fredag 21. juni 2013

ትውልድ ያናወጠ ጦርነት


the book

የመጽሐፉ ርእስ……………… ትውልድ ያናወጠ ጦርነት
ደራሲ……………………………. ንጋቱ ቦጋለ (ሻለቃ)
አሳታሚ…………………………. በግል
አታሚ……………………………. ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ የሕትመት ሥራ
የገጽ ብዛት………………………. 341
ዋጋ…………………………………. 55 ብር
ቅኝት………………………………. በአበራ ለማ
“. . . የሽሬ ውጊያ ብሎም በትግራይ ውስጥ የነበረው የመንግሥት ጦር አመራር በነመጋቢ ሃምሳ አለቃ ለገሠ አስፋው ችሎታ ማነስ ምክንያት፣ ምን ያህል ተፍገምግሞ እንደወደቀ ደህና አድርገህ ገልጸህዋል፡፡ መጋቢ ሃምሳ አለቃ ለገሠ አስፋው ጀምለው በያዙት ድርብ ድርብርብ ስልጣን ሳቢያ፣ አንድም የጦር መሪና አዛዥ በራሱ ተነሳሽንት፣ ያለበትን የጦር ሜዳውን ተጨባጭ ሁናቴ እያገናዘበ እንዳይንቀሳቀስ ተቀይዶ እንደነበር ያሰመርክባቸው ነጥቦችህ አንገት የሚያስደፉ ናቸው፡፡ በዚህም ሰበብ የበታቹ የቅርብ አለቆቹ አንዳችም የማዘዝ ኃይል እንደሌላቸው አውቆ ትእዛዝን መቀበል አሻፈረኝ ያለበት አስጠሊታ ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበር ትዝብትህን አካፍለህናል፡፡ ጀነራል ለገሠ አበጀ የጀግናን ገድል ፈጽመው ለጠላት እጃቸውን ላለመስጠት ሲሉ ሽጉጣቸውን ጠጥተው አከሱም ላይ ያሸለቡበትም ምክንያት፤ ይሄው በእዝ ጠገግ ውስጥ አልፎ መደማመጥ የጠፋበት ሥርዓተ አልበኝነት በጦሩ ውስጥ መስፈኑ እንደነበርም ላንባቢያን የሰጠህን ግንዛቤ እውስጣችን የሚኖር ቁስል ነው፡፡ ”በታሪካዊዋ አክሱም እምብርት ላይ መሰዋት ለኔ ኩራቴ ነው” ብለው መሰዋታቸውን የገለጽክበት ድምጸትም እውስጣችን እያንጎራጎርነው የምንኖረው ሰቆቃ ነው፡፡” (ይህ ከቅኝቱ ቀንጨብ ተደርጎ የተወሰደ ሲሆን ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar