July 11, 2013
ከብረሃኑ ተስፋዬ
በዚህ ሳምንት አንድ እህቴ የመለስን ፎቶ ከጎናቸው ሰቀለው ምን ያደረግላቸዋል አለች ታዲያ እኔም አንድ የማውቀው ታሪክ ትዝ አለኝ ታደያ ሃሳቤን የሞገተው አቶ ሀይለ ማሪያም እስከ መቼ ስለ መለስ እያሉ እየፈረሙ ይኖራሉ የሚለው ሃሳብ መጥቶ ድንቅር አለብኝ።
በመሆኑም ትዝታየን አጋርቻችሁ ወደ ዋናው ሃሳቤ እመለሳለሁ፣
እንዲህ ሆነላችሁ ወቅቱ በደርግ ጊዜ ሲሆን ቦታውም ወደ አቃቂ መውጫ በነበረው የእርሻ መሳሪያዎቸ ኮረፖሬሸን ዋና መስሪያ ቤት ነው ለማታውቁት ይህ ኮርፖሬሽን በመንግስት እርሻ ሚኒሰቴር ስር ከሚተዳደሩት ሰባት ኮረፖሬሽኖች አንዱ የነበረ ነው አሁን ከፊል ንብረቱ ወደ ትገራይ ተልኮ ቅሪቱን ወያኔ አዲስ ስም ሰጥቶት ያለ ነው።
ታዲያ በወቅቱ የነበሩት ያሰተዳደር መምሪያ ሃላፊ በሞት ይለዩና ፔርሶኔል የነበሩት ሰው ውክልና ይሰጣቸዋል ይህ ምንም አይደለም ሆኖም ከጽህፈት ቤታቸው የሚወጡ ደብዳቤዎች ሁሉ ተወካይ በመሆናቸው ስለ ብለው ይፈረሙና የሚያርፈው ቲተር የሞቱት ሰውየ ስምና ማእረግ የያዘ ነው።
ከለታት አንድ ቀን አንድ የመስክ ሰራተኛ ቢሮ ይገባና ችግሩም ያስረዳቸዋል በችግሩም መሰረት ወደ ዋናው መስሪያ ቤት እንዲያዛዉሩት ይጠይቃል አሉታዊ መልስ ስለሰጡት ይናደድና አፍ እላፊ አግቦ ያለው ዘለፋ ይወረዉራል ተወካዩም በንዴት ጦፈው የስንብት ደብዳቤ አዘጋጅተው ያባርሩታል፣ ፣ ደብዳቤው ሲደርሰው ከሳቸው ፊርማ ግርጌ የተመታው ቲተር የሞቱት አሰተዳዳሪ ሰለነበር ከቁብም ሳይቆጥረው ወደመስክ ስራው ይመለሳል።
እንደደረሰም አለቃው አንተማ ተሰባናብተሃል ይለዋል አሱም እየሳቀ እንዴ እየው እንጂ ሰውየዉ ከሞቱ አመት አልፎዋቸዋል ሰለዚህ አንተም ይህን ትእዛዝ ካከበርህ አንተም ከሞትህ አመት አለፈህ እንዴ ነበር ያለው።
አቶ ሀይለ ማረያም ታዲያ እነሆ ላመት ፈሪ በሆነው ሂደታቸው እያደረጉት ያሉት ስለ መለስ እያሉ ከማላዘንና ከላይ የራሳቸውን ልብስ ከውስጥ የአቶ መለስን ሰደርያ አድርገው እሰከመቼ እንደሚዘልቁ ሳስበው እኒህ ሰው ህሊናቸውን አንቅረው አውጥተው ጥለው አቶ መለስ የሞሉዋቸው የኮካ ኮላ ጠርሙስ ተምሳሌት ሆነው ሊዘልቁ ቆርጠው የተነሱ ይመስለኛል።
አቶ ሀይለ ማርያም እግዚአብሄር በቃችሁ ብሎ ከወሰደው ሰይጣን የሚለዩት በጃቸው ላይ ባለው የህዝብ ደም ብዛት ወይም ባደረሱት ሰቆቃ ሳይሆን መለስ አፈር የተጫናቸውና ያደረሱትን በደል ሊያሰተካክሉት የማይችሉ ላንዴም ለመጨረሻም የሄዱ መሆናቸው ሀይለ ማርያም ግን ግማሽ በድን ቢሆኑም በቁም ስላሉ ወደ ህሊና መመለስ የሚችሉ መሆናቸው ነው።
በመሆኑም እኔ ግን ላካፍላቸው የምወደው በርኖስ ሲገለበጡት በርኖስ መሆናቸውን ትተው ከቻሉ (ስልጣን የሌላቸው መሆኑን ሰለምገነዘብ ነው) ወደ ህሊናቸው ተመለሰው ወደ ህዝብ ጎራ መቀላቀል ባይችሉ እንኩዋን ያለውን ሰቆቃና የሰብአዊ መብት ረገጣ መኖሩን ተረድተውና ለህዘቡ አሰረድተተው ያሉበትን ቦታ በቃኝ ብለው መተው አለባቸው።
አለበለዚያ ሀይለ ማርያም ሆይ የገና በግ በፋሲካ በግ ይስቃል ነውና እንደ ጀበና ከስር የደገፉዎት ጉልቾች ያባተ ኪሾን የያረጋል አይሸሹምንና አሁን መስመር ላይ ያለውን የኡሞድን ጽዋ የሚያስጎነጩወት ሰአት ሩቅ አይደለም ምክንያቱም ለዚህ የሚሆኑ የሚሳቡ ካርዶች በራሰዎ መሳቢያም ዉስጥ እንዳሉ ራስዎ ያውቁታላና ነው።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም በልጆችዋ ተከብራ ትኖራለች

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar