lørdag 9. mars 2013

አለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በኦስሎ ኖርዌይ ንግስት ሶኒያ በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተከብሮ ዋለ


በኦስሎ Folketeateret በተባለው አዳራሽ በኖርዌጅያን የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 12.00 በዓሉ የተጀመረ ሲሆን በዓሉንም አስመልክቶ የኖርዌይ ንግስት የሆኑት ሶንያ

Ethiopian women in Norwayሃራልሰን የእንኳን አደረሳችሁ የደስታ መግለጫ በማስተላለፍ በአሉን የከፈቱ ሲሆን በመቀጠልም የተለያዩ የሴቶች ማህበራትን ወክለው የመጡ እንግዶች እንዲሁም ትውልደ ፓኪስታኒ የሆነችው የባህል ሚንስትርዋ ሃዲያ ታጂክ ጨምሮ በየተራ ድርጅታቸውን በማስተዋወቅ ንግግር አድርገዋል። በየመሃሉም አስተማሪና አዝናኝ የሆኑ የሙዚቃና የዳንስ ዝግጅቶች ተካሂደዋል። በመጨረሻም የምሳ ግብዣ ተደርጎ የጠዋቱ ፕሮግራም በ14፡00 ሰዓት የተጠናቀቀ ሲሆን።
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ክፍልም በበአሉ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በአዳራሹ ውስጥ ለታደመው ታዳሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሴቶች የሰብአዊ መብት እረገጣና ጭቆናን የሚገልጹ የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችን በመበተንና መፈክሮችን በመያዝ በሀገራችን ውስጥ ባለው የመንግስት ብልሹ አስተዳደር ምክንያት ሴቶች ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ መሆኑንም አሳይተዋል።
በተጨማሪም ምሽት 18፡00 ላይ በነበረው የሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቀደም ብሎ በመገኘት የሻማ ማብራት ስነስርዓት የተደረገ ሲሆን በስነስርዓቱም ላይ በድርጅቱ የሴቶች ክፍል ሊቀመንበር ወ/ዘሮ ገነት የእንኳን አደረሳችሁ የመክፈቻ ንግግር ካሰሙ በኋላ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዳዊት መኮንን አጭር ንግግር አድርገዋል።
በመቀጠልም በወ/ሪት ሔለን ንጉሴ በዓሉን አስመልክቶ አለም አቀፍ ይዘቱንና ጠቀሜታውን በመግለጽ እንዲሁም በአገራችን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ከፍተኛ ችግር አንስተው ይህንን ችግር ለመፍታት በሀገራችን ውስጥ ያለውን ብልሹ አስተዳደር በማስወገድ ለዲሞክራሲና ለፍትህ እንዲሁም ለሴቶች እኩልነት ከሚታገሉ ድርጅቶች ጋር በመወገን መታገል እንዳለብን የገለፁ ሲሆን ወ/ሮ ሥርጉት ሰው መሳይ አራዊት የተሰኘ ሴቶች እህቶቻችን በአረብ ሀገር የሚደርስባቸውን ግፍ የሚገልጽ ግጥም አቅርብዋል።
በአጠቃላይ ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን በመግለጽ በፕሮግራሙ ላይ ከጎናችን ተገኝተው ድጋፋቸውን ለሰጡን ወንድሞቻችን ሁሉ ምስጋና አቀርባለሁ።
ድል ለኢትዩጵያ ሴቶች
ብርሃን ለኢትዮጵያ
መሰደድ ይብቃ
ሄለን ንጉሴ ከኖርዌይ
ማርች 8 2013

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar