mandag 28. oktober 2013

ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?

እሳት አስነሳችሁ በሚል እስሩ ቀጥሏል

fire
በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተቃውሞ ቢያቀርቡም የኢህአዴግን ጆሮ ማግኘት ያልቻሉ ተበዳዮች ርምጃ ወሰዱ። ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት ከዘረፋ ተለይቶ እንደማይታይ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ውድመት የደረሰበት የህንድ ኩባንያ በልማት ባንክ ላይ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት አለ። ለደረሰው ጉዳት “ተጠያቂው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ተነስቷል። በጥርጣሬ የሚታሰሩ መበራከታቸው በክልሉ ባሉ ተመሳሳይ የእርሻ ኢንቨስትመንት ባለቤቶችን ስጋት ላይ ጥሏል።
ሻይ ቅጠል ለማልማት የተፈጥሮ ጥብቅ ደን እንዲያወድም የተፈቀደለት ቬርዳንታ ሀርቨስት የተባለ ኩባንያ በከፍተኛ ወጪ ያለማውና ለመለቀም በደረሰ ምርት ላይ ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች እሳት ለቀውበታል። ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓም ደረሰ በተባለው ቃጠሎ ኩባንያው የደረሰበት ሊሳራ እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ አስታውቀዋል።
አንጋፋ እድሜ ጠገብና ረዣዥም የተፈጥሮ ደን በመጨፍጨፍ ጣውላ እያመረተ ሲቸበችብ የነበረው ኩባንያ ሙሉ ንብረቱና ከፍተኛ መጠን ያለው የጣውላ ምርት ከተለያዩ ማሽኖች ጋር ወድሞበታል። የአካባቢው የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኩባንያው ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ለመሰብሰብ የደረሰውን የሻይ ቅጠል ማሳ አጋይቶታል።
በጋምቤላ ክልል በመዠንግር ዞን፣ በጎደሬ ወረዳ በጉማሬና በካቦ ቀበሌዎች የሚገኝ 5000 ሄክታር በደን የተሸፈነ መሬት በኢንቨስትመንት ስም እንዲሸጥ መወሰኑን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ አሰምተው ነበር። በወቅቱ ውሳኔውን “በባዕድ ወራሪ ሃይል እንኳን የማይፈጸም” በማለት የተቹና ቅሬታቸውን የገለጹ ነበሩ።
ሙሉ በሙሉ በደን የተሸፈነ 3012 ሄክታር ድንግል ለም መሬት በሄክታር111 ብር ሂሳብ ለ50 ዓመት የሊዝ ኮንትራት የተሸጠለት ይህ ኩባንያ ጥብቅ ደኑን ከማውደሙ በፊት ውሳኔው እንዲጤን የአካባቢው ህዝብ በወኪሎቹ አማካይነት ለፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጥያቄ አቀርበው ነበር። በወቅቱ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጊቱን በመቃወም የሚከተለውን ጽሁፍ አትሞ ነበር። ሰሚ ባለመገኘቱ የተፈራው ደረሰ።
ጡረተኛው ፕሬዚዳንት ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የተፈጥሮ ደኑ ከመጨፍጨፉ በፊት ውሳኔው እንዲመረመርና እንዲጠና ሚያዚያ 28 ቀን 2002 ዓ ም ለክልሉ ደብዳቤ ልኮ ነበር። ሟቹ ጠ/ሚኒስትር በወቅቱ የአፍሪካ የተፈጥሮ ጥበቃና የአየር ንብረት ተሟጋች ነኝ ያሉበት ወቅት መሆኑንን በማስታወስ፣ የፕሬዚዳንቱን መመሪያ በመጠቆም ባለስልጣኑ የጻፈውን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የክልሉ ፕሬዚዳንት ህዳር 10 ቀን በተጻፈ ደብዳቤ ደመሰሱት። ከላይ የተጠቀሰው ኩባንያ የ50 ዓመቱን ውል ቅድሚያ ክፍያ የአንድ ዓመት 19 ሺህ ዶላር ስለከፈለ ቦታውን እንዲረከብ ዞኑንን አዘዙ።
የበላይና የበታቹ በማይታወቅበት የመለስ አወቃቀር ጥብቅ ደኑ ያለበት መሬት ለህንዱ ኩባንያ ተላለፈ። ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ እስከ ፕሬዚዳንቱ ያደረሱት ሊቀመንበር እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው ከሃላፊነታቸው ተባረሩ። ህዝብ የኑሮው መሰረትና የህይወቱ ያህል የሚንከባከበው ደን ተጨፈጨፈ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ደኑ ሲጨፈጨፍ የነበረው ሃዘን በቃል የሚገለጽ አልነበረም።timber log
ባገኘው ከፍተኛ የደን ምርት ጣውላ ማምረት የጀመረው ኩባንያ መጋዘን ገንብቶ የጣውላ ንግድ ውስጥ ገባ። አሁን ድረስ ንዴቱና የበደል ስሜቱ ያለቀቀቃቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የተካሄደባቸውን ግፍ “ዝርፊያ” እያሉ ነው የሚጠሩት።
ህግን ጠብቀው ኢህአዴግን ያሳሰቡት የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ቢሆን በእስርና በድብደባ በማሰቃየት ኢንቨስትመንትን /ነዋሪዎቹ ዝርፊያ ነው የሚሉት/ በክልሉ ቀጣይ ማድረግ አይቻልም። አስቀድሞ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ኢህአዴግና ኩባንያው ጆሮ ሰጥተዋቸው ቢሆን ኖሮ እንዲህ ያለ አደጋ ሊፈጠር እንደማይችል አስተያየት ሰጡ አሉ።
92 ሚሊዮን ብር በላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እዳ ያለበት የእርሻ ድርጅት፣ ንብረቱ በእሳት ከወደመ በኋላ የተሸከመው እዳ አጀንዳ ሆኗል። የደረሰበት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ክልሉንና ኢህአዴግን ካሳ እንደሚጠይቅም ከወዲሁ ተሰምቷል። ዜናውን ያቀበሉ ክፍሎች “ህዝብ ላልተቀበለው ኢንቨስትመንት ካሳና የልማት ባንክ ላይ ለደረሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው” የሚል ጥያቄ መነሳቱን አመልክተዋል።
ለአበባ እርሻ ላስቲክና ኬሚካል በማስያዝ ልማት ባንክን እያለቡ የተሰወሩ በርካታ ድርጅቶችና ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ሸሪኮቻቸው መኖራቸውን በማስታወስ በጋምቤላ ተመሳሳይ ድርጊት ሊፈጸም እንደሚችል የዜናው ምንጮች ጠቁመዋል። ካራቱሪ በኪሳራ መንገዳገዱን፣ ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በ”ውክልና” ለሳዑዲ አረቢያ ቀለብ እንዲያመርት የተከሉት ሳዑዲ ስታርና ሌሎች የህወሃት ሰዎች ከተለያዩ የአገር ውስጥ ባንኮች ከፍተኛ ገንዘብ መበደራቸውን ገልጸዋል።
“ህዝብን ያለፈቃዱ በማፈናቀልና መሬቱን በመቀማት የሚከናወን ኢንቨስትመንት ሁሌም አደጋ ላይ መሆኑ አያጠራጥርም” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ገልጸዋል። “ኢንቨስትመንት እንኳን ደህና መጣህ በሚል ህዝብ ካልተቀበለው ዘረፋ ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ “በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ድምጹን ሲያሰማ ጆሮ ያጣ ህዝብ ተቃውሞውን ገለጸ” በማለት በደረሰው ውድመት ባይደሰቱም ለውድመቱ ተጠያቂው ኢህአዴግና ከኢህአዴግ ጋር ተሻርኮ ዝርፊያ ያከናወነው ድርጅት እንደሆነ አመልክተዋል።
ካሩቱሪና ሳዑዲ ስታርን ጨምሮ ህዝብ ላይ በተፈጸመ ግፍ ሃብት ለማፍራትና ለመበልጸግ የሚያስቡ ትልቅ ግንዛቤ ሊወስዱ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ኦባንግ “ኢህአዴግ ዝርፊያና ኢንቨስትመንትን ለይቶ መሔድ ካልቻለ ስጋቱ እየጨመረ ይሄዳልና ከስህተት በመመለስ ህዝብ በሚፈቅደው መልኩ ማስተናገድ ግድ ነው” ሲሉ አሁንም ጆሮ የለውም ለሚባለው ኢህአዴግ ማሳሰቢያ አዘል ምክር ለግሰዋል። ባለሃብት የሚባሉትም ከዚህ ታላቅና አሳዛኝ ውድመት ሊማሩና ህዝብ “እንኳን ደህና መጣችሁ እንዲላቸው ህዝብ ከሚቃወመው ዝርፊያና አሰራር ራሳቸውን ሊያገሉ ይገባል” ብለዋል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት ቃጠሎውን ማመናቸውን ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ያስታወቀ ሲሆን አጣሪ ኮሚቴ ተቃቁሞ አደጋውን ያደረሱት እነማን ናቸው የሚለው እየተመረመረ እንደሆነ ጠቁሟል። የክልሉ የጎልጉል ምንጮች በርካታ ሰዎች እሳት አስነስታችኋል በሚል መታሰራቸውና በፌዴራል አንጋቾች እየተመረመሩ መሆኑን አረጋግጠዋል። እሳት ያስነሱትን ለማጋለጥ በሚል በየመንደሩ በሚደረግ ማዋከብ ነዋሪዎቹ መማረራቸውን ተናግረዋል። ለጊዜው የእስረኞች ቁጥር ባይታወቅም ወደ ማዕከል የተላኩ በርካታ እንደሆኑም ገልጸዋል። በማያያዝም ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ኢህአዴግም ሆነ ማንም ተጠቃሚ ስለማይሆን ህዝብን ማዳመጥ ሊቀድም እንደሚገባው ጠቁመዋል። (ፎቶ፡ ለማሳያነት ብቻ)

tirsdag 22. oktober 2013

ዶ/ር መረራ የፍንዳታውን ዜና “እንጠራጠረዋለን” አሉ

"በአዲስ አበባው ፍንዳታ የሞቱት ኢትዮጵያዊያን ናቸው"

bole 1

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ሰፈር የደረሰውን ፍንዳታ አስመልክቶ ኢህአዴግ ያሰራጨውን ዜና የሚቃረኑ መረጃዎችና አስተያየቶች ቀረቡ። ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የድጋፍ አስተያየት ሲሰጡ ዶ/ር መረራ “አትፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አያጠፋም” ሲሉ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በፍንዳታው የሞቱት ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲል ስም ገልጾ የኢህአዴግን ዜና አጠጥሎታል።
በፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የጠየቁት ከኢህአዴግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚታሙ ፓርቲዎች “የጸረ ሽብርተኞች አዋጅ ሊጠናከርና ሊጠብቅ ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የኢራፓ፣ የኢሴዳፓ፣ ቅንጅትና አዲአን ተወካዮች በየተራ የኢህአዴግን ዜና የሚቃወሙና በጥርጣሬ የሚመለከቱትን አውግዘዋል። በወቅቱ የቴሌቪዥን ጣቢያውም አንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ጠርተውት በነበረው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ “የጸረ ሽብርተኛነት አዋጅ ለሌላ ተግባር መዋሉን እንቃወማለን” በማለት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ በማሳየት ዜናውን ለማጀቢያነት ተጠቅሞበት ነበር።
በግል አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው “ብዙዎች፣ እኔም ጓደኞቼም በጥርጣሬ ነው ያየነው” ሲሉ ከተቆረጠው ንግግራቸው ተደምጧል። ዶ/ር መረራ “አጥፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ ራሱን አያጠፋም” ካሉ በኋላ “ስለዚህ እውነት ተደርጓል?” የሚለው ትልቁ ችግርና የጥርጣሬው መነሻ እንደሆነ አመልክተዋል።
ስለዚህ በሚል ድምዳሜ “ሰው አንዳንድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ለራሱ ፖለቲካ ብሎ የሚያደርገው ያው የለመደው ስራ ነው” እንደሚል ዶ/ር መረራ በተቀነጨበው አስተያየታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል። በተቃራኒ ከላይ በስም የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማና የአልሸባብ ስጋት ላይ ያለች አገር በመሆኗ ኢህአዴግ ህዝብን የመጠበቅና ደህንነትን የማስጠበቅ አደራ ስላለበት እነሱን ጨምሮ እንዲጠብቃቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ የሚነሳውና በታጣቂ ሃይሉ ፈርጣማነት የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ  /ትህዴን/ በቦሌ ክፍለ ከተማ በቤት ውስጥ ፈነዳ በተባለው ፈንጂ ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸው ሁለት የሶማሌ ዜጎች አይደሉም ሲል ከሁሉም ወገን የተሰራጨውን ዜና በዜሮ አጣፍቶታ። በፈንጂው የሞቱት ሁለት ሰዎች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ስማቸውም “ምክትል ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባሉ የፖሊስ አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባሉ ሲቪል ናቸው” ሲል የገለጸው ትህዴን የሟቾቹ ስም በመታወቂያ መረጋገጡን አመልክቷል።የመታወቂያውን ቅጂ ግን በገጹ አላተመም። ከአደጋው ጋር በተያያዘ በስፍራው ታይታችኋል በሚል በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን በመግለጽ የሶስት እስረኞችን ስም ይፋ ያደረገው ኦክቶበር 19 ቀን 2013 በራሱ ኦፊሳላዊ ድረገጽ ላይ ነው። ኢህአዴግም ቢሆን ሞቱ የተባሉትን ሰዎች ይህ ዜና እስከተጻፈበት ቀን ድረስ በሰነድ አስደግፎ አላቀረባቸውም።
በሌላ በኩል ኦክቶበር16 ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 3ቀን 2006ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ማዞሪያና ቦሌ ሚካኤል መግቢያ አካባቢ በቦምብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈው ሁለት ሶማሊያውያን ሽብርተኞች መሆናቸውን ማረጋገጡን፣ የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ማስታወቁን ዘግቧል።
Bomb-Blast-Addisየአንድ ግለሰብ ሰርቪስ ቤት ተከራይተው ከነበሩት ሶማሊያውያኑ መካከል፣ አንደኛው ከ20ቀናት በላይ የቆየ ሲሆን፣ ሌላኛው ፍንዳታው ከመድረሱ ከሁለት ሰዓታት በፊት የደረሰ መሆኑን ግብረ ኃይሉ ማረጋገጡን ያመለከተው ሪፖርተር ሽብርተኛ የተባሉት ሶማሊያውያኑ ካፈነዱት ቦምብ በተጨማሪ መጠናቸው ያልተገለጸ ቦምቦችና አንድ ሽጉጥ ከሁለት ካርታ ጥይት ጋር መገኘቱን፣ የፈንጂ ማቀጣጠያና የአደጋ መከላከያ ጃኬቶች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሊያና ቀበቶዎች መገኘታቸውም ጠቁሟል፡፡ ከሶማሊያውያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎችና የቤቱ አከራይ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄባቸው መሆኑንም ግብረ ኃይሉ አክሏል በማለት ሪፖርተር ዘግቧል። አዲስ አድማስ በበኩሉ አልሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነት መውሰዱን አድራሻው አልተመዘገበ የትዊተር ማረጋገጫ በማመላከት ከዚህ በታች ያለውን ዜና አስነብቧል።
ባለፈው እሁድ በቦሌ ሚካኤል አካባቢ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ሁለት ተጨማሪ የፍንዳታ ጥቃት ለማድረስ አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ቡድን እንደዛተ የገለፀው የአሜሪካ ኤምባሲ፤ የዛቻው ተአማኒነት ባይረጋገጥም በኢትዮጵያ የሚገኙ አሜሪካዊያን ጥንቃቄ እንዳይለያቸው ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ በመግለጽ ዜናውን የከፈተው አዲስ አድማስ፣ “የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ቡድኖች ግጥሚያ በሚካሄድበት ሰዓት ጥቃት ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ሁለት ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት በማወጅና ሽብር ለመፈፀም በመዛት የሚታወቀው አልሸባብ “ድርጊቱ በኔ አባላት የተፈፀመ ነው” ብሏል በማለት አልሸባብ በቦሌ ሚካኤል ለተከሰተው ፍንዳታ ሃላፊነት እንደሚወስድ በትዊተር እንዳስታወቀ ማሰራጨቱን፤ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አካባቢ የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እንደዛተም ገልጿል፡፡
በቦሌ ሚካኤል በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተከሰተው ፍንዳታ ሁለት የሶማሊያ ተወላጆች መሞታቸውን የገለፀው ፖሊስ፤ ከሟቾቹ አንዱ የኢትዮጵያ ማሊያ በመልበስ ከኳስ ተመልካቾች መሃል የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደነበር መጠቆሙን አዲስ አድማስ በዜናው አውጇል። አዲስ አድማስም ሆኑ ሪፖርተር ፖሊስ የነገራቸውን ከመዘገብ ውጪ ከሌሎች ሚዲያዎች፣ በተለያዩ ማህበረ ገጾችና በቅርበት ከህብረተሰቡ የሚሰጡትን አስተያየቶች አስመለክቶ ዜናውን ላቀበላቸው ክፍል አላቀረቡም።
የኢህአዴግ አንደበትና የንግድ ድርጅት የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የደረሰው የፈንጂ ፍንዳታ በሁለት ሶማሊያውያን አሸባሪዎች የተፈፀመ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አብዩን ጠቅሶ አስታውቋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳለው ፍንዳታው የደረሰው በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ቀበሌ 01 በተለምዶ ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በአንድ የመኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። ፖሊስ ፍንዳታው ፈንጂ መሆኑንና በጥቅም ላይ የዋለው ቲ ኤም ቲ የተባለ የፈንጂ ዓይነት መሆኑን እንደደረሰበት አረጋግጧል። ፍንዳታውንም ሁለት ሶማሊያውያን ማቀነባበራቸውን ፖሊስ እንዳረጋገጠና ግለሰቦቹ የአሸባሪ ቡድኑ አልሸባብ አባል መሆናቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን ጄኔራል አሰፋ አብዩ መናገራቸውን የጠቆመው ፋና ከሁለቱ አሸባሪዎች መካከል አንደኛው ወገቡ ላይ የታጠቀና ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር የተዘጋጀ መሆኑን ያመላክታል ብሏል።
ሌላኛው አሸባሪ በሻንጣ ፈንጂ የያዘ ሲሆን፥ የፈነዳውም ፈንጂ በሻንጣው ውስጥ የነበረ መሆኑን ነው ጀነራል አሰፋ ያስረዱት። ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር ሲዘጋጅ የነበረው ግለሰብ የታጠቀው ፈንጂ ግን እንዳልፈነዳ አመልክተዋል። አሸባሪዎቹ በአጠቃላይ ሶስት ፈንጂዎችንም ይዘው ነበር። አሸባሪዎቹ ህዝብ ባለበት ስፍራ አደጋ ለማድረስ ተከራይተው በነበሩበት ቤት ውስጥ ሲዘጋጁ ፍንዳታው ደርሷል ብሎ ፖሊስ እንደሚጠረጥር ነው የጠቆሙት። ከአሸባሪዎቹ ጋር ፖሊስ የእጅ ቦምቦችንና ሽጉጥ ከነጥይቱ አግኝቷል።
የፋናን ዜና ተንተርሶ የተሰነዘሩ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ሪፖርተር በፈነዳው ፈንጂ ህይወቱ ያለፈው አንደኛው ሰው ሰውነቱ መበታተኑና የአይን እማኞችን ገልጾ መዘገቡን ያስታውሳሉሉ። ፈነዳ የተባለው ፈንጂ ከፈነዳ በሁዋላ አጥፍቶ ለመጥፋት የተዘጋጀው ሰው የታጠቀው ፈንጂ አለመፈንዳቱ መገለጹ ከሙያ አንጻር ጥያቄ የሚያስነሳ እንደሆነ፣ ከዚህም በላይ ድርጊቱን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ጋር ለማገናኘት የብሔራዊ ቡድን መለያ ሹራብ ተገኘ መባሉ ድርጊቱን ድራማ ያስመስለዋል ባይ ናቸው። (ፎቶ: ሪፖርተር)

mandag 21. oktober 2013

ኢትዮጵያ፡ በፖለቲካ እስረኞች ላይ የማሰቃየት ድርጊት ይፈጸማል

ፖሊስ በጋዜጠኞች እና በተቃዋሚዎች ላይ በደሎችን ይፈጽማል።

Maekelawi

(ናይሮቢ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2006 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ዋና የማሰሪያና የምርመራ ጣቢያ ውስጥ በፖለቲካ ሳቢያ የተያዙ  እስረኞችን እንደሚያሰቃዩ እና ለጎጂ አያያዝ እንደሚያጋለጡ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት  አስታወቀ፡፡ ማዕከላዊ በመባል በሚታወቀው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሚፈጸሙ ህገ ወጥ ተግባራትን ለማስቆም እንዲሁም የሚፈጸሙትን በደሎች በተመለከተ የሚቀርቡ ቅሬታዎች በገለልተኛ ወገን እንዲመረመሩ እና አጥፊዎቹንም ተጠያቂ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡
74 ገፆች ያሉት እና “ ‘የሚፈልጉት የእምነት ቃል ነው’ ፡ ማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያ” በሚል ርዕስ የወጣው ይኸው ሪፖርት ከ 2002 ዓ.ም ጀምሮ በማዕከላዊ የተፈፀሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፣ በህገ ወጥ መንገድ የሚካሄድ ምርመራን እና በዚያ ያለውን አስከፊ የእስር  ሁኔታ ይዘረዝራል። በማዕከላዊ ከሚታሰሩት መካከል ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪዎች እና ጎሳን መሰረት ያደረገ ትግል የሚያካሂዱ አማፂያንን ይደግፋሉ የሚባሉ ሰዎች ይገኙበታል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች ከ35 የሚበልጡ የቀድሞ ታሳሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ያነጋገረ ሲሆን እነሱም የማዕከላዊ ሃላፊዎች መረጃ እና የእምነት ቃል ለማግኘት ሲሉ እንዴት መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንደከለከሏቸው፣ እንዳሰቃዩአቸው፣ በተለያየ መልኩ ያልተገባ አያያዝ እንደፈጸሙባቸው እና የቤተሰብ አባላትን እና የሕግ ጠበቃ እንዳያገኙ እንደከለከሏቸው በዝርዝር ገልጸዋል፡፡
በሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ “መረጃ ለማግኘት ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በዋና ከተማዋ እምብርት በየጊዜው ጥቃት ይፈፅማሉ” ብለዋል፡፡ ሌፍኮ እንዳሉት “ድብደባ፣ ማሰቃየት እና በማስገደድ ቃል መቀበል ለጋዜጠኞች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የተገባ አይደለም።”
ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው በኢትዮጵያ ከ1997ቱ አወዛጋቢ ምርጫ በኋላ በሰላማዊ ተቃዎሞ ላይ የሚደረገው ጫና ተባብሷል። በማዕከላዊ  ተይዘው  ምርመራ የሚካሄድባቸው የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች ጥብቅ በሆነው የሀገሪቱ የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ መሠረት መከሰስን ጨምሮ የዘፈቀደ  እስር እና ፖለቲካን መሠረት ያደረገ ማሳደድ ይፈጸምባቸዋል።የማዕከላዊ ሃላፊዎች በዋናነትም መርማሪ ፖሊሶች እስረኞቹን በተለያየ መንገድ ያሰቃያሉ፤ ጎጂ አያያዝም ይፈጽማሉ፡፡ በተለይ በምርመራ ጊዜ ታሳሪዎቹ በጥፊ፣ በእርግጫ እንዲሁም በብትር እና በሰደፍ በተደጋጋሚ እንደተመቱ ለሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጸዋል፡፡ እስረኞቹ ሰውነታቸውን ለህመም በሚዳርግ ሁኔታ እንዲሆኑና በተለይም እጆቻቸውን ከግድግዳ ጋር ታስረው እንዲንጠለጠሉ ተደርጎ ለረጅም ሰዓታት ያለማቋረጥ እንደሚደበደቡ ተናግረዋል። ከኦሮሚያ ክልል የመጣ አንድ ተማሪ  ብቻውን ተነጥሎና በሰንሰለት ታስሮ ለበርካታ ወራት እንዲቆይ እንደተደረገ ተናግሯል፡፡ “ለመቆም ስሞክር እቸገራለሁ፡ ለመቆም ጭንቅላቴን፣ እግሮቼን እና ግድግዳውን መጠቀም ነበረብኝ ፡፡ ምግብ ስመገብ እንኳ በሰንሰለት ታስሬ ነበር። ስመገብ እጆቼ  በፊት ለፊት በኩል እንዲታሰሩ ይደረጋል ስጨርስ ደግሞ መልሰው ወደ ኋላ ያስሩኛል።”
በማዕከላዊ በሚገኙት አራቱ  ዋና የማሰሪያ ብሎኮች ያለው ሁኔታ አስከፊ ነው። ሆኖም በየብሎኩ ያለው ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ይለያያል፡፡ ‘ጨለማ ቤት’ በመባል በሚታወቀው በጣም የከፋ ብሎክ የቀን ብርሃን እና የመፀዳጃ አገልግሎት ማግኘት በእጅጉ የተገደበ መሆኑን የቀድሞ ታሳሪዎች የገለጹ ሲሆን  ‘ጣውላ ቤት’ በሚባለው ብሎክ የታሰሩት ደግሞ ወደ ደጃፍ ለመውጣት ያለውን ገደብ እና የክፍሎቹን በተባይ መወረር ገለጸዋል።  እስረኞቹ ለመርማሪዎቹ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በሚያደርጉት ትብብር መሰረት በቅጣት  ወይም በማበረታቻ መልኩ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውንና ሌሎች  የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሊከለከሉ ወይም ሊፈቀዱላቸው ይችላል፡፡ ይህም ታሳሪዎቹን ከአንዱ ብሎክ ወደ ሌላ ማዘዋወርን ይጨምራል፡፡ ከዓለማቀፉ ሆቴል ስያሜውን ወዳገኘው እና ‘ሸራተን’ በመባል ወደሚታወቀው ብሎክ መዛወር የተሻለ የመንቀሳቀስ እድል ስለሚያስገኝ ከመፈታት ቀጥሎ እስረኞች እጅግ የሚናፍቁት ነገር ነው።
በጨለማ ቤት እና በጣውላ ቤት የሚታሰሩ እስረኞች በተለይ በመጀመሪያዎቹ የእስር ወቅቶች የህግ ጠበቃ እና ዘመዶቻቸውን እንዲያገኙ አይፈቀድላቸውም፡፡  የታሰሩ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ በየቀኑ ወደ ማዕከላዊ ቢሄዱም  ምርመራው እስኪያልቅ በሚል ለተራዘመ ጊዜ ከእስረኞቹ ጋር ለመገናኘት ሃላፊዎቹ እንደማይቅዱላቸው በርካታ የቤተሰብ አባላት ለሂዩማን ራይትስ ዎች ገልፀዋል፡፡ በምርመራ ወቅት የህግ ጠበቃ አለመኖሩ ታሳሪዎቹ ላይ የሚፈፀመውን በደል እንዲጨምር ያደርጋል፣ በመርማሪዎቹ የሚፈጸሙ ጎጂ አያያዞችና ማሰቃየትን የሚመለከቱ መረጃዎች እንዳይመዘገቡ ያደርጋል፤ እንዲሁም ፍርድ ቤት ይህ ያልተገባ አያያዝ እንዲሻሻል መፍትሔ ሊሰጥ የሚችልበትን እድል ይገድባል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጿል።
“እስረኞች ከጠበቆቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ማድረግ በደል ሊፈጸም የሚችልበትን ዕድል ከመጨመሩም በላይ እስረኞች የመርማሪዎቹን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ብቻ እንዲሄዱ ከፍተኛ ጫና ይፈጥርባቸዋል” ያሉት ሌፍኮ “በማዕከላዊ የሚገኙ እስረኞች በምርመራ ወቅት ጠበቆቻቸው እንዲገኙላቸው፣ከዘመዶቻቸው ጋር እንዲገናኙ እንዲሁም በፍጥነት ክስ ተመስርቶ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መደረግ ይኖርበታል” ብለዋል።
መርማሪዎች ድብደባ፣ ማስፈራራትና  ሃይል በመጠቀም እስረኞች የሰጡት የእምነት ቃል ላይ እንዲፈርሙ እንደሚያደርጓቸው ሂዩማን ራይትስ ዎች መረዳት ችሏል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የፈረሟቸውን ጽሁፎች እንደማስፈራሪያነት በመጠቀም ከተፈቱ በኋላ ከመንግስት ጋር እንዲሰሩ ጫና ለመፍጠር የሚያውሏቸው ሲሆን  በፍርድ ቤት ማስረጃ ሆነውም እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡
Maekelawi
የካቲት 11:2005 ዓም በGoogle Earth ከአየር ላይ የተነሳው ይህ ፎቶ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የፌዴራል ፓሊስ ምርመራ ማዕከል በተለምዶ “ማዕከላዊ” ተብሎ የሚጠራውን ነው::
በ2004ዓ.ም በማዕከላዊ ታስሮ የነበረው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ታሳሪዎች የእምነት ቃል እንዲሰጡ ለማድረግ ስለሚደረገው ጫና ሲናገር “አብዛኞቹን ማዕከላዊ የሚገኙ ሰዎች ተስፋ ቆርጠው የእምነት ቃል እስኪሰጡ ድረስ ያቆዩአቸዋል። ቃለመጠይቅ ሳይደረግልህ ለሶስት ሳምንታት ልትቆይ ትችላለህ። የእምነት ቃል እስኪገኝ ድረስ ብቻ ነው የሚጠብቁት።ሁሉ ነገር የእምነት ቃል ማግኘት ላይ ብቻ የሚያጠነጥን ነው።ፖሊስ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሲቀርብ መላ ያገኛል ይላል ነገርግን ፍርድ ቤት ሲኬድ አንድም የሚገኝ ነገር የለም” ብሏል፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው ታሳሪዎች ለተፈጸመባቸው ጎጂ አያያዝ መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉባቸው መንገዶች ውሱን ናቸው። በተለይ ፖለቲካ ነክ  በሆኑ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ገለልተኝነት አይንጸባረቅባቸውም፡፡ በጸረ-ሽብርተኝነት ህጉ  መሰረት የተያዙ ሰዎችን ጨምሮ እስረኞች ስለሚፈጸምባቸው ጥቃት በርካታ ቅሬታ ቢያቀርቡም ቅሬታዎቹ አንዲመረመሩ ወይም ቅሬታ ያቀረቡ እስረኞች  የበቀል  ጥቃት እንዳይፈጸምባቸው ክትትል እንዲደረግ ፍርድ ቤቶች የወሰዱት በቂ  እርምጃ የለም፡፡
ያልተገባ አያያዝን በተመለከተ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ፍርድ ቤቶች በንቃት ምላሽ መስጠት አለባቸው።  ይህም ሊሆን የሚችለው መንግስት በነፃነት እንዲሰሩ ሲፈቅድ እና የሚሰጧቸውን ውሳኔዎች ሲያከብር ብቻ ነው። ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጿል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ በነፃ አካላት የሚደረግን የሰብአዊ መብቶች ምርመራ እና ሪፖርት የማድረግ ሥራ በእጅጉ ገድባለች። ይህም በማዕከላዊ ያለው የእስር  ሁኔታ ክትትል እንዳይደረግበት አድርጓል። መንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ማዕከላዊን ሶስት ጊዜ የጎበኘ ሲሆን ከሰዎች ጋር ግንኙነት እንዳይኖራቸው ተነጥለው የሚታሰሩ ሰዎችን አስመልክቶ ያለውን ስጋት በይፋ አስታውቋል፡፡ ይሁንና የቀድሞ እስረኞች ለሂዩማን ራይትስ ዎች እንደገለጹት በጉብኝቱ ወቅት የማዕከላዊ ሃላፊዎች ከኮሚሽኑ ከመጡት ጎብኚዎች ጋር ስለነበሩ የኮሚሽኑን አባላት በግል ለማነጋገር ሳይችሉ ቀርተዋል። ጉብኝቱን ተከትሎ የመጣ ለውጥ ስለመኖሩም እርግጠኞች አይደሉም፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች እንደሚለው በማዕከላዊ እና በሌሎች ማሰሪያ ቦታዎች የሚደረገው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል እንዲሻሻል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ እና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ የተሰኙት ሁለት አፋኝ ህጎች መሻሻል አለባቸው፡፡ በሁለቱ ህጎች ምክንያት ገለልተኛ የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ሥራ በእጅጉ ቀንሷል እንዲሁም ማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝን ለመከላከል የሚያስችሉ መሠረታዊ የሕግ ጥበቃዎች ተሰርዘዋል።
የኢትዮጵያ ህገ መንግስት እና ሀገሪቱ የገባችባቸው ዓለማቀፍ ግዴታዎች ባለስልጣናት በእስረኞች ላይ ያልተገባ አያያዝ እንዳይፈጸም እንዲከላከሉ የሚያስገድዱ ሲሆን  በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በደል የመፈጸም አሰራሮችን የማስቆም እና ፈጻሚዎችም በሕግ እንዲጠየቁ የማድረግ ሃላፊነት  አለባቸው ብሏል ሂዩማን ራይትስ ዎች፡፡ መንግስት የነደፈው የሦስት ዓመታት የሰብአዊ መብቶች የድርጊት መርሀ ግብር የታሳሪዎች አያያዝ መሻሻል ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ቢሆንም  መርሃ ግብሩ በአካል ላይ የሚፈጸም ጥቃትን እና ማሰቃየትን አይዳስስም። በስፋት የሚፈፀመውን በደል ለማስቆም መወሰድ ያለበትን ተጨባጭ ፖለቲካዊ እርምጃ ከመግለጽ ይልቅ የአቅም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።
“ተጨማሪ ገንዘብ እና የአቅም ግንባታ ስራ ብቻውን በማዕከላዊ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ማሰሪያ ቦታዎች  በስፋት የሚፈጸመውን ያልተገባ አያያዝ አያስቆምም” ያሉት ሌፍኮ “እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው በደሎቹን የሚፈጽሙት ሰዎች ላይ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እርምጃ ሲወስዱ እና ጥፋተኞች ተጠያቂ እንዳይሆኑ የሚያደርገው የአሰራር ባሕል እንዲወገድ ሲያደርጉ ነው።” ብለዋል።
ምንጭ: HRW

fredag 18. oktober 2013

Ethiopian police torture political detainees: Human Rights Watch

October 17, 2013

ADDIS ABABA (Reuters) – Ethiopian police investigators in Addis Ababa’s main detention center have tortured political detainees and regularly mistreat people in custody to extract confessions, Human Rights Watch (HRW) reported on Friday.Hailemariam Dessalege was mainly TPLF’s ethnic chauvinism ideology
The Ethiopian government, long seen by the West as a bulwark against militant Islam in the Horn of Africa, has denied frequent accusations that it uses state institutions to stifle dissent and silence political opposition.
In a report about conditions inside Addis Ababa’s Federal Police Crime Investigation Sector, known as Maekelawi, HRW said many former detainees were slapped, kicked and beaten with sticks and gun butts during investigations.
“Human Rights Watch found that investigators used coercive methods, including beatings and threats of violence, to compel detainees to sign statements and confessions,” the group said in a statement, referring to events over the past three years.
Ethiopia intensified its clampdown on peaceful dissent after the disputed 2005 election, the New York-based HRW said.
The Addis Ababa government said it would not comment on the allegations until it has seen the full 70-page report.
Human Rights Watch said scores of opposition politicians, journalists, protest organizers and alleged supporters of ethnic insurgencies have been detained in Maekelawi.
Interviews with more than 35 former detainees and their relatives formed the basis of the report, HRW said.
Some Muslims have complained the government has interfered with religious affairs as it tries to stop what officials say is a rise in Islamist ideology. Ethiopia has a Christian majority but about a third of its population is Muslim.
Prime Minister Hailemariam Desalegn last week dismissed the criticism during an interview with Reuters.
“The government has nothing to do with religion. “The only thing we say is there is a red line for any religion in the country which goes beyond the constitutional provision.

torsdag 17. oktober 2013

ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል

"ኢትዮጵያ ከሁለቱም ያተረፈችው እዳ ነው"

alamudi-

በኢትዮጵያ ባሏቸው ኢንቨስትመንቶች መልከ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው የሚነገርላቸው ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን የካሩቱሪን የእርሻ መሬት ለመግዛት ከድርድር ላይ ናቸው ተባለ። ድርድሩ በስምምነት ከተቋጨ የሳዑዲን የምግብ አቅርቦት ለመሸፈን የሚንቀሳቀሱት “ባለሃብት” በጋምቤላ ብቻ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ድንግል መሬት ባለቤት ይሆናሉ። በድርድሩ መሰረት እስከዛሬ ከወሰዱት በተጨማሪ ብድርም ከንግድ ባንክ ያገኙበታል።
የሳዑዲን የምግብ ኮታ ለመሸፈን ታስቦ እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሳዑዲ ስታር አግሮ ኢንዱስትሪ በ2001 ዓ ም 10ሺህ ሄክታር መሬት ተረክቦ በጋምቤላ ስራ ሲጀምር ተጨማሪ 500 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት እንደነበር በወቅቱ የተለያዩ መገናኛዎች ዘግበው ነበር።
ሳዑዲ ስታር የስራ አቅሙ ተገምግሞ መሬት እንደሚጨመርለት ቃል ቢገባለትም የወሰደውን 10 ሺህ ሔክታር በቅጡ አልተጠቀመም በሚል የግብርና ኢንቨስትመንት ሃላፊዎች ተጨማሪ መሬት ለመስጠት ሲያቅማሙ ቆይተው ነበር። ሆኖም ግን በአቋማቸው መዝለቅ ያልቻሉት ሃላፊዎች ለሳዑዲ ስታር ተጨማሪ 120 ሺህ ሔክታር መሬት ፈቅደዋል። በቅርቡ ከወራት በፊት በተካሄደ ግምገማ አነስተኛ የስራ ትጋት ውጤት ያስመሰዘገበው ሳዑዲ ስታር አዲስ ጥያቄ ማቅረቡን በጋምቤላ የሚኖሩ የድርጅቱ ባልደረቦች ለጎልጉል ገልጸዋል። ስማቸውን መናገር ያልፈለጉ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊም በሰራተኞቹ የተጠቆመውን ዜና አጠናክረው አምነዋል።
በዚሁ መሰረት ንግድ ባንክ 62 ሚሊዮን ብር እዳ እንዳለበት፣ እዳውም በገባው ውል መሰረት እንዳልከፈለ፣ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም አለመሰካቱን፣ በዚህም የተነሳ ንብረት ለመውረስ መመሪያ መተላለፉንና ጉዳዩ ወደ ህግ መመራቱ ይፋ የሆነበትን ካሩቱሪ በተረከበው ማሳ ላይ ያስቀመጠው ንብረት ካለበት የሊዝ ዕዳ፣ የተለያዩ ክፍያዎችና የክልሉ ዓመታዊ ክፍያዎች ጋር ተዳምሮ እዳውን ይሸፍናል ተብሎ እንደማይገመት ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ።
በክልሉ ኢህአዴግ በጠመንጃ ሃይል እየተተገበረ ያለው የመሬት ንጥቂያ ጉዳዩን በውል የሚያውቁ ዜጎችን፣ እንዲሁም የክልሉን ነዋሪዎች ቁጭት ላይ የጣለ መሆኑ “ባለሀብቶች” ተብለው በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩትን በሙሉ እረፍት እንደማይሰማቸው የሚጠቁሙት የጎልጉል ምንጮች “ካራቶሪን በሳንቲም ሂሳብ ተቸብችቦለት ከባንክ ብድር ጋር የተረከበውን መሬት መልሶ ለመውሰድ ከፍተኛ ኪሳራ አለ። ኪሳራው የአገርና በተለይም ለዚህ ፋይዳ ለሌለው ኢንቨስትመንት ንብረቱንና ቀዬውን በጠመንጃ የተነጠቀው የክልሉ ሰላማዊ ህዝብ ነው” በማለት ቁጭታቸውን ይገልጻሉ።
“በአካባቢው ሕዝብ ተቀባይነት ያላገኘ ኢንቨስትመንት፣ በተለይም ሰፋፊ እርሻዎች ሁሌም አደጋ ላይ ናቸው” በማለት አሁንም ኢህአዴግና ባለህብቶች ከቀድሞው ጥፋታቸው እንዲማሩ የሚመክሩ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት “ካራቱሪ ከቀረጥ ነጻ ሲነግድና የተፈጥሮ ደን ሲያወድም ቆይቶ በእዳ ፋይሉ ሲዘጋ መሬቱን ለሳዑዲ የምግብ ዋስትና እንዲውል እየተደረገ ያለው ሩጫ ዳግም ስህተት እንዳይሆን” ሲሉ ይመክራሉ።
3.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማዘጋጀት የአገሪቱን ምርት 39 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ለማሳደግ አቅዶ እንደነበር የሚገልጸው ኢህአዴግ ባለበት እየረገጠ እንደሆነ ማስረጃ በማጣቀስ የሚተቹት ብዙዎች ናቸው። በተለይ በጋምቤላና በቤኒሻንጉል ክልል ያለውን ድንግል መሬት ከነዋሪዎቹ ጋር በመስማማት ለአገሪቱ ሕዝብ የምግብ ዋስትና ሊያውለው እንደሚገባ የግብርና ባለሙያዎች በየጊዜው የሚወተውቱት ጉዳይ ነው።
ጎልጉል ምንጮች አጠንክረው እንደሚናገሩት ካሩቱሪ የውጪ አበዳሪዎቹና የአክሲዮን ደንበኞቹ ስለከዱት ከጋምቤላ ለቅቆ ይወጣል። ካራቱሪ ቀደም ሲል 300 ሺህ ካሬ ሄክታር መሬት የነበረውና በሂደት ተቀንሶበት 100 ሺህ ሔክታር እንደቀረው፣ ከዚሁ ላይ ማልማት የቻለው አስር በመቶ ብቻ እንደሆነ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?


TPLF-Logo

ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው።
በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሃገራችን አሁንም  እየፈፀሙት የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ ነው።
ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ  ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው።
ተሓህት ትግሉን በጀመረበት ወቅት ጥቂት ከነበሩት ታጋዮች ሊመሩን ይችላሉ ብሎ ከመረጣቸው መካከል፤ 1. አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር  2. ዘርኡ ገሰሰ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ገሰሰው አየለ 5. አባይ ፀሃየ 6. ሥዩም መስፍን 7. አለምሰገድ መንገሻ 8. አስፍሃ ሃጎስ ተመርጠው ተሓህትን መርተዋል።
በዚህ ጊዜ ነበር የማገብትን ውርስ ተሓህት ተረከበው ብሎ በጊዜው የነበረ ታጋይ ደስታውን የገለጸው። ውርስ ማለት ፕሮግራሙ ነው። በጊዜው የነበረ ሁሉም ታጋይ ግን የፕሮግራሙን ይዘትና ምንነትቱን አያውቅም ነበር።  ይህ ፕሮግራም ነበር በ1968 ቀስ በቀስም ተሓህትን ለሁለት የመሰንጠቅ አደጋ የፈጠረበት።
 የተሓህት-ህወሓት የመጀመሪያ መሰንጥቅ
ተሓህት ገና ከደደቢት በረሃ ሳይወጣ በፊት በሁለት ጎራ የተሰነጠቀበት ወቅት ነው። ይህን መከፋፈል የፈጠረው የፕሮግራሙ ባለቤት ነን የሚሉ አመራር በድብቅና ከታማኝ ታጋዮች ጋር በመተባበር ወስጥ ለውስጥ ፕሮግራሙ ይዘጋጅ ነበር። ይህን የማይደግፉና የሚቃወሙ አመራርም ነበሩ።
አክራሪና በአቋማቸው የጸኑ ግን ፕሮግራሙ በትክክል የተዘጋጀ ሃቀኛ የትግራይ ሕዝብ ምኞትና ፍላጎትን በጭብጥ ያስቀመጠ፤ ትግራይን እና ሕዝቧን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነፃ የሚያወጣ፣ የትጋላችን መርህ ፕሮግራም ነው አሉ። የዚህ ተሳታፊውች፤ 1. አረጋዊ በርሄ 2፣ አባይ ፀሃየ 3. ሥዩም መስፍን 4. ግደይ ዘራጽዮን 5. ስብሃት ነጋ 6. መለስ ዜናዊ 7. አስፍሃ ሃጎስ 8. አውአሎም ወልዱ 9. ስየ አብርሃ 10. ሃይሉ መንገሻ ናቸው። እነዚህ ሁሉ አመራር የነበሩና ጥቂቶቹ ደግሞ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ አመራር የመጡ ናቸው።
በሁለተኛ ደረጃ በተቃውሞ የቆሙትና ፕሮግራሙ በጣም አደገኛ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ፣ ሕዝብ በታኝ፣ ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው በማለት የተነሱት ደግሞ 1. ገሰሰው አየለ 2. አግአዚ ገሰሰ 3. አጽብሃ ዳኘው 4. ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ሲሆኑ፣ ከሻእቢያ መጥቶ ተሓህትን የተቀላቀለው መሃሪ (ሙሴ) ተክሌም 5ኛ ሆኖ ከነገሰሰው አየለ ጋር ተቀላቀለ። እነዚህ ሁሉም የተሓህት አመራር የነበሩ ናቸው።
ማህበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) ገና ሲፈጠር ጎባጣ፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ሆኖ ነው የተመሰረተው። ይህንን ውርስ ያስረከበው ለተሓህት በየካቲት ወር 1967 ነው። በደደቢት በረሃ ተጠናክሮ ፕሮግራም ሆነ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፕሮግራሙን በመቃወም የተሰለፉት ያነሱት ነጥብ፤
  1. ተሓህት በጸረ ኢትዮጵያና በሕዝቧ ተቀናጅቶ መፈጠሩ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር መበታተን አለባት የሚለው በገጽ 8 የተዘጋጀው የባእዳን ሴራና ጸረ ሃገር ነው፣
  2. አማራ የትግራይ ሕዝብ ጨቋኝና ረጋጭ፤ ለድህነት፣ ለሽርሙጥና፣ ለስደት፣ ለመከራ የዳረጋት ጠላት ነው የሚለው ትንተና ሃቅነት የሌለው የፈጠራ ወሬ ነው። የተጻፈው አማራን ሆን ብሎ ለማጥቃት ነው። ይህም ከፕሮግራሙ መወገድ አለበት፣
  3. ኤርትራ የአማራው (ኢትዮጵያ) ቅኝ ግዛት ናት የሚለው ቅንጣት ታህል ሃቅነት የሌለው እናንተ አመረር የፈጠራችሁት የተገንጣይ ዓላማ ነው፣
  4. ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ናት ማለት የአእምሮ ድህነትና ጠባብ ዘረኝነት ነው፣ ስለሆነም መወገዝ አለበት።
  5. ተሓህት የኢትዮጵያ ጥንታዊና ታሪካዊ ግዛትዋን እና የባሕር በሯን የሚያስነጥቅ ፕሮግራም ነው። ስለሆነም ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው። ፕሮግራሙ ይለወጥ ወዘተ. የሚሉ ሃሳቦች በማንቀሳቀስ ቀሪው ታጋይም የእነገሰሰው አየለን ሃሳብ መደገፉን በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች በትክክል ተናግረውታል።
 በተጨማሪም አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ የጨመሩበት ነጥብ ተሓህት በትግራይ ሕዝብ ተቀባይነት ወይም የውክልና መሰረት የሌለው፣ ፕሮግራሙን በትግራይ ሕዝብ ስም መዘርጋት አግባብነት የሌለው፣ በሕዝብ ስም ማጭበርበር ነው ብለው በማመን በወቅቱ የነበሩ አነስተኛ ታጋዮች በዚህ ሃሳብ ተስማሙ። በዚህ ጊዜ 1. በስብሃት ነጋ 2. መለስ ዜናዊ            3. አውአሎም ወልዱ 4. ስየ አብርሃ ወዘተ. ተባብረው በአቶ ገሰሰው አየለ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ። በስብሃት ነጋ እየተመሩ የገሰሰው አየለን ስምና ዝና በጥቁር ቀለም ቀቡት። ሻእቢያም ገሰሰው ከተሓህት ተቀላቅሎ መታገሉን ከመጀመሪያው ያልተቀበለው ስጋት ወስጥ ስለጣለው ነው። ሻእቢያ ለተሓህት አመራር ያስተላለፈው መልእክት፣ ገሰሰው አየለ በዚህ ከቀጠለ ተሓህትም ሆነ ሻእቢያ ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ተናግሯል። ገሰሰው አየለ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት የሚለውን የተህሓት ጥቂት አመራር ሃሳቡን ተቀበሉት።
የእነ ስብሃት ነጋ ቡድን በገሰሰው አየለ ላይ ሲያስፋፉት የነበረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ጥቂቱን እንመልከት፤
  1. ድርጅታችን ተሓህት የገሰሰው አየለ ፊውዳል ድርጅት ነው እየተባለ ነው። ይህንን ግለሰብ ከድርጅቱ ማስወገድ ስላለብን እንተባበር (መለስ ዜናዊ)፣
  2. ገሰሰው አየለ ፊውዳል፣ ጸረ-ትግራይ ትግል በመሆኑ በተመቸው ጊዜ ጠብቆ ተሓህትን ከማጣፋት አይመለስም። የትግራይን ነፃ ሃገርነትና የትግራይን መንግሥት አይቀበልም። ጸረ-ኤርትራ ትግል ነው። የመትከል አገራችን ሻእቢያም  ተማረውበታል። (ስብሃት ነጋ)፣
  3. ኤርትራና ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት አይደሉም፣ አልነበሩም። ሁሉም የኢትዮጵያ ጥንታዊ ግዛትና አካል ናቸው፣ ስለዚህ የተሓህት ፕሮግራም ውድቅ ነው እያለ እንደ ምስጥ ውስጥ ለውስጥ እየተሽሎከሎከ ከሕዝብ እየነጠለን ነው (ስብሃት ነጋ)።
በዚህ ጊዜ የነበሩ ታጋዮች እንደሚናገሩት ከሆነ በገሰሰው አየለ ላይ በስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ የሚመራው ቡድን የተሰማሩበት የስም ማጥፋት ዘመቻ በየቀኑ ይደርሰው ነበር። በመጨረሻ ተማሮ በህዳር 1968 ከማ/ኮሚቴ ሃላፊነቱ ራሱን አግልሏል። ይህ በመሆኑ በሃዘን እና በቁጭት የሚናገሩ በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች ነበሩ። አክራሪውን አመራር ለመቆጣጠር አቅም ነበረን ግን ስህተት ፈጸምን ያሉም አልታጡም።
የዲማ ኮንፈረንስ
የዲማ ኮንፈረንስ የተካሄድው በመጋቢት መጀመሪያ በ1968 ነበር። በዚህ ጊዜ አቶ ገሰሰው አየለ በስብሰባው አልታየም። በወቅቱ በዚህ ጉባኤ የተሳተፉት ታጋዮች ገሰሰው/ስሁል የት ሄደ ብለው ሲጠይቁ የተሰጠው መልስ በሥራ ምክንያት ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል የሚል እንደነበር ይናገራሉ። ኮንፈረንሱ ከመድረሱ በፊት የስብሃት ነጋ ቡድን በአግአዚ ገሰሰ፣ በጥቂቱም ቢሆን በግደይ ዘርአጽዮን ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል። ነገር ግን ውጤት አልባ ነበር።
በዲማ ኮንፈረንስ የተመረጡት 1. አረጋዊ በርሄ፣ የተሓህት ሊቀመንበር 2. ስብሃት ነጋ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ሥዩም መስፍን 5. አግአዚ ገሰሰ 6. አባይ ፀሃየ 7. ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ ነበሩ። ምርጫው ጸረ-ዲሞክራሲ ስለነበር የነበረው አመራር ስብሃት ነጋን መርጦ መለስ ዜንዊን ድምጽ ነሳው። በዚሁ ሁሉም ወደየሥራው ሄደ።
ቀደም ብዬ በአርእስቱ ላነሳሁት ጥያቄ መልስ ለመስጠት፣ የተሓህት – ህወሓት ጸረ-ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማን በመቃወም ለሁለት መሰንጠቁና የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው? ለሚለው ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እነሆ ፎቶግራፋቸውን ከዚህ በማያያዝ አቀርባለሁ።
   ገሰሰው አየለ       አግአዚ ገሰሰ         ሙሴ መሃሪ ተክሌ            አጽብሃ ዳኛው     ዶ/ር አታክልት ቀጸላ
አቶ ገሰሰው አየለ የበረሃ ስሙ ስሁል፣ ተወልዶ ያደገው ሽሬ አውራጃ ነው። ገና በወጣትነቱ የሽሬ አውራጃ ማዘጋጃ ቤት ዋና ሹም በመሆን አገልግሏል። በ1950 አጋማሽ ለፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል በመሆን ሠርቷል። ለሶስት ተከታታይ ምርጫ በማሸነፍ 15 ዓመት ሙሉ የፓርላማ አባል ነበር። በኢትዮጵያ የተቀጣጠለው አብዮት እየተጠናከረ ሲመጣ በ1966 የማገብት አባል ሆነ።
አቶ ገሰሰው አየለ የማገብትን አላማ፣ ተግባርና ፕሮግራም በጸረ-ኢትዮጵያነት የተሞላ መሆኑን ትኩረት ሳይሰጥ በየካቲት 11 ቀን 1967 ለተመሰረተው የትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም መስራች በመሆን በአመራር ደረጃ ግንባሩን ሲመራ ነበር። የተሓህትን ፕቶግራምና ዓላማ ካየ በኋላ ፍጹም ጸረ-ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብነትን የጨበጠ ፕሮግራምና በፋሽስት ጣልያን የተዘጋጀ ነው እስከማለት ደረሰ። በህዳር 1968 ከአመራሩ ወረደ።
አቶ ገሰሰው አየለ ያነሳው ተቃውሞ ብዙ ቢሆንም ከተራ ቁጥር 1-4 ያሉትን አንኳር ሃሳቦች አስነስቷል። ታጋዩም ድጋፍ ሰጠው። ከአመራሩም እንደነ አግአዚ ገሰሰ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክለት ቀጸላና መሃሪ ከጎኑ ተሰለፉ። በተሓህት ውስጥም ጭንቀትና ሽብር በአመራሩ ወስጥ ተፈጠረ። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድንም ገሰሰው አየለን በዘዴ ለማጥፋት እቅዱን ዘረጋ።
 የገሰሰው አየለ ደብዛ መጥፋት
ከዲማ ኮንፈረንስ በኋላና ክዛም ትንሽ ቀደም ብሎ ገሰሰው አየለ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ ሲሉ የት ገባ የሚሉ ታጋዮችም በዙ። በዚህ ጊዜ የተሓህት አመራር እርስ በርሱ የሚጋጭ ወሬዎች በድርጅቱ አሰራጨ።
  1. በአዲ ነብራኡድ ወስጥ በኢዲዩ ወይም ጠርናፊት ድንገተኛ ጦርነት ከፍተው ጠርናፊት ገደለችው፣
  2. እኔ ስለሸመገልኩ አልታገልም ገንዘብ ስጡኝና ሱዳን ሄጄ ልኑር በማለት ገንዘብ ከድርጅቱ ተሰጥቶት በመኪና ተሳፍሮ ሲሄድ በመኪና ውስጥ የነበሩ የኢዲዩ አባላት ገደሉት የሚል ነበር። ሁሉም ውሸት ነው።
ኢዲዩም ይህንን በተመለከተ ሰፊ መግለጫ በተነ። ገሰሰው አየለን እኛ አልገደልነውም፣ ልንገድለውም አንችልም። የወንድማቻቾች ደም በከንቱ አናፈስም የሚል ሲሆን፣ የገደለችው ተሓህት ናት አሉ።
በአዲ ነብራኡድ ተገደለ የተባለበት ምክንያት ሕዝቡ ራሱ ምስክርነቱን በሰጠበት በመጋቢት ወር ጦርነት አልነበረም። የደም መፋሰስ አልታየም አለ። የገደሉት ራሳቸው ወያኔዎች ናቸው ሲል ሕዝቡ ምስክርነቱን ሰጠ። አዲ ነብራኡድ የገሰሰው አየለ ቤት ነው። ጊዜው የአቶ ገሰሰው አየለ ስሁል አሟሟት እውነቱ ግልጽ ሆኖ የወጣበት ጊዜ ነበር። ገሰሰው በስብሃት ነጋ የሚመራው የተሓህት አመራር በማይታወቅ ቦታ ደብቀው ወይም እንደ ግዞተኛ አቆይተው በሰኔ 1968 በጥይት ደብደበው ሽላሎ ቡምበት አካባቢ ተገደለ። በግድያው የተሳተፉትም አውአሎም ወልዱና አሰፋ ማሞ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ግን አልታወቁም። ይህንን እውነታ ተከታትለው ሃቁን ያገኙት በተሓህት ወስጥ ለትግል የተሰለፉት የገሰሰው አየለ የቅርብ ዘመዶቹ ናቸው። በጊዜው ሃቁን አስቀምጠው አለፉ። ላደረጉት ጥረት የሚመሰገኑና ባለውለታም ናቸው። ጥቂቶቹ፣ ማለትም እንደነ አዘናው ገ/ጻዲቅ ታፍነው የት እንደገቡ የማይታወቁም አሉ።
የአቶ ገሰሰው አየለ በተሓህት ፕሮግራም ያስቀመጠው ነቀፌታና ሃሳቡን የደገፉት ግለሰቦች በከፍተኛ ዲግሪ ከቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ እንደነ እቁባዝጊ በየነ፣ አሰፋ ገብረዋህድ የመሳሰሉ ዘጠኝ ምሁራን የተሓህትን አመራር የውሸት ስም በመስጠት የሥልጣን ሱሰኞች ተብለው ሽራሮ ውስጥ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። እነዚህም በተሓህት አመራር ቅጥራኛ ባንዳዎች ተገድለዋል። ይሁን እና መልእክታቸውን አስተላልፈው ከዚች ዓለም በግፍ ተገድለው አልፈዋል። ስማቸው ግን አልጠፋም፤ ለዘላለም ይኖራል።
2.  ዘርኡ ገሰሰ
ዘርኡ ገሰሰ የበረሃ ስሙ አግአዚ ሲሆን፣ በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ነበር። ማገብትን ከመሰረቱት አንዱ ነው። በአመራርም እስክ እለተ ሞቱ ተሓህትን ከሚመሩት መካከል ነበር። ዘርኡ ገሰሰና አቶ ገሰሰው አየለ  በተሓህት ፕሮግራም ጠማማነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑ በሁሉም ነጥብ አይለያዩም፣ አንድ  አቋም ነበራቸው።
ዘርኡ ገሰሰ የተሓህትን ፕሮግራም አጥብቆ ያወግዘዋል፣ በታጋዩም ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ክብርም ያገኘ አመራር ነበር። ይህች ግን ለነስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን እና መለስ ዜናዊ አትዋጥላቸውም። አደገኛ መሪ ብለው ፈርጀው የሚጠበቀው ልክ እንደ ገሰሰው አየለ በዘዴ ማጥፋት ነበር።
ዘርኡ ገሰሰ በተሓህት ፕሮግራም በገጽ 8 ላይ የሰፈረውን እና ሌላውን ፕሮግራም ሁሉ አደገኛ ስለሆነ ፈጽሞ መወገድ አለበት በማለት ከብዙ አመራሮች ጋር መነጋገሩ የቅርብ ሰዎች የሚሉት ሃቅ ነበር። ነገር ግን ሰሚ አላገኘም። እነ ስብሃት ነጋ የሚገደልበትን ዘዴ ለማመቻቸት ይሯሯጡ ነበር።
አግአዚ ገሰሰ ከግደይ ዘርአጽዮን እና ከአረጋዊ በርሄ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው የሚያውቁ ታጋዮች በዚሁ ሴራ ሁለቱ ምንም ዓይነት ተሳታፊነት አልነበረባችውም የሚሉም ብዙ ናቸው። የሴራው አካላት ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ አውአሎም ወልዱና ስየ አብርሃ ናቸው በማለት ያረጋግጣሉ።
ይህ በእንዲህ እያለ የተሓህት አመራር ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ሆነው ዘዴውን አቀነባብረው ከጨረሱ፣ አግአዚን ጨምሮ በአክሱም ከተማ ትልቅ ሥራ እንዳለ አስመስለው ሃሳባቸውን በማቅረብ የሚፈጸመውም በአመራር ደረጃ ስለሆነ አግአዚ ተዘጋጅ ብለው በትንሽ ቀናት እንደሚገናኙ ተወሰነ። ስብሃትና አባይ ፀሃየ ጠላት በብዛት የሚገኝበት ለመንቀሳቀስም ሆነ መንገዱን መጠቀም በማይቻልበት ቦታ ወቅሮ ማራይ መሆኑ በሕዝብ ግንኙነት ጥናት አግኝተዋል። ወቅሮ ማራይ በደርግ ሚሊሺያ የታጠረ ነው። ቀኑ ደረሰ፣ አግአዚ ገሰሰና ነፃነት ሰንደቅ አብረው ከነስብሃት ጋር ሰመማ በሚባል ቦታ ተገናኙ። ስብሃት ነጋ ለአግአዚ በየትኛው ቦታ ለመሄድ አስበሃል ሲለው በመደባይ ታብር በኩል ሲለው የመረጥከው መንገድ አደገኛ ነው በማለት በሕዝብ ግንኙነት አጥንተን ወቅሮ ማራይ ነፃ መሆኑን፣ ሚሊሻም ሆነ የደርግ ሰራዊት የሌለበት ነው ካሉት በኋላ በህሳቡ ተስማምተው መንገዳቸውን ቀጠሉ። ነፃነት ሰንደቅ አብሮት ስለነበረ ሁሉንም ሰምቶታል። ወቅሮ ማራይ እንደገቡ በሚሊሻ ተከበው በተተኮሰ ጥይት አግአዚ ገሰሰ ወዲያውኑ ወድቆ ሞተ። ነጻነት ግን አመለጠ። እንደምንም ብሎ ዘና ወረዳ ገባ። እዛ ላገኛቸው ታጋዮች የደረሰባቸውን ሲነግራቸው፣ ነፃና ጥሩ መንገድ ነው ብለው ስብሃትና አባይ ፀሃየ አግአዚም የተናገሩትን አምኖ በሚሊሻ ተከበን የጥይት ናዳ ወርዶብን አግአዚን ገደሉት፣ እኔ አመለጥኩ። ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ባዘጋጁት የግደያ ዘዴ የሚቃወማቸውን አግአዚ ገሰሰውን አጠፉት ብሎ የተናገረው በተሓህት ውስጥ ተሰራጨ። ስብሃትና አባይ ተከታትለው ነፃነትን ለማግኘት የተፈጠረው ነገር ለማንም እንዳይነገር አስጠነቀቁ። ሆኖም ግን ነገሩ ተሰራጭቷል። አመራሩም የአግአዚን ሁኔታ አንዲት ቀንም ሳያነሳ ቆይቶ በ1ኛው ጉበኤ በጠላት ተገደለ ብለው ተናገሩ። የስብሃት የግድያ ሴራም ሰመረለት።
3.  መሃሪ ተክለ
መሃሪ ተክለ የበረሃ ስሙ ሙሴ ነው። በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ሲማር የቆየ፤ ከሻእቢያ ጋር የተሰለፈ የሻእቢያ ታጋይና አመራር የነበረ ሰው ነው። ሻእቢያና ማገብትን በማይበጠስ የብረት ሰንሰለት ያቆራኘው መሃሪ ተክሌ ነው። ማገብትን የመሰረቱት እነ አረጋዊ በርሄ በጥር 1967 ሳህል ኤርትራ በረሃ ወርደው በሻእቢያ ወታደራዊ ትምህርት ሰልጥነው ብረት ታጥቀው ደደቢት በረሃ እንዲወርዱ ትልቅ ሚና የተጫወተው መሃሪ ተክሌ ነው። መሃሪ ተክሌ በሻእቢያ ተፈቅዶለት በተሓህት ውስጥ እንዲታገል ደደቢት በረሃ ከነ አረጋዊ በርሄ ተቀላቅሎ የተሓህት ተዋጊም ሆነ።
 የሙሴ ያልተጠበቀ የአቋም ለውጥ
ሙሴ የሁሉንም ታጋይ ባህሪ ጥናት ለመውሰድ ጥቂት ወራቶች ቢወስድበትም የተሓህት ታጋይ ለምንም ለውጥ ዝግጁ መሆኑን አወቀ። የእነ ገሰሰው አየለ አግአዚ ወዘተ. በተሓህት ፕሮግራም ላይ ያላቸውን አመለካከት አወቀ። ከአስገደ ገ/ሥላሴም ጋር ጥሩ ግንኙነት መሰረተ። ታጋዩና ሙሴ ውህደት ፈጠሩ፣ ወደዱትም። በዲማ ኮንፈረንስ ለአመራር ብቁ ነው ብሎ ታጋዩ ወደ ተሓህት መሪነት አደረሰው። ም/ወታደራዊ አዛዥም ሆነ። ይህ በወቅቱ ለነበረው ታጋይ ታላቅ ድል ነበር።
ሙሴ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጸረ-ሻእቢያ አቋም ያዘ። ሻእቢያ ጸረ-ሕዝብ፣ በተለይ ደግሞ ጸረ-ትግራይ ሕዝብ ነው። ሻእቢያ የኔ ጠላት የትግራይ ሕዝብ ነው የሚል አክራሪ ድርጅት ነው፤ የተሓህት አመራር ደግሞ ሻእቢያን እንደፈጣሪ እየቆጠሩ ጠዋት ማታ እግሩን ይስማሉ በማለት በተጠናከረ መልኩ ጸረ-ሻእቢያ ቅስቀሳውን በማቀነባበር በስፋት ቀጠለበት፣ ታጋዩም አብሮት ቆመ።
አመራሩም ሙሴ ከመትክል የትግላችን አጋር ሻእቢያ እየለያየን ነው በማለት ሲናገሩ፣ በእንጻሩ ሙሴ ነፃ ሁኑ፣ አሽከር አትሁኑ፣ የሻእቢያ አገልጋይና ታዛዥ አትሁኑ ነው የምላችሁ ሲላቸው የተሓህት አመራር ሙሴን ማውገዙን ቢቀጥሉበተም በታጋዩ ተቀባይነት አላገኘም። ይበልጡኑ የሙሴ ተቀባይነት ከፍ አለ። በዚህ ምክንያት አመራሩ ሙሴ መሃሪ ተክሌ የሚጠፋበትን መንገድ ማጠንጠን ጀመሩ። የግድያ ሴራ በስብሃት ነጋ የሚመራው የመለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየና ሥዩም መስፍን በመተባባር እቅዱን አወጡ። ተግባር ላይ የሚያውሉት ደግሞ ስየ አብርሃና ጻድቃን ገብረተንሳይ ሲሆኑ ግድያውን የሚፈጸመው በርሄ ሃጎስ ሆኖ ተመረጠ። በርሄ ሃጎስ አሁን ካናዳ፣ ኦቶዋ በመኖር ላይ ያለ ግለሰብ ነው። በላፈው ግንቦት 2005 አማራው የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው እያለ አማራውን ኢትዮጵያዊ ሲሰድበውና ሲያንቋሽሸው የነበረ ሰው ነው። በገዘ ተጋሩ ፓል ቶክ።
ስየ አብርሃ በሚመራት ሃይል 41 አመቺ ጊዜ ሲጠብቅበት የነበረው ሙሴ ጻድቃን ገብረተንሳይ በኮሚሳርነት የሚመራት ጋንታ በርሄ ሃጎስ የነበረባት ጋንታ በመጠባበቅ ላይ የነበሩት ሁለቱ በአጋጣሚ ሓምሌ መጨረሻ 1968 ከሽራሮ ወጣ ብላ የምትገኘው ቁሽት ጫአ መስከበት ስየ አብርሃ ም/ሃይል መሪ በያዛት ሃይል በኢዲዩ ላይ ጥቃት እንደተጀመረ፣ ሙሴ ታጋዮቹን እያስተባበረ ጦርነቱን በመምራት ላይ እንዳለ በስተኋላው የነበሩት ጻድቃን ገ/ተንሳይና በርሄ ሃጎስ ውጊያው እየበረታ ሲሄድ በርሄ ሃጎስ አነጣጥሮ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌን ግራ እጁ ላይ ትከሻውን ጨምሮ ቆርጦ ጣለው። ዞር ሲል ጻድቃን ገ/ተንሳይና በርሄ ሃጎስ ከኋላ ሆነው እንደመቱት አወቀ። አይን ለአይንም ተገጣጠሙ። በርሄ ሃጎስ ሙሴን የመታበትን ደምመላሽ ጠመንጃም ለጻድቃን ሲሰጠው አየው። ክፉኛ የቆሰልውን ሙሴን በቃሬዛ ተሸክመውት ሲሄዱ የነበሩትን ታጋዮች ሁሉ የነገራቸው እኔ በኢዲዩ ጥይት አልተመታሁም፤ የመቱኝና የገደሉኝ ጻድቃን ገብረተንሳይና በርሄ ሃጎስ ናቸው እያለ ሲናገር እንደነበረና አንድ ሰዓት ተኩል ያህል ቆይቶ ከዚች ዓለም እንደተሰናበተ ይናገራሉ። አዲ ፀጸር ቀሽት ወስጥ ተቀበረ። ወዲያው በርሄ ሃጎስ ትንሽ ገንዘብ ተቀብሎ ሱዳን ገባ። ሙሴ  የተናገረውን ኑዛዜ አውአሎም ወልዱ ሰምቶታል፣ ምስክርነቱን ይስጥበት።
4.  አጽብሃ ዳኘው
አጽብሃ ዳኘው፣ የበረሃ ስሙ ሸዊት ነው። በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ ትምህርት የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበር። ማገብት እንደተመሰረተም ከወራት በኋላ አባል ሆነ። መጋቢት 1967 ከተሓህት ጋረ ተቀላቀለ።  ከጊዜ በኋላም በተሓህትን ፕሮግራም አደገኛነት ሂስ መሰንዘር በመጀመር ፕሮግራሙ ጸረ-ሃገር ሉአላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብና በታኝ፣ ሕዝብን እርስ በርሱ ለግጭት የሚዳርግ በመሆኑ አዲስ ፕሮግራም ማርቀቅ ይጠበቅብናል በማለት ከነ ገሰሰው አየለ – አግአዚ ገሰሰ ጋር በአቋም ተስማሙ። በሚሰነዝረው ሃሳብ በታጋዩ ተወዳጅ ሆነ፣ በድፍረቱም ምክንያት ስሙ ገነነ። በዚህ መልክ ሲቀጥል፣ ሱዳን፣ ካርቱም ለሥራ ሂዶ በነበረበት ወቅት መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ በአስቸኳይ አስጠርተው ሱዳን ባለህበት ጊዜ ጾታዊ ግንኙነት ፈጽመሃል በማለት በውሸት ከሰው 06-ሃለዋ ወያነ አስገብተው አሰሩት። አረጋዊ በርሄ ይህን እንደሰማ ከነበረበት ቦታ በቶሎ ደርሶ ከእሰር አስወጥቶ ሥራውን እንዲቀጥል አደረገ። ሐምሌ 1968 አመራሩ ወደ አምስት ስለወረደ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ በተሓህት አመራር ስለተገደሉ፤ በአመራር ላይ የቀሩት አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃየ ብቻ ነበሩ። ከላይ በጠቀስኩት ወርና ዓ.ም. አምስቱ አመራር ተሰብስበው የሚከተሉት ወደ አመራሩ ገቡ። መለስ ዜናዊ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ አውአሎም ወልዱና ስየ አብርሃ ወደ ተሓህት አመራር ወጡ።
አጽብሃ ዳኘው ለስልጣን እና ሹመት እጁን አልሰጠም። የተሓህት ፕሮግራም ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ፣ አውዳሚና በታኝ ስለሆነ መወገድ አለበት፣ ተሓህት ጠባብና ዘረኛ ስለሆነ ትግላችን ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት። ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ናት፣ አማራ ጠላት ነው ማለት ሕገወጥ የፖለቲካ አቋም ነው በማለት ተከራከረ። ክርክሩን እገላ ወረዳ ስብኦ ቁሽት ሲከራከሩ ስብሃት፣ መለስና አባይ ተናደዱ። ሆያ አዲጨጓር የሚገኘው 06-ሃለዋ ወያነ ሃላፊዎች፣ ሙሉጌታ አለምሰገድና ክንፈ ገ/መድህንን አስጠርተው ዛሬውኑ አጽብሃ ዳኘውን እና ጓደኛው መኮንን በዛብህን ግደሏቸው። ስብሃት ነጋ ጸረ-ተሓህት ናቸው የሚል ወረቀት ጽፎና አዘጋጅቶ ሰጣቸው። እነአጽብሃ መኮንን የተሰጣቸውን ወረቀት ይዘው በመሄድ ሆያ ላይ ጉድጓድ ተቆፍሮ በጥይት ተደብድበው በመገደል ከዚህ ዓለም ተሰናበቱ።
አረጋዊ በርሄ የአጽብሃ ዳኘውና የመኮንን በዛብህን መታሰር ሰምቶ ከነበረበት ተምቤን አካባቢ ሌት ተቀን ተጉዞ ሕይወታቸውን ለማዳን ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። ሆያ እንደገባ እነ አጽብሃ ወደኔ አምጡልኝ፣ ተፈትተዋል፣ ጥፋት የለባቸውም ሲል ከሙሉጌታ አለምሰገድ ጋር ያገኘው መልስ፣ ስብሃትና መለስ አባይ ሆያ እንደገቡ ሳይውሉ ሳያድሩ ይገደሉ ብለው ስላዘዙን ገደልናቸው አለው። የትእዛዝ ወረቀቱም የኸው ብሎ ሰጠው። አረጋዊ በርሄ ይህንን አሳዛኝ ግድያ ሰምቶ እነስብሃት ነጋ ወደሚገኙበት እገላ ሰብኦ፣ ቁሽት በመሄድ ተገናኛቸው። ነገር ግን ምንም አላደረገም። የተሓህት ሊቀመንበር እንደመሆኑ ለምን ይሆን በነስብሃት ነጋ፣ መለሰ ዜናዊ ወዘተ. ላይ እርምጃ ሳይወሰድ የቀረው የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር። አሁንም እየተነሳ ነው። መልስ መስጠት ያለበትም የወቅቱ የተሓህት ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ ነው።
 5.  ዶ/ር አታክልት ቀጸላ
ዶ/ር ራስወርቅ ቀፀላ የበርሃ ስሙ ዶ/ር አታክልት ቀፀላ የህክምና ባለሙያ ነው። ቀደም ሲል ከግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግገሓት) አባል ሆኖ በረሃ ሲንቀሳቀስ የግገሓት የትግል ስልት አደገኛ ነው በማለት በሰኔ 1967 ከተሓህት ተቀላቀለ። በተሓህትም ብዙ ስህተቶች እንደሚኖር አልተጠራጠርም ነበር። ነገር ግን ስህተቱን ለማስተካከልና ለማረም ብዙ ታጋዮች ይኖራሉ የሚለው እምነቱን እንደያዘ ቀስ በቀስ ፕሮግራሙን የማየት እድል ገጠመው። ከነገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪና አጽብሃ ዳኘው ጋር ጥሩ ግንኙነት ስለፈጠረ፣ እነዚህ ሁሉ የተሓህት ፕሮግራምን የሚቃወሙ ናቸው። አጽብሃ ዳኛው በነስብሃትና መለስ እንደተገደለም ዶ/ር አታክለት ቀጸላ በአጽብሃ ፈንታ የተሓህት አመራሩን ጨበጠ። ግን እጁን አልሰጠም።
ዶ/ር አታክለት በፕሮግራሙ መጥፎና አደገኛ፣ ሃገርንና ሕዝብን የሚበታተን ነው ብሎ በማመን ከተለያዩ አመራር ጋር ሲነጋገርበት እንደነበር ይታወቃል። ከግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ መግባባት እንደነበረውም ራሱ የተናገረው ነው።
ከመለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና ከሌሎቹ አመራር ጋር ግን የሻከረ ግንኙነት እንደነበረው ታጋዩ ሁሉ ያውቃል። ሌላው ቀርቶ ስብሃት ነጋ በየቦታው በሄደበት “የኢትዮጵያ ባንዲራ ራሱ ላይ ጠምጥሞ ዶ/ር አታክለት ቀጸላ በድርጅታችን ተሓህት ችግር እየፈጠረብን ነው” በማለት በየቦታው መናገሩን እኔ ራሴ አስታውሳለሁ። ዶ/ር አታክልት ቀጸላ በ1ኛው ጉባኤ የተሓህት የአመራር ምርጫ በከፍተኛ የድምጽ ቁጥር ተመርጦ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ም/ወታደራዊ አዛዥ ሆነ። የነስብሃት ነጋ የስም ማጥፋት ዘመቻ አልተሳካም። በነገሩም ተደናግጠው ነበር።
ይህ በየካቲት 5 ቀን 1971 በአዲነብር ኡድ ወረዳ ማይ አባይ በተባለው ቦታ የተካሄደው 1ኛ ጉባኤ፣ የተሓህት ውርስ ስብሃት ነጋ ሊቀመንበር የሆነበት ጉባኤ ወርሱን የተረከቡት ስብሃት ነጋና ህወሓት ናቸው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቀደም ብሎ የመጣው ፋሽስት ቡድን እውቅና ያገኘበት ጊዜ ነበር።
እነስብሃት ነጋ ዶ/ር አታክልትን ለማጥፋት ብዙ ጥናት በማካሄድ የተመቸ ጊዜ አገኙ። ግንቦት 1971 የውጊያው ዓይነት ጥቃት በኢትዮጵያ ሰራዊት፣ የውጊያው ቦታ ተምቤን፣ አብይ አዲ ጎንባስ ሞሞና ነበር። የህወሓት ሰራዊትም ይዘጋጅበት ነበር። ቀኑ ደርሶ ሁሉም የህወሓት ሰራዊት ወደ ውጊያው ቀጠና አመራ። ውጊያው የሚጀምርበት ጠዋት በስተምእራብ በኩል ከውጊያው ቦታ በግምት በ10 ኪ.ሜ. ርቀት ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና ሳሞራ የኑስ፣ የታጠቀው መሳሪያ ሲሞኖቭ ባለመነጽር ሆነው ዶ/ር አታክልት ቀጸላን የህወሓት ሊቀመንበር ስብሃት ነጋ ስለጦርነቱ ለመነጋገር ብሎ አስጠራው። እነሱም ለግድያው በመዘጋጀት በጠሩት መሰረት ደረሰ። ፊታቸውን ወደ ውጊያው ቀጠና ምስራቅ በማዞር ቀስ እያሉ መንገዱን ቀጠሉ። እኔና ዶ/ር አባዲ መስፍን ከነስብሃት ነጋ ፊት 500 ሜትር ያህል በሚገመት ርቀት ወደ ጦርነቱ ቀጠና እንጓዝ ነበር። ዶ/ር አታክለት ቀጸላ ስብሃት ነጋ እንዳሰናበተው በፍጥነት እየተጓዘ ሳለ ከ250-300 ሜትር ርቀት ከነሱ መካከል ሳሞራ የኑስ በያዘው ሲሞኖቭ ባለመነጽር ጠመንጃ አስተካክሎና አነጣጥሮ በመተኮስ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ የጀርባው አከርካሬ ላይ መታው። ‘Special Column’ ተመትቶ ሲወድቅ አዩት። አባይ ፀሃየ በፍጥነት ሩጦ ወደኛ ተጠግቶ አባዲ፣ አባዲ፣ ብሎ በመጥራት በእጅ ምልክት ኑ ሲለን ሄደን አገኘነው። ዶ/ር አታክልት ስለሞተ ቅበሩት፣ ነገር ግን ለማንም እንዳትናገሩ ብሎ ተመልሶ ከነስብሃት ነጋ ጋር ተቀላቀለ። በኋላም ሶስቱም ተያይዘው ሲሄዱ አየናቸው።
ዶ/ር አባዲ መስፍን እና እኔ ጉድጓድ ስንቆፍር እሱ እንደ ባለሙያነቱ ሬሳውን መመርመር ጀምረ። ጀርባው ላይ የመታችን ጥይት ሰውነቱን ከፍቶ አወጣት። በሲሞኖቭ ጥይት ሳሞራ የኑስ ገደለው ብሎ እምባውን መግታት አቃተው። ጥይቷን በወርቀት ጠቅልሎ ያዛት። እኔና ዶ/ር አታክልት አፈርና ድንጋይ በመጫን ቀብረን ተሰናብተን ወደ ጦርነቱ ተመለስን። ዶ/ር አታክልት ሞቶ ይቀበር እንጂ ታሪኩ ህያው ህኖ ይኖራል። እነ ስብሃት ነጋ መለስ ዜናዊ ወዘተ. በንጹሃን ደም መታጠብ የጀመሩት ገና ከጥዋቱ ነበር። እነዚህ ጀግኖች በሞት ቢለዩንም ድምጻቸውና የተቀደሰ ተቃውማቸው፣ የህወሓት ፕሮግራም ይውደም ያሉት ድምጻቸው ግን በታጋዩ ዘንድ ተሰራጨ። በዚህም ምክንያት ብዙ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችን በማንሳት የተሓህት- ህወሓት አመራርን አስጨነቁት። አመራሩ ተቃውሞውን አጠፍ በማድረግ በድርጅታችን ሕንፍሽፍሽ ተነሳ ብሎ ብዙ ታጋዮችን እና ንጹሃንን መጨፍጨፊያ ምክንያት አደረገው። የዲሞክራሲ ጥያቄው ተዋንያኖች፤ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ፣ አጽብሃ ዳኘውና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ያቀጣጠሉት ነው። የህወሓት ፋሽስትና አምባገነን መሪዎች የመጥፊያቸው ጊዜ እየቀረበ ነው፣ ተያይዘው በሕዝብ ሃይል ለፍርድ ይቀርባሉ።
 6. ግደይ ዘርአጽዮን
ግደይ ዘርአጽዮን ከአረጋዊ በርሄ ጋር በመሆን የማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡ ህወሓትን የፈጠሩት ሁለቱ ናቸው። ሌላ የለም። ግደይ የተፈጸሙ ጥፋትም ሆነ ወንጀል ካሉ ከነበሩት አመራር እኩል ተጠያቂ ነኝ በማለት በግልጽ ተናግሯል። በህወሓት አመራር አስከቆየሁበት በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ነኝ። ነጻ ነኝ ብሎ ራሱን ያላገለለ በመሆኑ ያስመሰግነዋል።
ግደይ ዘርአጽዮን የተሓህት-ሀወሓት ከፍተኛ አመራር የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር በነበረበት ጊዜ አመራሩ የሚፈጽመውን ግድያና ሽብር አውግዞ ከ1969 መጨራሻ ራሱ ነፃ በመሆን የስንት ታጋይና ሰላማዊ ዜጋ ሕይወት ያዳነ ነው። ግን ብቻውን በመሆኑ የህወሓትን አመራር ክሚፈጽሙት ወንጀል ሊያቆማቸው አልቻለም። በሰላማዊው ዜጋና በታጋዩ ግን ሰፊ የታማኝነት፣ አጋርነትና ክብር የተሰጠው ግደይ ዘርአይጽዮን ነው። ግደይ የታጋዩ ጥብቅ ጓደኛ ሆነ፣ ተወደደ። ማንኛውም ታጋይ ችግር ሲገጥመው ለግደይ ያናገራል። ግደይም ችግሩን ይፈታለታል። ግደይ ራሱም የታጋዩን እና የሕዝቡን ፍቅር ጣእሙን ስላወቀው ሁልጊዜም ደስተኛ ነበር።
መለስ ዜናዊ የሚመራውን ማርክሲስት ሌሊኒስት ሊግ ትግራይ ለማቋቋም የሃላፊነቱ ተሰጠው። በ1ኛው ጉባኤ በኮሚሽን ደረጃ እንደተቋቋመ በአቋም ልዩነታቸው እነ መለስ ዜናዊ፣ ግደይን እንደጠላት ማየት፣ ግደይ ዘርአጽዮንም በአቋሙ ስለጸና መፋጠጥ የጀመርንበት ጊዜ ነበር። የነበራቸው ልዩነትም የማይፈታ ሆነ። ሁለቱም በተጻራሪ መንገድ ቀጠሉበት።
በእነ መለስ ዜናዊና አበሮቹ የሚያቀርቡት፤     
ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ አብዮት የአብዮቱ መሰረታዊ ሃይሎች ድሃ ገበሬ፤ ላብ አደሩ ሲሆኑ፣ እነዚህን ካሰባሰብን የአብዮቱ ትግል ዓላማው እና ግቡን ይመታል። ሃብታም ገበሬ ከሁለት ጥንድ በሬዎች በላይ ያሉት ሃብታም ገበሬ ስለሆነ በማርክስ ሌኒናዊ ሳይንስ ሃብታም ገበሬ የትግላችን ጠላት ነው፣ በማለት አስረግጠው ተናግረዋል። ሃብታም ገበሬ መደምሰስ መጥፋት አለበት። ለምን የማርክስ ሌኒናዊ ጠላት ሃብታም ገበሬ ነው። መለስ ዜናዊ ይህንን በወይን መጽሔት እያተመ ታጋዩን ያስተምርበት ነበር።
ግደይ ዘርአጽዮን
ሃብታም ገበሬ የማርክሲዝም ሌኒኒዝም ጠላት አይደለም። አሁንም በህወሓት የሚመሰረተው ማርክሲስት ፓርቲ ሃብታም ገበሬ ጠላት ሳይሆን የትግል አጋራችን እና ወዳጃችን ነው ተብሎ በትግሉ እንደ ወዳጅ መታወቅ አለበት። ከሁለት ጥንድ በሬ በላይ ያለው ሃብታም ገበሬ ነው ስለሆነም ጠላት ነው እያላችሁ ምክንያት በመፍጠር ያምታጠቁት የትግራይ ሕብረተሰብ ፍጹም ጸረ-ሕዝብ ነው። ንብረቱ ሁሉ እየተወረሰ ለህወሓት ገቢ ሲደረግ ለተገደለው ሕዝብና ለፈረሰው ቤት ተጠያቂ ናቸው። ይህ የሃሳብ ልዩነት በነመለስ ዜናዊ ቡድን እና በግደይ ዘርአጽዮን መካክል ሰፍቶ በመውጣት ለዓመታት ቀጠለ።
መለስ ዜናዊ
በእኛና በግደይ ዘርአጽዮን መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። አብረን መታገልም አንችልም። ግደይ ዘርአጽዮን ሃብታም ገበሬ የማርክስ ሌኒናዊ የትግል አጋር ነው፣ ጠላት አይደለም ብሎ ያምናል። ይህ የሚያመለክተው ግደይ ዘርአጽዮን ጸረ-ማርክስ-ሌሊናዊና በራዥ ነው ሲል በያዘው አቋም የማይነቃነቀው ግደይ፣ አንተና ጓደኞችህ ናችሁ በራዥና ከላሽ ነህ ስለአለው ንትርኩ ሰማይ ወጣ። ግደይ ዘርአጽዮን አሁንም በዚህ ጉባኤ አቀርበዋለሁ። ሃብታም ገበሬ የትግላችን አጋርና ወዳጅ መሆኑ ሙሉ እምነቴ ነው። ሃብታም ገበሬ ጠላት ነው ብሎ ማስቀመጥ ጸረ-ሕዝብ ነው። እነ መለስ ዜናዊ ሃብታም ገበሬ ጠላት ነው ማለታቸው ማንነታቸውን በትክክል ይገልጸዋል።
 2.  በማለሊት ጉባኤ አመራሩ ዳግም ለሁለት መሰንጠቅ
የማለሊት ጉባኤ በዚህና በሌላውም ጸረ-ዲሞክራሲ ሲካሄድ ሰንብቶ ሐምሌ 21 ቀን 1977 ምርጫው ደረሰ። ይህ ምርጫ ሕገወጥነትን የተከተለና ሁለት ዋና ዋና ዓላማ የያዘ ነበር።
  1. የሥልጣን ሽኩቻ ዋና ዓላማው ነበር፣
  2. በዚህ የሥልጣን ሽኩቻ ማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠው በጸረ-ዲሞክራሲና በጸረ-ሕዝብነቱ አብረው እየመሩት የመጡት አንጋፋ አመራሮች ለማባረር በድርቅ የተጠቃው መከረኛው የትግራይ ሕዝብ እያለቀ ከአፉ ነጥቀው በነስብሃት ነጋ፣ በስንት ሚሊዮን ብር የተዘጋጀው ማለሊት ስልጣናቸውን ለማደላደል ነበር።
ምርጫው
በሙሉ ድምጽ የመራጭ ብዛት 250 ነበር። ምርጫው በምስጢር ሆኖ በወረቀት የምትፈልገውን መምረጥም ነበር። ምርጫው ተካሄደ። ድምጹ ተቆጠረ። በዝርዝር ተነገረ። 1ኛ. ግደይ ዘርአጽዮን፣ ያገኘው ድምጽ 247፤ 2ኛ. አረጋዊ በርሄ፣ ያገኘ ድምጽ 245፤ 3ኛ. ሃየሎም አርአያ፣ ያገኘው ድምጽ፣ 236፤ 4ኛ. ስየ አብርሃ ወዘተ. እያለ የድምጽ ቆጠራው ቀጠለ። ወደ መጨረሻው ድምጽ ቆጠራ ደረሰ። ይህንን የሚገልጸው ህብሩ ገብረኪዳን ነበር። በጥቁር ሰሌዳ ላይ የተመረጡት ያገኙትን ድምጽ እየጻፈ ሲገልጽ የሚይዘው የሚጨብጠውን አጣ። የጉባኤው ተሳታፊ ቀጥል ብሎ አፋጠጠው። ላብ ፊቱ ላይ እየወረደ ቀጠለ። 24ኛ. መለስ ዜናዊ፣ ያገኘው ድምጽ 130፤ 25ኛ. ስብሃት ነጋ፣ ያገኘው ድምጽ 127 በማለት የ25ቱን የማለሊት ተመራጮች የማለሊት ማ/ኮሚቴ ብሎ በጥቁር ሰሌዳው ላይ በማስቀመጥ ተመልሶ ወደ ቦታው ሄዶ ተቀመጠ። መለስ ዜናዊ ራሱን ደፋ። ፊቱ የተጠበሰ ስጋ መሰለ። ስብሃት ነጋ ደግሞ አዳራሹን ለቆ ወጣ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የጉባኤው ሊቀመንበር የነበረው ሥዩም መስፍን ከሰዓት በኋላ በ11 ሰዓት እዚህ እንገናኝ ብሎ ጉባኤተኛውን አሰናበተ። በዚህ ዓይነት ነበር ታጋዩ እነ መለስ ዜናዊን መሬት ውስጥ የቀበራቸው። ነገር ግን ተመልሰው ታጋዩን አጠቁት። ብዙ ነባር ታጋይ በእነ መለስ፣ ስብሃት ወዘተ. ተገደለ፣ ከሞት የተረፈውም ሸሸ።
ልክ በ11 ሰዓት ጉባኤው ተሰየመ። በስብሃት ነጋ አመራር የተመረጡት ማ/ኮሚቴ ማለሊት አሰባስቦ ሹመትና ሥልጣን እየሰጠ እንዲተባበሩት አደረገ። ከአረጋዊ በርሄ ስልጣን አገኛለሁ ብሎ ስየ አብርሃ በከፍተኛ ድምጽ የመረጥነው በግንባር ቀደምትምነት ክህደት ከነ ስብሃት ጋር ተሰለፈ። በዚሁ ጉባኤ የመጀመሪያው ተናጋሪ መለስ ዜናዊ፤ ቀጥሎ ስብሃት ነጋ፤ ቀጥሎ ስየ አብርሃ በመተባበር ግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ ከህወሓት ከማለሊት ተባረዋል ተባለ። ታጋዩ ተደናገጠ፣ አጉረመረመ አለቀሰ። ከአመራሩ ጻድቃን፣ ሥዩም ገብሩ፣ ወዘተ. በየተራ በሁለት አንጋፋ አመራር አሰነዋሪ የሆነ ስድብ አወረዱባቸው። የተባረሩትም ክኛ ጋር ተቀላቀሉ። እነ መለስ ዜናዊ ተደላድለው በህወሓት-ማለሊት ኮርቻ ላይ ተቀመጡ። የህወሓት ሁለተኛ መሰንጠቅ ይህ ነው።
የስየ አብርሃ ክህደት
ስየ አብርሃ ደፋርና ጎበዝ እንደነበረ አውቃለሁ። ከሃዲነቱን ግን አላውቅም ነበር። በ1969 የሕንፍሽፍሽ ዋና ተዋናይ ነበር ተብሎ በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን እስከ 1977 ድረስ በዓይነ ቁራኛ ሲከታተሉት እንደነበር አውቃለሁ። ከህወሓት ታጋዮች ደግሞ ለሰየ አብርሃ ጥብቅና እና ድጋፍ አልተለየውም ነበር። ከዚህም የተነሳ ነው በማለሊት ጉባኤ በከፍተኛ ድምጽ የመረጥነው። ነገር ግን ከሃዲውና እምነተ ቢሱ ስየ አብርሃ የሥልጣን ጥማቱን ለማርካት የህወሓት-ማለሊት ሙሉ ወታደራዊ አዛዥ ለመሆን ግደይ ዘርአጽዮንን እና አረጋዊ በርሄን በውሸትና በስም ማጥፋት ደበደባቸው። ሲጠብቀውና ሲንከባከበው የቆየውን ታጋይ ለምን መለስ ዜናዊን እና ስብሃት ነጋን በአነስተኛ ደምጽ መረጣችሁ ብሎ ነባሩን ታጋይ እንደ እባብ እራስ እራሱን ቀጠቀጠው። በየቦታው እየሄደ አጠፋው።seye
በህዳር 1980 የህወሓት ታጋይ ባነሳው ተቃውሞ ኤርትራም ሆነ ሌላ ቦታ ሂደን አንዋጋም። ትግራይን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነፃ አውጥተን የትግራይን መንግሥት መመስረት ነው እንጂ ከዚህ ውጭ የምናውቀው ነገር የለም። ኤርትራ ሄደው በረሃ የበላቸውና ያለቁት የትግራይ ወጣት ሴትና ወንድ እስከ አሁን 130,000 ደርሷል። የኛ ድርጅት ህወሓት ከየት ወረዳና ዞን መጡ የሚል ዝርዝር ስማቸው እንኳን አያውቀውም። እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ከብት እየታፈስን ሂደን ሞተን ቀረን። አሁንም ትግራይን ነፃ እናወጣለን እንጂ ሌላ ቦታ አንሄድም አለ። በዚህ ጊዜ እነ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ስየ አብርሃን አነጋግረው በ36,000 ታጋይ ላይ ሞት ፈረዱበት። ይህ ሁሉ ታጋይ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። በዚህ ግድያ የተሰማሩት መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሃየሎም አርአያ፣ ሳሞራ የኑስ፣ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተክለሃይማኖት፣ ስየ አብርሃ፣ ክንፈ ገብረመድህን፣ አርከበ እቁባይ፣ ገብሩ አስራት፣ ዓረጋሽ አዳነ፣ አውአሎም ወልዱ ወዘተ. ነበሩ።
የተግባሩ አፈጻጸም በስየ አብርሃና በክንፈ ገ/መድህን ትእዛዝና አመራር ነበር። ገዳዮቹ፣ ብስራት አማረ፣ ሃሰን ሽፋ፣ ወልደሥላሴ፣ ዘአማኑኤል ለገሰ (ወዲ ሻምበል)፣ ተስፋዬ ጡሩራ (መርሳ)፣ ተስፋዬ አፈርሰው (አጽብሃ) ወዘተ. ነበሩ። ከ200 በላይ የሃለዋ ወያነ (06) ታጋዮችን በማሰለፍ ታጋዩን ገደሉት። የሃውዜን ጥቃትም በደርግ ሚግ 21-23-27 በእጅ አዙር ያስደበድቡት እነ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ. ከዚህ ተነስተው ነው።
ስየ አብርሃ ይህንን ክህደትና አረመኔያዊ ተግባር ከመፈጸሙ ትንሽ ቀደም ብሎ ከነመለስ፣ ስብሃትና አባይ ፀሃየ ጋር ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ተጧጡፎ ቀጠለ። ስየ አብርሃ ሁሉንም ያጣ ብቻውን ሆኖ እየተናገረ መሄድ ጀመረ። ታጋዩ ሁሉ ጠላው፣ ራቀው። የፖሊት ቢሮ አባላት በየወሩ በስብሃት ነጋ የተፈቀደውን የኪስ ገንዘብ ብር 1,000 አልቀበልም አለ። ተወልደ፣ ገብሩ አስራትም እንደዚሁ አንቀበልም ብለዋል። ስየ አብርሃ በፈጸመው ክህደት እስከ ዛሬ በህወሓት ታጋይ እየተወገዘ ነው።
3.  የህወሓት ለሶስተኛ ጊዜ መሰንጠቅ
ወቅቱ ጥቅምት 1980 ነበር። የህወሓት ማ/ኮሚቴን ጨምሮ የማለሊት ማ/ኮሚቴ በአንድነት የተጠራ ስብሰባ ነበር። በዚህ ጊዜ የተነሱት ጥያቄዎች የስልጣን ሽኩቻ ሳይሆን የህወሓት-ማለሊት ፖሊት ቢሮ ዱሮ ከነበረውና ከተፈጸሙት ስህተቶች ያልተማረ፣ ብዙ ስህተት እየፈጸመ ነው። ከዚህ ስህተቱ መማር አለበት ወዘተ. በማለት የቀረበው ጥያቄ አነታራኪ ሆኖ በመቀመጡ፣ ስብሃት ነጋ በሚመራው ስብሰባ የቀረቡትን ጥያቄዎች በሙሉ ውድቅ አደረጋቸው። መለስ ዜናዊም የስብሃት ነጋን ሃሳብ ደገፈ። ጥያቄቆቹን ያነሱት በ1975 በ2ኛው ጉባኤ የተመረጡት የህወሓት አመራር ናቸው። እነሱም፤
  1. ክብሮም ገ/ማርያም የህወሓት ማ/ኮሚቴና የሰራዊቱ የሎጂስቲክ ዋና ሃላፊ የነበረ፣
  2. ኃ/ሥላሴ መስፍን፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴ፣ ጠቅላላ የህወሓት ክፍለ ጦሮች የኮሚሳሮች የበላይ ሃላፊና ተቆጣጣሪ የነበረ፣
  3. ሰአረ ገብረጻድቅ፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ጠቅላላ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ፖሊት ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበረ፣
  4. ተክሉ ሃዋዝ፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴና የቀድሞ የድርጅቱ ዋና የደህንነት ሃላፊ የነበረ ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱት አራቱ አመራር ባቀረቡት ሃሳብ አፈንጋጩ የእነ ግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ ደጋፊዎች ተብለው ተወነጀሉ። ወንጃዮቹ፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ገብሩ አስራት፣ አርከበ እቁባይ ናቸው፡ እነዚህ የፖሊት ቢሮ አባላት ተሰብሰበው ተወንጃዮቹን በማስጠራት እርማት እንዲያደርጉ ወሰኑ። በቀረቡበት ጊዜም፣ ያቀረባችሁት ሃሳብ ጸረ-ህወሓት-ማለሊት በመሆኑ፤ ከአመራርና ከሃላፊነታችሁ ተወግዳችሁ በተራ ታጋይነት ቀጥሉ ተብለው በስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ተሰናበቱ። ይህ ወቅት ህወሓት ለሶስተኛ ጊዜ የተሰነጠቀበት ወቅት ነበር።
5.  የህወሓት ለአራተኛ ጊዜ መሰንጠቅ
ይህ የህዋሓት ለአራተኛ ጊዜ መሰንጠቅ በ1993 የተፈጠረው ነው። ዋናው ዓላማ የስልጣን ሽኩቻ ነበር። ሌላው አንዱ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ሆኖ ሌላው ደግሞ ጸረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተፈጠረ መበታተን አይደለም። በእነ ስየ አብርሃ የሚመራው ቡድንም ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያን ያፈረሱ፣ የቀይ ባህር የባህር በሯን የሸጡና ያስነጠቁ፣ የዘር ማጥፋት እልቂት የፈጸሙ፣ ሕዝብን ለድህነት፣ ለችግር፣ ለበሽታና ለስደት የዳረጉ እነ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስየ አብርሃ፣ ተወልደ ወ/ማርያም፣ ገብሩ አስራት ወዘተ. ተባብረው በሕዝብና በሃገር ከባድ ወንጀል የፈጸሙ ናቸው። በሁለት የተሰነጠቁበት ቀንደኛ ምክንያት ደግሞ የስልጣን ሽኩቻ ነው። ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።
6.  የህወሓት ለአምስተኛ ጊዜ መሰንጠቅ
ህወሓት ኢትዮጵያን ወሮ በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረ በኋላ መሪው መለስ ዜናዊና የህወሓት አመራር ሁሉም በሃገራችን ከፍተኛውን የሥልጣን ወንበር ላይ ተደላድለው በመቀመጥ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት በገዙበት ጊዜ በሕዝብና በሃገር ከፍተኛ ወንጀል በመፈጸም የኢትዮጵያን ሃብት ዘርፈዋል። ሕዝብን ያደኸየውን ስርዓት የመሰረተው መለስ ዜናዊ ሰኔ 7 ቀን 2004 ከዚህ ዓለም በሞት ተቀጠፈ። ብስራት አብሳሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታና መመኪያ እንዲሁም ዓይን እና ጆሮ ኢሳት በጥዋቱ የመለስ ዜናዊን ሞት ነገረን። ለወዳጆቹ ሃዘን ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የእፎይታ ቀን ሆነ። አረመኔው መሪ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተቀጥፎ መኖሪያውን ሲኦል አደረገ። በዚህም ምክያት ህወሓት ለአምስተኛ ጊዜ ተሰነጠቀ። ከላይ እስከ ታች በቅራኔና በሥልጣን ሽኩቻ እንደ ዱባ ተፍረከረከ።
    1. የተህሓት ወግ አጥባቂ
ተረካቢ (Old guard)
    2. ተንኳሽ
(Catalyst)
    3. የመለስ ዜናዊ ውርስ
(Legacy)
ስብሃት ነጋደብረጽዮን ገ/ሚካኤልአባይ ወልዱ
ብርሃነ ገ/ክርስቶስጌታቸው አሰፋሳሞራ የኑስ
አርከበ እቁባይቴዎድሮስ አድሃኖምበየነ ምክሩ
ጸጋይ በርሄአለም ገ/ዋህድቴዎድሮስ ሃጎስ
አባዲ ዘሞክንደያ ገ/ሕይወት
ብርሃነ ማረት፤
ትርፉ ኪ/ማርያም
እነ ስብሃት ነጋ ያላቸው ደጋፊ ጥቂት ሲሆን፤ እነ አባይ ወልዱ የህወሓት ማ/ኮሚቴውን በብዛት ይዘዋል። እነ ደብረጽዮንም ከነአባይ ወልዱ ድጋፍ አላቸው። አንድ ተረት አለ፣ ‘ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ’ እንደሚባለው ነው። የህወሓት መንጋ ከአመራሩ ጀምሮ እስከ ተራ አባላቱ በወንጀልና በሰው ልጅ ደም የታጠበ ነው። በዚህ ዓይነት በሳሞራ የኑስ የሚመራው ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ ደህንነቱ፣ የፌደራሉ ሁሉ ወንጀለኞችና ጸረ-ሕዝብ ናቸው። መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበረበት ጊዜ በ1993 የተነሳው የስልጣን ሽኩቻ በሁለት ሲሰነጥቀው፤ አሁንም ተመሳሳይ ዓይነት እጣ የደረሰው ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ነው፤፡ ህወሓትን በሶስት የከፈለው ዋናው የሥስልጣን ሽኩቻ ብቻ ሳይሆን ኢፈርትን ማን ይምራ፣ ማንስ ይቆጣጠር የሚለው ነበር። በ’ለ’ ስር የተዘረዘሩት የኢፈርት ዋናው የዝርፊያ መሳሪያ ስለሆነ በኛ ይመራ ባዮች ናቸው። በ’ሀ’ ምደብ ስር ያሉት እነ ስብሃት ነጋ ከላይ እሰክ ታች ኢፈርትን መቆጣጠርና መምራት ያለብን እኛ ነን ብለው ቁመዋል። በተጨማሪም፣ ከሥልጣኑም የሚንስትርነት ቦታ ለኛም ይገባናል ባዮች ናቸው። በተለይ አዜብ መስፍን በሕገወጥ መንገድ ከስብሃት ነጋ የወሰደችው የኢፈርት መሪነት ለኛ tedrosይመለስልን ሲሉ በ’ለ’ እና በ’ሐ’ የተሰለፉት አልተቀበሉትም። አዜብ መስፍንን ከኢፈርት አስወግደን በሌላ ሰው እንተካታለን በማለት ተስማምተው ብርሃነ ኪዳነማርያምን በቦታዋ በዳይሬክተርነት አስቀመጡት። እነ ስብሃት ነጋ ግን ይህንን አልተቀበሉትም። የኢፈርት የበላይ ሃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ነው። እነ ስብሃት ነጋ በዚህ ግራ ተጋብተዋል።
በ’ለ’ ምደብ ያሉትን እነ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ትልቁ ጥረታቸው በአባይ ወልዱ የሚመራው በ’ሐ’ ምድብ ስር ያሉት በ’ሀ’ እና በ’ሐ’ ምድብ ያሉት እንዳይስማሙና በመካከላቸው ሆነው ነገር በመተንኮስ ቅራኔ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋሉ። አዜብ መስፍንን ካነሳን ዘንድ፤ አንበሳ ባንክን ወዘተ. ተቆጣጠሩ ተብሎ ለነስብሃት ነጋ የተሰጠ ገጸ በረከት ነው። የኤርትራው ተወላጅ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ‘ኢትዮ ቴሌኮምን’ የግል ሃብቱ በማድረግ የሃገርና የሕዝብ ሃብት እየበዘበዘ ገንዘቡን በቻይና ባንክ በማስቀመጥ ኢትዮጵያን እያደማ ይገኛል። በ2007 ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ፍላጎትም አለው።
ኤርትራዊው ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የሃገር ሃብት እየዘረፈ በማሌዢያና በተለያዩ ሃገራት ባንኮች ሃብቱን እያደለበ የሚገኝ የህወሓት መሪ ነው። ኢፈርትንም መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ በሃላፊነት የተረከበ ሰው ነው። በ2007 ምርጫም በእነ ወልዱ ድጋፍ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ያገኘ ሰው ነው። እነ አባይ ወልዱ በትግራይ ውስጥ የሚገኙት የኢፈርት ፋብሪካዎች፣ እንደ አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ፣ መሶብ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ መስፍን ኢንጂነሪንግ ወዘተ. ወፍራሙን ድርሻ ያገኛሉ። በዚሁ መሰረት ኢፈርት ከተመሰረተ ከ1985 ጀምሮ ለመንግሥት ግብር አይከፍልም። ከብሄራዊ ባንክና ከንግድ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ አይመልስም፣ እንዲያስከፍለው የሚያስገድደው ሕግም የለም። የተለያዩ እቃዎች ሲያስገባና ሲያስወጣ ቀረጥ ለመንግሥት አይከፍልም። ምክንያቱም ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ስር የያዘው የህወሓት ባለሥልጣናት የግል ንብረታችው ስለሆነ በማንም ሕግ የማይገዛ ኢፈርት ነው።debretsion gebremichael
መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ በህወሓት ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሯል፣ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሃይላቸውም የተበታነ እርስ በርሳቸው አለመተማመን ነግሷል። ሁሉም የህወሓት አመራርና አባሎቹ ደጋፊዎቹ በሙስና የተጨማለቁ በዘር ማጥፋት ወንጀል በመሰማራት ከ8.9 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የገደሉ ናቸው። ከ30 ሚሊዮን በላይም ኢትዮጵያዊ ከተወለደበት ከሚወዳት ሃገሩ ሠርቶ ከሚበላባት፣ ልጆቹን አስተምሮ፣ አሳድጎ ለቁም ነገር ካበቃበት መሬቱ በማፈናቀል ግማሹ ለስደት ግማሹ ለሞት፣ ግማሹ ለችግር፣ ለረሃብ፣ መኖሪያ አልባ አድርገውታል። ከዚህ በመነሳት ህወሓቶች በጽኑ አቋም የሚስማሙበት አጀንዳ አላቸው። ። ከህወሓት የተባባሩ አመራር የነበሩትም በዚህ በጸና አቋም ይስማማሉ።
  1. አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሕገመንግሥት የህወሓት ሕገመንግሥት ነው። ይህም ከ1967 እየታገልን ይዘነው የመጣን የሕይወታችን እና የንብረታችን መድን ነው። ይህ ሕገመንግሥት ከተናደ አሁን ያለነው የተባረሩት አመራርም ተለቅመን ታሰርን፣ ሃብታችን ተወረሶ እኛም እንገደላለን። ስለሆነም ያለውን ሕግመንግሥት መክላከል የግድ ይሆናል። ሁሉም በዚህ ይስማማሉ፣
  2. ኢፈርት የህወሓት ሃብት ነው። ኢፈርትም በኢትዮጵያ ያሉትን ገዢ ተቋማት በተዘዋዋሪና በቀጥታ የሚቆጣጠር ነው። ለምሳሌ፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ ንግድ ባንክ፣ መአድናት፣ ትራንስፖርት ወዘተ. የሃገሪቱ ንግድም ከትንሹ እስከ ትልቁ የሚቆጣጠር ነው። ይህ የደም ስራችን ከወደመ በሕዝብ ቁጥጥር ከዋለ ህወሓትና መሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ የህወሓት መንግሥታዊ ተቋማት ጭምር ይወድማሉ። ስለሆነም ባለን አቅማችን ኢፈርትን መከላከል በበለጠ ማሳደግ አለብን። በዚህም በማያወላውል መንገድ ይስማማሉ፣
  3. የሕዝብ የአመጽ ተቃውሞ ወይም አብዮት ከተነሳ ባለን መከላከያ ሰራዊት ደህንነት፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ልንመልሰው አንችልም። ሕዝቡ ከአሸነፈ የህወሓት አመራር አባሎችና ደጋፊዎቻችንን በእሳት እንደሚቀቅለን እናውቃለን። ለዚህ መድሃኒቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ በየጎሳ ከፋፍለን አሁን ባለው አይነት ደፍጥጠን ማጥቃት፣ ተቋዋሚ ድርጅቶችን ማዳከም፣ መግደል ማዋከብ አለብን። የአገዛዛችን መንገድ ሕዝቡን ማስጨነቅ፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ በስደት እንዲጓዙ ማድረግ እነዚህን በዋናነት እንደ መሳሪያ መጠቀም አለብን። ወጣቱን ዜጋ ደግሞ በሽርሙጥና፣ ሃሺሽ ወዘተ. በብዛት አስፋፍቶ ከጥቅም ውጭ ማድረግ። በጎሳ ከፋፍለንም ኢትዮጵያዊነት የሚል ስር የሰደደውን እምነት ማጥፋት፣ የአማርኛ ቋንቋን ማጥፋት፣ በየትኛውም ጎሳ የሚገኘውን ስር መሰረቱን ነቅለን እንዳልነበረ ማድረግ። በዚህም ሁሉም ይስማማሉ።
ኢትዮጵያን አሁን ማን እየመራት ነው?
መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር ተብሎ እንደተሰየመ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቀዋል። ነገር ግን ኃ/ማርያም የእውነት ሳይሆን የውሸት ጠ/ሚኒስቴር ነው። ኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ አሁንም መዋቅሩን የዘረጋው ህወሓት ነው። ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ኢትዮጵያን የሚመሩትና የሚያስተዳድሩት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ ቴዎድሮስ አድሃኖምና ንዋይ ገብረአብ ናቸው። ስለዚህ ኢትዮጵያን ማን እየመራት ነው ለሚለው ጥያቄ በትክክል ከላይ የተጠቀሱት ሶስቱ የህወሓት አመራር ናቸው። የስርዓቱን መዋቅርም በነዚህ ግለሰቦች ይመራል። ኃ/ማርያም ደሳለኝ አድርግ ያሉትን የሚያደርግ ጉልቻና ቃል አቀባይ ነው።
በ1922 የተወለደው የ83 ዓመቱ ዘራፊና ገዳዩ ሽማግሌ ስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ለባለሥልጣናቱ እንቅፋት አይሆንባቸውም። መሪዎቹ የሚፈልጉት ዝርፊያ ብቻ ነው። እነ አባይ ወልዱ ከነ ደብረጽዮን ጋር ተስማምተው በትግራይ ሪፓብሊክ መንግሥት ውስጥ እጃችሁን አታስገቡ። ገንዘብ እንፈልጋለን፣ ከፍተኛ ባጀት መድቡልን፣ እኛም የእናንተ ደጋፊዎች ነን በማለት ተስማምተዋል።
hailemariam speakingለሚቀጥለው የ2007 ምርጫ ህወሓት በአሸናፊነት ወጥቶ ለጠ/ሚኒስቴር፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚሆኑትን እጩዎቹን አዘጋጅቷል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናል ተብሎ የታጨው ቴዎድሮስ አድሃኖም ሲሆን፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊሆን የታሰበው ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ነው። “አባይ ማደርያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል” ማለት ይህ ነው። ህወሓት የተዳከመ፣ የበሰበሰ ግንድ ነው። በዚህ ደረጃ ላይ ያለ ፋሽስታዊ ድርጅት ኢትዮጵያን ረግጦ የመግዛት አቅም የለውም። በኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይል ክንድና አንድነት ይደመሰሳል። ይህንን ድክመታቸውን በመጠቀም ሃገር ቤትም በውጭ ሃገር የምንገኘውን ጨምሮ አንድነታችንን አጠናክረን በሕዝባዊ አመጽ ወያኔ ህወሓትን የመደምሰስ ጊዜው አሁን ነው።
የመለስ ዜናዊ ራእይ
በዚሁ ጥቂት ጥያቄዎችን በመለስ እደመድማለሁ። መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ማን ነው?
መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ የጠላት ጠላት ደመኛ ጠላት ነው። ከአባቱ፣ ከእናቱና ከአያቶቹ የወረሰው በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ የፈጸመው ግፍ፤ የሃገር ማፍረስ ድርጊት በታሪክ የማይረሳ ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን የህወሓት አመራርንም ይጨምራል። የስም ዝርዝራቸውን በተለያዩት ጽሁፎቼና ከዚህ በላይም ስላካተትኳቸው እንሱን መመልከትና ማመሳከር ይቻላል።
የመለስ ዜናዊ ራእይ በኢትዮጵያ ልማት፣ እድገት፣ ዲሞክራሲ ማለትስ ምን ማለት ነው? በእርሱ አመራር ለ21 ዓመታት ኢትዮጵያ በልማትና በዲሞክራሲ አብባለች የሚሉት የህወሓት ደጋፊዎችና አጋር ድርጅት ተብለው የሚጠሩት ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ኢትዮጵያ ስብስብ ብቻ ናቸው። ብዙ ለሆዳቸው ያደሩም አሉባቸው። ነገሩ የተጋላቢጦሽ ነው። መለስ ዜናዊ የሚመራው ህወሓትና አመራሩ በተፈጥሮው ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ዲሞክራሲ ነው። ህወሓት አፈጣጠሩ አምባገነን እና ፋሽስት፣ እንዲሁም ጸረ-ዲሞክራሲ ሆኖ ያደገ ከመቅጽበት የልማት፣ እድገትና ዲሞክራሲ አራማጅ ሊሆን አይችልም። ጎባጣና ጠማማ ሆኖ ያደገ ባህር ዛፍ ተቃንቶ ለኤሌክትሪክ ምሰሶ ወይም ለቤት መስሪያ ማገር ልታደርገው አትችለም። በምሳር ቆራርጦ ማገዶ ከማድረግ ውጪ። ህወሓትን በዚህ አይነት ልንመለከተው ይገባል። ስለሆነም የመለስ ዜናዊ ራእይ ጸረ-ሕዝብ፣ ጸረ-ልማት፣ ጸረ-እድገት፣ ጸረ-ዲሞክራሲ ነው። መለስና ግብረአበሮቹ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሰማሩ፣ በሙስና የሕዝብና የሃገር ሃብት የዘረፉ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ በፋሽስት መዋቅራቸው ያሰቃዩና የገደሉ ናቸው። እንደዚህ ያለ ጨቋኝና ፋሽስት መንግስት ልማታዊ ሊሆን አይችልም።
መለስ ዜናዊና ህወሓት ለኢትዮጵያና ሕዝቧ ምን ናቸው? በመለስ ዜናዊና በስብሃት ነጋ የሚመራው ፋሽስት ፓርቲ፣ ኢትዮጵያን ከግንቦት ወር 1983 ጀምሮ ከተቆጣጠሩ ወዲህ ኢትዮጵያና ሕዝቧ በወያኔ ሀውሓት ቅኝ አገዛዝ የወደቀችበት ወቅት ሆኖ፣ እነሆ ቅኝ ገዢው ህወሓት በሃገራችን አረመኔያዊ ድርጊት እየፈጸመ ይገኛል። በመለስ ዜናዊ የአገዛዝ ዘመን የኢትዮጵያ ሉአላዊንት ፈርሷል። ጥንታዊና ታሪካዊ የቀይ ባሕር ወደቦቿን አጥታለች። ሕዝብ በዘሩ እየታየ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል። ስለዚህ መለስ ዜናዊና ህወሓት እንዲሁም አመራሩ የኢትዮጵያ ደመኛ ጠላት ናቸው።
መለስ ዜናዊ የወታደራዊ ሳይንስና ስትራተጂ ባለ ራእይ ይባላል። ይህ አነጋገር ደረቅ ውሸት ነው። መለስ ዜናዊን የሚያውቁና አብረውት በትግሉ የነበሩ ታጋዮች የማይቀበሉት ጉዳይ ነው። የህወሓት መንጋ በምን ዓይነት የውሸት አዘቅት ውስጥ እንደሰመጠ በግልጽ የሚያሳይ ነው። መለስ ዜናዊ ከትግሉ መጀመሪያ አንስቶ ለብዙ ዓመታት አብረን ተጉዘናል። በጣም የሚተማመንብን ጓደኞቹ ተክሉ ሃዋዝና እኔ ገ/መድህን አርአያ ነበርን። በሚገባ ስለምናውቀው የወታደራዊ ስታርቴጂስት አልነበረም። እውቀቱም ችሎታውም ፈጽሞ አልነበረውም። ሃቁ ይህ ነው።
“ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” እንዳለው ዓይነት ነው። መለስ ዜናዊ ከፈሪነቱ የተነሳ በተለያዩ ጦርነቶች ፈርቶ የሸሸ፣ በህወሓት ታሪክ ውስጥ በፈሪነቱ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ግለሰብ ነው። ከሸሸባቸው ጦርነቶች ለአብነት፤
  1. በ1969 ከአድዋ ኦፐሬሽን ጦርነቱ እንደተጀመረ ፈርቶ የሸሸ፣
  2. በ1970 ከአዲ ደእሮ ፈርቶ የሸሸ፣
  3. በ1971 መጀመሪያ ላይ ከማይቅነጠል ውጊያ ፈርቶ የሸሸ፣
  4. በ1971 ህዳር ወር ከፈረስ ማይ ጦርነት ፈርቶ የሸሸ፣
  5. ሰኔ ወር 1971 ከሃገረ-ሰላም ውጊያ ታመምኩ ብሎ መሬት ላይ ሲንከባለል በበቅሎ ተጭኖ እንዲምለስ የተደረገው  ናቸው። በምስክርነት የሰራዊቱ የጦር አዛዥ አረጋዊ በርሄ የሚያውቀው ጉዳይ ነው።
በህወሓት ውስጥ ማንም ታጋይና አመራር የሚያውቀው ሃቅ አለ። ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ የነደፈው ጥናት እያደረገ ወታደረአዊ ስትራተጂ ወታደራዊ ታክቲክ የአሸዋ ገባታ ለረጅም አመታት ጥናት በማካሄድ የጻፈና ያዘጋጀ ብቸኛው አረጋዊ በርሄ ነው። ለሁሉም ወታደራዊ አመራር ስየ አብርሃ፣ ሃየሎም አርአያ ወዘተ. አስተምሮ ያሳደጋቸው አረጋዊ በርሄ ነው። ስየ አብርሃ ይሁን ሌላው የሚኩራሩበት ውሸት ነው። ወያኔ ህወሓት እስከ አሁን የሚጠቀሙበት ወታደራዊ ጉዞ በአረጋዊ በርሄ የተዘጋጀ እንጂ መለስ ዜናዊ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ወታደራዊ ሳይንስ ይሁን ስትራተጂ የጤፍ ቅንጣት የምታክል እውቀት አልነበረውም። ሁሉም የሚዋሸው ለሆዱ፣ ለጥቅሙና የሙስና ዘርፊያውን በስፋት ለመቀጠል ስለሚፈልግ የሚመታው የውሸት ነጋሪት ነው።
ግደይ ዘርአጽዮን ከህወሓት ወጥቶ ወደ ስደት ሲሄድ በህቡር ገብረኪዳን መሪነት ተክለወይን አሰፋ፣ ተሻለ ደብረጽዮንን ጨምሮ ተፈትሾ የያዘውን ሰነዶች ሁሉ፣ ብጣሽ ወረቀት ሳትቀር፣ ጠራርገው በመውሰድ ባዶ እጁን ሱዳን ገባ።
አረጋዊ በርሄ፣ ህቡር ገ/ኪዳን፣ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ እቁባይ ሁነው ለብዙ ዓመታት ሲያካሂዱት የነበረውን ወታደራዊ ጥናትና ስትራተጂ የአሸዋ ገበታ፤ በትልልቅ ወረቀቶች ላይ በሰእል መልክ የተዘጋጁ ጠቅላላ ወታደራዊ መጻሕፍት ብጣሽ ወረቀት ሳትቀር በሁለት የማዳበሪያ ከረጢት ሞልተው የወረሱትን በታጋዮች አሸክመው ለመለስ ዜናዊ አስረከቡት። ‘በሰው ደንደስ በርበሬ ተወደሰ’ እንደተባለው፣ መለስ ዜናዊ ባልሰራውና በማያውቀው ወታደራዊ ስትራተጂ የአሸዋ ገበታ ንድፈ ሃሳብና አረጋዊ በርሄ ደክሞ ያዘጋጀው ነው። አሁን ወያኔ የሚጠቀምበት ወታደራዊ አካሄድ የአረጋዊ በርሄ ሥራና ጥናት ነው። ባልሰራኸው፣ በማታውቀው ጥበብ የራስህ አስመስለህ መጠቀም ያስንቃል፣ ያዋርዳል። ስለዚህ መለስና የህወሓት መንጋ ውሸታምና በምን ዓይነት ድቅድቅ የውሸት ጨለማ እንደተዘፈቁና ማንነታቸውን እንዲያውቁ ይህንን የጽሑፍ ሰነድ ያንብቡ።
የስብሃት ነጋ መርዶ ነጋሪ
ቀደም ብሎ በተህሓት-ህወሓት የነበረው የኢትዮጵያውያን አመራር ነበር። እነ አቶ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ በምን ምክንያት በምን ዘዴ እንደገደሏቸው በትክክል አስቀምጬዋለሁ። በየካቲት 1981 በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የነበረው ደርግ ትግራይን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ወያኔ ህወሓት ካለምንም ውጊያና ውጣ ውረድ ትግራይን ተቆጣጠረ። ሃቁ ይህ ሆኖ፣ በ1983 በለስ ቀንቷቸው አዲስ አበባ ዘው ብለው ኢትዮጵያን እነደተቆጣጠሩ፣ ነብሰ ገዳዩ ስብሃት ነጋ በመርዶ ነጋሪነት ተሰማራ። የዶ/ር አታክልት ቀጸላ ወላጅ አባት የሚኖርበት ቤት በመሄድና እራሱን በማስተዋወቅ የዶ/ር አታክልትን ሞት ነገራቸው። በአረጋዊ በርሄ እንደተገደለ ሲነግራቸው፣ አረጋዊ በርሄ የማን ልጅ ነው ብለው ሲጠይቁት፣ የቀኛዝማች በርሄ ገብረማርያም ነው ሲላቸው፣ የልጅ በዛብህ ፍላቴ ልጅ? ብለው ጠየቁት፣ አዎን አላቸው። የቅርብ ወንድሙ ለምን ገደለው? ሲሉት፣ በአረጋዊ መገደሉን እንጂ ሌላውን ሳይነግራቸው መርዶውን አሰምቶ ተሰናበተ። በጅሮንድ ቀጸላም በሚወዱት ልጃቸው መርዶ የተነሳ ታመው ከብዙ ስቃይ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ስብሃት ነጋ ይህ አልበቃውም። አድዋ አቶ ዳኘው ገ/ሥላሴ ቤት ደረስ በመሄድ የአጽብሃ ዳኘው ወላጅ እናትና ጠቅላላ ቤተሰቡ ባሉበት፣ በአክብሮት ተቀብለው ቤት ያፈራውን ከጋበዙት በኋላ፣ እናቱ ወ/ሮ ማና ተፈሪ ልጄ ‘ሞላ’ (የቤት ስሙ) እንባቸውን እያፈሰሱ፣ ልጄ ጠፋብኝ፣ የምታውቀው ነገር አለ ወይ ብለው ሲጠይቁት፣ ስብሃት፣ አጽብሃ፣ ሰዊት ተገድሎ ከሞተ ብዙ ዓመት ሆኖታል አላቸው። አባትየው ቀበል አድርገው እንዴት ሞተ ሲሉት፣ አረጋዊ በርሄ ገደለው አላቸው። አረጋዊ፣ የቀ/አ በርሄ ገ/ማርያም ልጅ? ብለው ሲጠይቁት፣ አዎን አላቸው። ያሳደገው ወንድሙ ገደለው? የአጽብሃ ዳኘው እናት በዚህ ደንግጠው ታመው በሃዘን በሽታ ተሰቃይተው ሞቱ። ሽማግሌው አቶ ዳኘው ገ/ሥላሴ አሁንም በሕይወት አሉ። የዶ/ር አታክለት ቀጸላ ወላጅ አባትም በመርዶው ምክንያት ታመው፣ ራስ ወርቅ ልጄ እንዳሉ ሞቱ። በ1998 የሁለቱ ቤተውስቦች ስልክ በቀጥታ ወደ እኔ ደውለውልኝ ተነጋግረናል። በዚህ ሃሳብ ላይ እንዳለን፣ የዶ/ር አታክልት ቀጸላ ወላጅ አባት በጅሮንድ ቀጸላ ብሩ፣ ወላጅ እናቱና የእኔ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ገ/መድህን አርአያ ወላጅ እናቴ ወ/ሮ አጸደ ገብሩ እናት፣ የሁለቱ እናቶች ታላቅና ታናሽ የአንድ አባትና እናት ልጆች ናቸው። በዚህ መሰረት ነው የዶ/ር አታክለት ቀጸላ ቤተሰቦች አረጋዊ በርሄ በምን ምክንያት እንደገደለው የጠየቁኝ። እኔም ስብሃት (ወ/ሥላሴ) ነጋ የነገራችሁ ውሸት ነው። ዶ/ር አታክልትን የገደለው ስብሃት ነጋ ነው፣ በማለት በጽሑፍ እንደገለጽኩት ስነግራቸው አምነውኝ ተለያያን። ያመኑኝ ምክንያት የአታክልት መገደል ለእኔም የሚሰማኝ ልክ እንደ እነሱ ስለሆን ነው። ለእኔም ለነሱም ወንድማችን ነው።
ቀጥሎ ከትንሽ ወራት በኋላ በ1998 ከአጽብሃ ዳኘው ቤተሰብ ወንድሙ ከእንግሊዝ ሃገር ደወለልኝ። በጽሑፍ እንዳስቀመጥኩት ገልጬለት አልቅሶና አጽናንቼው ተለያየን። ቀጥሎ ለሁለተኛ ጊዜ በ2000 ወንድሙ ደውሎልኝ፣ ያቀረብኩለትን ሁሉ እንዳለ አምኖ ተቀበለኝ። ሌላው ያቀረበልኝ ጥያቄ ቤተሰቦቼ በአረጋዊ በርሄ ቅሬታ አድሮባቸው ነበር፤ በምን አይነት ይቅርታ ልጠይቀው፣ እባክህ ንገርልኝ ሲለኝ፣ የለም ከሆነ ባንተ ነው መሆን ያለበት ብዬው እንደሚደውልለት ነግሮኝ ተሰነባበትን። አረጋዊ በርሄ ግምት ያልሰጠው እውነት አለ። የህወሓት ፕሮግራምን ጽፎ ለ12 ዓመት በከፍተኛ አመራር ላይ ሆኖ ያስተዳደረው ድርጅት ነው። ማንም የማያቀውን የድርጅቱን ወንጀሎች በዝርዝር ያውቃል። ህወሓት በሥልጣን ላይ ሆኖ ለፈጸመው ግፍ ተጠያቂ እንዳይሆን አረጋዊ በርሄ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወያኔን ማጋለጥ አለበት።
እነ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ. በትግሉ ጊዜ የተገደሉት ታጋዮች፣ ሰላማዊ ዜጎች በስንት ሺህ የሚቆጠሩ ናቸው። ከ1982 በዘመቻ መልክ ተነስተው ያስፈጁትን አረጋዊ በርሄ እንደገደላቸው አድርገው ስሙን በክፉ መልክ አጥፍተውታል፣ አሁንም እንደቀጠሉበት ነው። የህወሓት አባላትና ደጋፊዎቹ እስከ አሁን እኛን የፈጀን አረጋዊ በርሄ ነው እያሉ ይገኛሉ። እሱም ይህንን ነገር በትክክል ያውቃል። አረጋዊ የሚለውና የሚሟገተው፣ ማስረጃችሁን አቅርቡ እያለ ነው። ይህ አባብሉ ግን ትክክል አይደለም። የፖሊት ቢሮ አባልት ሁሉ በየ06 ሃለዋ ወያነ እየተበተኑ ሕዝብ የጨረሱት አመራሩ ናቸው። በ06 ሃለዋ ወያነ ሃላፊዎች የምርመራ ሪፖርት ጭፍን ፍርድ ሲሰጥ የነበረው አመራር ነው። በሰነድ ተደግፎ የሚፈጸም ግደሏቸው የሚል ትእዛዝ በተህሓት-ህወሓት አሰራር አይታወቅም።
እነ ስብሃት ነጋ በአረጋዊ በርሄ ላይ የሚያካሂዱት የስም ማጥፋት እልባት ማግኘት አለበት ከሚል ሃሳብ ተነስቼ መጋቢት 2 ቀን 2000 በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ተወላጆች ማህበር፣ በዶ/ር ግደይ አሰፋ ሊቀመንበርነት፣ በአቶ ተስፋየ አጽብሃ የሚመራው ቡድን በተጠቀሰው ቀን ተሰበሰበ። ለአረጋዊ በርሄ ያቀረብኩት ሃሳብ በእነ ስብሃት ነጋና በወያኔ ስርዓት ስምህ እየጠፋ ነው። አንተም በመጀመሪያ ማድረግ ያለብህ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀህ በህወሓት የተፈጸሙትን ወንጀሎች ለሕዝብ አቅርብ። ያን ስታደርግ የአእምሮ እረፍት ታገኛለህ። በህወሓት በርካታና ከባድ ወንጀሎች ተፈጽመዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅር ባይ ነው የሚል ሃሳብ አቀረብኩለት። በወቅቱ የነበሩ አመራርና በቴሌ ኮንፈረንስ የነበሩት የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው። አረጋዊ በርሄ ለምን ደፈርከኝ ብሎ ብዙ ተናገረ። ቁም ነገሩ ቴሌ ኮንፈረንስ በመሆኑ ነው እንጂ በአካል አጠገቡ ብገኝ ኖሮ ረጋግጦ ያጠፋኝ ነበር። የሁላችንም ግንኙነት ከዚህ ጊዜ በኋላ ተቋረጠ። ጥሩ ምክር በመለገሴ ጠላት አፈራሁ። የመከራና የችግር ጊዜ ወንድሙን ጠላኝ። ይባስ ብሎ የህወሓት ጠላትና ጽንፈኞች በማለት፣ አስገደ ገ/ሥላሴን እና እኔ ገ/መድህን አርአያን ፈረጀን። ይህን ለማለቱ ብዙ የሰው ምስክሮችት አሉን። የተማረ ሰው ነው። በህወሓት ውስጥ ያለፈ አመራር ሁሉ፣ ከትግሉ መጀመሪያ አንስቶ፣ ብዙ ወንጀል ፈጽሟል፣ በመፈጸም ላይም ነው። ስለዚህ ማንም አመራር እኔ ነፃ ነኝ የሚል ካለ ተሳስቷል። ልክ እንደ ግደይ ዘርአጽዮን ጥፋተኛ ነኝ ብሎ ደጋግሞ እንደሚናገረው ሌላውም ይህንን አርአያነት መከተል አለበት።
ውድ ኢትዮጵያውያን የህወሓት ታሪክና እንወቀው የሚሉት ጽሑፎቼ በዝግጅት ላይ ናቸው። በጥቂት ወራት ውስጥ ለሕዝብ ይቀርባሉ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ሶስተኛው ጽሑፌ ደግሞ “ተጠያዊዎቹ እነማን ናቸው” ይሚለውን በማዘጋጀት ላይ ነኝ። ከማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመጡ አመራር አንድ በአንድ ምን ሰሩ፣ በምንስ ይጠየቃሉ የሚለው ሰፊና ግልጽ መጽሓፍ እየተዘጋጀ ነው።
ማሳሰቢያ፡ በድህረ ገጽ የማስተላልፋቸውን ጽሁፎች ኢትዮጵያዊ ሁሉ በማተም ሰብስባችሁ “የህወሓት ገበና” በማለት በማህደር አጠራቅሙት። ጥሩ የሰነድ ማስረጃ ነው። የህወሓት አመራርና ካድሬዎቹ በሕዝብ የሚፈረዱበት ቀን ደርሷል።
ገብረመድህን አርአያ
ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይል ይደመሰሳል!!!
አውስትራሊያ
2006 ዓም የነጻነት ዓመት ናት!!!