና ድርጅቶች ብዙም ውጤት ባንጠብቅ መልካም ነው፡፡ አገራት ቅድሚያ የሚሰጡት ለብሄራዊ ጥቅማቸው ነው፡፡ የእኛ በደል ይህን ያህል ሊያስጨንቃቸው አይችልም፡፡ በመሆኑም ተባብረን መታገል ይኖርብናል፡፡ በአሁኑ ወቀት ዲያስፖራው እየተነቃቃ ነው፡፡ አገር ውስጥ ያለነው ጋር ትስስር በመፍጠር በዜጎቻችን ላይ በሚደርሱትና በሌሎች ችግሮች ላይ የጋራ እርምጃ መውሰድ አለብን፡፡Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ማስወገድ


November 18, 2013
በዳዊት መላኩ (ከጀርመን)
ኢትዮጵያውያን የወያኔ ባናዳዎች ባፈሙዝ ሀይል ስልጣን ላይ ከወጡበት እለት አንስቶ በርካቶች ለስደት፤ለእስራት፤ለሞት እና ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡የሰሃራን በረሃ አቋርጠው ለማለፍ ሲሞክሩ የበረሃ እራት ሁነዋል፡፡ሌሎች ደግሞ ኩላሊታቸው ሳይቀር እየተዘረፉ ለከፋ አካላዊ እና አእምፘዊ ጉዳት ተዳርገዋል፡፡በባህር ሲያቋርጡ የተሳፈሩበት ጀልባ በሞገድ እየተመታ በብዙ ሺ የሚቆጠሩት ለዓሳ እራት ሁነዋል፡፡በታንዛኒያ እና በኡጋንዳ ሲያልፉ በኮንቴነር ታፍነው የሞቱትን ቤት ያቁጠራቸው፡፡ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን የመን ውስጥ ተጠልፎ በውስጡ የነበሩት የአየር መንገዱ ሰራተኞች እና ተሳፋሪዎች ባሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፏል፡፡
ይህ ሁሉ ህይወት እንደቅጠል ሲረግፍ የወያኔ ባለስልጣኞች አንድም ቀን ብለው የተጎዱ ቤተሰቦችን አጽናንተው አሰከሬናቸው በክብር እንዲያርፍ አላደረጉም፡፡በሰው ሰራሽ አደጋ ለሞቱትም ጥፋተኞችን ለፍርድ ለመቅረብ ተንቀሳቅሰው አያውቁም፡፡ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድም ዳግም ስህተቶች እንዳይፈጸሙ ስምምነቶችን ተፈራርመው ያውቁም፡፡በየሀገራቱ የሰገሰጉዋቸው ዲፕሎማት ተብየዎችም ቤተሰባቸውን እንዴት አንደላቀው እንደሚያኖሩ ፤ከነማን ጋር የንግድ ሽርክና እንደሚፈራረሙ እንጂ በስደት ለሚንገላታው ዜጋቸው መብት ተከራክረው ፡ የሀገሪቱን ጥቅም ለማስጠቀም አንዳች ስራ ሰርተው አያውቁም፡፡
ዲፒሎማቶች ከሙያ ብቃት ጀምሮ ህዝባዊ ወገንተኝነትም ስለሚጎድላቸው የፓርቲውን ህልውና ለማስጠበቅ ካልሆነ በስተቀር ለህዝብ የሚጠቅም ስራ ይሰራሉ ብሎ መገመት ያዳግታል፡፡የወያኔ ዲፕሎማቶች በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ እንዲከፋፈሉ ከላይ በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ብዙ የመከፋፈል ስራዎችን ሲሰሩ እነደቆዩ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ዛሬ በ40/60 የኮንደሚኒየም እና በዓባይ ግድብ ግንባታ ሰበብ በውጪ ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ዶላር ለመሰብሰብ ደፋ ቀና የሚሉት ዲፕሎማቶች ለይስሙላ ያክል እንኳን አንድም ቃል መተንፈስ አልቻሉም፡፡
በወያኔዎች ዘንድ ብሔራዊ የሀዘን ቀን የሚታወጀው እና ህዝቡ በግዳጅ እየወጣ የመንግስት አገልግሎች መስጫ ድርጅቶች ሳይቀሩ ለሁለት ሳምንተ ያልክ ተዘግተው ስራቸው ሀዘን ብቻ እንዲሆን መመሪያ የሚተላለፈው የስልጣን እና የጥቅም አጋራቸው ሲሞት እንጂ ሌላው ተራ ዜጋ እማ ሞቱን እንኩዋን የሚዘግበለት የሀገሩ የመገኛኛ ብዙሀን የለውም፡፡ ግብር የሚከፍልበት ቴሌቭዥን እንዲህ ያሉ ዜናዎችን ለህዝቡ እንዳያቀርብ እነሽመልስ ከማል አፉን ጥርቅም አድርገው ይዘውታል፡፡የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሜዲያዎች የዘገቡትን እውነት በወያኔ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የሀገሪቱ ቴሌቭዥን የቁጥር ጨዋታ ያዟል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተብየው ዶ/ር ቴወድሮስ አድሀኖም ችግሩ ተጋኖ ቀረበ ነው ሲሉ ተዘባበተውብናል፡፡
ሀገሪቱን እመራለሁ ብሎ የተቀመጠ ሀይል እንዴት እንዲህ ሀገራዊ ውርደት ሊያከናነብ ቻለ? መልሱ ቀላል ነው፡፡ መጀመሪያም ወያኔዎች ከሆዳቸው ባለፈ ሀገር እና ህዝብ ብሎ ነገር አይገባቸውም፡፡አሰራ ሰባት ዓመት ተዋጋንለት የሚሉትም የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት እንጂ ለህዝብ የሚጠቅም አንዳች ሀገራዊ አጀንዳ ኑፘቸው አደለም፡፡የወያኔዎች
ዋነኛ መገለጫቸው እና ግባቸው ሀገራዊ ውርደት ማሰፈን ነው፡፡ ይሕን ደግሞ ባለፉት አመታት ሁላችንም በደንብ የምናውቀው ነው፡፡ለግራዚያኔ ሀውልት ማቆምን የተቃወሙ ህዝቦችን አስረዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን በትነዋል፡፡የሀገሪቱን ቅርስ እና ታሪክ በማወደም ታረክ- አልቫ አድርገዋል፡፡የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም በተደጋጋሚ ለባእዳን አሳልፎው ሰጥተዋል፡፡አርሶ አደሮችን እያፈናቀሉ ለም መሬታችንን በርካሽ ዋጋ ሲቸበችቡት ቆይተዋል፡፡ዳር ድንበራችንን ለሱዳን አሳልፎው ሰጥተዋል፡፡በሰላም ማሰከበር ስም ወታደሮች በሶማሊያ መንገድ አስክሬናቸው እንዲበተን አድረገዋል፡፡ዜጎች እምነታቸውን በነፃነት እንዳያመልኩ አድርገዋል፡፡ሌላው እና መሰረታዊው ነገር ራሱ ወያኔ ዜጎችን አደህይቶ፤አደንቁሮ፤አዋርዶ መግዛት የአስተዳደር ስትራቴጅው ዋነኛ ማጠንጠኛው ነው፡፡
በሰሞኑ ያየነውም በአረብ ሀገራት የያኔን አንባገነን ስርዓት ሸሽተው የተሰደዱ ዜጎች በሳዉዲ ወሮበላ ፖሊሶች እንደ በግ ሲታረዱ ሰማያዊ ፓርቲ ሕዝቡን በማስተባበር ሐገራዊ ውርደት እንዲያቆም፤በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ ፤አሰገድዶ መድፈር እና እንግልት እንዲቆም በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ የወገን ተቆርቋሪ ዜጎችን በፌዴራል ፖሊስ ማስቀጥቀጥ፤የፓርቲውን አመራሮች ማሰር የወያኔ ብሄራዊ ውርደት ለፍተኛው ማሳያ ነው፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የሰራው መንግስት ሊሰራው የሚገባውን የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ነው፡፡
ምን እናድርግ?
የእነዚህ ሁሉ ችግሮች ምንጭ ወያኔ ነው!ስለዚህ መፍትሄውም የችግሩን ምንጪ ከመሰረቱ ማድረቅ ነው፡፡ወያኔን ለማሰወገድ ደግሞ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡ በሀገር ውስጥም ይሁን በውጪ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ሀዘናችንን አቁመን በልበ ሙሉነት ለዚህ ሀገራዊ ውርደት የዳረገንን አንባገነናዊ ስርዓት ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ዛሬ በሳውዲ ማጎሪያ ክምፕ ያለኸውም ሀገርህ ብትገባም ሊያስኖርህ የሚችል መንግስት አደለም ሀገሪቱን የሚመራት፡፡ያው ከመውጣትክ በፊት የምታውቀው በአንድ ዘር የበላይነት የተገነባው አብዛኛው ጾም የሚያድርበት ተቂቶች በብዙሀኑ ደም የሚንደላቀቁበት ነው፡፡ገብተህ ድምጽህን የምታሰማበት ምንም መንገድ የለህም፡፡ምናልባትም የሚጠብቅህ ሰበብ ተፈልጎ ቃሊቲ መወርወር ሊሆንም ይችላል፡፡ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የነፃነት ታጋዮችን በመቀላቀል ነፃነታችንን፤የተዋረደው ክብራችንን ፤በአለም አደባባይ የጎደፈው ስማችንን በጋራ ማደስ ይኖርብናል፡፡ እግዚያብሄር አምላክ የሞቱት እህት እና ወንዶሞቻችን ነፍስ በገነት ያሳርፍልን፡፡የጠላቶቻችንን ልብ ያራራልን፡፡
ሞት ረግጠው ለሚገዙን አንባገንን መሪዎች !ድል የነፃነትን ብርሀን ለመፈንጠቅ በየበረሀው ለምትንከራተቱ የቁርጥ ቀን ልጆች!

fredag 15. november 2013

መቋጫ ያጣው የወገኖቻችን ስቃይ እና በደል በሳውዲ አረቢያ አሁንም ቀጥሏል!


ethio saudi 10
ትላንት አመሻሹ ላይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርሽቶ በዋለው ተቃውሞ የሞተ ባይኖርም ኢትዮጵያውያኑ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው አማራው አንድነን … ትግሬውም አንድነን … ጉራጌው አንድነን … መብታችን ይከበር … እኛም ሃገር አለን ወዘተ… በሚል መፈክር ታጅበው ብሶታቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመበተን በከፈቱት ተኩስ አካባቢውን ወደ ጦርነት አውድማ ለውጦት ማምሸቱን ይገልጻሉ።
የጸጥታ ሃይሉ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች በመታገዝ የኢትዮጵያውያኑን ተቃውሞው መግታት ተችሏል ብለዋል። እነዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በማውሳት ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የጊዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወሰዱ ባሉት የተናጠል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመመለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በኢትዮጵያ መንግስ በኩል ባለመመቻቸቱ ከሳውዲያኑ ወረበሎች አሰቃቂ ግድያ ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ውሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት ቁም ስቅላቸውን እያዩ መሆኑ ተግልጾል።
ለሰው ልጅ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ያልተሟሉበት ማጎሪያ ውስጥ 4 ቀናቸውን እንዳስቆጠሩ የሚነገርላቸው ኢትዮጵያዊያን እና ሪያድ መንፉሃ ጅዳ እና መካ እስከነ ልጆቻቸው በየመገዱ ላይ ወድቀው ለመንገድ ላይ አዳሪ የተዳረጉ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ብሶት ለማድመጥም ሆነ ለማየት ከሃገር የመጣ የመግስት ባለስልጣን አለመኖሩ ታውቋል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ጅዳ ከተማውስጥ ኢትዮጵያውያኑ የሚኖሩበት አካባቢ በሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች እና በኢትዮጵያውያን መሃከል በተነሳ ግጭጥ 76 ሰዎች መቁሰላቸውን የሚገልጹት ምንጮች በዛ ቀውጢ የተኩስ እሩምታ በጥይት ተደብድቦ የተገደለ ኢትዮጵያዊ ሊኖር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ተቀማጭነታቸው ሪያድ እና ጃዳ ከተማ በሆኑት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር እና የቆንስላው ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች ላይ ተስፋ የቆረጠው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ወገናችንን ለማየት በኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ወደ ሳውዲ አረቢያ ተጉዘዋል የተባሉት የልኡካን ቡድን አባላት እሰከአሁን ምንም አይነት የሚጨበጥ ነገር መስራት ባለመቻላቸው ኢትዮጵያውያኑ ለከፋ አልቂት በመዳረግ ላይ መሆናቸው ተገልጾል።
ሰሞኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያውያኑ በሳውዲ አረቢያ እየተፈጸመባቸው ያለውን የጅምላ ግፍ እና በደል ይሄን ያህል የሚጋግነን እና ቦታ የሚሰጠው አለመሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት ምሽት መንፉሃ አካባቢ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከ17 በሚበልጡ አውቶብስ ተጭነው እንደተወሰዱ የሚነገርላቸው ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ህጻናት ሴቶች አረጋውያን የሚገኙበት አያሌ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከሪያድ የ6 ሰአታት ጉዞ በኋላ ያልታወቀ ምድረ በዳ የሆነ አካባቢ እንዲወርዱ መገደዳቸውን እና እስካሁንም ያሉበት ሁኔታ በውል እንደማይታወቅ ተገልጾል።
(Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በፌስቡክ በኩል የላኩት)

“Are Ethiopians without a country?”

SMNE holds KSA and EPRDF accountable!

ethio saudi
Press Release
Washington, DC, November 11, 2013
SMNE Calls on the Saudi government to stop this brutal and inhumane treatment of the Ethiopian migrant workers immediately And on the TPLF/ERPDF regime to Protect Ethiopian Citizens in Saudi Arabia
The Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE), a non-political and non-violent social justice movement of diverse people that advocates for freedom, justice, good governance and upholding the civil, human and economic rights of the people of Ethiopia, without regard to ethnicity, religion, political affiliation or other differences, is highly disturbed by reports, pictures and video footage of the violence being perpetrated against Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia. Please take a look at the video links here,here and here.
saudi ethioSince the November 3, 2013 deadline in Saudi Arabia, which marked the end of the amnesty period during which all undocumented foreign workers were required to legalize their status or face deportation, Ethiopians working in the Kingdom of Saudi Arabia (KSA) have faced beatings, torture, rape, and serious injury.
Please take a look at the pictures here. Although many of the over 16,000 migrants who have been arrested are Ethiopians, workers from other countries, such as the Philippines, are also represented.
Graphic pictures of blood, injury and death are circulating on websites and in the social media. We in the SMNE have received countless phone calls, emails, pictures, videos and messages telling about and showing Ethiopians who have been victims of these crimes. One was a heartbreaking picture of a young Ethiopian man who was shot dead on the street, the blood from his wounded body flowing onto the pavement. Eyewitnesses to his murder report that this man was shot in the head as he tried to run away. He may have feared arrest or the brutal treatment at the hands of Saudi police. In one reported case, a handcuffed man, already contained, was still beaten by the police. In another video clip, Saudi civilians can be seen beating up other men. According to reports to the SMNE from Ethiopians in Saudi Arabia, a total of 7 Ethiopians have been killed, 218 have been injured and over 368 are missing. This brutality is outrageous.
We call on the Saudi government to stop this brutal and inhumane treatment of these migrant workers immediately and to hold those who have committed these crimes accountable, including those in uniform as well as civilians. If the KSA seeks to deport undocumented workers, it is your right to carrysaudi ethio1 out your laws; however let it be done in a civilized and respectful manner. These people, most of whom entered the country legally with visas, should not be treated as criminals, beaten up and tortured for not having papers or not having the right papers.
A number of the injured have not received any medical care. Those arrested are taken by authorities without leaving any information of their whereabouts with family or friends. One young girl told of how she was raped on the street by a civilian mob of Saudi men who attacked and gang-raped her.
Another young girl reported being inside a house where she was staying with two other women and two men. She reports: “Saudi police in uniform broke down the door to our house and rushed in. They ordered all of us to lay flat on the floor and to give them our papers. We obeyed immediately. One of the other girls told the police that we were not illegal, saying, ‘We have papers.’ In response, one of the police kicked her in the head and demanded that she hand over the papers. When she gave them to him, he took them and tore them apart. She asked why and the police started beating everyone. Two police officers took the men in our group to some unknown place and left us girls with the five remaining police officers. Immediately, they started touching us inappropriately. We started screaming and then they forced us to do what they wanted to do with us.”
At this point in the story, she broke into tears and said she did not want to say any more, finally saying, “These people are treating us like animals. Even now, I don’t know where these men have been taken. One of them is my husband. The girl, whose papers were destroyed, was taken away by the police and I don’t know what has happened to her. They [the authorities] are saying that the law was put into place for those who do not have papers [undocumented workers] but we had all the proper papers and they are still treating us like this.”
saudi et1In another report, an Ethiopian man spoke of how he was providing safe shelter for nine women because it was so dangerous for young women to go outside. He stated that due to the absence of any law and order and civilian mobs prowling the streets for migrant workers, the possibility of these women being raped was extremely high. He had been in the country for over ten years and was running a business.
Men are also at risk for being beaten or tortured, which has happened in cases where they were not even asked to produce documentation of their status. Instead, it appears that non-Saudis are attacked at will for simply not being native-born. Compliance with the law does not seem to make a difference.
One man reported, “Several days ago, a mob of Arab men came to the place where we were staying and began to beat us. We started fighting back because whether you obey the law or not, you can still be beaten, tortured or killed. It leaves us no option but to take the law into our own hands to protect ourselves since no one here will protect us. Those in uniform are no different than the mobs in this respect. If they attack, we will fight back.” This is what is happening on the ground according to reports we have received from eyewitnesses.
One man said, “These same brutal attackers may be eating food grown in Ethiopia. Not only that, but some of the Ethiopians who have been beaten up like this may be here in Saudi Arabia seeking opportunity because they have been evicted from their land and their land has been given to Saudi investors.” This is very, very disturbing. Saudi Arabian investors have been leasing large sections of fertile, well-watered land in Ethiopia to grow food on mega-farms for export to Saudi Arabia while they are mistreating Ethiopians here. This should be exposed.
After receiving many desperate calls from Ethiopians in Saudi Arabia and in the Diaspora, starting on Tuesday, November 5, we in the SMNE called the United Nations High Commissioner for Refugees (UNHCR) in Geneva on Friday, November 9 to ask for help in addressing this mounting manmade crisis. They told us that it was not part of their mandate because these people were not refugees, but instead were migrant workers. When they were asked who would be the right organization to help, they suggested calling the International Labor Organization (ILO) or the International Organization for Migration (IOM), both of which are part of the United Nations.
We called IOM first and were told there was not much they could do about it because again, it was not part of their mandate because Saudi Arabia, as a sovereign country who had passed a law requiring undocumented workers to leave their country, it was considered an internal national issue.
Contact was then made with ILO. They said they were aware of the problem and did document such things but that there was not much they could do about it. They said the best group to deal with this would be the government of the country where the immigrants had originated—Ethiopia.
The next call was to the Ethiopian Embassy in Saudi Arabia where an Ethiopian official there answered the phone. He was not helpful, nor was he particularly sympathetic to the plight of the migrant workers, but instead he put the blame on the workers saying that they were given seven months to get papers and should have done so a long time ago. He was then told that there were numerous cases where these Ethiopian workers had the right paperwork, but that the papers were destroyed or ignored by the authorities or civilian groups. This embassy official was told that what has been done to “your own citizens” was wrong and that it was the responsibility of the embassy to take care of these Ethiopians like other countries are doing. It was also emphasized that the Ethiopian embassy should not just sit by, doing nothing, instead of trying to do more when Ethiopians were suffering like this. He became very irritated with this suggestion; saying he had nothing more to say and abruptly hung up the phone.saudi ethio2
We call on the international community, human rights organizations and the international media to expose the mistreatment and human rights abuses of these migrant workers in the KSA and take whatever action they can to protect these vulnerable people, including helping them to leave the country.
We call on Ethiopians, wherever they are, to make appointments at Saudi Arabian Embassies throughout the world to tell them to stop the torture, rape and brutality being waged against these migrant workers and to hold those who have committed the crimes accountable. As they have already made it clear, they do not want these migrant workers in their country and want to deport them, but at the very least they should still treat them with civility. This advocacy work is something Ethiopians should do in multiple places. Also, if Ethiopians have family or friends in Saudi Arabia who have been affected by these actions, get accurate details and give the information to the media.
These evil deeds thrive best in the darkness, so let the light shine on what happened. We commend those who have already done a remarkable job of exposing the truth through their eyewitness accounts, pictures and videos. Let the world know. However, the root solution to the plight of these migrant workers is for Ethiopians to have a government that cares for the welfare of all Ethiopians. Instead, many Ethiopians run to other countries for opportunities denied to them in their own country.
In the early eighties, the regime under Mengistu Hailemariam was known for the starvation of its people, but today the current regime under the TPLF/ERPDF is known for the constant flood of Ethiopians to other places in the world. Many do not ever make it and others suffer tragedy in other countries like they now are experiencing in Saudi Arabia.
Are Ethiopians people without a country? When will the government of Ethiopia be a government that cares about its people? Why should Ethiopians have to go in every direction for help except to their own government?
The heart of Ethiopia cries for its lost children who are dying abroad because their own country has become so inhospitable to life that they take huge risks that often end badly. No wonder they are the fifth largest group of people in the world subjected to human slavery.
Great numbers are also subjected to mistreatment, hardship and death as they fall into the open and greedy hands of human and sexual traffickers; dying in places like the Red Sea, Egypt, Yemen, Saudi Arabia, Kenya, Tanzania, Malawi, South Africa, Central America, and in a shipwreck offshore from the Italian island of Lampedusa. All of this is happening because of the lack of a government who cares for its citizens.
We call on all Ethiopians to find solutions to this urgent crisis in Saudi Arabia, but we cannot simply go from crisis to crisis. We must demand long term solutions. It is clear now that the only way Ethiopians can be respected as a people is to establish a government in their own country that sees all of them as precious human beings, putting humanity before ethnicity rather than the unhealthy system of the TPLF/ERPDF based on ethnic favoritism at the expense of everyone else. Ethiopians deserve a home where they can live freely and flourish, where people do not undertake horrendous risks for basic opportunities that should be theirs from the start.
We in the SMNE will continue to monitor the situation, but believe the TPLF/ERPDF regime should take immediate responsibility to resolve this current crisis by sending airplanes to bring their own citizens back home and to make the Saudis accountable for those who have been killed or injured. If the Saudis do not respond, Ethiopia should close down their embassy in KSA as a sign of strong condemnation for the barbaric mistreatment committed against the Ethiopian people. Furthermore, the TPLF/ERPDF should seek a moral solution to the longstanding problems within Ethiopia. How can the problem of mass migration be sustainably solved without deep and meaningful reforms, the restoration of justice and reconciliation?  None of us will be free until all of us are free.
May God protect these Ethiopian brothers and sisters in Saudi Arabia and give our diverse and beautiful people the strength and humility to come together as we struggle to create a more just, united, reconciled and hospitable Ethiopia for all.  =============================
For more information or media enquiries please contact:
Mr. Obang Metho,
Executive Director of the SMNE
910- 17th St. NW, Suite 419
Washington, DC 20006 USA
E-mail: Obang@solidaritymovement.org
Website: http://www.solidaritymovement.org
CC To:
Kingdom of Saudi Arabia Ministry of Foreign Affairs
Ministry of justice Kingdom of Saudi Arabia
Ministry of Interior Kingdom of Saudi Arabia
Saudi Embassy in Addis Ababa
Saudi Embassy in London, United Kingdom
Saudi Arabian Embassy in Canada
Saudi Arabian Embassy in Washington, D.C.
The office Prime Minister of Ethiopia
Addis Ababa, Ethiopia
American Embassy in Addis Ababa, Ethiopia
Ambassador Patricia M. Haslach
European Union
Ambassador Mr. Xavier MARCHAL
Head of Delegation
A24MEDIA
All Africa
BBC AFRICA
Bloomberg News
NCNB Africa
CNN
INDIAN OCEAN NEWSLETTER
REUTERS AFRICA
The East Africa
African Review
VOA Ameharic
VOA-English
U.N. High Commissioner for Human Rights
Human Rights Watch
UNHCR-
Amnesty International,
IOM
ILO

lørdag 9. november 2013

TPLF planted a seed of hate on me

November 9, 2013

by Surafel (Mamushe)
Yes……as a proud Ethiopian young man, I never thought for a second that I am crying a story over heard from the news outlets. In our culture, we, men, are usually hiding our heartfelt emotions inside on our heart, however, the despicable and indefensible crime committed against our people by the very small click of TPLF angered me more than ever before in my entire lifetime. Cultural implications and impacts are a pinpoint of societal behavioral reflections. We, Ethiopians, are well known for our cultural values; nevertheless, what’s happening in Ethiopia right now is far from our cultural norms. The devilish TPLF security agents compromise the decency of our cultural values.
Recently, when I noticed what’s happening in a TPLF torture camp against one of the central committee members of UDJ (Andenet), my anger reached on a climax. Beyond my extreme anger, my tears fall on my face like a rain.
Here the shocking story…..as always I do, I logged in on my face-book page to check the daily newsfeed. As soon as I scrolled down on my page, one of the news links surprisingly caught my attention. Eagerly, I clicked on the link and listening the interview conducted by Ethiopian Satellite Television a.k.a ESAT with the victim and highest-ranking member of UDJ (Andent), Ato Abebe Akalue. As Ato Abebe narrating the untold and shameful act of TPLF agents against him, I couldn’t believe what I have just heard from him. Since torture and heinous crime against our people is a normal routine in a TPLF torture camp, it doesn’t surprise me at all. However; what shocked me the most is the sexual harassment against Ato Abebe by the TPLF security agents. Forget about as a very conservative nation such as Ethiopians, I never saw anywhere in the world that security agents sexually harassed someone because he has different political views than the government.
Right after listen this horrific interview, I turned the audio off and sighed deeply. And then, I was numbed for a while, and confused, sad, mad and finally I felt those TPLF agents and their masters are planted a seed of hate on me. Yes a seed of hate that can cultivate revenge in my heart. Whether you are a supporter or against the TPLF lead government, in this specific case, the RED line was passed. They broke the core value of our cultural identity. We all know that sexually harassing a father and married man is an absolute taboo and insane.
I was one of the people who strongly believed that the only avenue to rid off any dictatorial regime is only through peaceful struggle, however, after this inhuman and monstrous act of TPLF, I convinced myself that peaceful struggle against these evils are a nightmare. As a result, now on, I am onboard for using anything to take back our country from TPLF and replanting the seed of peace, respect and unity among our great people.
Not a political, a moral question for Ethio-Tigrians in Diaspora.
To all Diaspora Tigria origin brothers and sisters….for how long and what cost, you will say “enough is enough” to this small group of merciless TPLF?
My and your forefathers were fought and died together as one nation to protect our country from domestic and foreign enemies. Their ultimate precondition to defend the country and its people from domestic and foreign enemy was simply “right or wrong” not demographical or geographical resemblance. I am not trying to challenge your right to affiliate with any political groups but I am challenging your reasoning to support the TPLF.
Today, for the sake of argument, I will set aside the political argument against you (Diaspora Ethio-Tigrians) but I will present to you a moral argument. I bet you all have heard what the TPLF security agents did against the ranking member of UDJ, an opposition political party. Recently, the TPLF Security agents abducted the victim from the street and took him some unknown place. Right after they got him in this unknown torture camp, they forced the kind of alcohol down into his throat and water boarding him consistently. Because this was not enough for the TPLF ruthless agents, they are sexually “molested” him. How this happened in Ethiopia?
My brother and sisters; what is the moral equivalency for this unusual and immoral satanic behavior of TPLF? This is beyond anybody’s imagination. I don’t know which world the Diaspora Tigrians lives in, but most of Ethiopians are outraged and angered by the sodomization of our God fearing people. Whether or not you are a TPLF sympathizer, this act of evil violates the universal code of conduct and our moral values.
Finally, I am very disappointed that I didn’t see any statement and hear any condemnation from the Diaspora Tigrians against this TPLF shameful act. It’s best for the good of the country to come together as one nation and people and say enough for these TPLF parasites spew hate and division among our people. Otherwise, I can assure you that our country will be the land of vengeance, retaliations and avenging.       http://ecadforum.com/

fredag 8. november 2013

የተከለከለውን እንደተፈቀደ…


ethio enadin
… ይህን ሁሉ ሰብአዊ ክብራችንን ያሳጣን ዘረኛ አስተዳደር፤ ይህ አልበቃ ብሎት በታሪካችን፣ በሐይማኖታችን፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጋችን ሳይቀር የተከለከለን ድርጊት የመንግስት የፀጥታና የደህንነት አስከባሪ ነን በሚሉ አስተሳሰበ ድውያን ሰሞኑን በአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል በአቶ አበበ አካሉ ላይ አስገድደው የአልኮል መጠጥ በመጋት የተፈፀመባቸውን የወሲብ ጥቃት ወንጀል ማህበራችን በፅኑ ያወግዛል። በረጅም ዘመን የነጻነት ታሪካችን በግብረ ሰዶማዊነት ራሳቸው ፈቅደው ከተሰማሩ ሰዎች ውጭ ሕግ እናስከብራለን በሚሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱ ነውር በእኛ ትውልድ ሲፈፀም በማየታችን በህሊናችን ውስጥ ጊዜ የማይሽረው ጠባሳ አሳርፈውብናል። የመጨረሻውንም የውርደት ሸማ ሊያከናንቡን በቅተዋል።… (የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

“በሳዑዲ ኢትዮጵያዊ ህገ ወጥ ስደተኞች ሳንጃና ቆንጨራ መታጠቃቸውን አረጋግጠናል” አምባሳደሩ

(አምባሳደሩ በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ስም በሚያንቀሳቅሱት የአሰሪ እና ስራተኛ ኤጄንሲ ለሞቱት 3 ሴቶች ተጠያቂ ናቸው)

eth saudi
ኖቬበር 4 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የምህረት አዋጅ የግዜ ገደብ መጠናቀቅ አስመልክቶ ለተለያዩ የልማት ማህበር አባላት ኤምባሲው አርብ ኖቬምበር 1 2013 በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበር የሚገልጹ ምንጮች ስብሰባው በኢትዮጵያውያን ቆጨራ እና ሳንጃ መታጠቅ ዙሪያ ኤምባሲው ማህብረሰቡን ለመነጋጋር አጀንዳ ይዞ መቅረቡ ስብሰባው በጣም አሳፋሪ እና ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ለመወንጀል ሆን ተብሎ የታቀደ ከስም ማጥፋት ዘመቻ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ገልጸዋል።
በተለይ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን በወቅቱ ለተሰባስቢው ስለአጀንዳው ሲገልጹ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ አያሌ በባህር የመጡ ኢትዮጵያውያን በተለምዶ «ባህር ሃይል እየተባሉ የሚታወቁ» መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ጠቀሰው እነዚህ ህገወጦች የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያወጣውን ህግ ተከትሎ የሚወሰድባቸውን እርምጃ ለመከላከል ሳንጃ መታጠቃቸውን ኤምባሲው በመረጃ አረጋገጦል ብለው መናገራቸው በአብዛኛው ተሰብሳቢ ዘንድ ተቃውሞን ቀስቅሷባቸዋል። አምባሳደሩ በዚህ ዙሪያ ሰላማዊ ወገኖቻችንን በመወንጀል የሃገራችንን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት በኤምባሲ ደረጃ አጀንዳ ተይዞ ስብሰባ መጠራቱ ያበሳጫቸው ተሰብሳቢዎች የአምባሳደሩን ጤናማነት እስከ መጠራጠር መድረሳቸውን ምንጮቻን አክለው ገልጸዋል። ድጋፍ እናገኛለን ብለው የጠሯቸው ታማኝ የልማት ማህበራቱ ስራ አመራር የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ያቀረቡት ክስ ከምን ጭብጥ ተነስተው እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጦቸው ስብሰባው ላይ ወጥረው ይዘዋቸው እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች ስብሰባው ገና ከመነሻው በተሳታፊው ከፍተኛ ተቃውሞ አለመግባባቶች ተፈጥረው እንደነበር ይገልጻሉ፡፡
mohammed hassenአንዳንድ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን አባባል ያንገበገባቸው አስተያየት ሰጪ የቀረበው አንጀዳ ስህተት መሆኑንን ገልጸው ሴት እህቶቻችን ጉልበታቸውን ያፈሰሱበትን የወር ደሞዛቸውን ተነጥቀው ተደብድበው እና ተደፍረው በየጎዳናው ወድቀው የፍትህ ያለህ እያልን ጣረሞት እያሰማን ባለንበት የስደት አለም እኛው አጥፊ እኛው ገዳይ አረመኔ እና ጨካኝ ተብለን በተለያዩ ሚዲያዎች ስማችን ሲጠፋ እና የሃገራችን በጎ ገጽታ በማጉደፍ በባእዳን ጥላቻ የተቃጣብንን የስም ማጥፋት ዘመቻ አምባሳደሩ እንደ አንድ ሃገር መሪ ተወካይ መጋፈጥ ሲገባቸው የዝሆን ጆሮ ይስጥኝ ብለው ከርመው ዛሬ በድፍረት እኛ ፊት ቆመው እኛኑ ለመወንጀል መቃጣታቸው በጣም ያሳዝናል ብለዋል።
በሌላ በኩል አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ሲናገሩ አምባሳደር መሃመድ ሃሰንን ከእንግዲህ እንደማያውቋቸው ገልጸው ስለኢትዮጵያውያን ለመናገር የሞራል ብቃት የሌላቸው ከሳቸው ይልቅ በዲፕሎማት ደረጃ አንቱ የሚባሉ እንደነ አቶ መስፍን እና መሰል ዲሲፒሊን ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የመንግስት ተወካዮች ስለኮሚኒቲው ችግር ህዝቡን ማወያየት እንደሚገባቸው በአጽኖት ጥቀስ በኤምባሲው ዝርክርክ አሰራር የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የተሳናቸው ወገኖቻችን ላይ ለሚደረሰው ማንኛውም አደጋ አምባሳደሩ ሃላፊነትን መውሰድ እንደሚገባቸው በሰጡት አስተያየት ከተሰብሳቢው በተደረገላቸው የድጋፍ ጭብጨባ በወቅቱ የስብሰባ አዳራሹን ድባባ ለውጦታል።
አምባሳደር መሃመድ ሃሰን በአምባሳደርነት ማዕረግ ተሹመው ወደ ሳውዲ አረቢያ ከተላኩ ጀምረው በተለያዩ የግል ንግድ ላይ በእጅ አዙር ተሰማርተው ያለአግባብ የበለጽጉ ከበርቴ አምባሳደር መሆናቸውን የሪያድ ነዋሪዎች ያናገራሉ። አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ኢትዮጵያ ውስጥ በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ስም በከፈቱት 2 የአሰሪ እና ስራተኛ ኤጄንሲ አማኝነት ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥተው እስካሁን ድረስ ህልፈተ ህይወታቸውን ቤተሰቦቻቸው ላልተረዱ 3 ሴት እህቶቻችን ሞት ተጠያቂ ከመሆናቸውም በላይ በቅርቡ 2 ሚሊዮን ሪያል «5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር» ወደ ሌላ ሃገር ለማሸሽ ሲሞክሩ በሳውዲ ደህንነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ከዋሉት ከቀድሞው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፋ ሁሴን አልዬ ጋር አምባሳደሩ እጃቸው እንዳለበት ይጠረጠራል።
በአጠቃላይ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን መንፍሃ ውስጥ ቆጨራ እና ሳንጃ ታጥቆ መሽጓል ብለው ለመወንጀል የፈለጉት የየተኛውን ብሄር አባል እንደሆነ ስብሰባው ላይ በይፋ ባይናገሩም በዚህ አካባቢ ቀደም ብሎ ጥቂት ስርዓት አልበኛ ኢትዮጵያውያን መሃከል አልፎ አልፎ በሚቀሰቀስ የጉሩፕ ግጭት በሳንጃ እርስ በእርሳቸው ይተራረዱ እንደነበርና በአካባቢው ማህበረሰብ የዕለት ተዕለት እንቅስቅሴ ላይ ቀላል የማይባል ተጸኖ ያሳድሩ የነበሩ ወጣቶችን ለማስታረቅ ኤምባሲው ቢጠይቀም ፈቅደኛ ሳይሆን መቅረቱ ይታወሳል። ይህ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ብዛት ያላቸው በባህር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የከተሙባት እና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በንግድ ዘርፍ የተሰማራባት በመሆኑ በመርካቶነት የሚሰይሙት ወገኖች ለአያሌ ኢትዮጵያውያን የእድገት ማዕከል በመሆኗ በማውሳት የአምባሳደሩን ንግግር ቀደም ሲል በተለያዩ ሚዲያዎች በኢትዮጵያውያን ላይ ከተቃጣ ውንጀላ ለይተው እንደማያዩት ይገልጻሉ።
የጎልጉል ደንበኛ በፌስቡክ የላኩት
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

የማዕድን ሙስና በኢትዮጵያ፤

November 6, 2013

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ
በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ ሙስናን አስመልክቶ ይሀ ለሰባተኛ ጊዜ ያቀረብኩት ትችት በማዕድኑ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በሙስና ላይ ያቀረብኳቸውን ሌሎችን ትችቶች “Al Mariam’s Commentaries” የሚለውን ድረ ገጽ በማየት ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ መዋቅራዊ ባህሪ እየያዘ በመጣው ዘርፈ ብዙ ሙስና ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ነቅቶ እንዲጠብቅ ለማስቻል በጉዳዩ ላይ አሁንም ትችቶቼን ቀጣይነት ባለው መልኩ አቀርባለሁ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ገዥው አስተዳደር የሕዝብ ትኩረትንና አድናቆትን ለማግኘት ሲል ጥቂት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣኖችና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ንክኪ አላቸው ባላቸው ጥቂት የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ላይ የሙስና ክስ በመመስረት የጸረ ሙስና ትግሉን በይፋ እንድታይለት ሰብስቦ በእስር ቤት አጉሮአቸዋል፡፡ እነዚህ በሙስና ተጠርጥረው በይስሙላው ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ቀርቦ እየተሰራ ያለው ድራማ ዓለም አቀፍ አበዳሪዎችና ለጋሽ ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት ግልጽነትና ተጣያቂነት ያለው ስርዓትን እንዲያሰፍን እያደረጉት ባለው ተጽዕኖ ምክንያት ለታይታ ያህል መንግስት የሚተገብረው የፖለቲካ ትወና ነው፡፡ ለአገር ውስጥ ህዝብ ፍጆታ ተብሎ ገዥው አስተዳደር እየተውነ ያለው ይህ የሙስና ድራማ ጥልቅና ስር ሰድዶ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተዋናይነት ተንሰራፍቶ ያለውን ከፍተኛ የህግ ልዕልና ሂደትን የሚጠይቀውን ያገጠጠና ያፈጠጠ ሙስና አሳንሶ በማቅረብ፤ የማታለል ዘዴ በመጠቀም እርባና የለሽና የጮሌነት ጭንብል በማጥለቅ ዋነኞቹን የሙስና ተዋናዮች ለመደበቅ የተዘየደ ተውኔት ነው፡፡
እውነታው ሲታይ ግን በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ያለው ሙስና እንዲህ በቀላሉ በጥቂት ታማኝ ያልሆኑና ህገወጥ በሆኑ ባለስልጣናት ጓደኞችና ተባባሪዎቻቸው አማካይነት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የጉምሩክ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በሚገቡ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ በሚደረግ የሙስና መሞዳሞድ ላይ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ሙስና መዋቅራዊ ሲሆን፤ በመላ አገሪቱ የፖለቲካ ሰውነት ላይ በስፋት ተሰራጭቶ የሚገኝ ነቀርሳ ነው፡፡ በመሆኑም የዓለም ባንከ ያዘጋጀውን ትልቅ ሪፖርት “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ የሚል ርዕስ መስጠቱ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ይልቁንም እንዲህ በሚል ሊነበብ ይገባዋል “በኢትዮጵያ በስፋት እየተሰራጨ ያለውን የሙስና ነቀርሳ መመርመር“::
ባለፉት ተከታታይ ትችቶቼ በግልጽ እንዳስቀመጥኩት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ የሚገኘው መዋቅራዊ ሙስና እራሱን በተለያዩ መንገዶች ይገልጻል:: ለምሳሌም “መንግስት አቀፍና“ (አድራጊ ፈጣሪና ሀብታም ግለሰቦች፤ ቡድኖች፣ የአገዛዙ ስርዓት ዘመዶች፤ ተባባሪዎችና ደጋፊዎች፤ የውስጥና የውጭ አጧዦች፣ ህግ አጣማሚዎችና በራዦች፤ የቁጥጥርና አስተዳደራዊ ስርዓቱን ለእራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ) የሚያካትት ሲሆን፤ “አስተዳደራዊ ሙስና“ (በቢሮክራሲው ልዩ ዘዴንና ስልጣኖቻቸውን በመጠቀም በገፍ የመንግስት ኃላፊዎችና የበታቾቻቸው፤ ያሉትን ህጎች፤ መመሪያዎች፤ ደንቦችና አሰራሮች በማጣመምና ለእራሳቸው ጥቅም እንዲውሉ በማድረግ) ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በሙስና አገዛዝ (የፖለቲካ ስርዓቱን በመቆጣጠር ጥቂት ቡድኖች በህዝብ ስቃይ እራሳቸውን ለማበልጸግ በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር በተጣበቁ ደም መጣጮች) የምትገዛ አገር ሆናለች፡፡ የዓለም ባንክ ባቀረበው ዘገባና በተለመደው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢሮክራሲያዊ ዘወር ያለ አቀራረብ “ሙስና በኢትዮጵያ በማዕድኑ ዘርፍ እንደ መሬት፤ ትምህርት፤ ቴሌኮሙኒኬሽን፤ ኮንስትራክሽን እና ሌሎች ዘርፎች ሁሉ በፈጣንና ተዛማች ነቀርሳ የተወረረ ነው“ በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡
እንደ ዓለም ባንክ ዘገባ “በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፉ የለማ አይደለም፤ ነገር ግን አገሪቱ በተፈጥሮ የማዕድን ሀብቷ የበለጸገች ናት” ይላል፡፡ በቅርብ ጊዜ ከታመኑ ምንጮች የወጣ ዘገባ እንደሚያስረዳው “የኢትዮጵያ መንግስት በያዝነው የበጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ 11 ወራት በባህላዊ የማዕድን አምራቾች ተመርቶ ወደ ውጭ ከተላከው የማዕድን ሀብት ውስጥ 419 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተገኝቷል፡፡ በዚሁ በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩት የማዕድን ሀብቶች ውስጥ ወርቅ ትልቁን ድርሻ በመያዝ 409.1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ያስገኘ ሲሆን ጌምስቶን (የጌጣጌጥ ድንጋይ) እና ታንታለም እንደ የቅደም ተከተላቸው 9.3 እና 1.6 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አስገኝተዋል፡፡ ይህ ገቢ የተገኘው 7878.3 ኪ/ግ ወርቅ፣ 20126.3 ኪ/ግ ጌምስቶን እና 32.95 ቶን ታንታለም ወደ ውጭ በመላክ ነው… ሚድሮክ የወርቅ ማውጣት ኩባንያ በአገሪቱ ውስጥ በወርቅ ማውጣት የስራ ዘርፍ ብቸኛው ኩባንያ ነው፡፡” ሌሎች መረጃዎች እንደሚጠቁሙት “ወደ ውጭ የሚላከው የማዕድን ሀብት የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት ረገድ በአገሪቱ የሁለተኛነት ደረጃን ሲይዝ በጠቅላላ አገሪቱ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ወጭ ምርቶች ውስጥ 23 በመቶውን ይሸፍናል፡፡”
የዓለም ባንክ “በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ” ውስጥ “ሰባት ዓይነት የሙስና አደጋዎችን” ነቅሶ ያወጣ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ “ሶስቱ ዋነኛ አደጋዎች” ተብለው የቀረቡት “ፈቃድ በማውጣት፤ በፈቃድ አያያዝ ላይ በሚደረጉ ስምምነቶች እና በማዕድን ገቢዎች ላይ የሚደረገው ነው፡፡” ሌላው አሳሳቢው የሙስና ዓይነት “ከካሳ ክፍያዎችና ከአካባቢ ነዋሪዎች ግዴታ፤ ኮንትራክተሮችና አምራቾች: ከማዕድን ካምፓኒዎች ጋር ከሚያደርጓቸው የስምምነት ውሎች፤ ከካምፓኒዎች ምርቶች ጥራት መዝቀጥ እና የማዕድን ምርቶችንና መሳሪያዎችን ከመዝረፍ” አንጻር የሚደረጉ የሙስና ዓይነቶች ናቸው፡፡
የዓለም ባንክ በግልጽ እንዳስቀመጠው “ፈቃድ በማውጣት ሂደት ጊዜ” “ባለስልጣኖች ፈቃድ ለማውጣትና ለመስጠት፤ ፈቃድ በቶሎ አውጥቶ ለመስጠት ወይም ደግሞ ብዙ ጉዳት የማያመጡ የፈቃድ ሁኔታዎችን ለመስጠት ከማዕድን ካምፓኒዎች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ገንዘብ ይወስዳሉ ወይም ጉቦ ይቀበላሉ፡፡” ሌላው ተመሳሳይ አደጋ “ባለስልጣኖች ፈቃድ በሚሰጡበት ወቅት ፈቃድ ከሚሰጡት ካምፓኒ ጋር በስውር ድርሻ እንዲኖራቸው ስምምነት ያደርጋሉ፤ ፈቃድ ለመስጠት የመሬት ባለቤትነትን ሊያገኙ ይችላሉ፤ የተወሰነ ድርሻ በአክሲዮን መልክ ወይም ከትርፍ የተወሰነ ድርሻን ይጠይቃሉ፤ ለእራሳቸው ወይም ለጓደኞቻቸው ቅድሚያ ምዝገባ እንዲያደርጉላቸው ከፈቃድ አውጭዎች ጋር ይሞዳሞዳሉ፡፡” በፈቃድ ስምምነት አያያዝ ጊዜ የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች ሆን ብለው የማዕድን ስምምነቶችን (ለምሳሌ ያህል የአካባቢ፤ የጤና እና የደህንነት ህጎችን እንዲሁም በአካባቢው የማዕድን ካምፓኒው በኃላፊነት የመጠየቅ ደረጃና ሁኔታን ያካትታል) በስራ አንዳይዉሉ ያጨናግፋሉ::
በማዕድን ገቢ አሰባሰብ ጊዜ የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች ለመሬት መጠቀሚያና ለታክስ የሚያደርጓቸውን ወጭዎች ለመቀነስ ሲባል ሆን ብለው ያመረቱትን ምርት መጠንና ትርፋቸውን በማሳነስ ወጭዎችን ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ገዥው አሰተዳደር ከማዕድን ካምፓኒዎች የሚገኘውን ገቢ በትክክል ለማወቅ ነጻ የሆነ የማረጋገጫ አካል የለውም፡፡ ለመሬት መጠቀሚያና የገቢ ግብር መጠን በአጠቃላይ የሚወሰነው የማዕድን ካምፓኒዎች በአመኑት የምርት መጠንና ትርፍ ላይ ተመስርቶ ነው፡፡ ምክንያቱም በፌዴራል፤ በክልልና በከተሞች አስተዳደር ያሉ የፈቃድ ሰጭ ባለስልጣኖች በካምፓኒዎች ስላለው ሀብት የሚገልጽ ዝርዝርና ተጨባጭ መረጃ ስለማይገኝ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ የማዕድን ካምፓኒዎች ካፒታላቸውንና የስራ ማስኬጃ ወጫቸውን ከፍ ሲያደርጉ ምርቶቻቸውንና የሚገኘውን ትርፍ ደግሞ ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥና የገቢ ማጭበርበር ክስተት መኖሩ ሲረጋገጥ የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች በመንግስት አካላት እርምጃ እንዳይወሰድባቸውና የሚመለከታቸው አይተው እንዳላዩ እንዲያልፏቸው ኃላፊነቱ ላላቸው ባለስልጣኖች ጉቦ ይሰጣሉ፡፡
በማዕድን ዘርፉ እስከ አሁን በተጨባጭ በተግባር የታዩና የተመዘገቡ የሙስና ዓይነቶች የሚከተሉትን ያካተታሉ፡- ጉቦ መቀበል፤ የሀሰት መረጃ መስጠት፤ በህገወጥ መንገድ ከማዕድን ካምፓኒዎች ገንዘብ መውሰድና ነጻነታቸውን ዝቅ አድርጎ ማየት፤ እና የውስጥ ህገወጥ መረጃዎችን በመጠቀምና ነጻነት የሌላቸወን ካምፓኒዎች በማጭበርበር ለአካባቢው ነዋሪዎች የተመደበውን ካሳ መስረቅ ሲሆኑ ሰፋ ባለ መልክ በማዕድን ዘርፉ የሚካሄዱ የሙስና ዓይነቶችንና ይዘታቸውን እንደሚከተለው እንመልከት፤
አንድ የማዕድን ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ለማውጣት ከፍ ያለ ገንዝብ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ታላላቅ ባለስልጣኖችና የካምፓኒ ባለቤቶች ይህንን ገንዝብ በሚስጥር ይይዙና ገንዘቡ በውጭ ባንክ አካውንት ለባለስልጣኖች እንዲደርስ ይደረጋል፡፡
አንድ ባለስልጣን የማዕድን ካምፓኒ ባለቤቱን የስራ ፈቃዱ በቶሎ እንዲወጣለት ከፈለገ ለለጋሽ ድርጅት በርከት ያለ ገንዘብ መስጠት እንደሚጠበቅበት ይነግረዋል፡፡ ለጋሽ ድርጅቱ ሀቀኛ መስሎ ቢታይም ለባለስልጣኖች ለግል ወይም ደግሞ ለቤተሰቦቻቸው ጥቅም ከመዋል ወይም ለፖለቲካ ፓርቲ ክፍያ ሊውል ይችላል፡፡
የማዕድን ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ለማውጣት እንዲችል ካለው አሰራር አንጻር የጤናና የደህንነት ዕቅድ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል፤ ነገር ግን ባለስልጣኑ ለካምፓኒ ባለቤቱ ጉቦ ካልከፈለ በስተቀር ተጨማሪና አላስፈላጊ የጤናና የደህንነት ግዴታዎች እንደሚጫንበት ይነግረዋል፡፡
የማዕድን ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ለማውጣት የአካባቢ ጥበቃ ዕቅድ እንዲያቀርብ ሊጠየቅ ይችላል፤ ይህም የሚያቀርበው ዕቅድ የአካባቢውን የውኃ አቅርቦት ከመርዛማ ኬሚካሎች በአስተማማኝ ሁኔታ ላያስወግድ ይችላል፡፡ አስተማማኝ የመርዛማ ኬሚካሎች ቁጥጥር ለማድረግ ወጭው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰለዚህ የተጓደለውን የቁጥጥር ስርዓት በመከተል ካምፓኒው ብዙ ወጭ ላለማውጣትና በተጓደለው ሁኔታ ለመስራት እንዲችል የስራ ፈቃዱን ለሚሰጠው ባለስልጣን ጉቦ ይሰጣል፡፡
ባለስልጣኖች ከማዕድን ካምፓኒው ትርፍ ድርሻ እንዲኖራቸው ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ የማዕድን ካምፓኒው ባለቤት የስራ ፈቃድ በባለስልጣኑ ውሳኔ መሰረት አገኛለሁ በሚል እምነት ለባለስልጣኑ ዘመድ ከማዕድን ፕሮጀክቱ ነጻ የትርፍ ድርሻ ሊሰጠው ይችላል፡፡
ባለስልጣኖች በድብቅ በእራሳቸው ለተያዙ ካምፓኒዎች የስራ ፈቃድ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ባለስልጣኖች የስራ ፈቃድ ሊጠየቅበት የሚችል መሬት በድብቅ ያገኛሉ፡፡
አንድ ባለስልጣን የአንድ የማዕድን ቦታ የስራ ፈቃድ ይወጣበታል የሚል ግንዛቤ ካለው ባለስልጣኑ የስራ ፈቃዱ ከመውጣቱ በፊት መሬቱን ቅድሚያ ሊያከራየው ይችላል፡፡ የስራ ፈቃዱ ከተሰጠ በኋላ ግን የመሬቱ ዋጋ ሊጨምር ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት ባለስልጣኑ ወይም ባለስልጣኗ በመሬቱ ላይ ያለውን ወይም ያላትን የመሬት ባለቤትነት መብት በመጠቀም ለመሸጥ ወይም ለካምፓኒው የስራ ፈቃድ በመስጠት ለማከራት ይችላሉ፡፡
ካምፓኒዎች የተሰጣቸውን የስራ ፈቃድ ሊሸጡ ይችላሉ፡፡ ባለስልጣኖች የስራ ፈቃድ የምዝገባ ስራን ማጭበርበር ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡
አንድ በመንግስት መ/ቤት መምሪያ የማዕድን ስራ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስችል ባለስልጣን አንድ ካምፓኒ የስራ ፈቃድ ማውጣት እንደሚፈልግ አስቀድሞ ሊያውቅ ይችላል፡፡ በመሆኑም ባለስልጣኑ ካለው ግንኙነት አንጻር የቢዝነሱ ሰው በዚያ ቦታ ላይ በፍጥነት የስራ ፈቃድ ማውጣት እንዲችል ሊያሳስበው ይችላል፡፡ ባለስልጣኑ ለቢዝነሱ ሰው የስራ ፈቃዱን ሊሰጠው ይችላል፡፡ ከዚያም የማዕድን ካምፓኒው ከቢዝነሱ ሰው ጋ የስራ ፈቃዱን ይገዛውና የቢዝነሱ ሰው ከባለስልጣኑ ጋር ትርፍ ሊጋራ ይችላል፡፡
አንድ አሳሽ ማዕድን ያለበትን ቦታ ሊያገኝ ይችላል፡፡ በቦታውም ላይ ምልክት በማድረግ ጉዳዩ ወደሚመለከተው የስራ ፈቃድ ሰጭ አካል ጋ በመቅረብ የባለቤትነት ሰርቲፊኬት ማግኘት እንዲችል ሊያመለክት ይችላል፡፡ ሙሰኛ ባለስልጣን ግን ይህንን ግኝት ተቀብሎ አስሶ ባገኘው ስም አይመዘግብም፤ ይልቁንም የቢዝነስ ጓደኛ በመፈለግ በቢዝነስ ጓደኛው ስም እንዲመዘገብ ያደርጋል፡፡ ይኸ ሙሰኛ ባለስልጣን በመጀመሪያ አስሶ ያገኘውን ሰው ሀሰት በመንገር የማዕድኑን ሀብት ከእርሱ በፊት ሌላ እንዳገኘው ይነግረዋል፡፡
ባለስልጣኖች ዘመዶቻቸው የኮንትራት ስምምነት በመፈራረም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ህገወጥ በሆነ መልኩ ከማዕድን ካምፓኒ ባለቤቶች ጋር እንዲፈራረሙ ያደርጋሉ፡፡ ፈቃድ ሰጭው አካል ኮንትራቱን ከመስጠት አንጻር ወይም ማህበረሰባዊ የልማት ዕቅድን ከማምጣት አኳያ በካምፓኒው ሙሉ ወጭ ብዙ የመሰረተ ልማት ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበት ለካምፓኒው ይነግረዋል፡፡ ለምሳሌ ካምፓኒው መንገድ፤ ትምህርት ቤት ወይም ሆስፒታል እንዲገነባ ወይም አንዲጠግን ሊገደድ ይችላል፡፡ በዚህ መሰረት የመንግስት ባለስልጣኑ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን የመሰረተ ልማት ስራዎች ኮንትራት በድብቅ ለባለስልጣኑ ዘመድ በኮንተራት እንዲሰጥ ይነገረዋል፡፡
ባለስልጣኖችና የአካባቢ ማህበረሰብ መሪዎች ለአካባቢው ማህበረሰብ አባላት መድረስ ያለባቸውን ካሳዎች ይበላሉ፡፡ የማዕድን ስራ ካምፓኒዎች ለማህበረሰቡ የሚሰጡ ካሳዎች ዋጋ ከትክክለኛው ግምት በታች ዝቅ እንዲል ለባለስልጣኖች ጉቦ ይሰጣሉ፡፡
የአካባቢ ኗሪ ማህበረሰብ አባላት በመሬት የስራ ፈቃዱ መሰረት በሀሰት መሬቱን እንዳገኙ ይናገራሉ፡፡ ኮንትራክተሮችና አምራቾች በተጭበረበሩ የጨረታ፣ ይዞታዎችና ችግር ያለባቸውን ስራዎች በመደበቅና በማጽደቅ ይሰማራሉ፡፡
የማዕድን ካምፓኒዎች ስለማዕድኖች ዓይነትና ጥራት ወይም ደግሞ ለአጽዳቂዎች ጉቦ በመስጠት የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ሙስና ይሰራሉ፡፡ በአሁኑ ጊዙ ይህ ዓይነቱን ሙስና በሚመለከት በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የዓለም ባንክ ዘገባ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ የሚታየውን የገዥውን አስተዳደር ከፊል ችግሮች በመጥቀስ ብቃት የለሽነት ማለትም በማሰባሰብ፤ በማሰማራትና የባለሙያውንና የቴክኒካዊ የሰው ኃይሉን፤ የመመሪያዎችን ቁጥጥርና የአስተዳደራዊ ስርዓቱን ደካማነት አጉልቶ አሳይቷል፡፡ ገዥው ስርዓት ከፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታዎች ጋር በተያያዙ ውስብስብ ሁኔታዎች አንጻርና የፈቃድ ጥያቄዎች እየበዙ ከመምጣት አኳያ ጥያቄውን በተገቢው ሁኔታ ለመመለስ የሚያስችል በብቃት የሰለጠነ ፈቃድ የሚሰጥ የሰራተኛ ኃይል የለውም፡፡ ፈቃድ ከመስጠት አኳያና ገቢን ከማስላት አንጻር የማዕድን ስራውን ሂደት የሚገመግሙና በፈቃድ ስምምነት ሁኔታዎች ላይ ክትትል የሚያደርጉ እንዲሁም ካምፓኒዎች በትክክል ለመሬት ኪራይ የሚከፈለውንና በምርትና በትርፍ ላይ የሚጣለውን የገቢ ግብር የሚገመግሙና ቁጥጥር የሚያደርጉ ባለሙያዎች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ አካባቢን፤ ጤናንና ደህንነትን እንዲሁም ማህበራዊ ሁኔታዎችን የሚያስቃኙ የስራ ፈቃድ ከመስጠት ጋር በተያያዘ መልኩ የተዘጋጁ ዝርዝር መመሪያዎች የሉም፡፡ የዝርዝር መመሪያዎች አለመኖር በፈቃድ አሰጣጥና ክትትል ወቅት እርግጠኛ አለመሆንን በማስከተል ለሙስና በር ይከፍታል፡፡
የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት በሁለተኛነት ደረጃ የሚይዘው እንዲሁም ዘርፉን በበላይነት የሚቆጣጠረውና የሚያስተዳድረው የማዕድን ሚኒስቴር በጠቅላላ ቁጥጥር የስራ ክፍሉ ውስጥ 13 ብቻ ሰራተኞችና በመላ ሀገሪቱ ተሰራጭተው የሚገኙትን 160 የፌዴራል የስራ ፈቃዶች የሚቆጣጠሩ 3 የአካባቢ ተቆጣጣሪዎች ብቻ መኖራቸው ለማመን የሚያስቸግር እንደሆነ ያመለክታል፡፡
የጸረ-ሙስና ጦርነት ወይም የይስሙላ ሙስና?
ገዥው ስርዓት በወረቀት ላይ ሙስናን በውል ለመለየት፤ ለመከላከል፤ በህግ ለመዳኘትና ቅጣት መቅጣት የሚያስችሉ ህጎች አሉት፡፡ “የፌዴራል ስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 235/2001 እና A33/2005” ሲቋቋም የወንጀለኛ ህግ መቅጫ በሙስና እና ከሙስና ጋ ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች በሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ላይ ከፍተኛ ቅጣትን ጥሏል፡፡ እነዚህ ህጎች ግን የተጻፉበትን ወረቀት ያህል ዋጋ የላቸውም፡፡ ህጎቹ እየተመረጡ የገዥው ስርዓት ባለስልጣናት የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቂያነት እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ በህይወት የተለዩት የገዥው ስርዓት ቁንጮ የጸረ ሙስና ህጎችን የፓርቲው የመጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረሩትን (ታምራት ላይኔ)፤ የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩትን (ስዬ አብርሀ) እና ሌሎች በስርዓቱ የተጠሉትን ሰራተኞች ለማጥቂያነት በዘዴ ተጠቅመውባቸዋል፡፡ በቅርቡ በሙስና በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያለው ቡድን በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረው ቡድናዊ ያለመግባባት ትግል መገለጫ እንጅ በእውነትና የጸረ-ሙስና ህጉን በጽናት ለመተርጎም ታስቦ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ እነዚህን በቁጥጥር ስር ማዋል ደግሞ ዋና መልዕክቱ ገዥውን ስርዓት ወደፊት ይቃወማሉ ብለው ለሚጠረጥሯቸው ተቃዋሚ ኃይሎች ማስፈራሪያና አፍ ማስያዣ ነው፡፡
የሙስና የፍርድ ሂደት ለገዥው ስርዓት ጠንካራ አርጩሜና በአገሪቱ ያሉ የተቃዋሚ ፖለቲካ አባላትንና የንግዱን ማህበረሰብ አንገት በሸምቀቆ ለማስገባት የተዘየደ ነው፡፡ እውነታው ግን በአሁኑ ጊዜ በሙስና ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣን ኃላፊዎች በእርግጥ ጥፋተኞች ናቸው ከተባሉ የእነርሱ አሳሪዎችም ከእነርሱ እኩል የወይም በለጠ ጥፋተኞች ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በአንክሮ እንደተመለከትኩት ወደ ኋላ መለስ ብለን የኢትዮጵያን አባባል በመጥቀስ “ከዝንጀሮ ቆንጆ ምኗን ይመርርጧል” የሚለውን አባባል እንድናስታውስ እንገደዳለን፡፡
የዓለም ባንከ የ2008 ዓመታዊ የስነምግባርና የጸረ- ሙስና ኮሚሽን የስራ ሪፖርት መሰረት በማድረግ የገዥውን ስርዓት በጠራራ ፀሐይ በሚሊዮኖች የሚያወጣ አስደንጋጭ የወርቅ ዘረፋ አስመልከቶ የሚከተለውን አስፍሯል፡፡
በበጀት ዓመቱ በብሔራዊ ባንክ የተፈጸመ ሌላም ታላቅ ቅሌት ተስተናግዷል፡፡ ይህም ክስተት በብዙዎች ዘንድ “የዓመቱ ታላቁ ቅሌት” የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶታል፡፡ ማጭበርበሩ እንዲህ ተከስቷል፤ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ ማስቀመጥና መግዛት በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ነው፡፡ ለብሔራዊ ባንክ ወርቅ እንዲያቀርቡ የተፈቀደላቸው ጥቂት የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ወርቅ በማቅረብ ፈንታ ብዙ ኪሎ ግራም የሚመዝን የተጠፈጠፈ ብረት ወርቅ ቀለም ቀብተው አቀረቡ፡፡ በዚህ አደገኛና አስቀያሚ ቅሌት ውስጥ የባንኩ ጥቂት ሰራተኞች፤ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፤ ማኔጀሮችና ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች ተሳትፎ እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡ በዚህ ታማኝነት በጎደለው የወርቅ ማጭበርበር ቅሌት ምክንያት መንግስት 16 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲያጣ ተደርጓልል፡፡
አገዛዙ ሙስናን ለመዋጋት የሚያደርጋቸውን የይስሙላ እንቅስቃሴዎች መንግስት እራሱ የሚያወጣቸው ሪፖርቶች እውነታውን ይናገራሉ፡፡ ከመንግስት በተገኙ ዘገባዎች መሰረት በጠቅላላ በፌዴራል ደረጃ 422 ሙስና ጉዳዮች ፋይል ተከፍቶላቸው: ከእነዚህ ውስጥ 57ቱ ወይም 13.5 በመቶው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡ አገዛዙ በስነ ምግባርና በጸረ-ሙስና ኮሚሽን የስራ እንቅስቃሴ ላይ ጣልቃገብነት ስለሚያደርግ የኮሚሽኑ ግኝቶችና ዕቅዶች ብዙ ጊዜ በተግባር ላይ ሲውሉ አይታዩም፡፡ የአገዛዙ የሚጠበቀው ምላሽ በሙስና የተጠረጠሩበትን ሁኔታ መካድና የቀረቡትን ትችቶች ባልሰለጠነ መልኩ መልሶ መተቸት ነው፡፡ እውነታው ግን የጸረ-ሙስና ትግሉ እየተባለ የሚደሰኮረው ዓለም አቀፍ አበዳሪዎችንና ለጋሽ ድርጅቶችን ለማታለልና እውነተኛ ትግል በማስመሰል እርዳታ ለማግኘት የተቀነባበረ የመድረክ ትወና ነው፡፡ የበርቴልስማን ፋውንዴሽን የ2012 የኢትዮጵያ አገራዊ ሪፖርት የአገዛዙን የጸረ-ሙስና ጦርነት ባዶነት በግልጽ ያስረዳል፡-
የኢትዮጵያ የስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በመንግስት ተመስርቶ እስከ አሁንም ድረስ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለ ተቋም ነው፡፡ ቀልጣፋነቱ ትልቅ ነው የሚባል ተቋምም አይደለም፡፡ ህጉን የሚጥሱትና የሙስና ድረጊቶችን የሚፈጽሙ የመንግስት ባለስልጣናት ጉዳይ ለህግ አይቀርብም፤ አንዳንድ ጊዜ ግን ለመንግስት ታማኝ ያልሆኑ የመንግስት ሰራተኞችን በሙስና ሰበብ በመያዝ ለብዙሀን መገናኛ ፍጆታ ያውሉታል፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት የሚፈጽሙት ሙስና በውል እንዲመረመር አይፈለግም፤ ወይም በማንኛውም ደረጃ ጉዳያቸው በፍርድ እንዲታይ አይደረግም፡፡ ጥቂት የኢህአዴግ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በህገወጥ መንገድና በሙስና አማካይነት ሀብት አካብተዋል፡፡ ግልጽነት የጎደላቸውና በሙስና የተዘፈቁ
ሆኖም ግን ለመንግስትና ለገዥው ፓርቲ ቅርብ የሆኑ በርካታ ካምፓኒዎች አሉ፡፡ የጸረ-ሙስና ፖሊሲው በምንም መልኩ ስኬታማ ሊሆን አልቻለም፡፡ የቁጥጥርና ሚዛኑን ስልት ፍጹም በሆነ መልክ አጥፍቶ የሚዋቀር የፖለቲካ ስርዓት በምንም ዓይነት መልኩ የፖለቲካ መቻቻልንና ፍትሀዊነትን የተላበሰ ባህል ሊያጎናጽፍ አይችልም፡፡ የሕወሀትና የኢህአዴግ አራቱ ተጣማሪ ፓርቲዎች አመለካከት በታማኝነት እሴት ባህል የተሞላና ጊዜው ባለፈበት የጦርነት የአስተሳሰብ ባህል የተዘጋ ነው፡፡
እነሱ ዎርቅ ያፍሳሉ፣ ኢትዮጵያውያን አፈር አቅም በሌለው አገዛዝ መሪነትና የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት እንዲሁም አምራች ድርጅቶች በቅልጥፍና በማይሰሩና ጠንካራ የአስተዳደር ስርዓት ዝርጋታ በሌለበት ሁኔታ የማዕድን ዘርፉ በቀላሉ ለሙስና ዒላማ የተጋለጠ ይሆናል፡፡ ይህ ቢባልም ማንም ሊስተው የማይችለው እውነታ ግን የአገዛዙ አቅመቢስ መሆን በበቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል የተጠናከረ አለመሆን የማዕድን ዘርፉ ተጠያቂነትና ክትትል የማይደረግበት ውስብስብ እና የተሰላ ስልት ነው፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የአገዛዙ ባለስልጣኖችና ተባባሪዎቻቸው በሙስና መረብ ውስጥ አስካሉ ድረስ ሙስናን ለመለየት፤ በሙስና የተዘፈቁትን ባለስልጣኖችና ተባባሪዎቻቸውን እንዲሁም በማዕድን ዘርፉ የተሰማሩትን የውጭ ተወካዮችን ይዞ ሙሰኞቹን በህግ ለመጠየቅና ቅጣት ለመስጠት ፈጽሞ የሚቻል አይሆንም፡፡
ማጭበርበር፤ በህገወጥ መንገድ ወይም ሀይልን በመጠቀም ጥቅም ለማግኘት መሞከር፤ በሙስና ገንዘብ ማግኘት፤ እምነተ ቢስ መሆን፣ ሁለት ምላስ መጠቀም፤ በማስፈራራት ገንዘብ መውሰድ፤ ማዋረድ እና የመሳሰሉት በማዕድን ዘርፉ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ የተንጠለጠሉ የሙስና ፍራፍሬዎች ናቸው፡፡ የዓለም ባንክ ዘገባ እንደሚያሳየው በማዕድን ዘርፉ ተሳትፎ ያላቸው የአገዛዙ ባለስልጣኖች በፈቃድ አሰጣጥ ላይ፤ ስምምነት በመዋዋልና ገቢን በማረጋገጥ ሂደት ላይ የተፈጠሩትን ድክመቶች በመጠቀም ለሙስና ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ፡፡ በአጠቃላይ አገዛዙ ተጠያቂነት በሌለውና ድብቅ በሆነ መልኩ የሚሰራ ስለሆነ የትክክለኛ ሪፖርት መቅረብ ጥየቄዎችን ያስነሳል፡፡ ለምሳሌ ከማዕድን ዘርፉ ወደውጭ ተልኮ የተገኘው 419 ሚሊዮን ዶላር ከማዕድን ዘርፉ የተገኘ መሆን አለመሆኑን በእርግጠኝነት የሚያረጋግጥ የለም፡፡ የዚህን መጠን እጥፍ ወይም 3 ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ቁጥሩ ለህዝብ ከመገለጹ በፊት ከላይ ያሉ ባለስልጣኖች የራሳቸውን ድርሻ ይቆርጣሉ፡፡ አገዛዙ ነጻ የሆነ ኦዲተር ስማይታገስ ከማዕድን ዘርፉ የሚገኘው ገቢ አስተማማኝ መሆኑን ለማረጋገጥ ነጻ በሆነ ኦዲተር መረጋገጥ አለበት፡፡ ለማስተዋስ ያህል በእ.አ.አ 2006 የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ዋናው ኦዲተር 4.8 ቢሊዮን ብር በፌዴራል መንግስቱ በጀት ድልድል ውስጥ ያልተካተተ ነው ብለው ሪፖርት ሲያቀርቡ ከሰራ ተባረዋል፡፡ በበእ.አ.አ 2009 ተተኪው ዋና ኦዲተር የመንግስትን በከፍተኛ ደረጃ መበደር እና አየጨመረ በመጣው የዋጋ ግሽበት ላይ ትችት በማቅረባቸው እንዲባረሩ ተደርጓል፡፡
በበእ.አ.አ 2011 ላይ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቴ የተባለው ድርጅት ባዘጋጀው ሪፖርት ኢትየጵያ 11.7 ቢሊዮን ዶላር በ2000 እና በ2009 ባሉት ዓመታት መካከል በህገወጥ መልክ ከሀገር ውጭ ሄዷል ብሎ አትቷል፡፡ ሪፖርቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ተዘርፏል በማለት አጠቃሏል፡፡ ኢትዮጵያ ከከፋና ከከረፋ የድህነት አረንቋ ለመውጣት ጥረት እያደረገች ቢሆንም በህገወጥ የካፒታል መውጣት እየዋኘች ትገኛለች፡፡ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ቀደም ሲል “ኢትዮጵያ እየተዘረፈች ያለች ሀገር“ በሚል ርዕስ ትችት ማቅረቤ ይታወሳል፡፡
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በ2001 በግልጽ እንዳስቀመጡት የሙስናው ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ የመንግስት ድርጅቶችን እያጠቃ እንደሚገኝ ጠቅሰው መንግስት በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ብቸኛ መለያ እየሆነ የመጣውን ሙስናና ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ለማስቆም በርትቶ መስራት እንዳለበት አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ በ2013 የሙስናው እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ወቅት ሲሆን መንግስት ለስለስ ባለ መልኩ እየተከላከለው ይገኛል፡፡
አገዛዙ ጥቂት የንግዱን ማህበረሰብ አባላትና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናትን በማጥመድ የጸረ-ሙስና ትግሉን እያጠናከረ መሆኑን ለህዝብ ለማሳየት ሞክሯል፡፡ አገዛዙ ለሙስና ምንም ዓይነት ትዕግስት እንደሌለው ለማሳየት መሞከር አለበት፡፡ ይህም ማለት መንግስት የተቀነባበር የሙስና ማስወገጃ ዘዴዎችን (ህጎችን፤ ደንቦችን እና መመሪያዎችን) ግልጽነት ባለው ሁኔታ በማውጣት፤ ጠንካራ የምርመራ ስርዓትን በመጠቀምና የፍርድ ሂደቱን በማጠናከር እንዲሁም የሲቪሉን ማህበረሰብ ተሳትፎ በማሳደግና የቁጥጥርና ክትትል ስርዓቱን በማጎልበት የባለስልጣናቱን ሙስና ማጋለጥ አለበት፡፡ ይህም ሆኖ በሙስና በምትዳክረው ሪፑብሊክ ኢትዮጵያ: ሙስና በቅርብ ጊዜ የመጥፋቱ ሁኔታ በጣም አጠራጣሪ ነው፡፡ የፕሬዚዳንትነት ስልጣኑን የተቆጣጠረችው የመጀመሬዋ ሴት የህንድ ፕሬዚዳንት ፕራቲብሃ ፓቲል በግልጽ እንዳስቀመጠችው “ሙስና የመልካም አስተዳደርና የልማት ጸር ነው፤ መወገድ አለበት፤ መንግስትና በአጠቀላይም ህዝቡ በአንድ ላይ ተባብሮ ሙስናን የማስወገዱን አገር አቀፋዊ ዓላማ ማሳካት ይኖርበታል“ በማለት ሀሳቧን አጠቃላለች፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሙስናን ለማስወገድ ፍላጎቱም፤ ችሎታውም፤ ዝግጁነቱም አለው፡፡ ነገር ግን ስራውን በብቃት ለማከናወን ብቃት ያለው መንግስት ያስፈለገዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሙስናን ማዕድን ለማውጣት የለገደንቢን ብጫ የወርቅ መንገድ ተከተል!    ECADF Ethiopian News