tirsdag 30. juli 2013

የአንድነት ከፍተኛ አመራር የህይወት ታሪክ እንዳይነበብ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች ከለከሉ July 30, 2013 9:25 am - See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5122#sthash.uJxIRiZA.dpuf

የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት አባል የነበሩት አቶ ግርማ ወ/ሰንበት የቀብር ስነስርዓት ላይ የህይወት ታሪካቸው እንዳይነበብ የፈለገህይወት አቡነ ገ/መንፈስቅዱስ ቤ/ክ አስተዳደር ከለከለ፡፡
ዛሬ ሐምሌ 23 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ ወዳጅ በተገኘበት የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈፅሟል፡፡ የቀብር ስነስርዓታቸው ላይ የህይወት ታሪካቸውን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለማንበብ ሲዘጋጁ የሳሪስ ፈለገ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም አስተዳዳሪዎች ከልክለዋል፡፡
አስተዳዳሪዎቹ የሰጡት ምክንያት አቶ ግርማ የህይወት ታሪካቸውDSCN2285 እንዳይነበብ ተናዘዋል የሚል የሐሰት መረጃ የህይወት ታሪካቸው እንዳይነበብ ከመከልከል አልፈው የፖለቲካ ተሳትፏቸው የሌለበትን የህይወት ታሪክ እንዲነበብ አድርገዋል፡፡ በሁኔታው ቅር የተሰኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ይህንን ህገወጥ ድርጊት መሆኑን በመግለፅ የአቶ ግርማ የህይወት ታሪክ ከቀብር ስነስርዓት በኋላ በዛው በቤተክርስቲያና አውደምህረት ላይ በአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ተነቧል፡፡DSCN2287    DSCN2288DSCN2289DSCN2332DSCN2301
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5122#sthash.uJxIRiZA.dpuf

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar