søndag 3. mars 2013

ተጋዳላይ ማትያስ ሹመት ያዳብር!


እንዳይነቀሳቀስ አጁን በስንሰለት ጠፍረህ አሰረኸው፡
ሽጉጥክን ደግነህ ተናዘዝ ብትለው፡
በእምነቴ አትምጣ ከፈለክ ያውልህ ደረቴን ለጥይት፡
ከቶ አልበገርም በባዶ ድራማ አድማጭ የለሽ ተረት፡
ሞቴን ከነምነቴ ብሎ በመጽናቱ ግራ የተጋባህ፡
ደንባራ ወያኔ ፊልም መቆራረጥ መቀጣጠል ገባህ፡፡
አንተ አቡ በከር አንድ ጎኔን ሞቀው በጣም አኮራኸኝ ፡
አኩል አልሞቅ አለኝ አንዱ ጎኔ ሳስቶ ክፉኛ በረደኝ ።
እንኳንስ ተከታይ፤ አስተማሪው ካህን መነኩሴው ጳጳሱ፡
ለምነት አልቆም አለ አሳሳችው ነፍሱ።
ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መሆኗ ቀረና የእምነት ማህደር፡
ታጋይ ተፈራርቆ ይሾምባት ጀመር።
የሃይማኖት መሪ በግዜር ይመረጣል ተብይ አድጌ፡
አገር በጾም ጸሎት ትጸናለች ሲባል ተምሬ አድጌ፤
ታጋይ ጳጳስ ሲሆን ስተቱ የማን ነው? መልስ አጣሁ ፈልጌ።
በመርዝ በጥይት ወገኑን ጨርሶ የመጣ ሹመኛ ደብሩን ቢረከበው፡
እግዜር የሾመው ነው በሚል አጉል ባህል መስቀል ልሳለም ነው?
ወይስ
አንተ እርኩስ መንፈስ ተጣልቼሃለሁ፡
መስቀልህ ይቅርብኝ ቤቴ ጸልያለሁ፡
ገንዘቤም በኪሴ ለምን ጦርሃለሁ፡
ብዬ ላሳርፈው?
ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን የምትሆነው ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው የሃይማኖት መሪ ሲኖራት እንጂ የፖለቲካ ስልጣን በተቆጣጠሩ ባለስልጣናት የሚሾም ካድሬ ቁጥጥር ስር ሆና አደለም ፡ ስለዚህ ለተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ ማስተላለፍ የምፈልገው ምልእክት፡ ስርዓት እሰኪከበር ድረስ ጸሎታችሁን በቤታችሁ ገንዘባችሁን በኪሳችሁ እንድታረጉት እንዲሆን ነው፡ በገዛ ገንዘባችሁ ወያኔን የምታዳብሩበት ምክንያት አይኖርም፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
እስከ ነጻነት

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar