ዘ-ሐበሻ) አዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሃመድ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ም/ቤት አባል ወ/ሪት ወይንሸት ሞላና የእስልምና እምነት ተከታዮች በአንድ ላይ በተከሰሱበት መዝገብ አዚዛ፣ ወይንሸትና ኡዝታዝ መንሱር በ5 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ሲወስን የተቀሩት ግን 14ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከአዲስ አበባ ጠቆሙ።
አንዋር መስጊድ ላይ ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ለማሰማት የወጡትን ሙስሊሞች የሕወሓት መንግስት ወታደሮች ሕዝበ ሙስሊሙን እያሰቃየ ባለበት ወቅት መርካቶ አካባቢ የነበረችው ወይንሸት ፖሊስ ደብድቦ ፍርድ ቤት ያቀረባት መሆኑን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ ይታወሳል። የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ጋዜጠኛም የአንዋር መስጊዱ ብጥብጥ ላይ ሙያዋ የሚያዛትን ፎቶ በማንሳት ላይ እያለች መታሰሯ ይታወሳል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar