onsdag 27. august 2014

ሙስና ለሶስት የሰነጠቃቸው ቡድኖች

ኢህአዴግ በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ላይ ፊጥ ካለ ድፍን 23 ዓመት ቆጠረ፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ በአንቀልባ አዝሎ ለሥልጣን ያበቃው ዛሬ አምርሮ የሚጠላው ሻዕቢያ ነው፡፡ ወያኔ እና ሻዕቢያ ውሃ በወንፊት እንቅዳ ባሉበት የፍቅር ዘመን እነኢሳያስ አፈወርቂ ኦፊሻል ባልሆነ መንገድ ጥሬ ሥጋ ለመቁረጥ በየሳምንቱ አዲስአበባ ይመላለሱ እንደነበር የቅርብ ሰዎች የሚያስታውሱት ነው፡፡
Muktar-300x142ዛሬስ፤ እነዚህ ሁለት ኃይሎች ለመጠፋፋት የሚፈላለጉ ሆነው ተፋጠዋል፡፡ የሚገርመው ወያኔ፤ የሻዕቢያ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ ሀገርን ያህል ነገር ማስገንጠሉን፣ አሰብን አስረክቦ ሀገሪቱን ያለወደብ ማስቀረቱን ጭምር እየረሳ የዛሬ ተቃዋሚዎችን ለምን ከሻዕቢያ ጋር ታያችሁ፣ገንዘብ ተቀበላችሁ እያለ በሀገር ክህደት ጭምር ለመክሰስ ሞራል አግኝቶ ሲወራጭ ማየት ነው፡፡ የትላንቱ የነጻነት ታጋዮች ለሕዝብ ነጻነትና ዴሞክራሲ ታግለናል እያሉ ከ20 ዓመታት ጉዞ በሁዋላ የተትረፈረፈ ነጻነቱን ለራሳቸው ሰጥተው ሌላውን ለመጨፍለቅና ትላንት ባወገዙት የደርግ መንገድ ለመጓዝ አላቅማሙም፡፡
ወደ ሰሞነኛ ጉዳይ እንመለስ ጄኔራል ባጫ ደበሌ አሜሪካን ሀገር ቤት ገዛ የሚል ገራገር ዜና ሰሞኑን በማህበራዊ ድረገጾች ሳነብ አባይን ያላየ ምንጭ ያደንቃል ብዬ በውስጤ አጉተምትሜያለሁ፡፡ የሌባው ቡድን መስረቅን እንደመብት ቆጥሮ በአዲስአበባ ከተማ ቀብረር ያለ ህንጻ በዘመድ አዝማዱ ሰም ሲገነባ ትንሽ እንኳን ሼም እንደሌለው ስትታዘብ ጄኔራሉ በአድራጎቱ አፍሮ ትንሽ ራቅ፣ ደበቅ ለማለት የመፈለጉን ነገር ታመሰግናለህ፡፡ የሌባው ቡድን 5ሺ ብር የማትሞላ ወርሃዊ ደመወዝ ይዞ ልጆቹን በውጪ ሀገር ውድ ት/ቤት ጭምር ሲያስተምር፣ ሚስቱ የሚሊየን ብሮች መኪና ስታሽከረክር፣ ባለቅንጦት ቪላ ገንብቶ ሲንጎማለል ስታይ ጄኔራሉ አንድ ቤት ቢገዛ ታዲያ ምን ይጠበስ ልትል ትችላለህ፡፡ እናም የመከላከያ ወታደሮችን ይጭነቃቸው እንጂ ጄኔራሎቹማ ዛሬ ቢጠሩዋቸው የማይሰሙ ቱጃሮች ሆነዋል፡፡ የሚገርመው ግን እነዚህ ጄኔራሎች ነገ ጥቅማቸውን የሚነካ ነገር ቢመጣ ብረት ላለማንሳታቸው ልማታዊ መንግሥታችንም እንኳን እርግጠኛ መሆን አለመቻሉ ነው፡፡ ኢህአዴግ ነፍሴም «ሙስናን እንዋጋለን» በሚል መፈክር ታጥሮ የሚኖረው ለዚህ ሳይሆን ይቀራልን?!
በአሁን ወቅት ገዥያችን ኢህአዴግ ለሶስት የመሰንጠቅ አዝማማያ እየታየበት ይገኛል፡፡
ቡድን አንድ የደረጀው የሌባ ቡድንን ያቀፈ ነው፡፡ ይህ ቡድን ከፍተኛ መንግሥታዊ ሥልጣኑን የተቆጣጠረ ስለሆነ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ማንኛውንም የኃይል እርምጃ የሚወስድ፣ ጥቅሙ ሲነካ ወይንም ይነካል ብሎ ሲሰጋ ሰዎችን የሚያስር፣ የሚያሳድድ የጨካኞች ስብስብ ነው፡፡ እስከታችኛው ድረስ የራሱ መዋቅር የዘረጋና ብዙ ጀሌዎች ያሉት በመሆኑ ተጽእኖው የሰፋ ነው፡፡
ቡድን ሁለት ሟቹ ጠ/ሚኒስትር በአንድ ወቅት እንዳመነው ነገ ይቀናኝ ይሆናል ብሎ የተቀመጠ ተስፈኞች የተሰባሰቡበት ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የሌባው ቡድን ስላላስጠጋው አምርሮ እየተቃወመና ብሶቱን እየገለጸ ያለና እንደእስስት ገላውን የሚቀያይር ቡድን ነው፡፡ በተመቸው ጊዜ የሚደግፍ፣ ያልተመቸው ሲመስለው የሚቃወም እበላ ባይ የአደገኛ ሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ይህ ቡድን በአመዛኙ በታችኛው እርከን ላይ ተከማችቶ የሚገኝ በመሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በማባባስና በማወሳሰብ ዘወትር ቢወቀስም ምንም ለውጥ ማምጣት ያልቻለ ነው፡፡
ሶስተኛው የኢህአዴግ አባልም ደጋፊም ሆኖ እውነተኛ ዜጋ ሲሆን ሁለቱን ወገኖች የሚጠላ፤ ግን ተጋፍጦ ለመታገል አቅምና ድፍረት ያጣ ነው፡፡
በሒደት አንዱ ነጥሮ መውጣቱ የማይቀር ነው፡፡
( የእኔ የለጣፊው አስተያየት- አጠቃላይ ድርጅቱ የሚጠፋበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar