የ አብርሃ_ደስታ ጀግንነት ብርታትና ጥንካሬ በሶሻል ሚዲያ ላይ ብቻ የሚለካ አይደለም መከራውን ሲጋፈጥ እኛስ መሬት ላይ ምን እያደረግን ነው? አብርሃ ሲታሰር የበቀል ርምጃ የተወሰደባቸው ቤተሰቦቹም ጭምር ናቸው፣ ከመቐለ እዚህ ድረስ መከራን በማዕከላዊ እንዲቀበል ሲመጣ ቤተሰብም አብሮ ይጉላላል፣ ብዙም በማያውቁት ከተማ በዚህ የኑሮ ውድነት እኛ እያለን ለምንስ ይቸገራሉ ለምንስ ያስቸግራሉ?… የአንድ ሰው መታሰር የአንድ ሰው መታሰር ለሚመስላችሁና ሌሎች ለምን ለምን አልታሰሩም ለምትሉ ግብዞች ልብ ብላችሁ አድምጡኝ የአንድ ሰው መታሰር የቤተሰብ መታሰር ነው! አይደለም አንድ አብርሃ ብዙ ሺ አብርሃዎች መፈጠር የሚችሉት እነሱ ሲታሰሩ እኛ ከቤተሰቦቻቸው ጎን የምንቆም ከሆንና ብርታት መሆን ከቻልን በፕሮፓጋንዳ እንዲሸማቀቁ የተደረጉትን ቀና ብለው እንዲሄዱ ማድረግ ከቻልን የእነአብርሃ ደስታም ሆነ ሌሎች ቤተሰብ አስተዳዳሪዎችና ጧሪዎች እኛ መርዳት ከቻልንና ይረዱት የነበረው ቤተሰብ በሞራል የሚጠገን ከሆነ በቁስ የማይቸግረው ከሆነ ስለእውነት ለምንከፍለው መስዋዕትነት ኩራት እንጂ ሃዘን አይሰማንም፡፡ በደህንነቶች ክትትል ሰላም ለሚነሳችሁ፣ ሳታውቁትም በማታውቁት ጉዳይ ምንም ባልተፈጠረበት በደንባራነታቸው ላይ conspiracy ጨምረው እናንተን በመማገድ እንጀራቸውን ለመጋገር የሚታትሩ ጆሮ ጠቢዎች (ደህንነት ብዬ ከፍ አላረጋቸውም) ተቋቁማችሁ ላላችሁና ለተረበሻችሁ ማንም ባያውቅላችሁም ቅሉ በንጹህ ኅሊናችሁ፣ ሆድ አደሮቹ አንገታችሁን ሊያስደፉ ደስታችሁን ሊቀሙ ቢጥሩም ስለብርታታችሁ ምስጋና ይግባችሁ፡፡ በፖለቲካ አቋማችሁ የምታምኑት አጥታችሁ የሆዳችሁን በሆዳችሁ አድርጋችሁ በስጋት ላላችሁ አይዞን፡፡ ይህ መልዕክት አብርሃ ደስታን በምሳሌነት ያነሳ ይሁን እንጂ ስለ ዞን ዘጠኞች ማኅሌት_ፋንታሁን፣ በፍቃዱ_ኃይሉ፣ ዘላለም_ክብረት፣ ናትናኤል_ፈለቀ፣ አቤል_ዋበላ፣አጥናፍ_ብርሃነ ጋዜጠኞቹ አስማማው_ኃ_ጊዮርጊስ፣ ተስፋለም_ወ_የስ፣ ኤዶም_ካሳዬ፣ እስክንድር_ነጋ፣ ውብሸት_ታዬ፣ ርዕዮት_ዓለሙ፣ እንዲሁም እነአንዷለም_አራጌ በቀለ_ገርባ ን፣ ኦልባና_ሌሊሳን፣ ሃብታሙ_አያሌው፣ የሺዋስ_አሰፋ ፣ ዳንኤል_ሺበሺ ፣ ኢብራሂም_አብዱልሰላም፣ አደይ_አልጋነሸ_ገብሩ እና ስለ ሌሎችም ነው የእነዚህ ሁሉ ቤተሰቦች ቀና እንዲሉ አለንላችሁ እንበላቸው የኛም ቤተሰቦች የእነሱን ቤተሰቦች እንዲጠይቁ ብናድርግስ የለውጥ ጥማት አንድ ያደረገን ቤተሰቦች ነንና፡፡ እንደነ አብርሃ ጦር ሜዳ ካልገባን እኛ እንደራሳችን ደጀን እንሁናቸው፡፡ It is so!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar