lørdag 16. mars 2013

ሰላማዊ ትግል እንደ እስላማዊ ትግል…!

የልጅነት ወዳጄ ሁሴን ከድር እንደነገረኝ “እስላም” የሚለው ስም ራሱ የመጣው ሰላም ከሚለው ነው፡፡ ሁሴን የነገረኝ ሀሰት እንደሌለው ያረጋገጥኩት፤ ያኔውኑ የእርሱን ሰላማዊነት ስመለከት ነበር፡፡ ሁሴን እጅግ ሰላማዊ ሙስሊም ወዳጃችን ነው!

እስላም ማለት ሰላም ማለት ነው… የሚለውን በደንብ ለማስረገጥ ከፈለጉ ደግሞ ከድፍን አንድ አመት ሞልቶ የፈሰሰውን ሰላማዊ ትግል አይቶ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህንን መረዳት ካልተቻለ የህክምና እርዳታ ያስፈልገናል ማለት ነው፡፡ሰላማዊ ትግል እንደ እስላማዊ ትግል…!
ሁሌ ክበር የሚሉት አላህ ብርታቱን የሰጣቸው ሰላማዊ ሙስሊም ታጋዮች በተለያየ ጊዜ መንግስታችን ስም ማውጣት ብርቁ ስላልሆነ አንዴ አሸባሪ አንዴ አክራሪ ቢላቸውም እነርሱ ግን ከአመት በላይ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተሞላበት ፍፁም ሰላማዊ ትግል እያከናወኑ መንግስታችንን ኩም አድርገውታል፡፡
ችግሩ መንግስት “ኩም” ሲያደርጉት ምንም ሳይነካ እሪ… ብሎ እየጮኸ በድምሩ “እሪ… ኩም” እያለ ዘፈን አይሉት ልቅሶ ሲያሰማ ነገሩ እጅግ አስቂኝ ሆኖ ከርሟል፡፡ ይሄኔ እኛም “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል” የሚለው ተረት ስለተያዘብን እንደ አቅማችን አዲስ ተረት ተርተንለታል “መንግስታችን ራሱ በጥፊ ተማትቶ ራሱ ጯ! ብሎ ይጮሃል!”
ለማንኛውም ለመረጃ ያህል በዛሬው ጁምአ በመላው ሀገሪቱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለአላህ ተማፅኗቸውን ለመንግስት ደግሞ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ይቀጥላሉ! መንግስት የሚሰማ አይመስለንም ለራሱ ጮክ ብሎ እየጮኸ ስለሆነ ሌሎችን ለመስማት መቻሉን እንጃ…! አላህ ግን ይሰማል! መልሱም ያለው እርሱ ዘንድ ነው!
እኔ የምለው ግን በሀገር ቤት የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎቻችን ሰላማዊ ትግልን ከእስላማዊ ትግሉ ቢኮርጁ ማርክ የሚቀንስባቸው ማነው…! የምሬን እኮ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያለኝ አክብሮት ከፍ ያለ ነው፡፡ ተቃዋሚዎቻችን ሁልግዜም ያቺኑ ምርጫ ጠብቀው በአይሱዙ እና በሚኒባስ “ጃ ያስተሰርያል!” የምትለዋን ዘፈን እያዘፈኑ ምረጡን ብለው ሲቀሰቅሱ ስሰማ ደስ ለኛል፡፡ እርግጥ ነው ይሄ አዝናኝም አስደሳችም የሆነ ሰላማዊ ትግል ነው፡፡ ነገር ግን ዘጠና ሚሊዮን ለደረሰው ህዝብ እና ከዘጠና ሚሊዮን በላይ ለሆነው ጉስቁልናችን በቂ ትግል አይደለም፡፡
እና… እናማ ሰላማዊ ትግሉ እንደ እስላማዊ ትግሉ አይነት ነገር ይጨመርበት! ቢቻል ከዛም ተጨማሪ ነገር ጨመርመር ማድረግ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ተፈቀደም አልተፈቀደም ሰልፍ መውጣት፣ አደባባይ መዋል፣ ጩኸት ማሰማት እና ወዘተ መወዘት… ሰላማዊ ታጋይ የሚያስብለው ዋናው ሰላማዊ ሆኖ መገኘት ነው እንጂ የተፈቀደ ያልተፈቀደ እያሉ በትግል ላይ መሽኮርመም አግባብ አልመስልህ ብሎኛል! ምንም ማድረግ አይቻልም…
ከመሰለኝ እንግዲህ መተንፈስ ነው! ታፍኜ አልሞትም! (ተቃዋሚዎች ሰምታችኋል!)
የልጅነት ወዳጄ ሁሴን ከድር እንደነገረኝ “እስላም” የሚለው ስም ራሱ የመጣው ሰላም ከሚለው ነው፡፡ ሁሴን የነገረኝ ሀሰት እንደሌለው ያረጋገጥኩት፤ ያኔውኑ የእርሱን ሰላማዊነት ስመለከት ነበር፡፡ ሁሴን እጅግ ሰላማዊ ሙስሊም ወዳጃችን ነው!
እስላም ማለት ሰላም ማለት ነው… የሚለውን በደንብ ለማስረገጥ ከፈለጉ ደግሞ ከድፍን አንድ አመት ሞልቶ የፈሰሰውን ሰላማዊ ትግል አይቶ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህንን መረዳት ካልተቻለ የህክምና እርዳታ ያስፈልገናል ማለት ነው፡፡
ሁሌ ክበር የሚሉት አላህ ብርታቱን የሰጣቸው ሰላማዊ ሙስሊም ታጋዮች በተለያየ ጊዜ መንግስታችን ስም ማውጣት ብርቁ ስላልሆነ አንዴ አሸባሪ አንዴ አክራሪ ቢላቸውም እነርሱ ግን ከአመት በላይ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተሞላበት ፍፁም ሰላማዊ ትግል እያከናወኑ መንግስታችንን ኩም አድርገውታል፡፡
ችግሩ መንግስት “ኩም” ሲያደርጉት ምንም ሳይነካ እሪ… ብሎ እየጮኸ በድምሩ “እሪ… ኩም” እያለ ዘፈን አይሉት ልቅሶ ሲያሰማ ነገሩ እጅግ አስቂኝ ሆኖ ከርሟል፡፡ ይሄኔ እኛም “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል” የሚለው ተረት ስለተያዘብን እንደ አቅማችን አዲስ ተረት ተርተንለታል “መንግስታችን ራሱ በጥፊ ተማትቶ ራሱ ጯ! ብሎ ይጮሃል!”
ለማንኛውም ለመረጃ ያህል በዛሬው ጁምአ በመላው ሀገሪቱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለአላህ ተማፅኗቸውን ለመንግስት ደግሞ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ይቀጥላሉ! መንግስት የሚሰማ አይመስለንም ለራሱ ጮክ ብሎ እየጮኸ ስለሆነ ሌሎችን ለመስማት መቻሉን እንጃ…! አላህ ግን ይሰማል! መልሱም ያለው እርሱ ዘንድ ነው!
እኔ የምለው ግን በሀገር ቤት የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎቻችን ሰላማዊ ትግልን ከእስላማዊ ትግሉ ቢኮርጁ ማርክ የሚቀንስባቸው ማነው…! የምሬን እኮ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያለኝ አክብሮት ከፍ ያለ ነው፡፡ ተቃዋሚዎቻችን ሁልግዜም ያቺኑ ምርጫ ጠብቀው በአይሱዙ እና በሚኒባስ “ጃ ያስተሰርያል!” የምትለዋን ዘፈን እያዘፈኑ ምረጡን ብለው ሲቀሰቅሱ ስሰማ ደስ ለኛል፡፡ እርግጥ ነው ይሄ አዝናኝም አስደሳችም የሆነ ሰላማዊ ትግል ነው፡፡ ነገር ግን ዘጠና ሚሊዮን ለደረሰው ህዝብ እና ከዘጠና ሚሊዮን በላይ ለሆነው ጉስቁልናችን በቂ ትግል አይደለም፡፡
እና… እናማ ሰላማዊ ትግሉ እንደ እስላማዊ ትግሉ አይነት ነገር ይጨመርበት! ቢቻል ከዛም ተጨማሪ ነገር ጨመርመር ማድረግ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ተፈቀደም አልተፈቀደም ሰልፍ መውጣት፣ አደባባይ መዋል፣ ጩኸት ማሰማት እና ወዘተ መወዘት… ሰላማዊ ታጋይ የሚያስብለው ዋናው ሰላማዊ ሆኖ መገኘት ነው እንጂ የተፈቀደ ያልተፈቀደ እያሉ በትግል ላይ መሽኮርመም አግባብ አልመስልህ ብሎኛል! ምንም ማድረግ አይቻልም…
ከመሰለኝ እንግዲህ መተንፈስ ነው! ታፍኜ አልሞትም! (ተቃዋሚዎች ሰምታችኋል!)

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar