torsdag 28. februar 2013

እንደ መጥምቀ ዮኋንስ መንገድ ጠራጊው፤ በሀገረ ብራስል በበልጄይም ከተማ አንዲህ ሲል ተደመጠ…

“የእኔ እናት ከብረት የተሰራች ናትን ወይንስ ….?”
የአምስተርዳም ኢሰአት 25.02.2012 ከአቀረበው ዕለታዊ ዘገባ
ከሥርጉተ ሥላሴ 26.02.2013
አናትዬ እንኳንም ተፈጠርክ።
ስንት ኪሎ እንደሚመዝን አላውቅም። ምን ያህል ጊዜ እንዳቆዬኝ ግን አውቃለሁ። ረጅም ነበር። ብቻዬን ቤቱ እስኪነቃናቅ ድረስ አደባለቁት። አዳራሽ ውስጥም ብሆንም እንደዚያው አነቃንቀው ነበር። ከልቤ የምሰቀው በዓመት አንድ ወይንም ሁለት ጊዜ ይሆናል። ማለት ሲዊዞችም አስተላልፈውብኝ ነው መሰል እነዛን ፈንጠርጣራ ጥርሶቼን ፈገግ- ፈርከክ አደርግና እንደ ነገሩ አስመርቅላሁ። ተዚያንላችሁ … ሳቄ እንደ ተናፈቀች እኔ እህታችሁ ፈትለክ … ዘወትር
እንዲህ  ዓይነት ናደው የሆነ ገጠመኝ ቀን ጀባ ሲለኝ ግን በቃ …. አለፈለት ነው ዓወደ ምህረቱ።  እስኪበቃው።  ቅቤ በትልቅ ጉርና ሲወጣ ጉርናው የታሰረበት ባለ እንጨቶች እና  ከውስጥ ያለውንም እርጎ እንደሚናጠው አካሌንም ሆነ አድባሩን  አደባልቀዋለሁ። አወና! ማን ጌታ  አለበኝ – በነፃነት ሀገር። የተሰደድኩት ይህ ለማግኘት አይደል።
እውነት ኢትዮጵያ ብሆን በእኛ ሳቅሽ ተብዬ አጋዚ እንዳሻው በፈነጨብኝ። የኢትዮጵያ ህዝብ የመተንፈሻ ባንቧው ኦክስጂን አስገብቶ ካርንቦንዳይኦክሳይድን የሚያሰወጣበት ሲመለከቱ እኮ የግድ ሆኖ እንጂ ተፈጥሮ እሱንም ከርችሞ ፈጥሮት ቢሆን ደስታውን ባልቻሉት – አረሞች።
ተሳህለነ! ህዝባችን ያን ሁሉ ሰቀቀን ችሎና ታግሶ ቆሞ ሲሄድ ቅናት ብጥልጥል ያደርጋቸዋል። ብሽቀት ይልጣቸዋል። ንዴት ይፍቃቸዋል። የእነሱ ዓላማና ተልዕኮ የወገናችን አካሉንም መንፈሱንም አላሽቆ ሽባና የተሽመደመደ ማደረግ ነው። ኢትዮጵውያን ጠንከረው፤ ኃይል ፈጥረው፤ ጉልበት አግኝተው ሲታዬ ወያኔ በሰቀቀን ይርመጠመጣል። ትልዕኮው እውኃ የበላው ቅል የሚያደርገው የኛ የጽናት አይበገሬነታችን ብቻ ነውና።
አሁን ወደ ነጥቤ፤ ሳልጀምረው ደከምኝ። እቴ ምን ሆኜ ነው? ሳቁ አደከመኝ። የእውነት ዕንባዬ እስኪወርድ ደረስ ነው … እንደአሻህ ያልኩት። ይህቺ የዛሬዋ ማምሻ ላይ ሳትታሰብ ከወደ ብራስልስ ዱብ ያለችው ልዩ ሳቄ የእውነትልዩ ሽልማት ናት። እግዚአብሄር ይስጥልኝ ብያለሁ መንገድ ደልዳዩን። ለሰጪ ይስጠው። ለንፉግም ልብ ይስጠው ብያለሁ። በእውነት ፍጹም ከሆነው ንጹህ ልቤ የፈለቀች ነበርች፤  እንደ ወትሮው ከነዛ ዘርዛሮቼ ላይ ተንጠልጥላ የቀረች ለምስል አልነበረችም። … ሥርጉተ ትሙት። የምር … እንመራማር።
አዬ ታማኝ ሆዴ! ዛሬ ብታዬኝ በዚህ ቀፋፊ ብርድ፤ ዝናቡ ወጀቡ፤ እጅግ ቀዝቃዛ አዘል ውርጩ … በዚህ ላይ ደግሞ የማያበራው የወገን ሮሮ፤ ምሬትና ሰቀቀን ቁፍ ያለች ዶሮ አስመስሎኝ ሲያባትለኝ ውሎ እንዳያድር አምላክ አንተን ፈጠረና ዕድሜ ላንተ። አልኩልሃ እኔ እህትህ። … በዚህ ደመመን በተጫነው፤ ጭንቅ በሚጠራ ማዕልት  … ዕንባዬ እስኪ ወርድ ድረስ …. ብቻዬን አስከናካሁት።
የሰበዕዊው ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በዬን ከኛም መጥቶ በነበረ ጊዜ የስላይዱ አቀማማጥ አልጥመው ብሎ „ እኛ አንሻፈነው ወያኔ አንሻፎ“ ብሎን ነበር … ያን ጊዜ እንደ ምልክት የምተቆጠር ጥሪት ቆጥሬ ነበር፤ ዛሬ ወጣልኝ እላችኋለሁ – ውዶቼ።
የማከብራችሁ …. አዎን የእኔ ነገር እኮ ገደብ ካልተሰራለት እንደ አባይ ወንዝ ሲሄዱ ማደር ነው። እሷ አይደከምታ፤ ሰውም ይደክመዋል የማትል ይሉኝታ ቢስ ሞገደኛ ናት። እስኪ ዛሬስ ወግ ይድረሰኝ መሰል በፈረንጅኛው ቋንቋ ቅብጥና ቅልጥ ልብልበታ!  አሃ! ፓርትነሬ -  እሜቴ ብዕሬ። ይዛኝ ሳትከነፍ እርካቡን ጠበቅ አድርጌ ያዝኩና ተግ አሰኛኋት። መጪ ልትል …. ለዛውም እኮ ከዛ የሥነ ምግባር ጠርዝ ጋር ከሆነው …. ከእእእ ሚስጢር ፍርኃት ጋራ …. አይደረግም ብዬ …. በደሜ ቅመም ገታኋት – ዋዘኛ!
እውነትህን ነው ወንድሜ የአንተ ወላጅ እናት የወያኔ ማዕከላዊ ኮሚቴም አባል አይደሉም። ከብረትም አልተሰሩም። እንደ እኛ ሰው ናቸው። ግን ከጣይቱ የወረሱት አለ። ባለቤታቸውም አምላካችን ከቅዱሳኑ ጎን ያሳርፋቸው፤  አፈሩ ይቅለላቸውና እውቅ አርበኛ ነበሩ። ዕድለኛም ናቸው። ባለቤታቸው አርበኛ ልጃቸውም አርበኛ። ሲታደሉትና ሲቀቡት የሚገኝ የፈጣሪ አምላክ ሽልማት ይሉኃል ይህ ነው።
ወንድሜዋ ስታድግ ዬልጅነት ጊዜህ እየተቧከስክ አስቸግረህ ነበር ይባላል። አሁን ደግሞ ካስካቸው። የተመረጥክበት የዕንባ ጥሪ አንባሳደርነት ቢያኮራቸው እንጂ አንገታቸውን የማያሰደፋቸው መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁታል። የቀደሙት ፍርኃትን ሳያውቁት ነው የተላለፉት። ደፋሮች ነበሩ። ጀግኖች ነበሩ …. አይደለም የሰው ልጅ ሳር ቅጠሉ፤ ዱር ገደሉ ጠረኑ የኢትዮጵያ ድፈረት ነበር። አዬሩም ያልተበከ ንፁህ።
ተሳህለነ! እኛ በሰላም ሀገር ተቀምጠን ስለምን እንደምንርበተበት እኔም አይገባኝም። ወንድም፤ እህት፤ ወላጅ ማመኃኛ ነው እንጂ እኛ ተሰልበናል። አንተም እንዳልከው „የለንም ሙተናል። ሥጋችን ቀጥ አድርጎ እንዲቆም የተፈጠረው አጥንታችን ወጥቶ ሥጋ ቀር ስለሆን ተልፈስፍሰናል“ አልክ። እውነት ነው። ይጋባል – ያሰኛልም ብለናል። ውጪ ሀገር  የአጋዚ ጦር ሰራዊት አንድ ሻለቃ ጦር በዬአህጉሩ ቢቀመጥ እኛን ያዬ ሰው። ድብዛችን ባልተገኘ።  እግሬን አውጪኝ ነው …. አይደል?! የብቂላ ዘሮች አይደለን እንሸመጥጠው …..
እግዚኦ! የኛ ስልብነት እኮ ብዙ ነው። የኢትዮጵያዊነት ጥያቄ ውጪ ሀገር ተቀምጠን እያስቀረነው ነው። የአውራጃም የወረዳም እንዲሁ። በጣም ወርደን አጥቢያ እያሰኘን ነው … አሁን ደግሞ ወያኔ የሰራለትን ቀመር ያውቃል። አዲስ ስልት  ፈልጓል። ያው የሄሮድስ የሙት መንፈስ በአጥቢያ ብሎ ዓውጆልን የለ። እኛ አዎን እኛ አብረን ቁልቁል ወረድ ነዋ።  አስር ፍርፈሪ ስለምን እንደሚያሰኘኝ አይገባኝ —– ም።  ወያኔከጎሳ የስለላ ተግባሩ ሰርቶለታል። ብዙም አትርፎበታል። የአሁን ደግሞ በጎጥ  እዬሰለሰለን ነው። ምንጠራ የአኃታዊነት።  እያችሁት ጨዋታ …. እህ! ሳናውቀው ቀጥ ብለን ከወያኔ የምኞት ጓዳ መቀርቀር።  አይጣል? ስለምን ከመነሻ ጣቢያችን ላይ አይደለነም ያለነው። ዓለምን ከፈጠረ ሚስጢር አፈንግጠናል።
… ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏት የሥነ -ልቦና ባለሙያዎች እስከ 1997 ድረስ ከ10 የማይበልጡ እንደነበሩ አውቃለሁ። አሁን ምን ያህል እንደ ጨመረ አላውቅም። ብቻ የወያኔ ትልቁ የማጥቂያ መሳሪያ ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት፤ ማሟሟት፤ እንዲሟሽ ማደረግ ነው። ይህ በከፍተኛ መዋለ ንዋይ ያነቀሳቀሰው ፕሮጀክቱ ነበር። ሰፊ የሰው ኃይልም መድቦበታል መቼም አብዛኛው የጹሑፌ ታዳሚዎች „ብርቱ ሚስጢር“ በሚል ውጪ ሀገር የምነገኘውን ልክ ሀገር ቤት እንዳሉ ወገኖቻችን ደጃችን፤ አውዳችን፤ አልጋ ስራችን ሳይቀር ፍርኃት፤ ስጋት እንደዲነግስበት ማደረግ። ጉሩባችን ለማናቅ ያደረገው ሴራ በተወሰነ ደረጃ ሰርቷል ማለት ይችላል።
ሀገር ቤትማ አብዛኛው ሰው የሥነ -ልቦና ህመም ተጠቂ እንደሚሆን አያጠራጥርም። ያለን ባለሙያ ደግሞ ኢሚንት ነው …. ጭንቀት በሽታ እራሱ በቁም የሚቀብር ነው። ይህም አልበቃውም ወያኔ በሞፈር ዘመት ባህር አቋርጦ እየገዘገዘን ነው። እኛም አረገረግንለት፤ አስረገደን /// „ከደደቢት የወጡ ሰባት ሰዎች“ አለ ታማኝ። ኢትዮጵያ አልበቃ ብሏቸው አውሮፓ፤ አሜሪካ፤ ካናዳ ወዘተ …. ሚሊዮን ለኢሚንት … ሬሾውን እናውጣው ብንል ከቁጥር በታች ነው የሚሆነው .00000000001 ምናንም
የዚህ ጥቃት ማገዶ የምንሆንበት ምክንያት ደግሞ ኢትዮጵያዊነት በሸሸነው፤ በራቅነው፤ ባገለልነው ቁጥር   ከባዕታችን ነገረ – ሚስጢር እቅፍ እንወጣለን። ወንድሜ ታማኝ ያነሳው ነጥብ ከእቅፏ የመውጣተቻን አስኳለ ሚስጢር ነው የተረጎመልን። ኢትዮጵያዊነት ከተቀመመባቸው፤ ከተቀመቀመባቸው፤ ከተጠለፈባቸው መንፈሳዊ ሥነ -ሃብታት አንዱ ድፈረት ነበር። የጀግንነታችን፤ የአርበኝነታችን፤ የአትንኩይ ባይነታችን ትኩስ ትንታግ ደም፤  ለአፈራችን ቀናዕይ፤ ለመሬታችን ቁጡና እልህኛ የነበር ነው አኮ ማዕቀፉ ኢትዮጵያዊነት ስለነበር ነው። …. አሁን ከዛ ወንበር ወረድ ብለን መንደርን፤ ጎጥን ስናሰላ ያ …  ሰማያዊ ተፈጥሯዊ ቅመምና ጸጋ ይተናል፤ ይበናል፤ ይሰደዳል።
አርቲስት ታማኝ… አሁን አሜሪካ፤ አውሮፓ፤ አውስትራልያ፤ ካናዳ ያለውን ሰው ከቶ ምኑ ነው እንዲህ የሚያንዘፈዝፈው ብለህ ስታሰላው ሌላ ምንም ነገር አይደለም። ከኢትዮጵያዊነቱ ማዕቀፍ ውስጥ ስለወጣ። ማንነቱን እራሱ በራሱ ገልቦ – ግልብ ስላደረገው። ያን ተፈሪ ገጽ ውኃ ሲሄድበት የዋለ አለት ስላደረገው፤  ከውስጡ ጋር በፈቃዱ ስለተፋታ ብቻ ነው።
ወንዶቹንማ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ እነ ጋዜጣኛ ርዕዮትዓለሙ፤ እነ አቶ አንዱዓለም አራጌ፤ እነ አቡበከር፤  እኮ ከዛም ሆነው እያፋጠጡ ይሞግቱታል። ለማስታረቅ የሄዱትን አይደል አንበሲት „እኔን የመጠዬቅ ብቃት የለዎትም“ ብላ በተግሳጽ አሳፍረና አዋርዳ ነው የመለሰች። ሄሮድስ ሲሞቱም ተመሳሳይ ሁኔታ ነበር የፈጸመቸው። እንግዲህ በበለኃሰቦች የተያዘች ነፍስ ይህን ያህል ድፈረት አላት።
ሙቀቷ ያለው የሚንቀለቀለው ማንነት ያለው ከብሩህ ራዕዮዋና ከኢትዮጵያዊነቷ ነውና!። ሌላው የ21ኛው ምዕተ ዓመት ነብይም አበበ ገላው የዓለም መሪዎች በተገኙበት በዛ ታላቅ ዓለም-ዓቀፍ ጉባዔ ላይ በድፍረት ፊት ለፊት ወጥቶ ለ80 ሚሊዮን ህዝብ ዕንባ ሲል ቤተሰቡንም እሱንም እንደ አዛርያ፤ አናንያና ሚሳኤል ለእሳት አሳልፎ ሲሰጥ በሙሉ ልብ፤ በግርማ ሞገስ፤ ነበር ሞትን ለማስተናገድ የፈቀደው …  የቀረጠው… ታዲያ እኛ የነዚህ ደም ዘር … ቤተኛ ወይንስ…
ትናንትን ከረንት ላይ ተለጥፎ ያዳመጥኩት ነገርም ነበር። አቶ ግርማ ሰይፉ ከወያኔ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እናት ትውለድ፤ ወላድ በድባብ ትሂድ ያሰኛል። … እኛ ደግሞ ውጪ ሆነን ላብ በላብ። … እፍረቱ ያርመጠምጣል፤ ይነህርራል፤ ውረዴቱ የጋማ ከብት በሽታ ታውቁታላችሁ? እንደ ከርክርና ጎርምድ ነው። ለሰባት ሰው ሚሊዮን ማርገድ፤ ሰጥ ለጥ ብሎ፤ አቤት ወዴት ብሎ በስደቱም ሀገር መንዘፍዘፍ….
እናንተዬ ይህ የጤና ይመስላችኋልን? ወያኔ እኮ ሲገባ አህያ እዬገደለ ነበር የገባው። ያ አዚም ይሆን? እንጃ እንደ እኔ ውጪ ሀገር ሆኖ ለፍርሃት የሚያሸበሽብ ድውይ ባይፈጠር ይሻለዋል።
እንዲያው እኔ ገርሞኛል። ትናንትና የኖርወይን የተግባር ክንውን እያዬሁ
ኢሰአት ፍርሃትን ገደለ
ድፈረትን ወለደ። ስል ነበር። ስለምን? በግንቦት ሰባት ህዝባዊ ብሄራዊ ስበሰባዎች ፎቶ ካሜራ ቪዲዮ የሚቀረጸው ከጀርባ ነበር። ያው ለታዳሚው ተብሎ። በኢሰአት ግን እንዲያውም ሁሉም ታዳሚ ለካሜራ እራሳቸውን ሲያመቻቹ ነበር ያዬሁት። ደንቆኛል። ገርሞኛል። ትናንትና አንድ መጣጥፍ ፃፍኩና ሳላርመው ተኛሁ። ዛሬም በሌላ ነገር ተጠምጄ ዋልኩ። አሁን ደግሞ አዲስ ገጠመኝ – በለጠብኝምና እዬሳቁሁ ጀመርኩት …. እንጂ አንድ ብዬ ነበር፤
እስኪ በሥርጉተ ሞት የኖርዎይን ደግማችሁ ተመልከቱት። …. እና እኔ እንደማስበው ወያኔ ሰፊ በጀት መድቦ፤ መጠነ ሰፊ ኃይልም አሰልፎ ሲያቅራራ የነበረበትን የውጭ ሀገር ኢትዮጵያውያንን ወኔ የመስለብ ተልዕኮ ኢሰአት ሰብሮታል ብላችሁ ከእኔ መንፈስ ጋር ትስማሙ ይሆናል። ማን ያውቃል? ነገም ሌላ ቀን ነውና የተበተነው ኃይል ተሰባስቦ ዝብርቁና ቅይጡ ፍላጎት ተገርቶና መስመር ይዞ — የድል አውጅም ቅርብ ይሆናል። ለማንኛውም በሁሉም ቦታ ማለት በአውሮፓ፤ በአውስትራሊያ፤ ባካናዳ፤ በኖይዝላንድና በደቡብ አፍሪካ እኔ የተገነዘብኩት ፍርኃት እዬተርገበገበ መሆኑን ነው። በመክሰምና … በመንገደጋድ መሃል … እንዳለ ይሰማኛል። የእናንተን እንጃ! ….
ሁሉንም ስበሰባዎች ሥራዬ ብዬ ተከታትያቸዋለሁ። አንደም ሰው ሲሸማቀቅ አላዬሁም። እንዲያውም ፎቶ ለመነሳት አብሮ ለመጨፈር ሽሚያ ነው ያዬሁት። በአብዛኖቹ ቦታዎች በትግል ልምዳቸው፤ በአደረጉት ከፍተኛ አስተዋፆ የተመረጡት ወገኖችም በድፈረት ነበር የተመደበላቸውን የድርሻቸውን  መድረክ ላይ ወጥተው ሲናገሩ ያዬሁት።
እና መንገድ ጠራጊው እንደ መጥምቀ – መቼም ሁሉ ነገር በወያኔ ስለምናላክክ እንጂ በነጭ ሀገር እኛ የራሳችን ጌታ ነበርን። እኛ ከቻልን አቅሙ ከኖረን ዓመቱን ሙሉ፤ ቀንና ሌሊቱን ብንሰበሰብ፤ ብንደራጅ ማን ከልካይ አለብን? ማንም። አሳዛኙ ገጠመኝ ሀገር ቤት አልበቃ ብሎ ፍርኃትን በነጭ ሀገር በገንዘባችን ገዝተን አሽኮኮ አድርገን እንዳሻህ ማለታችን ነው። የሽብርተኛ ህጉ እኮ ከውጪ ሀገር ለተቀመጠ ሁሉ እዬመጣ እያንኳኳ እጃችን አንጠልጥሎ የሚወስደን ያህል ነው እያረገድንለት ያለነው።  በሰላም ሀገር ለወያኔ አፋኝ ህጎች፤ ጎሳዊ ደንብና አፈጻጻሞች ፈቅድን ሰጥ – ለበጥ ብለን እንገዛለን። መብትና ነፃነታችን እንዳወጣ ገብያ ላይ እንቸበችበዋለን። ረመጥ!
ይህ መቼም ብንነት፤ ጤና ማጣት ነው እንጂ የሌሎች ሀገር ህዝቦች መስዋዕትነት ከፍለው ባገኙት የነፃነት ቦታና ሀገር ተቀምጠን ንዳድ እንደያዘው መንደፍደፍ አሳፈሪ ነው። ትውልዱን አንገት ያስደፋል። በሌላ በኩል ጋብቻ ላይ የምንወስደው አቋምም ተጽዕኖ የሚያደርግ ይመስለኛል። ተው! ጊዜ ለእኔ ብቻ! ፖለቲካን ሌሎች ይሰሩት፤ አንተ ልጆችህን አሳድግ ከምትል ጋር መኖርም አለ፤ በጣም በጣት የሚቀጠሩ እህቶች እንዲያው ዘንቦ ተባርቆ ከተገኙም ወንዱ፤ ትዳርሽን፤ ሀገር ቤት – የጀማመርነውን እረሳሽውን? አርፈሽ ተቀመጪ ወዘት በማለት መቅኖ ሊያፈስ የሚችልም ይገጥማል።
የሆነ ሆኖ ግን ነፃነት ከሌላ እንጃ ኑሮ እራሱ መራራ ነው። ስንት ዘመን በሰው ሀገር? ነገ እንደ ፍልስጤም ህዝብ፤ እንደ ኩርዱሾችም የብትን አፈር ለማኞች ከመሆን ዛሬ ጠበቅ ብሎ መታገል ያስፈልጋል። ደግሞስ ውጪ ሀገር የሎቢ ተግባር ቢፈጸምበት እንጂ የትኛው ጦር ግንባር ሲኬድ ነው ….
እሳት ላይ ተቀምጠው እንኳን እነ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሽሽትን አልመረጡም። „ሀገሬን ጥዬ አልሰደድም“ ብሎ ይሄው በቀላጤ ነፍሱን እያጠፉት ይገኛሉ። ሶስት ልጆቿን ብትን አድረጋ እስር ቤት የምትማቅቀው የነፃነት ቀንዲልስ … እና እኛ የምንችለውን ለማደረግ አለመቻል … ግፍ ነው።  …. በሰላም ሀገር ለፍርኃት እጅ መስጠትም የቁም በድንነት ነው። ያነን ታቅፋ የምትኛ እህትም … እናጃ ምኑ ሊሞቃት … ልዝ …
በል መንገድ ደልዳዩ፤ ትንሳዬ ደርሳለችና ተሰባሰቡ እራሳችሁን ፈታትሹ እያልከን አይደል? አይዞህ ከራሳችን ጋር ታርቀን መንገዳችን አውቀን ፍቱን ለማላት ዛሬ ብለናል!
እንደ መቋጫ …. እናንተዬ አንድ ነገር አልናፈቃችሁም። የመንገድ ደልዳዩ የጉዞ ማሳረጊያ ቦታ። ለእርገት የተመረጠ ቅዱስ ሥፍራ …. እኔማ የናፈቀኝ የፍራንክፈርት አማይን ነው። ማስታወቂያው ነስፍ ያለው ነበር። አስደስቶኛል። አሁን የቀረኝ ሁሉንም ቦታ በድርጊት ረቶ የመጀመሪያውን የሀገረ ጀርመን የኢሰአት ስትዲዮ እስከ መክፈት የሚያደርስ እርምጃ እጠብቃለሁ። እና ደግሞ የትናቶችም የነፃነት ትግሉ አባወራዎች፤ የዛሬዎችም ወጣት ትንታጎች ከመጥምቀ ጋር – ጥምቀት ላይ በድል ብያለሁ!
ልብንትን የረታ ድፈረት አጠን እንደ ገና እንውለድ!
ድል ካለ ልበ ሙነት የህም እንጀራ ነው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar