tirsdag 29. juli 2014

በአሜሪካ ጠፍተው ከነበሩት አራት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሦስቱ ተገኙ

ጠፍተው ከነበሩት አራት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሦስቱ ተገኙ
140728missing-athletes660
በአይኤኤፍ የአለም ተተኪ ሻምፒዮንሽፕ ለመካፈል ወደ አሜሪካ የኦሪገን ክፍለ-ግዛት ዩጂን ከተማ ከመጡት በርካት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አራቱ ሰሞኑን መጥፋታቸው በተለያዩ የዜና ምንጮች ሲዘገብ ቆይቷል:: ዛሬ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ሶስቱ መገኘታቸውን ገልጿል::
አማኑኤል አበበ የ17 አመት፣ ዱሬቲ ኢዳኦ የ18 አመት፣ መዓዛ ከበደ የ18 ዓመት፣ በሙሉ ደህንነት ከሚያቋቸው ሰዎች ጋር እዛው በኦሪገን ክፍለ-ግዛት ቤቨርተን ወረዳ አርፈው እንደሚገኙ ታውቋል:: እስከ አሁን ያልተገኘችው የአትሌት ዘይቱና መሃመድ ጉዳይ በፖሊስ የጠፋሰው መዝግብ ስር ነው::
ምንጭ:-kval.comh

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar