torsdag 13. juni 2013

ወያኔ በሁመራ ከአርበኞች ጋር መዋጋቱን አመነ

 

June 12, 2013
ECADF – ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር “ነበልባል” በመባል የሚታወቀው ባብዛኛው በወጣቶች የተገነባው ተዋጊ ሀይል በሁመራ አካባቢ 35ኛውን የወያኔ ክፍለጦርና ሚሊሻዎችን ገጥሞ አንጸባራቂ ድል እንደተቀናጀ አስታውቆ ነበር። ዜናውን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ።
ቁስለኞቹን እና የተገደሉ ወታደሮቹን ሲያሸሽ የከረመው ወያኔ ከሶስት ሳምንታት በሗላ አርበኞችን ገደልኩ… ብሎ ዜና ሰርቶ ለቋል።
በሁመራ አካባቢ የተደረገውን የአርበኞቹን የውጊያ ውሎ የግንባሩ ሬድዮ በበኩሉ እንደሚከተለው ዘግቦታል፣
“35ኛው የወያኔ ክፍለጦር አባላት አዳዲስ ኦራል መኪና በመንዳትና አዳዲስ ዩኒፎርም በመልበስ አስፈሪ የጦር ሀይል ይመስሉ ነበር… ይሁንና ያን ሁሉ ኩራት እና መመጻደቅ ግንቦት 24 ቀን ነበልባሉ አርበኛ ውሀ ቸልሶበታል.. አዳዲሶቹ ኦራል መኪኖችም የወያኔዎቹን ቁስለኛና ሟች ወታደሮች ሲያጓጉዙ ሰንብተዋል።”
እንደ ሬድዮው ዘገባ የጎንደር ነዋሪዎች በአርበኞቹ የወጊያ ብቃትና ጀግንነት እጅግ ተደንቀዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሬድዮ ዘገባን ያዳምጡ።
Ethiopian People Patriotic Front Fighters in Action
Ethiopian People Patriotic Front fighters

4 Responses to ወያኔ በሁመራ ከአርበኞች ጋር መዋጋቱን አመነ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar