søndag 7. juli 2013

የሚተላለፈው። ፖለቲካ አዘል ፈጠራ፡፡

July 5, 2013

ዳዊት ዳባ
ትናንትና ማታ ከአስራ ስድስት ሰዓት ስራ በሗላ ለደከመው ሰውነቴ እረፍት ለመስጠት በጥድፊያ ነው ወደ አልጋዬ የሄድኩት። በርግጥም ጅርባዬ አላጋዬ ላይ እንዳረፈ ነው ጭልጥ አድርጎ እንቅልፍ የወሰደኝ። መጥፎነቱ ስልኬን ማጥፋት ረስቼ ኖሮ  ስልኬ ሊረብሸኝ  የጀመረው ብዙም ሳይቆይ ነበር። ጭህቱን ለመርሳት ሞክሬ ስላልተቻለኝ ልጠረቅመው ስልኩን ማንሳት ነበረብኝ።  ቁጥሩን ሳየው  ያገር ቤት ስልክ ስለነበር ደስ ሳይለኝ አንስቼ ማውራት ጀመርኩ። ናፍቆት ያለበት በሚመስል ሞቅ ያለ ሰላምታ የሰጠችኝን ልጅ አላወኳትም። ድምጿን ለማጥናትና ማንነቷን ለማወቅ ጥረት እያደረኩ የሰላምታውን አጸፋ እንቅልፍ ባጎረነነው ድምጽ መመለሱን ግን ቀጠልኩ። ስሟን ትዝታ  ብላ ብትነግረኝም አገር ቤት የማውቀው ትዝታ የሚባል ስምም ድምጿም በቶሎ ሊታወሰኝ አልቻለም።   ቆያይቼ ልትመጣልኝ እንዳልቻለች ደስ ሳይለኝ መናገር ነበረበኝ።
ሀይ እስኩል፤ ኮከበ ጽበሀ፤ ጎበዝ ተማሪ ትዝታ አለችኝ። አሁን ላስታውሳት የቻልኩ መሰለኝ። አግራሞቴ ግን የባሰ ነው የጨመረው። በርግጥም ከዘጠነኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ስማር ክፍላችን ውስጥ ትዝታ የምትባል ልጅ ነበረች። ከክፍላችንም ከሴክሽንም አንደኛ የምትወጣ ጎበዝ ተማሪ ሰለነበረች ለማስታወስ ቀላል ነው። ነግር ግን እስከማስታውሰው ክፍል ውስጥ ካንገት ሰላምታ ያለፈ መቀራረብ አልነበረንም። ካስራ ሁለተኛ ክፍል በሗላ ተገናኝተንም ስለሷ ሰምቼም አላውቅም። በጎበዝ ተማሪነቷ እኔ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ውስጥ የተወሰኑ ቀናት ታስባኝ ወይ አንስቻት ይሆናል። እሷ ግን ከዚህ ሁሉ ጊዜ በሗላ ልተደውልልኝ አይደለም ልታስታውሰኝ የምትችልበት ምንም ምክንያት የላትም። ክክፍላችን ውስጥ አስቀያሚውም ዝምተኛውም እኔ ነኝ። በትምህርት ጎበዝ ፤ ተደባዳቢ ወይ ድርዬም አልነበርኩም።
ኮከበ ጽበሐ ትምህርት ቤት ክፍላችን የነበርች ጎበዟ ተማሪ ትዝታ ነሽ ብዬ እንዳልሽኝ ልውሰድ። ክዚህ ሁሉ አመት በሗላ ምን ታምር ተፈጠረና አስታውሰሽ ደወልሽልኝ?። መውጣቴን በምን አወቅሽ? ቁጥሬንስ ከየት አገኘሽ? ግራ በመጋባትም፤ የሆነ ሰው እያፌዘብኝ የሆናል በሚል ፍራቻም ጥያቄዎችን ደረደርኩ።
ዳዊት እንደሚገርምህ አውቃለው። ለራሴም ሳስበው ግርም እያለኝ ነው። ያለህበትን ለማወቅና ስልክ ቁጥርህን ለማግኘት ያሳለፍኩት ውጣ ውረድ ቀላል አይደለም። ዝርዝሩን ለመንገር አሁን አልችልም። ለማንኛውም ብዙ ደቂቃ የለኝም። የደውልኩልህ ህልም አይቼ ላንተ መናገር  ስላለብኝ ነው አለችኝ።
የበለጠ ግራ በመጋባት ምን እያልሽ ነው ስል ጠየኳት?
ህልም አይቼ የግድ ላንተ መናገር ስላለብኝ ነው ስትል ደገመችው።
ትዝታ ምንድን ነው የምታወሪው። ታዲያ ዳዊት ህልም ፈቺ ነው ያለሽ ማነው አልኳት?። አበሳጭታኛለች።
ኖ- ኖ እንደሱ አይደለም ስልሚተላለፈው ህልም የሰማህ መስሎኝ ነበር። እዚህ ሁሉም ሰው ስለሚተላለፈው ህልም ያውቃል። ብዙ ሰውም እየተላለፈበት ነው።ካልሰማህ ለመጀመርያ ጊዜ የታያቸው ዋልድባ ገዳም የሚኖሩ ሞነክሴ ናቸው  ይባላል። ለኔ ያስተላለፉብኝ ሰፈራችን የሚኖሩ አሮጊት ናቸው። መንገድ ላይ አቁመው ነው የነገሩኝ። እኔ ያየሁት ህልም ውስጥ ላንተ እንዳስተላልፍ ነው የታዘዝኩት። ይህን ካላደረኩ እንቅልፍ ሊወስደኝ አይችልም። ህልሙን ካየሁኝ ይህው ዛሬ ሳምንት ሆነው።  ሳምንቱን ሙሉ እንቅልፍ አልወሰደኝም። እንዳልኩህ በእንቅልፍ እጦት ላብድ ነው።  ለማንኛውም ጻፈው ተብለሀል። ደቂቃሽ አልቋል እያለችኝ ስለሆነ ዛሬ አንተም ህልም ታያለህ ። ያየህውንና የምትታዘዘውን …።  ስልኩ ተቋረጠ።
አሁን እንቅሌፌ ጠፍቷል። ስልኩን ጆሮዬ ላይ እንደያዝኩ ነው። ዛሬ ህልም አያለው። በህልሜ ውስጥ የምትዛዘውን ስል ደገምኩ። መልሼ ልደውልላት አሰብኩ። መደወያ ካርድ ደግሞ የለኝም። ተነስቼ ለመግዛት ታሰበኝ። የደወለችልኝ በኢንተርኔት ስልክ ይሆናል ቁጭ ብላ አትጠብቀኝም ብዬ ይህንንም ሀሳብ ተውኩት። ቁጥሯን ደግሞ አልተቀበልኩም። ወይ መአልቲ አልኩ። መልሳ ትደውል ይሆናል በሚል ተስፋ አልጋዬ ላይ ገለል ብዬ ስለሁሉም ነገር እየደጋገምኩ መብሰልሰሉን ማቆም አልቻልኩም። ፍረሀት ነገርም ተሰምቶኛል። ሰአታት መቆጠር ጀመሩ። ብጠብቅ ብጠብቅ ግን ስልኬ መልሶ አልጮህ አለ።  በመጨረሻ የደወለችበትን ጉዳይ ህልሟን ጨርሳ እንደው አልነገረችኝም ስለዚህ ይተላለፋል የምትለው ህልም እኔ ላይ ሊተላለፍ አይችልም የሚለው መጽናኛ ከድካሙ ጋር ተጨምሮ እንቅልፍ የወሰደኝ ይመስለኛል።
ስነቃ ትዝታን አመንኳት። ባለተራ ሆኜ እኔም የታዘዝኩትን ካላደረኩ  እስከጭራሹ እንቅልፍ እንደማይወስደኝ አወቄያለው።  ስለዚህ  የግድ ተነስቼ አሁኑኑ አድርግ የተባልኩትን ስራ መጀመር አለብኝ። ነገና ከነገ ወዲያ ደግሞ አስራ ስድስት ሰዓት ነው የምሰራው ። ያለ እንቅልፍ ስራዬን እንዴት እንደምችለው አላውቅም። ጊዜ የለኝም። ከሁሉ ያሳሰበኝ እንደታዘዝኩት እንደነገሩ ልጽፈው እችላላው። እንዴት ነው ለስድስት ሺ ህዝብ የማደርሰው። እንዴት ነው ዘመቻ ሊሆን የሚችለው የሚለው ነው?። ወይ መዓልቲን ደገምኩት።
በእውኑ አለም አይቼው የማላውቀው አይነት ዝናብ ይንዠቀዠቃል። ከሀይሉ ብዛት ጣርያው እየተቀደደ አዳራሹ በውሀ ተጥለቅልቆ ነው የሚታየኝ። አጨላለሙ የጸሀይ ግርዶሽ የሆነ ይመስላል።  ቤተ መንግስት ውስጥ የተሞሸረ ሰው የነበረ ይመስለኛል። አሉ የሚባሉ ባለስልጣናት በሙሉ ተሰብስበው እየተቀባበሉ መዝፈን ከጀመሩ ከርመዋል።።  ፍክክርም የያዙ ይመስለል። ካንደበታቸው የሚወጡ ቃላት ግኡዝ ሂወት ያላቸው ነብሳት እየሆኑ ነው የሚታዩኝ። ነብሳቶቹ አይቻቸው የማላውቀው አስገራሚና ዘግናኝ የሆነ ቅርጽ ነው ያላቸው። በአየሩ ላይ አቀሳሳፋቸው የለሊት ወፍ አይነት ነው። ዘፈን የመሰለኝ አንዳንዴ መፈክርም አንዳንዴ ዲስኩር፤ አንዳንዴ መግለጫም ሆኖ ይሰማኛል። እየተቀባበሉ ሲዘፍኑ በሚያወጧችው ቃልት  ምክንያት ነብሳቶቹ እንዳይነኩኝ ለመሸወድ እንደቦክሰኛ ከመወራጨት ብዛት ትንፋሽ አጥሮኝ አለከልካለው። የባለስልጣናቱ አደናነሳቸው የማይክል ጃክሰን ትሌረል የዘፈን ክሊፐ ላይ ያሉት አውሬዎች አይነት ነው።
ዘፍን በተራ በተራ ሲያወርዱ የሚያወጧቸው አጸያፊዎቹ ነብሳት ብዙውን ጊዜ ብዙም ሳይርቁ  በባለስልጣናቱ ፍትና ስውነት ላይ ይለጠፋሉ። አንዳንዶች ከፍትለፍት ያሉትን ሰዎች አልፈው ግርግዳ ላይ ይፈርጣሉ። አንዳቸውም ግን ቤተ መንግስቱን አልፈው ህዝብ ጋር ሊደርሱ አልቻሉም። ሁሉንም ሰአት አፍንጫዬን በመሀረብ ሸፍኜ ነበር። አስተናጋጆቹና የተወሰኑ ሰዎች እንደኔው አፈናጫቸውን በጨርቅ ሸፍነው አይቻለው። ነብሳቱ ሲፈርጡ በቃላት ሊገለጽ የማይቻል ክርፋት ነው ያላቸው። የሆነ ሰአት ላይ በረከት ይመስለኛል ዘፈን ሲያወጣ  አንዷ አስቀያሚ ነብሳት ከነበሩበት አዳራሽ ተምዘግዝጋ ለጥቂት ያዳራሹን በር አልፋ ልትወጣ ነበር። የብዙዎችን አትኩሮት ስባ ነበር። መቀበላቸውንና መጨፈራቸውን ትተው ጮክ ብለው አለፈች አለፈች ያሉም ነበሩ። ብዙም ሳትርቅ በሩ ላይ የቆመ ወታደር ፍት ላይ ፈረጠች፡፡ አፍንጫውን በጨርቅ ሸፍኖ በር ላይ ተገትሮ የነበረው ወታዳር  ሽታውን ሊቋቋመው ስላልቻለ ሻታውን በቆመበት ለቀቀው። ከበረከትም በተሻለ ርቆ የሄደው የሀይለማርያም ነብሳት ነበሩ። በዛ ግዙፍ ሰውነቱ ባለ በሌለ ሀይሉ ሲያንቧርቅ ጆሮዬን ያዝኩኝ። እንደሁሉም የሱም ቃላቶች የበለጠ አስፈሪ ያውሬ ቅርጽ እየያዙ በአየር ላይ መቅሰፍ ጀመሩ። ገሚሶቹ  ከመነሻው በየባለስልጣናቱ ፍትና ሰውነት ላይ ሌሎቹ ግርጊዳው ላይ ሲፈርጡ የተወሰኑት ያዳራሹን በር አልፈው መብረር ጀመረው ነበር። ሄድ ሄዱ እያሉ ወደበሩ ተከተሏቸው።  አዳራሹ በር ላይ ቆመው እየተጋፉ ማስተዋል ጀመሩ። የግዙፉ ሰውዬ እውነትም የተወሰኑት ፍጥነትም ጥንካሬም፤ ድጋፍም፤ ነበራቸው። እየበረሩ ወደ ውጪው አጥር አቀኑ። አለፉ አለፉ ሲባል  በሚያሳዝን ሁኔታ አጥሩ አናት ላይ የተተበተቡት የኤሌክትሪክ ሽቦ ጠለፋቸው። ሽቦው ላይ እየተለጠፉ ሁሉም ፈረጡ። ከዛ መናደድ ባለበትና ተስፋ በቆረጠ ስሜት  መዝፈኑን ቀጠሉ።
ለካ ዝናቡ በሙሉ አዲስ አበባ አልነበረም። ከቤተመንግስቱ አጥር ውጪ ጸሀያማ ደስ የሚል ቀን ሆኖ ነው የሚታየኝ። ሁሉም ሰው ነጭ ልብስ ለብሷል። ሰዉ ሁሉ ፍት ላይ ከዚህ በፊት አይቼው የማላውቀው አይነት ልዩ የሆነ ደስታ ይታየኛል። ህዝቦች በጋራ ሲያዜሙ ይሰማኛል።
ተመስገን ደስ አለኝ፤
ተመስገን፡ ተመስገን። ተመስገን፡ ተመስገን።
ተመስገን ደስ አለኝ።
ወታደሮች  ነጭ የደንብ ልብስ ለብሰው ሰብሰብ ሰብሰብ ብለው ይታዩኛል። ግን ሁሉም አይደሉም። ነጭ የለበሱት በደስታ ወደሰማይ እየተኮሱ እኛም አንወዳችሗለን እያሉ ወደ ህዝቡ ይጮሀሉ። ከዛም ፍጽም ጸጥታ ሆነ። ልዩ የሆነ ብረሀን ታየኝ። በብረሀኑ ውስጥ ጥርት ብሎ የሚሰማ ደምጽ መጣ።  መደበኛውን የደንብ ልብስ የለበሱት ወታደሮች በሙሉ ነጭ እንዲለብሱ ይሁን አለኝ። ከህዝብ የወጣ የህዝብ ወገን ነው የሚል ዘመቻ ይጀመር የሚለው መልኬቴ እንዲሰማ አድርግ አለኝ።
ያነበባችሁና ያዳመጣችሁ በሙሉ ዛሬ ስትተኙ የየራሳችሁን ህልም ታያላችሁ። እንዴት ዘመቻውን እንደምስታጀምሩ ይመስለኛል።  ህልሙን ተላላፊ እንዴት እንደምታደርጉ ግን በግልጽ ይታያችሗል። ሳልተኛ ነጋ። ነገ ከባድ የስራ ቀን ይኖረኛል። ጥሩነቱ ማታ እንቅልፍ ስለሚወስደኝ እሱን እያሰብኩ እወጠዋለው። መልካም ቀን።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar