søndag 31. august 2014

በድርጅቶች ውህደትና ቅንጅት አገርን ማዳን!!!

ኢትዮጵያዊያንን በዘር እና በሀይማኖት ለያይቶን እርስ በርስ እያጋጨን በመግዛት ላይ ያለውን ወያኔን ለማሸነፍ እና ከምትኩም ከራሷ ጋር የታረቀች፤ ፍትህ የሰፈነባት፤ እኩልነት የተረጋገጠባት እና በኃያላን አገሮች እርጥባን ሳይሆን በራሷ አቅም የምትተማመን ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን የነፃነትና የዲሞክራሲ ኃይሎት መተባበር እንዳለባቸው ሲነገርና ሲወተወት ቆይቷል። ይሁን እንጂ በህወሓት የከፋፍለህ ግዛው ፓሊሲ እና በፓለቲካ ባህላችን ኋላቀርነት ምክንያት እስካሁን የተደረጉ የትብብር ጥረቶች የተፈለገውን ውጤት ሳያስገኙ ቀርተዋል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ቀድሞ የተደረጉት ጥረቶች የተጠበቀውን ውጤት አለማስገኘት ተስፋ ሳያቆርጠን ከእያንዳንዱ ጥረት ልምድ እየወሰደን የኢትዮጵያዊያን አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ የትብብር ጥረቶችን ማድረግ ያለብን መሆኑ ያምናል። በዚህም መሠረት የትብብር መርህ ነድፎ ትግል ውስጥ ካሉ ሁሉም የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር ሲነጋገር እና ሲደራደር ቆይቷል። እንደሚታወቀው የንቅናቄዓችን አበይት የትብብር መርሆች ሁለት ናቸው። መርህ አንድ፣ ለውጥ እንዲመጣ የምንታገለው ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ መሆኑ ማመን ነው። መርህ ሁለት ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም እርከኖች የመንግሥት ሥልጣን መያዝ የሚገባው በሕዝብ ነፃ ምርጫ ብቻ መሆኑን መቀበል ናቸው።
በምድር ላይ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ኃይሎች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ሁለቱንም መርሆዎች የሚያሟሉ ናቸው። እነዚህ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ከንቅናቄዓችን የተለየ አቋም የላቸውም። በአለፉት ሁለት ዓመታት ድርጅቶቹ ተቀራርበው እንዲሠሩ በመደረጉ ከአመራር አልፎ አባላት መካከል መልካም ወዳጅነት መመሥረት ተችሏል። የነፃነት ትግላችን የደረሰበት ደረጃ እና የድርጅቶቹም ቅርርብ በመገምገም ሶስቱ ድርጅቶች ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄና እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ መዋሃዳቸው ትግሉን ያራምዳል ተብሎ ታምኖበታል። በዚህም መሠረት ሶስቱ ድርጅቶች ለመዋሃድ ተስማምተን ስምምነታቸንን ይፋ አድርገናል። ድርጅቶቹን የማዋሃድ ዝርዝር ሥራም ተጀምሯል።
ከስትራቴጄ አንፃር የትብብር ጥረታችን በዚህ አያበቃም። በዓላማ የምንቀራረብ ሆኖ የአደረጃጀት ልዩነት ያለን የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር በጥምረት እየሠራን ድርጅቶቻችን ይበልጥ ለማቀራረብ ጥረት እያደረግን ነው። በዚህ ረገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሹ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ነው። ንቅናቄዓችን ከትህዴን ጋር ከፍተኛ በሆነ መቀራረብና መተማመን ይሠራል። ይህ መቀራረብና መተማመን ጎልብቶ አንድ የጋራ አመራር የሚፈጥርበት ጊዜ እንዲቀርብ ጥረት እናደርጋለን። ምድር ላይ ከሚገኙ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ጋርም በመደጋገፍ እንሠራለን። በመጨረሻም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ካሉ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር ለመወያየት ዝግጁዎች መሆናችንን ደግመን እናረጋግጣለን። ልዩነቶቻችን ማጥበብ እንኳን ባንችል የምንተባበርባቸው መንገዶች ይኖራሉ ብለን እናምናለን።
የጦር ኃይሉንና የስለላ መዋቅሩን ዘረኛ በሆነ መንገድ የገባውንና የኢትዮጵያን ሀብት በመዝረፍ የደረጀው ህወሓትን ለማሸነፍ ትብብር ወሳኝ ጉዳይ ነው። ከወያኔ አገዛዝ ውድቀት በኋላ ወደ ተረጋጋ ሰላምና ልማት ፊታችንን የምናዞር መሆናችን ዋስትና የሚሰጠን በአንድ እዝ የሚመራ የአገር አድን ሠራዊት ማደራጀት ስንችል ነው። የአሁኑ ውህደት የዚህ አገር አገር አድን ሠራዊት ጥንስስ ሊሆን ይችላል ብለን እናምናለን።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ በኋላ የሚመጣው ምን እንደሆነ ባለማወቅ ሥጋት ውስጥ ሊገባ አይገባም። በዋና ዋና የአገሪቱ የፓለቲካ ድርጅቶች ውህደት እና ቅንጅት የተዋቀረ በአንድ ማዕከላዊ አመራር ሥር የሆነ አገር አድን ሠራዊት በተቻለ ፍጥነት ሊገነባ ይገባል።
ሶስቱ ድርጅቶች ለማድረግ በወሰነው ውህደት የዚህ የአገር አድን ሠራዊት ምሥረታን ጀምረናል። ስለኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ላለ ማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ደህንነት ያገባናል የምትሉ ወገኖቻችን ሁሉ በዚህ አገር አድን ሠራዊት ምሥረታ ላይ እንድንነጋገር አበክረን እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ ሕዝብም የትብብሩ መንፈስ አገርን የማዳን ግብ ያለመ መሆኑን በመገንዘብ ከተባበረው ድርጅት ጎን እንዲቆም ጥሪ እናደርጋለን። የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጉዳይ የሚያገባው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲቀላቀለንና እንዲያግዘን ጥሪዓችንን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

lørdag 30. august 2014

ጠበቃ አቶ ተማም እና ማአከላዊ እስር ቤት

ከይድነቃቸው ከበደ
ይድነቃቸው ከበደ
ይድነቃቸው ከበደ
ጠበቃ አቶ ተማም አባ ቡልጉ በጥብቃና ሙያችው እጅግ በጣም ዝና ያተረፉ ናቸው፡፡በተለይ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በገዥው የወያኔ መንግስት ለእሰር ከተዳረጉበት ጊዜ አንስቶ ጉዳያቸውን በመከታተል ለእነ አብበከር ጠበቃ በመሆን አገራዊ እና ሙያዊ ግዴታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ ይህ በእንዲ እንዳለ የግንቦት ሰባት ዋና ፃሃፊ አቶ አድርጋቸው ፅጌ በህግ ወጥ መንገድ መያዝን ተከትሎ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ፓርቲዎች መካከል የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ም/ት ሰብሳቤ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ከአንድነት አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ከአረና አቶ አብረሃ ደስታ በወያኔ መንግስት በሃይል መያዛቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ጠበቃ አቶ ተማም ከእረዳታቸው ከጠበቃ ከአቶ ገበየሁ ጋር በመሆን በፍርድ ቤት የእነ ሀብታሙን ጉዳዩን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡
እነ አብርሃ ደስታ ለእስር ከተዳረጉ ሁለት ወር ሊሞላቸው የተወሰነ ቀናት ይቀራቸዋል፤በነዚህ ቀናት ውጥ ከታሰሩ ለ20 ቀናት ከቤተሰብ፣ከጠበቃ እና ከወዳጅ ዘመድ እንዳይገኛኙ የተደረጉ ሲሆን፡፡ ጠበቃ አቶ ተማም ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል እነ የሺዋስ ከጠበቃቸው ጋር እንዲገኛኙ ማህከላዊ እስር ቤት በወቅቱ ሊፈቅድ የቻለ ሲሆን በዚህም ምክንያት ታሳሪዎች ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ለመገኛኘት ችለዋል፡፡ይሁን እንጂ በተያዙ በ28 እና በ29 ቀናቸው ፍርድ ቤት ቀርበው መንግሰት “በሽብርተኝነት” ከከሰሳቸው በኋላ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸው ሲሆን የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት ከፈቀደበት ቀን አንስቶ ይህ ፁሁፍ እስከቀረበት ወቅት ታሳሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ተደርጓአል፡፡
ጠበቃ ተማም አባቡልጉ
ጠበቃ ተማም አባቡልጉ

ነሃሴ 21 ቀን 2006 ዓ.ም ጠበቃ አቶ ተማም ወደ ደንበኞቻቸው እነ ዳንኤል ሽበሺ ጋር መአከላዊ እስር ቤት የሄዱ ቢሆንም ለመገናኘት አልቻሉም፡፡በወቅቱ ስለ ገጠማቸው ነገር ከእኔ ጋር ስንወያይ የገለፁልኝ ነገር እጅግ በጣም የሚያስገርም ነገር በመሆኑ ለዚህ ፁሁፍ አንባቢ ሁኔታውን ለማካፈል እውዳለው፡፡ ጠበቃ አቶ ተማም ወደ ማእከላዊ እስር ቤት በመሄድ ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል “ደንበኞቼን ለማነጋገር ነው የመጣሁት” በማለት አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው የጠየቁ ቢሆንም ጉዳዩ የሚመለከተው ፖሊስ “ማናገር አትችልም፣ሂድ ውጣ” ይላቸዋል ፡፡ እሳቸውም “እንዲ ማለት አይገባህም እኔ ለደንበኞቺ ህጋዊ ጠበቃ ነኝ ስለ ደንበኞቼ ማውቅ የሚገባኝ ነገር ስላለ ልተከላከለኝ አይገባም” በማለት ከፖሊሱ ጋር ከፍተኛ የሆነ የቃላት ግብግብ ይፈጠራል፡፡ በዚህን ወቅት ሌሎች ፖሊሶች ገላጋይ ሆነው በመቅረብ ጉዳይ እንዲረግብ ጥረት ያደርጋሉ፡፡በወቅቱም የቀረበው ማስታረቂያ ሃሳብ ጉዳዩ ለበላይ አካል ይቅረብ ፤ይህን ጉዳይ የሚመለከቱት ስብሰባ ላይ ስለሆኑ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ይመለሱ በማለት ማስታረቂያ ሃሳብ ፖሊሶች ያቀርባሉ፡፡የነገሩ ሁኔታ ያላማራቸው እና ጉዳዩን በጥበብ ለማለፍ የፈለጉት ጠበቃ አቶ ተማም ዋና ሃላፊ የተባለው ሰው ከስበሰባ እስኪወጣ ብና ልጠጣ በማለት ከማአከላዊ ጊቢ ይወጣሉ፡፡

የዕለቱ አስገራሚ ነገር ከዚህ ይጀምራል፡፡አቶ ተማም ከማህከላዊ እስር ቤት ፍለፊት ወደሚገኘው ሐረር ብና ወደሚባለው ካፊ በመሄድ በካፊው ውስጥ ከሚገኘው መቀመጫ ወደ አንዱ በማምራት ለመቀመጥ ሲሉ ድንገት ዞር ሲሉ በማአከላዊ እስር ቤት አላስቆም አላስቀምጥ ያላቸው ፖሊስ ፊለፊት ከአጠገባቸው ቆሞ ያገኙታል በዚህወቅት “ እባክህ ብና ጠጣ ና ቁጭ በል በማለት በአክብሮት ይጠይቁታል” ፡፡ይህ ፖሊስ በክፈተኛ ሁኔታ ከእነ የሺዋስ ጋር አቶ ተማም እንዳይገናኙ ሲከላከል የነበረው ነው ፡፡ ለአቶ ተማም አክብሮት ፖሊስ ጠብ ያለሽ በዳቦ አይነት ጨዋታ ያማረው ስለሆነ ምላሹ “እኔን በግቦ አትደልለኝም እከስአለው” በማለት እየተውረገረገ ወደ ማአከላዊ ያመራል ፡፡ለነገሩ ዋናው ተልኮ ይህ ስለሆነ ተላላኪው ፖሊስ የእለቱ ግዳጁን ይወጣል፡፡
አቶ ተማም ለ30 ደቂቃ ያህል ብናቸው እየጠጡ ጊዚያቸውን ካሳለፉ በኋላ ተመልሰው ወደ ማአከላዊ ያመራሉ ፡፡ከበር ሆኖ የሚጠብቃቸው ፖሊስ “ሃላፊው ቢሮ ይፈለጋሉ፤ወደ-ዚያወ ይሂዱ” ብሎ ይነግራቸዋል ፤እሳቸውም ወደ ተጠቀሰው ቢሮ ይሄዳሉ፡፡ወደተጠቀሰው ቢሮ ሲገብ ያልጠበቁት ነገር ይገጥማቸዋል “አቶ ተማም !ከእርሶ ይሄ አይጠበቅም እንዴት ፖሊስን ለመደለል ይሞክራሉ ? እርሶ የህግ ባለሙያ ኖት እንዲ አይነቱ ነገር መፈፀም ወንጅል መሆኑ ያወቃሉ፤በመሆኑም ክስ ተከሰዋል” በማልት ይነግራቸዋል፡፡ እሳቸውም በሁኔታው በመገረም “እኔ ሙያዊ ግዴታዬን ጠንቅቂ የማውቅ ሰው ነኝ! ደግሞም ከደንበኞቼ ጋር መገናኘት መብትም ጭምር ነው፡፡ይህ መሆን እያወኩ አንተ የምትለው አይነት ስእተት አልሰራም፤ይህ ሐሰት የሆነ ነገር ነው” በማለት ይመልሳሉ፡፡ ሃላፊ የተባለው ፖሊስ “ለማንኛውም እዚህ ይቆዩ” በማለት መውጣትም በማይቻልበት ቢሮ ውስጥ ጥሏቸው ይሄዳል፡፡ እዚህ ቆዩ ያላቸው ፖሊስ መጥቶ አንድ ነግር ይለኛል ብለው ቢጠብቁም ለተወሰነ ሰዓታት ያህል ከማንም እንዳይገናኙ ተደርገው በአንድ ቢሮ ውስጥ ታግተው ሊቆዩ ችለዋል፡፡ ከሰዓታት ቆይታ ኋላ ሃላፊ ነው የተባለው ፖሊስ በመምጣት “ ከአንድ ባለሙያ የማይጠበቅ ነገር ነው ያደረከው፤ለማንኛውም ለዛሬ ጉዳዩን ትተነዋል ፡፡ አሁን እስረኛ መጠየቂያ ጊዜ ሰዓቱ ስላለፍ አርብ መጥተ መጠየቅ ትችላለ” በማለት ያስናብታቸዋል፡፡
አቶ ተመማ በገጠማቸው ነገር እጅግ በጣም ቢበሳጩም ሙያዊ እና አገራዊ ግዴታቸውን ቅድሚያ በመስጠት፤ ይህ በሆነ ከአንድ ቀን ቆይታ በኋላ ማለትም ዛሬ ነሃሴ 23 ቀን 2006 ዓ.ም በድጋሚ ወደ ደንበኞቻቸው ማአከላዊ እስር ቤት ይሄዳሉ፡፡ሆኖም ግን ከማአካለዊ እስር ቤት የፊተኛው በር ጀምሮ እስከ ሚመለከተው ቢሮ ድረስ ከፍተኛ የሆነ ውጣ-ውረድ ደርሶባቸዋል፡፡በስተመጨረሻም ዋና አላፊ ነው የተባለው ሰው “እስረኞችን ማግኘት የምትችለው በችሎት ነው፤አሁን ልናገናኝ አንችልም” በማለት አሰናብቷቸዋል፡፡በሆኖም ነገር ጠበቃ አቶ ተማም ከልብ ማዘናቸውን ለመረዳት ችያለው፡፡
የገዥው መንገስት ህግመንግሰት እንደሚለው ከሆነ “በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ መልኩ የመያዝ እና ከህግ አማካሪያቸው፣ ከዘመዶቻቸው እና ከጠያቂዎቻቸው የመገናኘት መብት አላቸው፡፡” በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 21/ ንዑስ አንቀፅ 1እና2 ተፅፎ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ እስረኞች አያያዛቸው ክብርን ከመንካት አልፎ በህይወታቸው ላይ አደጋ የሚያስከትል ነው፡፡በተጨማሪ ከቤተሰብ፣ከወዳጅ መጠየቅ የማይሞከር ነገር ነው፤ የመጠየቅ እድል ያላቸው እስረኞች እድላቸው በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ነገር ግን እንዲህ አይነቱ የለየለት መንግሰትዊ ውንብድና የአምባገነን መንግሰት ስርዓት የመጨራሽ የውድቀቱ ምልክት እንደሆነ ግልፅ ማሳያ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

fredag 29. august 2014

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ታስረው ዋሉ ።

ፖሊስ እና ደህንነቶች የተቃዋሚ አመራሮችን በሰበብ አስባቡ ማንገላታቱን ቀጥሏል።
AEUPበዛሬው እለት የመኢአድ አመራሮች ታስረው መዋላቸውን የድርጅቱ ምንጮች አስታውቀዋል፡፤ አመራሮቹ ለእስር በማያበቃ እና በፈጠራ ክስ አዲስ አበባ ሰራተኛ ሰፈር መግቢያ ከጣይቱ ሆቴል ፊት ለፊት ካለው የወያኔ ፖሊስ ጣቢያ ከጽ/ቤታቸው ትፈለገላችሁ ተብለው ከተወሰዱ በኋላ ሲያጉሏሏቸው ውለው በዋስ እንደተለቀቁ ተናግረዋል።
አመራሮቹ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባን ይመኢአድ ቢሮ ማህተሞች እና ሰነዶች ይዞ እንደጠፋ የሚታወቀው መቶ አልቃ ሃይለማርያም የተባለ ግለሰብ ከደህንነቶች ጋር በማበር ወደ ጽ/ቤቱ ፖሊሶችን በማምጣት ‘ወላሞ ‘ብለው ሰድበውኛል የብሄር ብሄረሰብ መብት በተከበረባት ሃገር …ወዘተ በሚል የፈጠራ ክስ ድርጅቱን እና አመራሮቹን ወደ እስር ቤት አስወስዶ ቃል እንዲሰጡ ያደረገ ሲሆን ማስረጃ ባለመገኘቱ ማስረጃ እስኪመጣብሚል ተለቀዋል። ፖሊስ የተቃዋሚ አመራሮችን በማይረባው እና በምማፈለግ አጋጣሚን እየፈለገ ማንገላታቱን ቀጥሏል።

የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መበራከት

አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ
መንግሥት በአንዳንድ የግል ጋዜጦች ላይ ክስ ከመሠረተ እና ባለፈው ግንቦትም ዘጠኝ ጋዜጠኞች እና የድረ ገፅ አምደኞች ከታሰሩ ወዲህ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ጋዜጠኞች ኢትዮጵያን ለቀው ወጥተዋል።

43f5db4e4
ባለፉት ጊዚያት ሀገር እየለቀቁ የወጡት ግን ጋዜጠኞች ብቻ አይደሉም፣ ብዙ ወጣቶችም በተለያዩ መንገዶች መሰደዳቸውን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ያሳያሉ። ለጋዜጠኞች ደህንነት የሚሟገተው ድርጅት፣ የ«ሲ ፒ ጄይ» የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠሪ ቶም ሮድስ፣ ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸውን ለአደጋ እያጋለጡ የሚወጡበት ጉዳይ ከሰብዓዊ መብት ጋ የተያያዘ ነው ይላሉ።
ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን በየመን ፣ በኬንያ እና ታንዛንያ፣ እንዲሁም በሱዳን እና በሊቢያ በኩል እያደረጉ አደገኛ በሆነ ጉዞ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ደቡባዊ አፍሪቃ እና አውሮጳ ለመግባት ይሞክራሉ፣ በዚሁ ሙከራቸው ወቅት በየበረሃው እና በየጫካው ወድቀው የሚቀሩት እና ባህር የሚበላቸው ጥቂቶች እንዳልሆኑ እና የሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች ሰለባም እንደሚሆኑ በየጊዜው የዜና ምንጮች የሚያወጡዋቸው ዘገባዎች ያሳያሉ፣ ከጥቂት ጊዜ በፊት በዚምባብዌ በኩል አድርገው ደቡብ አፍሪቃ የገቡ 24 ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ ስላልነበራቸው በሀገሪቱ ፖሊስ መያዛቸው የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያውያኑ ራሳቸውን ለዚህ ሁሉ መከራ የሚያጋልጡበት የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ለጋዜጠኞች ደህንነት የሚሟገተው ድርጅት፣ «ሲ ፒ ጄይ» የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠሪ ቶም ሮድስ ገልጸዋል።
« ሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ያሉ ይመስለኛል። የመጀመሪያው፣ መንግሥት ማንኛውንም ትችት ወይም ተቃውሞ በቸልታ የማለፍ ልማዱም ሆነ አሰራር በፍፁም የለውም። እና ከማንኛውም ትችት የሚሰነዝር ቡድን ጋ የሆነ ግንኙነት ካለህ፣ ምንም እንኳን ግንኙነቱ ደካማ ቢሆንም፣ የመንግሥት ክትትል ዒላማ ልትሆን ትችላለህ። ሁለተኛው ደግሞ፣ የፍትሑ አውታር በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ነው ፣ እና አንዴ በመንግሥት ክስ ከቀረበብህ ወደ ወህኒ መውረድህ የማይቀር ነው፣ ስለዚህ ብዙዎቹ የረጅም ዓመታት የእስራት ቅጣት እንዳይደርስባቸው መሸሹን መርጠዋል። »
የ«ሲ ፒ ጄይ» ቶም ሮድስ
ለብዙዎች ሀገር እየለቀቁ መውጣት ከሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ጋር የተያያዘ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት ቶም ሮድስ በሚቀጥለው ዓመት በሀገሪቱ የሚካሄደው ምርጫ ማበርከቱንም ቶም ሮድስ ይናገራሉ።
« ምርጫ በሚቀጥለው ዓመት ግንቦት ወር ይደረጋል። ይህም፣ ምንጮች እንደነገሩኝ፣ በመንግሥቱ ውስጥ ያሉት ፣ ሥልጣን እንደያዙ ለመቆየቱ ስለሚፈልጉ፣ ሊነሳ የሚችል ማንኛውንም ትችት ለማፈን እየሞከሩ ነው። ተመሳሳይ ሁኔታ ካሁን ቀደም አይተናል። እአአ በ2005 ዓም ተቃዋሚው ወገን ምርጫውን ሳያሸንፍ አልቀረበትም የተባለው ምርጫ ውጤት ክርክር ባስነሳበት ጊዜ ተመሳሳይ ሁኔታ ተመልክተናል። እና ከዚያን ጊዜ ወዲህ እምነት ያጣው መንግሥት፣ በሥልጣን ለመቆየት ሲል ጋዜጠኞችን ብቻ ሳይሆን የሲቭል መብት ተሟጋችቾችን እና ጠበቆችንም ጭምር ለመምታት ወደኋላ አላለም። »
ቶም ሮድስ፣ ጋዜጠኞች እና ብዙ ወጣቶችን ከስደት እና በሰበቡ ከሚደርስባቸው መከራ እና ስቃይ ለመታደግ የኢትዮጵያ መንግሥት ፖሊሲውን ሊከልሰው ይገባል ባይ ናቸው።
«መንግሥት አንዳንድ ፣ ለምሳሌ፣ እአአ በ2009 ዓም የወጣውን የፀረ ሽብርን የመሳሰሉትን ሕጎች ዳግም ማጤን ይኖርበታል። ፖሊሲውን በጥሞና ስንመለከተው፣ በሀገሪቱ የሕግ ሥርዓት ውስጥ ፍትሓዊ አሰራር የተጓደለበት ሁኔታ ሰዎች በሕጉ ሥርዓት ላይ እምነት እንዳያድርባቸው አድርጓል። ይህ ባይሆን ኖሮ ብዙ ሰው ሀገር እየለቀቀ ሲሸስ ባልታየ ነበር። እርግጥ፣ ጉዳዩ የተወሳሰበ ነው። የሀገሪቱ መንግሥት ልማትን በተመለከት ጉልህ መሻሻል አድርጓል። በዚህም የተነሳ በኤኮኖሚ ምክንያት መውጣት የሚገደዱት ኢትዮጵያውያን በጣም ትንሽ ነው። ይሁንና፣ የልማቱ እንቅስቃሴ የሚደረገው ለሰብዓዊ መብት መከበር ትኩረት ሳይሰጥ ነው። ይህም ሰዎች ሀገራቸውን እንዲወጡ ያስገድዳል። መንግሥት የሚሰራበት የመሬት መቀራመትን ፖሊሲ ምን ያህል ብዙ ወጣቶችን እንደሚነካ መመልከት ይበቃል። »
የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብቱን ይዞታ እንዲያሻሽል እና የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና ሊያሳርፍ እንደሚገባ ድርጅታቸው በተደጋጋሚ ቢያሳስብም፣ እስካሁን ይህ ነው የሚባል የረባ ውጤት ሊያስገኝ የሚችል ግፊት ባለማሰረፉ ቶም ሮድስ አልተደሰቱም
« በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሰራር ብዙ ጊዜ ቅር ተሰኝቼአለሁ። ምክንያቱም የሚናገሩት እና የሚያደርጉት የተለያየ ነውና። እና ለምሳሌ ዩኤስ አሜሪካ እና ብሪታንያን የመሳሰሉ ዓበይት ለጋሽ ሀገራት ለኢትዮጵያ ሊያቀርቡት ያቀዱትን ግዙፍ ርዳታ፣ የሰብዓዊ መብት ይዞታን ከግንዛቤ ሳያስገቡ ሊሰጡ አይገባም። »

torsdag 28. august 2014

13 የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው

arkabe equbay
አቶ በረከት
አቶ በረከት
Samora Yenuswerekeneh gebeyehuana gomez and aba dula gemeda
አቶ አባይ ጸሐዬ
አቶ አባይ ጸሐዬ

(ኢሳት ሰበር ዜና) 13 የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው ሲል ኢሳት በሰበር ዜናው ዘገበ።

እንደ ኢሳት ቲቪ ዘገባ አርከበ እቁባይ፣ በረከት ስምኦን፣ አባ ዱላ ገመዳ፣ ሳሞራ የኑስ፣ አባይ ጸሃየ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፣ ሃሰን ሺፋ፣ ሙሉጌታ በርሄ፣ ነጋ በርሄ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ኮማንደር ሰመረ እና አንድ ስሙ ያልተገለጸ ሰው በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ በስቃይ፣ ሰዎችን በማንገላታትና በህገወጥ መንገድ በማሰርና ሌሎችንም ተመሳሳይ ወንጀሎች በመፈጸም በስዊድን አለማቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸዋል።
የስዊድን ታዋቂ ጠበቆች ያዘጋጁት የክስ ቻርጅ የስዊድ የአለማቀፉ ወንጀል መርማሪ ፖሊስ ተረክቧል።
ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያንም የ130 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር ካሳ መጠየቁን የዘገበው ቴሌቭዥኑ ከስዊድን አለማቀፍ የወንጀል መርማሪ ፖሊስ የተሰጠው መልስ እጅግ አስደሳች መሆኑን አዘጋጆች ለኢሳት መግለጻቸውን ዘግቧል።
የስዊድን ፖሊሶች ምርመራ መጀመራቸውን ያስታወቁ ሲሆን የክሱ አላማ በምርጫ 97 ወቅት ለተገደሉትና ለቆሰሉት ፍትህ መስጠት ነው።

onsdag 27. august 2014

ያልተገራው ገሪ …. ኢቲቪ (ጌታቸው ሺፈራው)

በጌታቸው ሺፈራው
ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ደቡብ አፍሪካ ያሉ አገራት ነጻነታቸውን አግኝተው የዓለም ቀጣይ ኃያል አገራትን ተቀላቅለዋል፡፡ አብዛኛው የዓለም ማህበረሰብ ዴሞክራሲያዊ በሆኑ ስርዓቶች ለመተዳደር እድል አግኝቷል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ግን ስልጣን ከያዘ ማግስት በህግ ፈቀድኩት ያለውን የሚዲያ ነጻነትን ጨምሮ በማፈን፣ በዛው በርሃ ውስጥ በነበረው ‹‹ውርጋጥነቱ›› ቀጥሏል፡፡ አሁንም ቢሆን ‹‹ሲቪል›› ነኝ ብሎ የሚያስበው በአፈሙዝ ነው፡፡ በአንድ በኩል ዴሞክራትነቱን እያስወራ በተግባር ግን የአምባገነኖች ቁንጮ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአጠቃላይ በርሃ ከነበረበትም በባሰ አሁንም እንዳፈተተው በኢትዮጵያውያን ላይ ስልጣኑን የሚያስጠብቅለትን እርምጃ መውሰዱን ቀጥሏል፡፡ ኢህአዴግ አልተገራም፡፡
safe_imageእንዲያም ሆኖ ግን ሌሎቹን ስለ መግራት ያወራል፡፡ ትናንትና ማታ (ነሐሴ 19/2006) በልሳኑ ያሳየው ‹‹ያልተገሩ ብዕሮች›› የተሰኘ ፊልም የሚያሳየውም ይህንን ከአለ-አቅም መንጠራራትን ነው፡፡ ኃይሌና ገና በጋዜጠኝነት ተመረቁ የተባሉ ወጣቶች የእነ ፕሮፌሰር መስፍንን፣ የእነ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራን፣ የእነ ተመስገን ደሳለኝን፣ የእነ ዓለማየሁ ገላጋይን ብዕር ‹‹ሊገሩ›› ሲፍጨረጨሩ ማየት በእጅጉ የሚያስገርም ነው፡፡
ሲያሸንፍም በስሜት የዘለልንለት፣ ሲሸነፍ የተሸነፍንለት የድሮው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ከስርዓቱ ጋር አብሮ ‹‹ሚዲያ ኑክሊየር ነው!›› ሲል ‹‹አጥፊነቱን›› መስክሯል፡፡ በእርግጥ ኃይሌ በህዝብ ላይ ሲቀልድ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ከአመት በፊት በሰይፉ ፋንታሁን የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ስለ መምህራን የደሞዝ ጭማሬ ተጠይቆ የመምህራኖቹ የደምወዝ ጭማሬ ቅብጠት መሆኑን ተናግሯል፡፡ ከአንድ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ እንዳገኘሁት ከሆነ ኃይሌ ገብረስላሴ ለስርዓቱ አፋኝነትም በግልጽ ድጋፉን እያሳየ እንደሚገኝ ነው፡፡ የመረጃ ምንጩ እንደጠቀሰልኝ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የሚታጎሩበት የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማስፋፊያ የተሰራው በኃይሌ ገብረስላሴ የገንዘብ እገዛ ነው፡፡ ለዚህ ፖሊስ ጣቢያ ካቴና ከውጭ አገር ያስመጣውም ኃይሌ ገብረስላሴ እንደሆነ ምንጩ ገልጾልኛል፡፡
በርካታ ኢንቨስትመንቶቹ በገዥው ፓርቲ ይሁንታ እንደሚቀጥሉ ያመነ የመሰለው ኃይሌ ትናንትናውም ቢሆን የስርዓቱ መሳሪያ ሆኖ ሚዲያውን ሲተች ያመሸው ከራሱ የኢኮኖሚ ጥቅም አንጻር ነው፡፡ ኃይሌ ከኑክሊየርም በላይ አፍራሽ ነው ያለውን ሚዲያ መተቸት የጀመረው በአንድ ዘገባ ምክንያት አንድ የውሃ ፋብሪካ መዘጋቱን በመግለጽ ነው፡፡ ኃይሌ ይህን ወደ ራሱ አስጠግቶ ሲያጠናክርም ‹‹በእኔ ላይ በመጻፉ ልጆቼ፣ ቤተሰቤ ያያሉ፡፡ በስሬ 1500 ሰራተኛ አለ፡፡ አዋሳ፣ ባህርዳር፣…ያሉት ሰራተኞችም ያዩታል፡፡ ሰራተኞችም ይህ ሰው ምን ነካው ይላሉ፡፡ ቢዝነስ ‹ኮላፕስ› ያደርጋል፡፡›› ሲል ነበር የገለጸው፡፡ እንግዲህ ገና የኃይሌ ልጅ ትሰማለች ተብሎ፣ ሰራተኞቹ ‹‹ምን ነካው!›› ስለሚሉ፣ ‹‹ቢዝነሱ ኮላፕስ›› ስለሚያደርግ ኃይሌ ምንም ያህል ቢያጠፋ ሚዲያው ትንፍሽ ላይል ነው ማለት ነው፡፡ ይህን የኃይሌን ሀሳብ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት ውስጥ መምህር ነች የተባለችውም ‹‹የሰዎች ጓዳ (መቼስ ሚስጥር ማለቷ ነው) ሚዲያ ላይ መውጣት የለበትም፡፡›› ስትል ሀሳባቸውን ተሰብስበው የተስማሙበት አስመስላዋለች፡፡ በቃ ሚዲያ ሚስጥር የማውጣት ሚናውን በእነ ኃይሌ ዳኝነት ተቀማ ማለት ነው፡፡ እነ ኃይሌና ዶክተር አሸብር ለስርዓቱ ክንድ በሆኑበት በዛው ፊልም ላይ ካሳ ተከፍሏቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ኃይሌ ገብረስላሴ ሊወዳደር ነው፣ ዶ/ር አሸብር አምባገነን ነው›› የሚሉ ዜናዎችና ትችቶች ሳይቀር በአጥፊነት የተፈረጁላቸው፡፡
ሚዲያ ከሌለው መንግስት ይልቅ መንግስት የሌለው ሚዲያ ይሻላል የሚል መርህ የሚከተሉትን የእንግሊዝና የአሜሪካን ዴሞክራሲ አውቀዋለሁ ያለው ኃይሌ ገብረስላሴ ‹‹ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው›› በሚል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሚዲያ ‹‹ያልተገራ›› በመሆኑ በሚያሳስብ መልኩ ያ ስቅስቅ ብሎ ያለቀሰለትን ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹ራዕይ›› እናስጠብቃለን የሚሉ አካላት እርምጃ እንዲወስዱ ፍርደ-ገምድልነቱን አሳይቷል፡፡
ስርዓቱን የማዳን እርብርብ
በዚህ ፊልም ላይ ስለ ሰራዊት ፍቅሬ የፍቅር ደብዳቤ መጻፍ፣ በሞቅታ ስለሚጨፍሩት አርቲስቶች አስተያየት መስጠት በአውዳሚነት አስፈርጇል፡፡ ይህ የሆነው እነዚህ ‹‹ልማታዊ አርቲስቶች›› ያልተገራው ስርዓቱ ቅቡልነት እንዲያገኝ ሳይታክቱ የሚሰሩ በመሆናቸው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ‹‹አባይ ለፕሮፖጋንዳ አይዋል›› ማለት ብሄራዊ ደህንነትን ተጻርሮ የቆመ አስመስሏል፡፡ ከምንም በላይ ስርዓቱ ለስልጣኑ መሰረት አድርጎ የሚወስዳቸው አንጓዎች በሚዲያው ሊነኩ የማይገባ ‹‹ቀይ መስመሮች›› ተደርገው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ መቼም አንድ ተቃዋሚ መንግስትን የተቆጣጠረውን ፓርቲ ከስልጣን አውርዶ መንግስት ለመሆነ ነው የሚሰራው፡፡ ያልተገራው ‹‹መንግስት›› መሳሪያ የሆኑትና እነሱም ከስርዓቱ ጋር በጥቅም ከመጋራታቸው ውጭ የተገራ ነገር ያልታየባቸው ነገር ግን የተገሩትን ሲያጣምሙ የታዩት የፊልሙ ሰሪዎች ግን ‹‹ህዝብ ሌላ መንግስት ለማየት ፍላጎት አለው›› የሚለውን ከኑክሊየርም በላይ አጥፊ ነው ብለው ፈርጀውታል፡፡ ጋዜጠኝነት ‹‹በራዲካል ሮል›› ፖሊሲ የማስቀየር ሚና አለው ብለው ሳይጨርሱ ‹‹የብሄር ፌደራሊዝሙ እርምት ያስፈልገዋል›› የሚልን መካሪ ጽሁፍ በአሉታዊነት ለፈውታል፡፡ የ‹‹ብሄር ፖለቲካው›› ላይ ምንም አይነት ትችት መቅረብ የለበትም አይነት ያልተገራ አቋማቸውን ዳግመኛ አሳይተውበታል፡፡ ጠባብ አለመሆናቸውን ማሳመን ሲያቅታቸው ጠባብነታቸውን የሚተቹትን ሚዲያዎች ያልተገሩ ሲሉ ወርፈዋቸዋል፡፡ እነሱ አንዳንድ ተቋማት ስለ ‹‹መንግስት›› ያወጧቸውን መልካም የሚባሉ ነገሮች አመት ሙሉ እንደማይደጋግሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ስለ ድህነት፣ የመፈንቅለ መንግስት ስጋትና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ያወጧቸውን ሪፖርቶች የግል ሚዲያው እንዳያወጣ ቅድመ ክልከላ አውጀዋል፡፡ ማጎሪያ ቤት ውስጥ ያለውን ስቃይ ማስተባበል ሲያቅታቸው ‹‹ማረሚያ የሚያስፈልገው ማረሚያ ቤት›› የተሰኘን መካሪ ጽሁፍ በህገ ወጥነት ፈርጀውታል፡፡
ኢህአዴግ የውድቀት ዋዜማ፣ ኢትዮጵያ ለምን አሚሶንን ተቀላቀለች? ፍትህ በሌለበት የፍትህ ሳምንት፣ ለአክራሪነት አስተማሪው ማን ነው? ለተሰኙት መልስ መስጠት ሲያቅታቸው፣ እውነት ሆኖ እንቅልፍ ሲነሳቸው በጸረ ሽብር ህጉ አውድ አሸባሪ ብለው ፈርጀዋቸዋል፡፡ በጣም የሚገርመው አብዛኛዎቹ ጽሁፎች በጥያቄ የቀረቡና ኢህአዴግን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርጉ ሲሆኑ ኢህአዴግ ግን ቀድሞ ‹‹እኔን ነው›› ብሎ ለራሱ ወስዷቸዋል፡፡ ሚዲያው ገለልተኝነቱን እያሳየም ቢሆን እነሱ የአንድ አካል አፈ ቀላጤ ይሉታል፡፡ ለዚህ እንደ ማስረጃ ያቀረቡት ደግሞ ‹‹ማንን እንመን?›› በሚል የወጣን አንድ ጽሁፍ ነው፡፡ ይህ ጽሁፍ ዶ/ር ብርሃኑንና በረከት ስምዖንን ያፋጠጠ ጽሁፍ ነው፡፡ ከሁለቱ አካላት ማንንን እንመን ተብሎ በማነጻጸሪያነት የወጣውን ይህን ጽሁፍ ራሱን የማያምነው ኢህአዴግ ‹‹እኔን ነው የማያምኑኝ›› ብሎ ጥፋቱን ቀድሞ ወስዶ ‹‹የአንድ አካል አፈቀላጤ ሆነዋል›› ሲል ይከሳል፡፡
በአጠቃላይ ‹‹ያልተገሩ ብዕሮች›› በሚል የቀረበው ፊልም የኢህአዴግን ፖሊሲ መተቸት ህገ ወጥነት እንደሆነ የታየበት፣ የስርዓቱ ዋና ዋና የስልጣን ማቆያ ፖሊሲዎችን መንካት ስርዓቱን ሊያፈራርሰው እንደሚችል ባልተገራ አንደበት የተነገረበት ፊልም ነው፡፡ በፊልሙ ተዋናይ የሆኑት አካላት እዛው ፊልሙ ላይ ‹‹ፌቨር›› እየተሰራላቸው በትውልዱ ላይ ሲፈርዱ ስርዓቱን ለማዳን እርብርብ ላይ እንደሆኑ በግልጽ ለማየት ተችሏል፡፡ ሁሉንም ነገር ከኢኮኖሚ አንጻር ሲቃኝ ያመሸው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ‹‹ጦርነት ከፈታው ወሬ የፈታው›› በሚል ኃይል በእጁ ለሆነው ያልተገራ ስርዓት በቅኔ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡ የስፖርት ጋዜጦች ድረስ ተሂዶ የተደረጉበት ጥቃቅን ትችቶች በህገ ወጥነት የተፈረጁለት ዶክተር አሸብር በግልጽ አገልጋይነቱንና ስርዓቱን ለማዳን የቆመ መሆኑን አሳይቷል፡፡ ፓርላማ ላይ ኢትዮጵያ ምንም አይነት ጥቅም ሳታገኝ ለጅቡቲ ውሃ የሚለግሰውን አዋጅ ከተቃወሙት መካከል ዶክተሩ አንዱ እንደነበሩ በሚዲያ ተገልጾ የነበር ቢሆንም ዶክተሩ ግን ስለ አዋጁ ያላቸውን ይሁንታ ሲገልጹ ‹‹ከእኛ ጋር ሳይደርስ ለምን አይጸድቅም?›› የሚል ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የህዝብ ተወካይ ነኝ ብሎ አንድን ህግ ‹‹ፓርላማ ሳይመጣ ለምን ራሱ ኢህአዴግ አያጸድቀውም›› ማለት ስርዓቱን ለማዳን እርብርብ ላይ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
በአጠቃላይ በፊልሙ ላይ በአሉታዊነት የተፈረጁት ጽሁፎች ቢበዛ መካሪ ቢሆኑ እንጂ ይህ ነው የሚባል ‹‹አለመገራት›› አይታይባቸውም፡፡ ነገር ግን ባለመገራቱ ሳይነካ የሚደነብረውን ስርዓት ይበልጡን የሚያስበረግጉ መሆናቸው የሚያስገርም አይሆንም፡፡
እነ ኃይሌ ዴሞክራሲን አይቼባቸዋለሁ ባሏቸው አገራት ሚዲያ አራተኛ የመንግስት አካል ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ሶስቱ የመንግስት አካላትም ሆነ መንግስት ባለመኖሩ አራተኛ መንግስት ሊሆን አልቻለም፡፡ ከዚህ ይልቅ መንግስት በሌለበት፣ ካልተገራ ዘመናዊ የቤተ መንግስት ወንበዴ ጋር ግብ ግብ የሚገጥም ብቸኛው የመንግስት አካል ሆኖ ለማገልገል ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህ ደግሞ መንግስትም ሆነ የመንግስት አካላት እንዳይኖሩ የሚፈልገውንና ልጥ ሲያይ እባብ ነው ብሎ የሚደነብር ያልተገራ ስርዓት እጅጉን አስደንብሮታል፡፡ ስለ ተገራና ስላልተገራ ብዕር ይህ ነው የሚባል እውቀት የሌላቸው፣ የማያገባቸው እነ ኃይሌም ያልተገራው ስርዓት ጋር የተጋሩትን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሉ ስርዓቱ በሚዲያው ላይ እርግጫውን በመሰንዘር እራሱን እንዲያድን እርብርብ አድርገዋል፡፡ የእነ ኃይሌ ምክር ስርዓቱ እንደለመደው እንዲራገጥ የሚገፋፋ ቢሆንም ማዳን አለማዳኑንም ሆነ እነሱ በትውልዱ ላይ እየፈጸሙት ያለውን በደል ግን ታሪክ የሚፈርደው ይሆናል፡፡

ሙስና ለሶስት የሰነጠቃቸው ቡድኖች

ኢህአዴግ በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ላይ ፊጥ ካለ ድፍን 23 ዓመት ቆጠረ፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ በአንቀልባ አዝሎ ለሥልጣን ያበቃው ዛሬ አምርሮ የሚጠላው ሻዕቢያ ነው፡፡ ወያኔ እና ሻዕቢያ ውሃ በወንፊት እንቅዳ ባሉበት የፍቅር ዘመን እነኢሳያስ አፈወርቂ ኦፊሻል ባልሆነ መንገድ ጥሬ ሥጋ ለመቁረጥ በየሳምንቱ አዲስአበባ ይመላለሱ እንደነበር የቅርብ ሰዎች የሚያስታውሱት ነው፡፡
Muktar-300x142ዛሬስ፤ እነዚህ ሁለት ኃይሎች ለመጠፋፋት የሚፈላለጉ ሆነው ተፋጠዋል፡፡ የሚገርመው ወያኔ፤ የሻዕቢያ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ ሀገርን ያህል ነገር ማስገንጠሉን፣ አሰብን አስረክቦ ሀገሪቱን ያለወደብ ማስቀረቱን ጭምር እየረሳ የዛሬ ተቃዋሚዎችን ለምን ከሻዕቢያ ጋር ታያችሁ፣ገንዘብ ተቀበላችሁ እያለ በሀገር ክህደት ጭምር ለመክሰስ ሞራል አግኝቶ ሲወራጭ ማየት ነው፡፡ የትላንቱ የነጻነት ታጋዮች ለሕዝብ ነጻነትና ዴሞክራሲ ታግለናል እያሉ ከ20 ዓመታት ጉዞ በሁዋላ የተትረፈረፈ ነጻነቱን ለራሳቸው ሰጥተው ሌላውን ለመጨፍለቅና ትላንት ባወገዙት የደርግ መንገድ ለመጓዝ አላቅማሙም፡፡
ወደ ሰሞነኛ ጉዳይ እንመለስ ጄኔራል ባጫ ደበሌ አሜሪካን ሀገር ቤት ገዛ የሚል ገራገር ዜና ሰሞኑን በማህበራዊ ድረገጾች ሳነብ አባይን ያላየ ምንጭ ያደንቃል ብዬ በውስጤ አጉተምትሜያለሁ፡፡ የሌባው ቡድን መስረቅን እንደመብት ቆጥሮ በአዲስአበባ ከተማ ቀብረር ያለ ህንጻ በዘመድ አዝማዱ ሰም ሲገነባ ትንሽ እንኳን ሼም እንደሌለው ስትታዘብ ጄኔራሉ በአድራጎቱ አፍሮ ትንሽ ራቅ፣ ደበቅ ለማለት የመፈለጉን ነገር ታመሰግናለህ፡፡ የሌባው ቡድን 5ሺ ብር የማትሞላ ወርሃዊ ደመወዝ ይዞ ልጆቹን በውጪ ሀገር ውድ ት/ቤት ጭምር ሲያስተምር፣ ሚስቱ የሚሊየን ብሮች መኪና ስታሽከረክር፣ ባለቅንጦት ቪላ ገንብቶ ሲንጎማለል ስታይ ጄኔራሉ አንድ ቤት ቢገዛ ታዲያ ምን ይጠበስ ልትል ትችላለህ፡፡ እናም የመከላከያ ወታደሮችን ይጭነቃቸው እንጂ ጄኔራሎቹማ ዛሬ ቢጠሩዋቸው የማይሰሙ ቱጃሮች ሆነዋል፡፡ የሚገርመው ግን እነዚህ ጄኔራሎች ነገ ጥቅማቸውን የሚነካ ነገር ቢመጣ ብረት ላለማንሳታቸው ልማታዊ መንግሥታችንም እንኳን እርግጠኛ መሆን አለመቻሉ ነው፡፡ ኢህአዴግ ነፍሴም «ሙስናን እንዋጋለን» በሚል መፈክር ታጥሮ የሚኖረው ለዚህ ሳይሆን ይቀራልን?!
በአሁን ወቅት ገዥያችን ኢህአዴግ ለሶስት የመሰንጠቅ አዝማማያ እየታየበት ይገኛል፡፡
ቡድን አንድ የደረጀው የሌባ ቡድንን ያቀፈ ነው፡፡ ይህ ቡድን ከፍተኛ መንግሥታዊ ሥልጣኑን የተቆጣጠረ ስለሆነ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ማንኛውንም የኃይል እርምጃ የሚወስድ፣ ጥቅሙ ሲነካ ወይንም ይነካል ብሎ ሲሰጋ ሰዎችን የሚያስር፣ የሚያሳድድ የጨካኞች ስብስብ ነው፡፡ እስከታችኛው ድረስ የራሱ መዋቅር የዘረጋና ብዙ ጀሌዎች ያሉት በመሆኑ ተጽእኖው የሰፋ ነው፡፡
ቡድን ሁለት ሟቹ ጠ/ሚኒስትር በአንድ ወቅት እንዳመነው ነገ ይቀናኝ ይሆናል ብሎ የተቀመጠ ተስፈኞች የተሰባሰቡበት ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የሌባው ቡድን ስላላስጠጋው አምርሮ እየተቃወመና ብሶቱን እየገለጸ ያለና እንደእስስት ገላውን የሚቀያይር ቡድን ነው፡፡ በተመቸው ጊዜ የሚደግፍ፣ ያልተመቸው ሲመስለው የሚቃወም እበላ ባይ የአደገኛ ሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ይህ ቡድን በአመዛኙ በታችኛው እርከን ላይ ተከማችቶ የሚገኝ በመሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በማባባስና በማወሳሰብ ዘወትር ቢወቀስም ምንም ለውጥ ማምጣት ያልቻለ ነው፡፡
ሶስተኛው የኢህአዴግ አባልም ደጋፊም ሆኖ እውነተኛ ዜጋ ሲሆን ሁለቱን ወገኖች የሚጠላ፤ ግን ተጋፍጦ ለመታገል አቅምና ድፍረት ያጣ ነው፡፡
በሒደት አንዱ ነጥሮ መውጣቱ የማይቀር ነው፡፡
( የእኔ የለጣፊው አስተያየት- አጠቃላይ ድርጅቱ የሚጠፋበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም

mandag 25. august 2014

የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ነገረ ኢትዮጵያ 
• የኢትዮጵያ የባህር በር ለኤርትራ መሰጠቱ ስህተት ነው

• የኢኮኖሚ እደገቱ እውነት አይደለም 
• የትምህርት ስርዓቱ ወድቋል
• የተማረ ሰው ክብር አይሰጠውም
addis_universityአዲስ አበባ ውስጥ ሳውዝ ካምፓስ (ልደታ)፣ አቃቂ (AASTU)፣ ፍቼ የግብርና ኮሌጅ፣ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ፣ አአዲስ አበባ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስት ትምህርት ክፍልና ሌሎችም አካባቢዎች ከነሃሴ 15 ጀምሮ ልጠና ላይ የሚገኙ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ተቃውሟቸውን መሳማታቸውን እንደቀጠሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ ገዥው ፓርቲ አለ በሚለው እድገት፣ የባህር በር፣ የተማረው የማህበረሰብ በሚደርስበት በደል፣ የትምህርት ጥራት፣ የመምህራን የእውቀት ደረጃ ማነስ፣ ድህነትና አጠቃላይ ኢኮኖሚ ውድቀት ላይ ጠንከር ያለ አስተያየትና ተቃውሞ መሰንዘራቸውን ተገልጾአል፡፡
የኢኮኖሚ እድገት
ተቃውሞ ከገጠማቸው ጉዳዮች መካከል የኢኮኖሚ እድገት አለ የለም የሚለው ሲሆን ተማሪዎቹ ‹‹በአክሱም ዘመን ገናና የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚው መስክ ጭራ›› መሆኗን በመግለጽ እድገቱ አለ መባሉ ስህተት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ጨምረውም ‹‹በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ የማይችል ማህበረሰብ ይዘን አድገናል ማለት አንችልም፡፡›› በሚል እድገት አለመኖሩን ተከራክረዋል፡፡ ‹‹ሀገራችን ውስጥ የምግብ፣ የቤት፣ የትምህርት፣ የኔትወርክና ሌሎች ችግሮች አሉ፡፡ ስኳርና ዘይት ለመግዛት ህዝብ ቀበሌ ተሰልፎ ነው የሚውለው፡፡ በ400 ብር ደምወዝ ቤተሰብ የሚያስተዳድር ህዝብ ያለባት ሀገር የሌሎችን እድገት ፈዛ እያየች ያለችን ሀገር አድጋለች ልንል አይገባም፡፡›› ማለታቸው ተገልጾአል፡፡
በተመሳሳይም ‹‹2 በመቶ የሚሆነው የአሜሪካ አርሶ አደር ዓለምን በሚመግብበት በአሁኑ ወቅት 85 በመቶ አርሶ አደር ይዘን ለምን እንራባለን?›› የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውንም የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹አድገናል ብለን ራሳችን ማወዳደር ያለብን ከ40 አመት ከነበረ ስርዓት ጋር መሆን የለበትም፡፡ እድገታችን መለካት ካለበት ከሌሎች አገራት ጋር ነው፡፡ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት በ2020 እንመደባለን ከተባለ መንግስት መቀየር ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ይህን ስርዓት ለ20 አመት አይተነዋል፡፡ ባለፉት አመታት ለውጥ ሊያመጣ አልቻለምና በ2020ም ለውጥ ያመጣል ብለን አንጠብቅም፡፡›› የሚል ጠንካር ያለ ሀሳብም አቅርበዋል፡፡
እድገት ላይ ነው የሚባለው የኮንስትራክሽን ዘርፍ የጥራት ደረጃው ዝቅተኛ መሆኑን በተለይ በዘርፉ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች አንስተዋል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹እድገት የምንለው የህንጻዎችን ወደላይ ማደግ ወይንም መብዛት ሳይሆን የማህበረሰቡን አስተሳሰብና አኗኗር ዘይቤ መቀየር ነው፡፡›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ በስልጠናው ወቅት ገዥው ፓርቲ የቻይናን ፈለግ ተከትሎ እድገት ማስመዝገቡን በመቃወም ‹‹ቻይና ከ2.3 እስከ 2.7 በመቶ እያደገች እንደሆነ ይነገራል፡፡ የእሷን ፈለግ ተከተለች የተባለችው ኢትዮጵያ ከ11.2 በመቶ በላይ አደገች ነው የሚባለው ከየት አምጥተነው ነው? ወይስ እንደ ቀን አቆጣጠራችን እድገታችንም ይለያያል?›› ሲሉም አሰልጣኖቹን ጠይቀዋል፡፡
የባህር በር
ተማሪዎቹ ለኤርትራ መሰጠቱ አግባብ እዳልሆነ፣ የባህር በርና ወደቡ ለኢትዮጵያ ቀጣይ እድገት፣ ደህንነትና ታሪክ አንጻር አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ገዥው ፓርቲ በባህር በር ላይ ያለውን አቋምና ፈጸመ ያሉትን ስህተት ተችተዋል፡፡ ወደብ አልባ በመሆናችን ኢኮኖሚያችን ወደኋላ መቅረቱንም አንስተዋል፡፡ በሌላ በኩል ‹‹በአገራችን የሚመረቱ ሰብሎችና ፍራፍሬዎች ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርቡት ከውጭ ከተላከው ሲተርፍ ነው፡፡›› በማለት በኤክስፖርት ዘርፍ ያለውን ችግር፣ አገር ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን የኑሮ ውድነት ከዚሁ ችግር መመንጨቱን ጠቅሰዋል፡፡
የትምህርት ጥራት
ተማሪዎቹ የራሳቸውን ተሞክሮ በመጥቀስ የትምህርት ስርዓቱ ችግር ያለበት መሆኑን በመከራከሪያነት አቅርበዋል፡፡ ‹‹ለተማረ ሰው ክብር እየተሰጠ አይደለም፡፡›› በሚል የእነሱም እጣ ፈንታ ተመሳሳይ መሆኑን ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹የሚያስተምሩን አስተማሪዎች የእውቀት ደረጃ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው፡፡ በየ ዩኒቨርሲቲው በአመራር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች እውቀት የላቸውም፡፡›› በማለት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተደቀነውን አደጋ አንስተዋል፡፡
ዲግሪ ይዘው በስራ ፈጠራ ስም በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲደራጁ የሚደረገውን የተቃወሙት ተማሪዎቹ ‹‹የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተደራጅተው ካፌ ከፈቱ፣ ኮብልስቶን አነጠፉ ሲባል ነው የምንሰማው፡፡ ለዚህ ስራ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ መማር አያስፈልገውም፡፡ ይህን ስራ ለመስራት የሶስት ወር ስልጠና በቂ ሆኖ እያለ ዩኒቨርሲቲ መማር ባላስፈለ›› ሲሉ የትምህርት ስርዓቱ ውድቀት እንደገጠመው መግለጻቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ በቀጣይም የተማሪዎችን ጉዳይ እየተከታተለች ታቀርባለች!

አርበኞች ግንባር፣ ግንቦት 7 እና የአዲሃን ወደውህደት የሚያደርሳቸውን ውይይት ሊጀምሩ ነው

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር፣ ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲ ሃይሎች ንቅናቄ ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ውይይት ሊጀምሩ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ በላኩት መግለጫ አስታወቁ።
“የወያኔውን ዕድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን” በሚል ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ “ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉባት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ድረጃ መድረሳችንን የወያኔውን ቡድን ነፍጥ አንስተን እየተፋለምን ያለን ድርጅቶች ተጣንሪባ አንድ ሆኖ መታገል እንዳለብን ካመንን አመታትን አስቆጥረናል” ብለዋል።
ሙሉ መግለጫው የሚከተለው ነው፦
arbegnoch ginbar and ginbot 7

ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል

(ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)
better

ጉልበት አራዊት የሚተዳደሩበት ሕግ ነው፤ ሕገ አራዊት የሚባለው አራዊት የሚተዳደሩበት ጉልበት ነው፤ በአራዊት ዓለም ማናቸውም ነገር በጉልበት ያልቃል፤ በሰዎችም መሀከል ጉልበት አድራጊ-ፈጣሪ ሆኖ ጎልቶ ሲወጣ የአእምሮንና የኅሊናን መዳከም ወይም ጭራሹኑ አለመኖር ያመለክታል፤ ጉልበት አለን በማለት፣ ወይም ተመችቶናል በማለት፣ ወይም ጠያቂ የለብንም በማለት የማንኛውንም ሰው ሰብአዊ መብቱንና ሰብአዊ ክብሩን መግፈፍ ሦስት ነገሮችን ያመለክታል፤ አንደኛ ጉልበት እንጂ አእምሮና ኅሊና እንደሌለ፣ ሁለተኛ ጉልበት እንጂ ሕግ እንደማይከበር፣ ሦስተኛ በአንተ ላይ እንዲያደርጉብህ የማትፈልገውን አንተም በሰዎች ላይ አታድርግ የሚለውን ሕግ መጣስን ያሳያል፤ በመጨረሻም፣ ዘግይቶም ቢሆን በራስ ላይ ቅሌትን መጋበዝን ያስከትላል፤ የሌላውን ሰውነት ስናረክስ ሰውነትን በጠቅላላው ማርከሳችን ነው፤ ሰውነትን በጠቅላላው ስናረክስ ራሳችንን ከነጉልበታችን ማርከሳችን ነው፤ ራሳችንን፣ ሰውነታችንን ካረከስን በኋላ ዋጋ የለንም፤ ለራሳችን ዋጋ ከሌለን ለሌለች ሰዎችም ዋጋ አንሰጥም፤ ያኔ ክፉ በሽታ ይይዘናል፤ እግራችን ስር በወደቀ ሰው ስቃይ የምንደሰትና የምንስቅ፣ የምንፈነድቅ  እንሆናለን፤ ያን ጊዜ የለየለት በሽተኛ ሆነናል።
ይሄ በሽታ ያቃዣል፤ ከሰው ሁሉ በላይ ያሉ ያስመስላል፤ አግሩ ስር የወደቀው አንድ ሰው የሰው ልጅ በሙሉ ይመስለዋል፤ በሽተኛነቱን ስለማያውቅ በሽታው ከሰው በላይ ያደረገው ይመስለዋል፤ እንዲህ ዓይነቱ በሽተኛ በሕግ አሰከባሪነት ሥራ ውስጥ ሲገባ ሕግ የአንድ ማኅበረሰብ ትምክህትና መከታ በመሆን ፋንታ የበሽተኞች በትር ይሆናል፤ በደርግ ዘመን የአራት ኪሎው ግርማ የሠራውን እናውቃለን፤ ዛሬ ደግሞ ልዩ ግርማዎች አሉ፤ መልካቸውን ከካሜራው ጀርባ ደብቀው በሰው ስቃይና አበሳ በሳቅ እየተንከተከቱ ጀብዱዋቸውን በቴሌቪዥን የሚደረድሩ ጀግኖች መጥተዋል፤ መሣሪያ ይዞ መሣሪያ ባልያዘ ሰው ላይ ጀግና መስሎ ለመታየት የሚሠራው ጨዋታ ራስን ክፉኛ ከማጋለጥ በቀር ሌላ ፋይዳ የለውም።
በኢትዮጵያዊ ሰውነት ላይ ማናቸውንም ከሕግና ከሰብአዊነት ውጭ የሆነ ሙከራ ለማድረግ የውጭ አገር ሰዎች ዕድሉን ይፈልጉት ይሆናል፤ ለነሱ ሰዎች ስላልሆን ሰብአዊነት አይሰማቸውም፤ ከአገራቸው ሕግም ውጭ በመሆናቸው በሕግ አይገዙም፤ ዋናው ውጤት ግን ለኢትዮጵያ ሕግ አስከባሪዎች የሚያስተምሩት ግዴለሽነት ነው፤ መታሰር በብዙ ምክንያቶች ይመጣል፤ ስለዚህ በሠለጠነው ዓለም የተለያዩ እስረኞች በተለያየ ሁኔታ ይጠበቃሉ፤ አንዳንዶቹ እንዲያውም በቤታቸው ውስጥ እየተጠበቁ ይቆያሉ፤ ኢትዮጵያ በራስዋ ሥልጣኔ በምትተዳደርበት ዘመን መሳፍንትና መኳንንት የሚታሰሩት በወርቅ ወይም በብር ሰንሰለት ነበር፤ ግዞትም፣ የቁም እስርም ነበር፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ እስረኞች ሁሉ እኩል ናቸው፤ በቃሊቲ ለየት ያለ አያያዝ የሚታየው ለሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎች ብቻ ነው።
ጉልበትን በጉልበት እቋቋማለሁ የሚል ሰው ሲሸነፍ አያስደንቅም፤ አዲስም አይደለም፤ በአለፉት አርባ ዓመታት እየተሸነፉ ከትግሉ ሜዳ ወጥተው በተለያዩ የምዕራባውያን አገሮች የሙጢኝ ብለው የተቀመጡ አሉ፤ በተባበሩት መንግሥታት ደንብ የሙጢኝ ማለት መብት ነው፤ ይህንን መብት መጣስ የመንግሥተ ሰማያትን በር መድፈር ነው፤ በጎንደር የአደባባይ ኢየሱስን ቤተ ክርስቲያን በር መድፈር ነው፤ በአዲስ አበባ የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን በር መድፈር ነው፤ በአዲስ አበባ የአንዋር መስጊድን በር መድፈር ነው፤ ወደመሬት ስንወርድም የሙጢኝ የተባለው አገርን መንግሥት መድፈር ነው፤ የተባበሩት መንግሥታት ደንብን መጣስ ነው፤ ለነገሩ የመንግሥተ ሰማያትን በር መድፈር ከተቻለ ሌላው ምን ያቅታል!
የሙጢኝ ያለን ሰው በአፈና መያዝና ወደአገር ማስገባት አንድ ችግር ነው፤ ይህ የጉልበተኛነት መገለጫው ነው፤ ሁለተኛው ችግር የተያዘው ሰው መብቱና ክብሩ ሳይጓደልበት ማስረጃዎችን ሰብስቦ ለነጻ ፍርድ ቤት አለማቅረቡ ነው፤ በቴሌቪዥን እንደታየው አካላዊ ጉዳት እንደደረሰበት ባይታወቅም፣ ጥልቅ መንፈሳዊ ጉዳት እንደደረሰበት ይታያል፤ በብዙ አገሮች ሕጎች አንድ ሰው ራሱን እንዲወነጅል አይገደድም፤ ሕጋዊ ምርመራም በቴሌቪዥን በአደባባይ አይካሄድም።
ስለዚህም በተጠርጣሪው ላይ የተደረገው ሁሉ ሕጋዊ አይደለም፤ በነጻ ፍርድ ቤት ቢቀርብም በቴሌቪዥን የተናገረው ሁሉ ቢያስታውሰውም በማስረጃነት የሚያገለግል አይመስለኝም፤ ስለዚህም ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል።
ከአፍሪካ አህጉር ወጥቶ የቀይ ባሕርን አቋርጦ አንድ ሰው፣ ገና ወደፊት ክፉ ሊሠራ ይችላል በሚል ሂሳብ በጉልበት አፍኖ ማምጣት የብዙ ነፍሶች ዕዳን ተሸክመው በኢጣልያ ኤምባሲ የሙጢኝ ብለው ተደላድለው የተቀመጡትን የደርግ አባሎች ማስታወስ ግዴታ ይሆናል፤ አድርጋችኋል የተባሉትን ሰዎች የሙጢኝ የማለት መብት አክብሮ አስበሃል የተባለውን ሰው የሙጢኝ የማለት መብት መጣስ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል።
ከፖሊቲካና ከምናምኑ፣ ጉልበተኛነትንም ከማረጋገጡ በላይ ሌላ ትልቅ ነገር አለ፤ አገር የሚባል ነገር አለ፤ ይህ በአንድ ግለሰብ ላይ የተገኘ ጊዜያዊ ድል የአገርን ከብር የሚያጎድፍና የሚያቀል ይሆናል፤ የአንድ አገርን የመንግሥት ሥልጣን የያዘ አካል አንድ ግለሰብን በአደባባይ ከሕግ ውጭ ለማጥቃት ሲሞክር የራሱን ክብር ዝቅ ያደረግበታል፤ ስለዚህም ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል።
በእኔ ዕድሜ ሰው በአደባባይ ሲገረፍ አይቻለሁ፤ ሰው ተሰቅሎ አይቻለሁ፤ የዚያን ዘመን የእውቀት ደረጃ የዚያን ዘመን የሰው ልጆች የመንፈስ እድገት ደረጃ ያመለክታል፤ የእውቀትም የመንፈስም ደረጃ በጣም ዝቅተኛ ነበረ ማለት ነው፤ ስለዚህም ይህንን ያደረጉትን ዛሬ አንወቅሳቸውም ይሆናል፤ የታሪካችን ጉድፍ መሆኑን ግን ልንፍቀው አንችልም፤ ስለዚህም ሌላ ጉድፍ እየጨመርንበት ታሪካችንን ማቆሸሹ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ይበልጣል።
ቅጣት በሕግና በሥርዓት ይደረግ ማለት ያጠፋ ሰው አይቀጣ ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ምንም አቅም የሌለውን ሰው ይዞ በአደባባይ ማሰቃየትና ማዋረድ አገርንና ሕዝብን ማዋረድ ነው፤ የሰብአዊነትንም የሕጋዊነትንም ሚዛኖች ይሰባብራል።
ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

søndag 24. august 2014

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሀብታቸውን በግልጽ እንዲለዩ የዓለም ባንክ አሳሰበ

Ethiopian Electric Power Corporationየቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለሁለት ተከፍሎ የተፈጠሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ሀብታቸውን በግልጽ ለይተውና ተካፍለው የየራሳቸውን የሒሳብ መዝገብ እንዲይዙ የዓለም ባንክ ማሳሰቡን ምንጮች ገለጹ፡፡
የዓለም ባንክ ማሳሰቢያውን የሰጠበት ምክንያት ለአገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት (Grid) ማጠናከሪያና ማስፋፊያ የሰጠው ብድር በአግባቡ ሥራ ላይ እየዋለ መሆኑን ለማረጋገጥ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
እ.ኤ.አ. በግንቦት 2012 የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት የ200 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሟል፡፡
በስምምነቱ መሠረት የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ ፈጻሚ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ መሆን የጀመረው እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 2013 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ሥራው ከተጀመረ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንን ለሁለት በመክፈል ራሳቸውን የቻሉ ሁለት ተቋማትን ፈጥሯል፡፡ የተፈጠሩት ሁለት ተቋማት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኢንጂነር አዜብ አስናቀ የሚመራ ሲሆን፣ ኃላፊነቱም የኃይል ማመንጫ ግንባታዎችን እንዲሁም የመስመር ዝርጋታዎችን የተመለከተ ነው፡፡ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ሥርጭትንና ጥገናን የተመለከተ ኃላፊነት ተሰጥቶት ማኔጅመንቱም በሁለት ዓመት ኮንትራት ለህንድ ኩባንያ ባለፈው ዓመት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለሁለት መከፈሉ የኃላፊነት መዛባትን ያስከትላል የሚል ሥጋት የገባው የዓለም ባንክ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ጋር ወዲያውኑ ውይይት ማድረጉን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡
የተደረገው አዲስ አወቃቀር የፕሮጀክት ትግበራውን ያስተጓጉላል፣ ተጨማሪ ወጪ ያስከትላል፣ በፕሮጀክቱ ከሚሳተፉ ኮንትራክተሮች ጋር ግጭት ይፈጥራል በሚል በቀረበ ሐሳብ መሠረት ቀድሞ በተፈረመው የብድር ስምምነት ውስጥ የሚካተት የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ፕሮጀክቱ መቀጠሉን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ እስኪፈረም ድረስ መጠነኛ የሥራ መጓተት መፈጠሩን ለመረዳት ቢቻልም፣ አሁንም ቢሆን በሚፈለገው ፍጥነት ፕሮጀክቱ እየሄደ አለመሆኑን ምንጮች ያስረዳሉ፡፡
ለአብነት ያህልም የዓለም ባንክ ለፕሮጀክቱ ከፈቀደው 200 ሚሊዮን ዶላር ብድር ውስጥ፣ ፕሮጀክቱ በተጀመረ በአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ውስጥ የተጠቀመው ዘጠኝ በመቶውን ብቻ እንደሆነ ይጠቅሳሉ፡፡
ሁኔታው ያሳሰበው የዓለም ባንክ ከሁለት ሳምንት በፊት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ኃላፊዎች ጋር ፕሮጀክቱን በመገምገም ማሳሰቢያዎችን መስጠቱን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡
የኢትዮጵያ አሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ግልጽ የሆነ የሀብት ክፍፍል አድርገው ባለመለያየታቸው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የፋይናንስ አማካሪ ድርጅት በመቅጠር ሀብታቸውን እንዲለያዩና ግልጽ የሆነ የየራሳቸው የሒሳብ መዝገብ እንዲፈጥሩ ማሳሰቡን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቱን ተግባራዊ በሚያደርግበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ትብብርን የሚሹ ጉዳዮች የሚኖሩ በመሆናቸው እነዚህ ትብብር የሚሹ አካባቢዎች በግልጽ እንዲለዩ ባንኩ ማሳሰቡ ታውቋል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀን ለማግኘት የተደረገው ጥረት መሳካት አልቻለም፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዋየር ቢዝነስ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ቢትወደድ ገብረ አሊፍ ሥራው በአግባቡ እየተሠራ መሆኑንና በጥሩ ደረጃ ላይም እንደሚገኝ ይገልጻሉ፡፡
‹‹ሥራውን ተከፋፍለናል፡፡ ሥራውን ስንከፋፈል ሁሉም ወደሚመለከተው ይሄዳል፡፡ ነገር ግን አብሮ የመሥራትና የመተባበር ጉዳይ የሚቀር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥራ ተከፋፈልን እንጂ ፍቺ አይደለም የፈጸምነው፡፡ እንዲህ ብንረዳው ይሻላል፤›› ብለዋል፡፡
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከመፍረሱ በፊት ከሰጣቸው ብድሮች መካከል ለየኢትዮ-ኬንያ የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክት የሚውል ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ይገኝበታል፡፡ ነገር ግን ይህ ፕሮጀክት በአሁኑ ጊዜ በመግባባት እየተከናወነ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

lørdag 23. august 2014

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

 የሸክ ኑሩ ግድያ ሴራ ነው
• ኢህአዴግ በሉዓላዊነት ላይ ያለውን ፖሊሲ ተቃውመዋል
• ‹‹አማኞችን በአሸባሪነት መክሰስ ትውልዱን ለመግደል የተደረገ የኢህአዴግ ሴራ ነው፡፡››
• ህወሓት ከስሯል
• የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ
• አዲሲቷ ኢትዮጵያ የትኛዋ ናት?
ነገረ ኢትዮጵያ ባህርዳር፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ፣ ደሴ፣ ወልደያ፣ ደብረታቦርና ሌሎችም የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ባገኘችው መረጃ መሰረት የተነሱትን ዋና ዋና ተቃውሞወች እንደሚከተለው አቅርባለች፡፡
SONY DSCአርሶ አደሩ አሁንም ድረስ ኢህአዴግ እየተደረገ ያለው የመሬት ድልደላ የፓርቲው አባል አይደሉም የሚባሉት አርሶ አደሮችን መሬት አልባ በማድረግ ለደጋፊዎቹ እየሰጠ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተገልጾአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በ1997 ዓ.ም ምርጫ ቅንጅትን መርጣችኋል እየተባሉ አሁንም ድረስ ጫና እየደረሰባቸው እንደሚገኝና፣ ይህም ለምርጫው ዝግጅት እንዳይሆን ተማሪዎቹ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
የእምነት ነጻነት በርካታ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለሶስት አመታት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጻቸው እንዲሰማ ቢጥሩም መንግስት እየወሰደው ያለው አፈና አግባብ አለመሆኑን፣ በተለይም በርካታ ቁጥር ያለውን ሙስሊሙን ማህበረሰብ በጅምላ አሸባሪ ብሎ መፈረጅ ስህተት መሆኑን በተማሪዎቹ ተነስቷል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹ኢህአዴግ ማህበረ ቅዱሳንን አሸባሪ የሚልበት ምክንያት ምንድን ነው?›› የሚል ጥያቄ የተነሳ ሲሆን የግቢ ጉባዔ የማህበረ ቅዱሳን አንድ ክንፍ ነው ተብሎ በመፈረጁ አዲስ ህግ ወጥቶ ዩኒቨርሰቲ ውስጥ በጾም ወቅት ይሰጠን የነበረው አገልግሎትን ጨምሮ እምነታችን እንዳንተገብር መከልከላችን ለጣልቃ ገብነቱ ማሳያ ምክንያት ነው›› ብለዋል፡፡
ይህም መንግስት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በእምነት ላይ ጣልቃ እየገባ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡ እንደ ምሳሌም በ1989ና 1994 ዓ.ም የኃይማኖት አባቶች በተለይም ቄሶች የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል ተብለው ድብደባ እንደደረሰባቸው በመግለጽ የጣልቃገብነቱን አስከፊነት ገልጸዋል፡፡ ሉዓላዊነት ሉዓላዊነትን በተመለከተ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ጥያቄ የተነሳ ሲሆን በተለይም በባህርዳር፣ ጎንደር፣ ወልደያ፣ ደሴና ደብረማርቆስ ዪኒቨርሲቲዎች ዋነኛ የመወያያ አጀንዳ እንደነበር ለመረዳት ችለናል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹መሬቱን ቆርሶ የሰጠው ኢህአዴግ ነው፣ በሉዓላዊነት ጉዳይ ላይ አገራችን ከነበራት ክብር እያሳነሰው ነው፣ ኢትዮጵያ አንድነትን ለመጠበቅ የጣረውን ምኒልክን እየወቀሰ ኢህአዴግ በአሁኑ ወቅት መሬት ቆርሶ መስጠቱ አላማውን በግልጽ የሚያሳይ ነው›› በማለት በሉዓላዊነት ላይ የተሳሳተ ፖሊሲ እንዳለው ተከራክረዋል፡፡
በተጨማሪም ‹‹ኤርትራ ተገንጥላለች፣ አሰብን አጥነተናል፣ ባድመ ላይ ወጣቱ አልቆ መሬቱን አሳልፎ ሰጥቷል፣ አሁን ደግሞ የመተማን መሬት አሳልፎ ለመስጠት በድብቅ መፈራረሙ በሉዓላዊነታችን ላይ ያለውን አሉታዊ አቋም የሚያሳይ ነው፡፡›› በሚል በሉዓላዊነት ላይ ያለውን የተሳሳተ ፖሊሲ ተቃውመዋል፡፡ በተመሳሳይ ተማሪዎቹ አያሌው ጎበዜ የፕሬዝዳንትነት ስልጣኑን ሳይጨርስ የወረደው መሬቱን ፈርሜ አልሰጥም ስላለ ነው፡፡›› ያሉት ተማሪዎቹ ለጥያቄዎቻቸው መልስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ የሸህ ኑሩ ግድያ ደሴ ላይ የተማሪው ትልቅ መወያያ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የሸህ ኑሩ ግድያ በቀዳሚነት እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
slide-15ከተወያዮቹ መካከል ‹‹የሸክ ኑሩ ገዳይ የኢህአዴግ ደህንነቶች ናቸው፡፡ ይህም የተደረገው ኢህአዴግ በሙስሊሙ መካከል ልዩነት ለመፍጠርና እርምጃም ለመውሰድ እንዲመቸው የወሰደው ነው፡፡›› ማለታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አንዳርጋቸው ጽጌ ደብረማርቆስ በሚገኙ ተወያዮች አጀንዳ ከነበሩት ጉዳዮች መካከል የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ይገኝበታል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹የመን አንዳርጋቸውን አሳልፋ መስጠቷ ትክክል አይደለም፣ የአንዳርጋቸው ጉዳይ ሽብርን መዋጋት ነው ወይንስ የፖለቲካ ባላንጣነት? የእንግሊዝ ዜጋ የሆነውንና እንግሊዝ በአሸባሪነት ያልፈረጀችውን ሰው አሸባሪ ማለቱ ጸረ ሽብር ህጉ ከእንግሊዝ ተመሳሳይ ህግ ጋር በምን ቢለያይ ነው? በጸረ ሽብር ኢህአዴግ ከእንግሊዝ በልጦ ነው ወይ? አሁን ያለበት ሁኔታም ለህዝብ ይፋ ሊሆን ይገባል የመሳሰሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ማፈናቀል የከተማ ነዋሪዎችን ማፈናቀል በባህርዳር፣ ጎንደርና ደብረማርቆስ ከተማ ውስጥ የሚገኙት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተነስቷል፡፡
ተማሪዎቹ ‹‹በተለያዩ ከተሞች ድሃዎችን በማፈናቀልና ቤታቸውን በማፍረስ ለሀብታም እየተሰጠ ነው፡፡ ይህ የጭቆና የመጨረሻው ደረጃ ነው፡፡›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ‹‹የመሬት መቀራመት መሬት በቀብሬ ላይ ይቀየራል ከሚለው የኢህአዴግ ፖሊሲ የመነጨ ነው፡፡ የመሬት ክፍፍሉ አርሶ አደሩን ያገለለና ለስርዓቱ መጠቀሚያ የሆነ ነው፡፡ የሊዝ ህጉ መሰረዝ ይገባዋል፣ አርሶ አደሩ ከመሬት እየተነቀለ ነው፣ 1ለ5 አርሶ አደሩን ለማፈን የተደረገ ነው፡፡ መሬት የኢትዮጵያ ህዝብ እንጅ የመንግስትና የፓርቲ መሆን የለበትም›› የሚሉ ተቃውሞዎች ተነስተዋል፡፡ የባህር ዳሩ ግጭት የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠረው ግጭትን በተመለከተ ደሴ፣ ደብረታቦር፣ ባህርዳርና ጎንደር ላይ መወያያ ሆኖ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ባህርዳር ላይ በተደረገው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ላይ የተፈጠረው ግጭት ብአዴን በበላይነት የመራው ሴራ መሆኑን፣ ይህም አማርኛ ተናጋሪውን እንደማይወክል፣ የብአዴን ፖለቲከኞች እንወክለዋለን የሚሉትን ህዝብ በአደባባይ ሲሳደቡ መስተዋላቸው የሚያሳየው ለህዝብ ያልቆሙ እንደሆነ ተማሪዎቹ አጽንኦት ሰጥተው እንደገለጹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ርዕዮት-ዓለም በተለይ ባህረዳር ውስጥ ድባንቄ የተባለ ቦታ ላይ የሚገኙት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሰልጣኞች በርዕዮት ዓለም ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹እስከ 1994 ዓ.ም ኢህአዴግ ፖሊሲ አልነበረውም፣ ተቃዋዎችን ፖሊሲ የላቸውም እያለ ለመተቼት ምን ሞራል አለው፣ ሌብራሊዝም ተቃዋሚዎቹ ስለሚከተሉት ብቻ ትክክል እንዳልሆነ እየተነገረን ነው፣ ከቻይና ተገለበጠ የሚባል ርዕዮት ዓለም ለኢትዮጵያ እየጠቀመ አይደለም፣ መነሻውና መድረሻው የማይታወቅ የኢህአዴግ ርዕዮት ዓለም ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም፣ ማህበረቅዱሳንንና ሙስሊሙን ማህበረሰብ አሸባሪ ማለት እምነት አልባ ትውልድ ለመፍጠር የተደረገ ሴራ ነው፣ ይህ ትውልዱን ለመግደል የተደረገ የኢህአዴግ ሴራ ነው፡፡››
ትምህርት ‹‹ትምህርትን በኢህአዴግ ዘመን ወድቋል፡፡ ትምህርቱ ጥራት ቢኖረው ኖሮ ተመርቆ ስራ አያጣም ነበር፡፡ አሁንም ስራ እንይዛለን የሚል ተስፋ የለንም፡፡ ኢህአዴግ ዘመን ትምህርት ወድቆ ትምህርት ስርዓቱን የጀመሩትን ስርዓቶች የማውገዝ ሞራል አላችሁ ሆይ?›› የሚሉ ተቃውሞዎች ቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹በየ ዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ሴቶች በትምህርት ስርዓቱ ውድቀትና በድህነት ምክንያት ገላቸውን እየሸጡ ነው፡፡ ኢህአዴግ በግብረ ሰዶማውያን ላይ ያለው አቋም የተሳሳተ ነው፡፡ ይህም የሚደረገው ትውልዱ ማንነቱን ትቶ ውድቀት ላይ እንዲወድቅ ለማድረግ ነው፡፡ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሌብራሊዝምን እያንቋሸሸ የወሲብ ሌብራሊዝምን ግፍ ከሚገባው በላይ ለቆታል፡፡ ይህ ኢህአዴግ ስልጣኑን ለማቆየት የሚያደርገው ስልት ነው፡፡ ይህ በተሳሳተ የኢኮኖሚ ምክንያት በመጣው ድህነት የተነሳ ነው፡፡ በትምህርት ውድቀትና በድህነቱ ምክንያት ተማሪዎች ድንጋይ መቀጥቀጥ አማራጭ ሆኖ በመቅረቡ ሴቶች የወሲብ ንግድን እንዲቀላቀሉ እንዲሁም ወንዶች የጎዳና ተዳዳሪ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው፡፡ የሚሉ ተቃውሞዎችን ማቅረባቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡›› የሚሉ ተቃውሞዎች ተነስተዋል፡፡
ኢዲሲቷ ኢትዮጵያ የትኛዋ ናት? ለስልጠና በቀረቡት ሰነዶች አብዛኛዎቹ ክፍሎች ውስጥ ‹‹አዲሲቷ ኢትዮጵያ›› የሚል ቃል የተደጋገመ ሲሆን ተማሪዎቹም ‹‹ኢዲሲቷ ኢትዮጵያ የትኛዋ ናት? ኤርትራ የተገነጠለችባት፣ በቋንቋ የተከፋፈልንባት፣ ወደብ አልባ የሆንንባት፣ የኢትዮጵያ ገናናነት የወረደባት ኢትዮጵያ አዲሲቱ ኢትዮጵያ ልትባል ትችላለች? የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹ብሄር ማለት ምን ማለት ነው?›› የሚለው ወልደያ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ በሚገኙ ሰልጣኞች ሰፊ ክርክር አስነስቷል፡፡ ፋብሪካዎች ደብረማርቆስ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ‹‹ደብረ ማርቆስ ውስጥ ሊገነባ የነበረ የመኪና መገጣጠሚያ እንደገና እንዲቀር ተደርጓል፣ በክልሉ የቢራ እንጅ ሌሎች ፋብሪካዎች እንዲስፋፉ አይደረግም›› የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹በስፋት ደን ይመነጠራል፡፡ ደን እየተመነጠረ እንዴት አረንጓዴ ልማት አለ ይባላል?›› የሚሉ ጥያቄዎችን ተጠይቀዋል፡፡
ህወሓት ከስሯል
በመቀሌ ዪኒቨርሲቲ የሚገኙ ሰልጣኝ ተማሪዎች በተለይም በህወሓት ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አሰልጣኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹የትግራይ ህዝብ በህወሓት አምኖና ከሌላው ህዝብ ተለይቶ እንዲኖር ህወሓት ብዙ ስራ ሰርቶ ነበር፡፡ ከክፍፍሉ በኋላ ግን ህወሓት ከስሯል፡፡ የትግራይ ህዝብን ጥያቄ ያልተመለሰ ለመሆኑ የአረና መፈጠር አንድ ማሳያ ነው፡፡›› ማለታቸውን አሰልጣኙ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም አብርሃ ደስታ ላይ የተወሰደው እርምጃም መነጋገሪያ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል፡፡ ተማሪዎቹ አብርሃ ደስታ መፈታት እንዳበት መጠየቃቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል በአብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች ጥያቄውን ያነሱት ተማሪዎች በቡድን ውይይት ወቅት ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነም ተገልጾአል፡፡ በጅማ፣ አዳ፣ ሀዋሳና ሌሎች ከተሞች የሚሰለጥኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያሰሙትን ተቃውሞና መከራከሪያዎች በቀጣይነት ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡