torsdag 31. juli 2014

የተደራጁ ወንበዴዎች ለመፍጠር እየፈለጉ ያሉትን ብዥታ ለማጥራት (ዳንኤል ተፈራ)

ከዳንኤል ተፈራ
daniel tefera
(ዳንኤል ተፈራ
ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በጣም ወሳኝ የሆነ ስራ ሲሰራ ነበር፡፡ እሱም ውህደት ነው፡፡ የአንድነት/መኢአድ ውህደት ወሳኝና መሰረታዊ ድርድሮችን አልፎ የቅድመ ውህደት ፊርማው ከተቀመጠም ከወር በላይ ሆነው፡፡ከፊርማው በኋላ ውህደት አመቻች ኮሚቴ ተዋቅሮ በአጭር ጊዜ ነገሮችን መልክ ለማስያስ የቻለ ሲሆን ውህደቱም የሁለቱ መስራች የጉባዔ አባላት በተገኙበት ነሐሴ 3 እና 4 ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ታዲያ ከመስራች ጉባዔው አስቀድሞ ሁለቱ ፓርቲዎች በተናጠል ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት የውህዱን ፓርቲ ደንብና ፕሮግራም፤ ለውድድር የሚቀርብ እጩ ፕሬዘዳንት መምረጥ፣ አዲስ ስያሜ በመጠቆም እንዲሁም ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎችን በመስራት ይጠናቀቃል፡፡ በነገራችን ላይ የተናጠሉ ጉባዔ ስራውን የሚጀምረው አዲሱን የጋራ ደንብ በማፅደቅ ይሆናል፡፡ አጠቃላይ ውህደቱን ተቀበለው የሚባለው ደንብና ፕሮግራሙን ሲያፀድቅ ይሆናል፡፡
በአንድነት ፓርቲ በኩል በምክር ቤት ደረጃና በተለያዩ መዋቅሮቹ የሀሳብ ክርክር ማድረግ የተለመደ እንጅ ብርቅ አይደለም፡፡ የሃሳብ ክርክር ሲደረግ ‹‹ተባሉ፣ ምናምን›› እያሉ የሚጮሁት ከክርክሩ ትርፍ ለመሸመት የተሰለፉ ባእድ ሃይሎች እንጅ አንድነቶች አይደሉም፡፡ ነገዳቸው የሃሳብ ክርክር ከማውቀው ጎራ ስለሆነ የአንድነት አባላት የሃሳብ ፍጭት ሲያደርጉ ይደነግጣሉ፡፡ በአንድነት በኩል እጩ ፕሬዘዳንቶችን አስመልክቶም የተለመደው ክርክር ተደርጎ፤ እጩ ፕሬዘዳንቶቹ ወደ ጠቅላላ ጉባዔ ሄደው ከሦስቱ አንዱ እንዲመረጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በድምፅ ተወሰነ፡፡ የቀረቡት እጩ ፕሬዘዳንቶች ከታወቁ በኋላም ደጋፊዎቻቸው እከሌ ቢመረጥ ይሻላል የሚል ሀሳብ የማቅረብ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ እኔም እከሌ ቢመረጥ ፖለቲካውን የተሻለ ያንቀሳቅሰዋል የሚል መብት አለኝ፡፡ ይህንን መብት የሰጠኝ ማንም ሳይሆን አንድነት ነው፡፡
ሀቁ ይሄ ቢሆንም የአንድነት ወገን ያልሆኑ ስማቸውን የደበቁ ወሮበላ ተላላኪዎች ሶሻል ሚዲያውን በመጠቀም የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ ለማስፈፀም መንፈራገጣቸው አልቀረም፡፡ ዘመቻ ከተከፈተባቸው መካከል ደግሞ አንዱ እኔ መሆኔ ፈገግ ያሰኘኛል፡፡ ብዥታውን ማጥራት ያስፈለገኝም ለምን ስሜ ተጠቀሰ ብየ ሳይሆን የሀሰት ዘመቻውን አንድምታና ከየት አቅጣጫ እንደተሰነዘረ ለመጠቆም ነው፡፡ ዘመቻው የውሸት ስሞችን በመጠቀምና ማስጃ አልባ የተቀነባበሩ ስድቦችን በማዥጎድጎድ ብዥታ መፍጠር ነው፡፡ በተለይም ስርዓቱ ምንደኛ የሆኑ ተላላኪ ግለሰቦች ‹‹አሉላ እንደገና፣ ሰለሞን ሳልሳዊ፣ የፍቅር ቃልና አፄ ልብነድንግል›› የሚሉ የተልኮ ስሞችን በመጠቀም ውህደቱ ከመደረጉ በፊት ክፍፍል ለመፍጠር ኢህአዴጋዊ ተልዕኮ ተሰጥቷዋቸው እየባዘኑ ይገኛሉ፡፡ አንድነት አበቃለት እያሉ ስማቸውን ደብቀው እንደተራበ ቁራ ያንቋርራሉ፡፡ እነዚህን ከሙታን የሚለያቸው በድን ተንቀሳቃሽ መሆናቸው ነው፡፡ ህሊናቸውን የሸጡ ርካሽ ፍጡራን ናቸው፡፡
ዋናው ቁምነገር ዘመቻው ለምን ተከፈተ የሚለው ነው፡፡ የሚጠበቅም ነበር፡፡ ዘመቻው በተለይም በእኔና ጓዶቼ ላይ የተከፈተው ስለለውጥ፤ የተቃዋሚ ጎራውን የማይናድ መሰረት ስለማስያዝና የተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ስለተናገርን ብቻ ነው፡፡ ስለሰራን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ መስራትን ደግሞ የአንድነት ልጆች ይደግፉታል እንጂ አይቃወሙትም፡፡ የሚቃወመው ሃይል ‹‹ተቃዋሚው ማንሰራራት የለበትም፤ እግር ማውጣት የለበትም›› ብሎ የሚያምነው ኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ የስም ማጥፋት ዘመቻው በቀጣይ አመት የሚካሄደው ምርጫ ላይ የሚኖረንን ተሳትፎና ትግል አጋጣሚውን ተጠቅሞ የመምታት ነው፡፡ እነዚህ ከላይ የተቀስኳቸው የሀሰት ስም ተጠቃሚ ባንዳዎች ሀብታሙ አያሌው ላይ ተመሳሳይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተው ነበር፡፡ ስም በማጥፋት እንደማይበገር ሲያውቁ አሰሩት፡፡
አንድነት ካቀረባቸው ሦስት ጠንካራ እጩዎች መካከል የጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊው አንዱን ይመርጣል፡፡ ዋናው የሂደቱ ዴሞክራሲያዊ መሆን ነው፡፡ ኢንጅነር ግዛቸውና አቶ ትዕግስቱ ለአንድነት እዚህ መድረስ ያደረጉት ትልቅ አስተዋፅኦና የከፈሉት ዋጋ ሳይዘነጋ ነገር ግን አሁንም የእኔ እምነትና ፍላጎት ሀቅን መካድ ስለማይቻል ለአንድነት ፓርቲ አሁን ያለበት ከፍታ ላይ መድረስ በላይ ፈቃዱ ዋናው ስለሆነ፤ ትግሉን ወደ ህዝቡ ለማውረድና ከቢሮ ለማውጣት በነበረው ትንቅንቅ ላይ እውቀቱን፣ ገንዘቡንና ጊዜውን ያለ ምንም ስስት ሲሰጥ ስላስተዋልኩ፤ በላይ ፍቃዱ የሚታወቀው ሀሳብ በማመንጨትና ያ ሀሳብም ተግባራዊ እንዲሆን ሳይደክም በመስራት ስለሆነ፤ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› የሚለው ወሳኝ ህዝባዊ ንቅናቄ ስያሜ በበላይ በኩል የቀረበ እንደነበር ስለማውቅ እንዲሁም በላይ ፈቃዱ ፓርቲያችን የማተሚያ ማሽን ሊኖረው ይገባል የሚል ሃሳብ በማቅረብና በመተግበር ውጤት ያሳየም በመሆኑና በአጠቃላይ የጀርባ ሞተር ሆኖ የቆየ ውድ የአንድነት ልጅ ነው ብየ ስለማምን ለበላይ ድጋፌን እሰጣለሁ፡፡
ታዲያ ይህ ግልፅ እምነቴ በድብቅ ስሞች ስም ለማጉደፍ በሚሯሯጡ በገዥው ፓርቲ ምልምሎች በኩል የተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲከፈትብኝ አድርጓል፡፡ ልብ በሉ ‹‹ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው›› ነውና በወሬኞች ላለመፈታት እንጠንቀቅ፡፡ ስም አጥፊዎቹ የአንድነት ልጆች ቢሆኑ ኖሮ እንደዘረዘሩት የሀሰት ውንጀላ አንድ ቀን አናድርም ነበር፡፡ የውሸት ስም መጠቀም ሳያስፈልጋቸው ቢፈልጉ ፕሬዘዳንቱ ጋ አሊያም የምክር ቤት ሰብሳቢው ጋ በማምጣት ባቀረቡ ነበር፡፡ አድናቆቴ ከፍ ይል የነበረውም ይህንን ማድረግ ቢችሉ ነበር፡፡ አሁንም እስከነፃነት ትግሉን እንቀጥላለን፡፡

ፖለቲካና ግለሰብ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
Prof. Mesfin
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ለእኔ ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ እንደውሃና ዘይት የማይደባለቁ ነገሮች ይመስሉኛል፤ አጼ ምኒልክ ‹‹አመልህን በጉያህ›› ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ዘይትና ውሀ በባሕርያቸው የሚለዩትን ያህል ፖሊቲካና ግለሰብም የባሕርይ ልዩነት አላቸው ማለት ነው፤ የወያኔ መሪዎች ምንም ነገር የማይሰምርላቸው፣ ከመጀመሪያውኑ እነዚህን ሁለት የማይደባለቁ ባሕርዮች አደባልቀው በመንሣታቸው ነው፤ ፖሊቲካ ለማኅበረሰቡ መቆርቆር ነው፤ ለሕዝቡ መቆርቆር ነው፤ ለአገር መቆርቆር ነው፤ የፖሊቲካ መነሻም ይኸው መሆን አለበት፤ ዓላማውም የማኅበረሰቡ፣ የሕዝቡ ልማት እንጂ ጥፋት አይደለም፤ የነበረውንና ያለውን ማጥፋት የፖሊቲካ ዓላማ ሊሆን አይችልም።
የደርግ መንደር ምሥረታ የሕዝብ ዓላማ ነበረው፤ የዓላማው መሣሪያ ግን የሕዝብ ሳይሆን ወታደራዊ ጉልበት ነበር፤ በዚህም ምክንያት የሕዝብ ዓላማ ያለው ሥራ የሕዝብን ህልውና በሚፈታተን የጉልበት መንገድ መከተሉ ዓላማው እንዳይሳካ፣ ሕዝብና አገዛዙ ባላንጣዎች ሆኑ፤ ጥሩው ዓላማ በከሸፈ ጉልበተኛነት ሳይሳካ ቀረ፤ በመንደር ምሥረታው ዓላማ ደርግ ክፋት ወይም ቂም ቋጥሮ አልተነሣም፤ ስሕተቱ ከውትድርና ባሕርይ የመጣ ይመስለኛል፤
ማጥፋት ዓላማ ሲሆንና ጉልበት የማጥፋት መሣሪያ ሲሆን ፍጹም የተለየ ነው፤ማጥፋት የሚመጣው ከግል ጠብና ከግል ቂም ነው፤ የራሱን ወይም የአባቱን፣ ወይም የእናቱን ቂም በልቡ ቋጥሮ ፖሊቲካ ውስጥ የሚገባ ሰው ለጥፋት የተዘጋጀ ነው፤ ለጥፋት የተዘጋጀ ሰው ፖሊቲካ ውስጥ ሲገባ እሳት አደጋ መኪና ላይ ቆሞ ቤት እንደሚያቃጥል ሰው ነው፤ አታላይ ነው፤ ዓላማውንም የዓላማውንም መሣሪያ አያውቅም፤ የሚንቀሳቀሰው በጥላቻና በቂም ነው፤ ወይ የሕጻን ልጅ ወይም የተስፋ-ቢስ ደደብ ጠባይ ነው፤ እንዲህ ያለ ሰው ፖሊቲካ ውስጥ የሚገባውም በዚሁ በደደብነቱ ምክንያት ነው፤ የደደቡ ፖሊቲከኛ ሥራ የማያስወቅሰው ፖሊቲከኛውን ብቻ አይደለም፤ በዚያ ፖሊቲከኛ የሚመራው ሰው ሁሉ አብሮ የሚወቀስ ነው፤ እንዲያውም በፖሊቲከኛው እውቀትና ችሎታ ማጣት የተነሣ የሚደርሰው ስቃዩና መከራው፣ ችግሩና አበሳው በዚህ ዓይነቱ ፖሊቲከኛ ላይ አይደርስም፤ ሰቃዩንና መከራውን፣ ችጋሩንና አበሳውን የሚጋፈጠው በዚህ ዓይነቱ ፖሊቲከኛ የሚመራው ሕዝብ ነው፤ ሕዝብ መሪውን በትክክል መምረጥ ያለበትም ለዚህ ነው፤ ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ የሚባለው ይደርሳል።
ዛሬ እያጎረሰ ምረጠኝ የሚለው ነገ ቆዳህን ልግፈፍ ይላል፤ እንደምንሰማው ወደቦሌ አካባቢ ‹መቀሌ› የሚባል የሰማይ-ጠቀስ ፎቆች መንደር አለ ይባላል፤ የዚህ መንደር ባለቤቶች የወያኔ ባለሥልጣኖች ለመጦሪያቸው የሠሩአቸው ናቸው ይባላል! በአንጻሩ እኔ የማውቀው አንድ ወያኔ አለ፤ በውጊያ ላይ በደረሰበት ጉዳት ይመስለኛል አንድ ዓይኑን ክፉኛ የታመመ ነው፤ ስለሚሸፍነው የጉዳቱን መጠን ባላውቅም ጉዳቱ ይሰማኛል፤ ሚስትና ሁለት ልጆች አሉት፤ ሚስቱ ጠዋት በጀርባዋ ከባድ ነገር አዝላ ልጆቿን ወደተማሪ ቤት ታደርሳለች፤ እንደምገምተው አንድ ቦታ ገበያ ዘርግታ የምትሸጠውን ትሸጣለች፤ ወደማታም እንደጠዋቱ ተጭና ወደቤትዋ ከልጆችዋ ጋር ትመለሳለች፤ የዚህ አንድ ጉዳተኛ ወያኔ ቤተሰብና የባለሰማይ-ጠቀስ ሕንጻ ባለቤቶች የሆኑት ወያኔዎች ኑሮ የሰማይና የመሬት ያህል የተራራቀ ነው፤ ለአንድ ዓላማ አብረው የተነሡ ሰዎች በሃያ ዓመታት ውስጥ ይህንን ያህል መራራቃቸው በጣም ያሳዝናል ብሎ ማለፉ አይበቃም፤ ደሀው ወያኔ ሕመሙንና ስቃዩን የምገነዘብበት መንገድ ባይኖረኝም አንድ ዓይኑን ማጣቱ ብቻ ጉዳቱን ያሳየኛል፤ እንግዲህ ባለሰማይ-ጠቀስ ወያኔዎችና ይህ ደሀ ወያኔ በጦርነት ላይ ያደረጉት አስተዋጽኦ በጉዳታቸው ቢመዘን የዚህ ደሀ ወያኔ እንደሚበልጥ አልጠራጠርም፤ ቢያንስ እንደአንዳንድ መሪዎቹ አልሸሸም፤ ታዲያ በምን ተበላልጠው እነሱ እዚያ ላይ እሱ እዚያ ታች ሆኑ? ይህንን አሳዛኝና አገርንና ሕዝብን የሚጎዳ ሁነት የሚያመጣው እሳት አደጋ መኪና ላይ ቆሞ ቤት እንደሚያቃጥለው ሰው ያሉ ፖሊቲከኞች-ነን-ባዮች የተዛባ ሚዛን ነው፤ በዚህ የተዛባ ሚዛን በየጦር ሜዳው አሞራ የበላቸው የታደሉ ናቸው፤ ተስፋቸው ትርጉም አጥቶ ሳያዩ፣ ውርደት ሳይሰማቸው፣ ችግርንና ግፍን ሳይቀምሱ ቀርተዋል፤ ለነገሩ ነው አንጂ እንኳን ወያኔ በሥልጣን ምኞት ከወገኑ ጋር የተዋጋውና ከኢጣልያ ወራሪ ጦር ጋርም የተዋጉት አርበኞችም ተመሳሳይ ዕድል ገጥሟቸው ነበር፤ ዛሬ ኢትዮጵያን ለክፉ ነገር የዳረጋት የእነዚህ ሰዎች ጡር ይመስለኛል።
የፖሊቲካ ተግባሮቻቸውን ከግል ጠባዮቻቸው እየለዩ የሚኖሩ ፖሊቲከኞች በአንዳንድ አገር አሉ ለማለት ይቻላል፤ ከአውሮፓ ስዊድንና ኖርዌይ፣ ስዊትዘርላንድ፣ ከእስያ ዛሬን እንጃ እንጂ በነኔህሩ ዘመን ህንድ የሚጠቀስ ነበር፤ በአብዛኞቹ አገሮች ግን ፖሊቲከኞቹ እንደየደረጃቸው ለሀምሳ፣ ለሠላሳ፣ ለሀያ፣ ለአሥር ሰዎች የሚበቃ የተሟላ ቤት ውስጥ አምስት መቶ ሰዎችን የሚያስተዳድር ደመወዝ እያገኙ የሚኖሩ ሲሆኑ ምግባቸው ግን አብዛኛውን ጊዜ የአንድ ሰው ይመስለኛል፤ የዚህ ትርጉሙ ምንድን ነው? ለፖሊቲከኞቹ መቀማጠል በላባቸው የሚከፍሉት ደሀዎች ናቸው፤ ከተፎካካሪዎቻቸው ተንኮል የሚጠብቋቸው ደሀዎች ወታደሮች ናቸው፤ ምርጫ ሲደርስ በነቂስ ወጥተው ፖሊቲከኞቹን የሚመርጧቸው ጦማቸውን የሚያድሩት ደሀዎች ናቸው፤ እነዚህም ጊዜያዊና ትንሽ የግል ጥቅምን ከዘላቂው የአገርና የሕዝብ ጥቅም መለየት ያልቻሉ የሕዝብ ክፍሎች ከተበላሹት ግለኛ ፖሊቲከኞች የማይለዩ ናቸው።
ወደፍሬ ነገሩ ልምጣና፤- በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ፖሊቲከኞች የሚወጡትና የሚወርዱት ለየትኛው ዓላማ ነው?
የበትረ መንግሥቱን ሥልጣን ከወያኔ ፈልቅቆ ለማውጣትና ለመያዝ?
በምክር ቤት ገብቶ የወያኔ አጫፋሪ በመሆን ደህና ደመወዝና ነጻ ቤት ለማግኘት?
ከውስጥ ሆኖ ወያኔን ለማጋለጥ?
የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖሊቲካ ቡድኖችን ሲደግፍ የፖሊቲካ ቡድኖቹን ዓላማዎች አጣርቶ በማወቅ መሆን አለበት፤ አለዚያ በሎሌነት እየኖሩ ጌታ መለወጥ ነው።

onsdag 30. juli 2014

በጋምቤላ በመዥንገርና በደገኞች መካከል ግጭት ተፈጠረ

-17 ሰዎች መገደላቸው የተሰማ ቢሆንም መንግሥት ሕይወት አልጠፋም አለ
በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መዥንገር ዞን የሪ በተሰኘ ቦታ ላይ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በተከሰተ ግጭት 17 ሰዎች መገደላቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡
284903EE-7935-4928-8B1C-D65A9A50A515_mw1024_s_nመንግሥት ግን በግጭቱ ጥቂት ሰዎች ቢፈናቀሉም የአንድም ሰው ሕይወት እንዳልጠፋ ገልጿል፡፡
የዓይን እማኞች ለሪፖርተር እንደገለጹት ከሆነ፣ የዞኑ ቀደምት ነዋሪዎች የሆኑት የመዥንገር ብሔር አባላት በአካባቢው ሠፍረው የሚገኙትን በአብዛኛው የአማራና የትግራይ ተወላጆች የሆኑትንና ‹‹ደገኛ›› ወይም ‹‹ሐበሻ›› በመባል የሚታወቁትን ነዋሪዎች ‹‹ከአካባቢው ይውጡልን›› በማለት ቅሬታ ማቅረባቸው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለመደ ሆኗል፡፡
የሪ በተሰኘው ቦታ ላይ በቡና ልማት ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩት ደገኞች ላይ የተወሰደው ዕርምጃ ግን ለየት ያለና የፖለቲካ ድጋፍ ያለው እንደሚመስል ምንጮች አመልክተዋል፡፡
ነባር ነዋሪዎች መሣሪያ ታጥቀው እንደነበር የጠቆሙት ምንጮች፣ ግጭቱ የተከሰተው ነባር ነዋሪዎች በገዛ ፈቃዳቸው መሬታቸው ላይ ደገኞቹ ቡና እንዲያለሙ ሰጥተው፣ ቡናው ሙሉ በሙሉ ከለማ በኋላ ደገኞቹ ያለ ምንም ዓይነት ካሳ እንዲለቁ በመጠየቃቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
የቡና መሬቱን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባልሆኑ ሰዎች ላይ በተወሰደው ዕርምጃ 17 ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት ምንጮች፣ አስከሬኖቹን በወቅቱ ለማንሳት እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡ በክልሉም ሆነ በፌዴራል መንግሥቱ በኩል ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ከመሻት ይልቅ የማደባበስ ነገር እንደሚስተዋል የጠቆሙት ምንጮች፣ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ጊዜያዊ መፍትሔ ብቻ በመስጠት ሳይገታ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት በጥልቀት ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡
ሪፖርተር የጋምቤላ ክልል ባለሥልጣናትን ለማነጋገር ጥረት ያደረገ ሲሆን፣ ግጭቱ ስለመከሰቱ ባይክዱም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል፡፡ ነገር ግን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አበበ ወርቁ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በነባር ነዋሪዎችና በደገኞቹ መካከል የተፈጠረው ግጭት ከባድ የሚባል አይደለም፡፡
ግጭቱ ጥቂት ደገኞችን ማፈናቀሉን የጠቆሙት አቶ አበበ፣ የፌዴራል መንግሥት በቦታው በመገኘት ግጭቱን በቁጥጥር ሥር ካዋለው በኋላ የተፈናቀሉትም ቢሆኑ ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ መደረጉን አመልክተዋል፡፡ ሪፖርተር 17 ሰዎች ስለመሞታቸው ጥቆማ እንደደረሰው የተገለጸላቸው አቶ አበበ፣ መረጃው ከእውነት የራቀ እንደሆነና የአንድም ሰው ሕይወት እንዳልጠፋ አስተባብለዋል፡፡
ግጭቱ እንዲፈጠር ያደረጉት የራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት ያላቸው የአካባቢው ባለሥልጣናት እንደሆኑ መታወቁን ያመለከቱት አቶ አበበ፣ የአካባቢው አመራር ተገምግሞ እጃቸው እንዳለበት በተረጋገጠ አባላት ላይ ዕርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል፡፡
በነባር ነዋሪዎችና በደገኞች መካከል ለሦስት ቀናት ውይይት ከተደረገ በኋላ የጋራ መግባባት መፈጠሩን የጠቆሙት አቶ አበበ፣ አሁን በአካባቢው ሰላም ሙሉ በሙሉ መስፈኑንና ነዋሪዎችም ወደ መደበኛ ሕይወታቸው መመለሳቸውን አመልክተዋል፡፡

የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ (አስቂኙ ክስና አስቂኙ ማስረጃ)

zone 9
 አገራችን ኢትዮጵያ በጥሩ ልትጠራባቸው የምትችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው በድህነት በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በሙስና እና ሃሳብን ነጻነት በመግለጽ መብት የተለመዱ የምናፍርባቸው ጉዳዩች ሆነውመቀጠላቸው እሙን ነው፡፡ ሃሰብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ ሶስት ወራትን ከፈጀ ምርመራ በኋላ በብዙ የፓሊስ ድብብቆሽሂደት የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ባለፈው አርብ ክስ መመስረቱም አብሮ ይታወሳል:
ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባትየምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰትእድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁንግን ክሱ አንድ የዞን 9 ጦማሪን ጨምሮ በይፋ በመመስቱ እነዲሁም በክሱ ላይ ተጠቀሱት ክሶች አንዳቸውም እውነት ባለመሆናቸውክሱን አስመልክቶ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ መስጠት እነዳለብን ተሰምቶናል፡፡
ክሱ በአጭሩ
በአስሩ ተከሳሾች ላይ የተጠቀሱት የክስ አይነቶች ሁለት ሲሆኑ አንዱ የሽብር ተግባርን ማቀድ ማሴር ማነሳሳትና መፈጸም ሲሆን(የጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ አራት) ሁለተኛው ህገ መንግሰታዊ ስርአቱን በሃይል መናድ( የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንቀጽ 238)የሚሉ ናቸው ፡። ክሱ ላይ በፓርላማ በሽብተኝነት ላይ ከተፈረጁ ድርጅቶች ቀጥታ ትእዛዝ በመቀበል በህቡእ በመደራጀት የሽብርተግባር ላይ መሰማራት እና የመሳሰሉት ክሶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ ከሶቹ ሲጠቃለሉ
1. ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል
2. ስሙ ባልተጠቀሰ የህቡእ መደራጀት እና ስራ ክፍፍል መፍጠር
3. Security ina boxን ጨምሮ ስልጠና መውሰድ
4. አመጽ ቡድኖችን ማደራጀትና አመጽ ማነሳሳት  የሚሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል
ከዚህ በፊትምእነደተናገርነው  ማንኛቸውም የዞን9 ጦማርያን በፓርላማ በሽብርከተፈረጁ ወገኖች ጋር ምንም ግንኙነት የለንም፡፡  ብዙ  የዞን9 ነዋሪያንንም አንደሚረዱት አብዛኛዎቹ የዞን9 ጦማርያን እነዚህአካላት ላይ በሚያደርጉት ከፍተኛ ትችት እየታወቁ ጉዳዩን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ መሞከር ፣መንግስት የፈረጃቸውንድርጅቶች እነደፈለገ ማንንም ሰው ለመክሰስ አንደሚጠቀምበት ከማሳየት ባለፈ ትርጉም የማይኖረው ነው፡፡ ለማጠቃለል ያህልማንኛቸውም የዞን9 አባላት አገር ውስጥም ሆነ ውጪ አገር ያለ የፓለቲካ ደርጅት አባላት አይደሉም፡፡ ይህንን የሚያሳይ መረጃምመንግሰት ለማቅረብ አንደማይችልም አናውቃለን፡፡ ( የማስረጃ ዝርዝር ላይ ወደታች የምንመለስበት ይሆናል)

ስሙ ባልተጠቀሰ የህቡእ መደራጀት እና ስራ ክፍፍል መፍጠር
በክሱ ላይ ስሙያልተጠቀሰ የህቡእ ሽብር ድርጅት በመመስረት ተከሰናል፡፡ በመሰረቱ መንግስት ዞን9 የሚለውን ስም አንድም ቦታ በክሱ ላይለመጠቀም ያልፈለገው የጦማርያኑን ቡድን ይበልጥ ታዋቂ እነዳይሆን ለማድረግ አንደሆነ አንገምታለን፡፡ ይህ አስቂኝ ክስ አንድምቦታ ላይ የዞን9 ስም ባያነሳም በደፈናው በህቡዕ መደራጀት ብሎ ከሶናል፡፡ በመሰረቱ መንግሰት እኛን ለማግኘት ምንም አይነትየደህንነት ስራ እነዳላስፈለገው አናውቃለን፣. ምክንያቱም ሁሉም የዞን ፱ ጦማርያን ስማቸውና ፎቶአቸውን ማስቀመጣቸው ቋሚየምንስማማበት እሴት ስለነበር ነው፡፡ የምንጽፈው ነገር በተናጠል ሃላፊነትን አንድንወስድ አንዲሁም ሌሎችን ሃሳብ መግለጽንለማበረታታት በማሰብ በአደባባይ  እነዲታይ የወሰነውን የጦማርያንንስብስብ ‹‹ህቡዕ›› ብሎ መጥራት ማንን ለማሞኘት አንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ዞን፱ ድብቅ እነዳልሆነ እያንዳንዱ ጽሁፍምበተናጠል ሃላፊነቱን የሚወስድ ጸሃፊ የቡድን ጽሁፎች ሲሆኑ ደሞ የቡድን ሃላፌነት አንደምወስድ ማንም የጦማራችን አንባቢያውቀዋል፡፡ መንግስት የዞን፱ አይነት ጦማሮችንም ሆኑ የአንተርኔት አንቅስቃሴዎቸን የሚመዘግብበት አሰራር አለመኖሩ ደሞ የእኛጥፋት ተብሎ ሊቆጠር አይችልም፡፡ተሰብስቦ መጦመርን የሚከለክል ምንም አይነት የህግ ክልከላም የለም፡፡ በመሆኑም ተሰብስበንመጻፋችን  ራሳችንን ገልጸን ሃሳባችንን መግለጻችን የጣስነው ምንምሕግ የለም፡፡ፓሊስም ሆነ መንግሰት ሶስት ወር በፈጀ ምርመራው ህቡዕን ትርጉም ትርጉም በሚገባ አለማወቁም ጉዳዩን አስተዛዛቢባስ ሲልም መሳለቂያ ያደርገዋል፡።

Security in a boxን ጨምሮ ስልጠና መውሰድ
Security in a box ኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የኢንተርኔትአንቅስቃሴን በጥንቃቄ ለማድረግ የሚረዳ ኦፕን ሶርስ የስልጠና ማንዋል ሲሆን ይህንን ስልጠና መውሰድ በምንም መልኩ ወንጀልሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የስልጠና ማንዋል ለማንኛውም የሰብአዊ መብትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሚያሳስባቸው ሰዎችአንዲያገኙት ሆኖ የተዘጋጅ  ፍሮንት ላየን ዲፌንደርስ እናታክቲካል ቴክ የተባሉ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት ያዘጋጁት ስልጠና ነው፡፡ በመሰረቱ ይህንን ስልጠና ወንጀል አድርጎከማቅረብ በፊት ጎግል ላይ አስገብቶ መፈለግና ውጤቱን ማየት ከአንደዚህ አይነት አሳፋሪ ክስ ያድን ነበር፡፡ ይህ በበጎ መልኩአንረዳው ካልን የፍትህ አካላቱ ከቴክኖሎጂ ጋር ያላቸውን ከፍተኛ ርቀት የሚያሳይና መንግሰትም በሰፊውና በቅንጅት ሊሰራበትየሚገባ ክፍተት ሲሆን ከዚያ ባለፈ ካየነው ደሞ መንግሰት እሱ የማያውቀውን ማንኛውንም ነገር ያለምንም የህግ ክልከላ  ወንጀል ብሎ ለመፈረጅ ያለውን ጉጉት ያሳያል ያ በራሱ ደሞ መንግስትንራሱን ህገ ወጥ እነደሚያደርገው ያለምንም የህግ እውቀት ማሰብ ብቻ ለሚችል ሰው የሚገለጥ ሀቅ ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ ወንጀልተብለው የተለያዩ ስልጠናዎች በሚል የተጠቀሱት የኮምኒኬሽን ስልጠና የስትራቴጂክ ስልጠና የአድቮኬሲ ስልጠና የመሳሰሉትመሆናቸውን ለመጥቀስ አንወዳለን፡፡ በመሰረቱ በተለያዩ ድርጅቶች ግብዣ ስልጠና መውሰድና የሰብአዊ መብት ፎረሞች ላይ መገኘትንወንጀል የሚያደርግ ህግ አለመኖሩን መንቀሳቀስም የዜጎች ሰብአዊ መብት መሆኑን ለአቃቢ ህግ ህግና ፓሊስ ካላወቁ ማን ሊያውቅነው ??
የተደራጁት የአመጽቡድኖችን ማደራጀት  እና 48 ሺህ ብር ለአመጽ ማከፋፈል
መንግሰት የአመጽቡድኖችን ማደራጀት በሚል ያቀረበውን ክስ ለመመለስ ያህል አንድ ጥያቄ ብቻ አንጠይቃለን? የታሉ የተደራጁት ቡድኖች?  ምንም የተደራጀ ቡድን በሌለበት ይህንን ክስ ማቅረብ በፍትህ ስርአቱማፌዝ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምን ይባላል? በ48 ሺህ ብር የአመጽ ማነሳሳት ክሱን ከብሩ ማነስ በላይ ይበልጥ አስቂኝየሚያደርገው የማስረጃው ዝርዝር ላይ ያለው ማስረጃ እና ክሱ የተለያዩ መሆናቸው ነው፡፡ ክሱ 48,000 ብር ከውጪ በመቀበልበማለት በደፈናው ላኪውን ሳይጠቅስ ያለፈው እና ለሽብር ተግባር የተባለው አርቲክል 19 ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትለታሰሩ ጋዜጠኞች ቤተሰቦች የሚደረግ ድጋፍ ሲሆን በወቅቱ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ባንክ ስለሚሰራ ተቀብሎ ለጋዜጠኛ ርዩት አለሙቤተሰቦች እስር ቤት መመላለሻ ተብሎ የተሰጠ ድጋፍ ነው፡፡
የተያያዘው የባንክደረሰኝም ያንን የሚያሳይ ሲሆን ክሱ ላይ በይፋ መጥቀስ ያልተፈለገው ለምን ይሆን? (ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹን መታሰር ተከትሎመንግስት ፋይል የከፈተበትን ከሰብአዊ መብት ተቋማት ነን ከሚሉ ድርጅቶች የሃሳብና የገንዘብ ድጋፍ በመቀበል ሶሻል ሚዲያንበመጠቀም አመጽ ማነሳሳት የሚለውን ክስ ተከትሎ የተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራመስራት ወንጀል ሊሆን አይገባም በሚል ርእስ እስሩን የሚያወግዝ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል)
ማስረጃውሲገመገም
እስካሁን በእጃችን የደረሰውን የማስረጃ ዝርዝር በሶሰት ከፍለን ማየት አንችላለን ፡፡ከማስረጃ ዝርዝሩ ውስጥ አብዛኛውን ቦታ የሚይዘው በተለያየ ወቅት የተጻፉ የጦማርያኑ ጽሁፎች ሲሆኑ ጋዜጠኞቹ ላይ ደሞ ጭራሽየመረጃ ዝርዝር ለማቅረብም አልተቻለም፡፡(አቃቤ ህግ የሁሉንም የበይነ መረብ ዘመቻዎች መግለጫ እና እቅድ እንደማስረጃአቅርቧል)  በሁለተኛ ደረጃ የቀረቡት የተለያዩ የጉዞ ትኬቶችአለም አቀፍ ስብሰባ ማስታወሻዎች አንዲሁም ፕረዘንቴሽኖች  ሲሆኑሁሉም ጦማርያኑ ያደረጓቸው አለም አቀፍ ጉዞዎችን የሚያሳዩ የተሳተፉባቸው ሰብአዊ መብትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትየተመለከቱ የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ የተደረጉ ጉዞዎችን ናቸው፡፡
በማስረጃ ዝርዝር ውስጥከተካተቱት የሽብር ተግባር የተደረጉ ጉዞዎች ተብለው መሆኑ ይበልጥ ክሱን አሳፋሪ ያደርገዋል፡፡ መንግሰት ጉዞዎቹ የተደረጉትምሆነ የስልጠና ግብዣዎቹ የመጡት ከአለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አንደሆነ እያወቀና እና ማስረጃው ላይም በግልጽእየታየ የሽብር ቡድኞች ብሎ ግንቦት ሰባትና ኦነግን ጣልቃ ማስገባቱ አስገራሚ ነው፡፡ (የፍርድ ሂደቱ ላይ እነዚህ ተቋማት ጋርየተደረጉ ግንኙነቶቸን አንዴት ብለው በፓርላማ ከተፈረጁ የሽብር ተቋማት ጋር እነደሚያገናኛቸው አብረን የምናየው ይሆናል)  በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጡት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የተደረጉ የስልክልውውጦች ሲሆኑ በፍርድ ቤት ሂደቱ ውስጥ በዝርዝር የምናያቸው ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ተከሳሽ ቤት ተገኘ የተባለውና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት ከግንቦት ሰባት ጋር የተገናኙ ዶክመንቶች እናየአባላት መጽሄት ሲሆን በፍተሻው ወቅት ፓሊሶች ራሳቸው ፍሪጅ በስተጀርባ አገኘን ብለው በፍተሻ ወቅት ከፍተኛ አለመግባባትተፈጥሮ የራሳቸውን ምስክሮች ብቻ አስፈርመው መሄዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
እንዲሁም ፓሊስ 18 የሰው ማስረጃ ለማሰማት የስም ዝርዝር ማስገባቱን እና የስም ዝርዝሩም እጃችን ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከፍርድቤት ለሚመጣው የፍርድ ውጤት ሳይሆን በአጠቃላይ የፍትህ ስርአትን ማክበር ሃላፊነት ስላለብን ብቻ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ ላለማካተትወስነናል፡፡
እንደማጠቃለያ
የዞን፱ ጦማርያን ከዚህ በፊትም በተለያየ ወቅትአንደተናገርነው የመንግሰት ይህን ሁሉ ጊዜ ወስዶ ይዞ የመጣው ማስረጃ የአደባበይ ጽሁፎች እና በተለያየ ወቅት የተደረጉ የአደባባይሁነቶች( public events) ጥርቅም መሆኑ የክሱን ፓለቲካዊነት ያረጋገጠ ነው፡፡ ጦማርያኑ የፍርድ ቤት ስርአቱን የተለያዩአለም አቀፍ የወንጀል ስነስርዓት ደረጃን በጠበቀ መልኩ ህጉን አክብረው የሚከታተሉ ሲሆን እኛም ሂደቱን በተቻለ መጠን ለዞን ፱ነዋሪያን ለማሳየት ለማሳወቅ የምንጥር መሆኑን ለማሳወቅ አንወዳለን፡፡ በተደጋጋሚ ተፈትኖ የወደቀው የአገራችን ፍርድ ቤት እና የፍትህስርአት ገለልተኝነት ይህንን እድል በመጠቀም ራሱን ለማሻሻል መፍቀዱን እነዲያሳይና ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹን አይቶ ክሱን እነዲዘጋጥሪ እያደረግን ይህንን በማድረግ የአገሪቱን የፍትህ ሂደት አንድ ደረጃ የማራመዱን እድል ዳኞች እንዲጠቀሙበት መንግስትን ከወራትበፌት የሰራውን ስህተት ለማስተካከል እድሉ ዛሬም ያልመሸ መሆኑን ለማስታወስ አንወዳለን፡፡
የታሰራችሁ ጦማርያንን እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ለከፈላችሁት መስዋእትነት ውለታችሁ አለብን፡፡ እንኮራባችኋለን!!
ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ሰነዶች ለፈገግታ ያህል
ዞን ዘጠኝ ላይ የታተሙ ጽሁፎች
  1. ነጻነትና ዳቦ - በናትናኤል ፈለቀ
  2. ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል - በናትናኤል ፈለቀ
  3. ስደትና ፍቅር - በሰለሞን አብርሃም(ከአውሮጳ)
  4. ዋኤል ጎኒሞ ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ ….? - በበፍቃዱ ሃይሉ
  5. ልማታዊ ጋዜጠኝነት ወይስ ይሁንታን ማምረት? - በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤል
  6. እኛና ሶማልያ – በናትናኤል ፈለቀ
  7. ድምፃችን ይሰማ - በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤልና እና በፍቃዱ ሃይሉ
  8. እንዴት እንደመጥ - በማህሌት ፋንታሁን
  9. የመለስ ውርስ እና ራዕይ - በሶሊያና ሽመልስ
  10. የቅድመ ምርመራ ቅድመ ምርምራ - በማህሌት ፋንታሁን
  11. ትግራይና ሕዋሐት ምንና ምን ናቸው ? -በበፍቃዱ ሃይሉ
  12. ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ በዘላለም ክብረት

ከበፍቃዱ ብሎግ(www.befeqe.com) የተገኙ 
  1. ከ21 አመት በኋላ ዴሞክራሲ ሲሰላ
  2. ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት መመሪያ በማክበር መሥራት ይቻላል?
  3. አብዮት ወረት ነው
  4. የእህአዴግ ‹‹ትርፍ›› እና ኪሳራ
  5. የኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች
  6. ከእከሌን አሰሩት እስከ እከሌን አገዱት
  7. ሰማኒያ ሚሊዮን እስከምንደርስ እንታገላለን
  8. “ድር ቢያብር” ለአምባገነኖች ምናቸው ነው ?
ከሌሎች ብዙ ዝርዝሮች በጥቂቱ
  1. “ኢትዮጵያዊ ማንነት ከሌለ ትግሬያዊ ማንነት የለም” – (በአብርሃ ደስታጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
  2. “መንግስት የለም ወይ ?” የምንና ምን አይነት መንግስት(የመስፍን ነጋሽጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
  3. የሁለተኛው ዘመቻ ዕቅድ ( ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
  4. የ2ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ (ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
  5. ዳዊት ሰለሞን ስለአዲሱ የጋዜጠኞች ፎረም ፕሬዚዳንት ፌስቡክ  ላይ የፃፈው እና አጥናፍ ለበፍቄ ኢሜል የደረገለት ጽሑፍ
  6.  “ፍርሃታችንየት ያደርሰናል ?” በሚል በኤልያስ ገብሩ ተጽፎ በፍቄ ላፕቶፕ ውስጥ የተገኘ(ለዕንቁ መጽሄት ተዘጋጅቶ ያልታተመ ጽሑፍ)
  7. የ3ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ ( ዴሞክራሲን በተግባር እናውል የሰላማዊሰልፍ መብታቸን ይመለስ)
  8. “ሰልፍና ሰይፍ ” በሚል በበፍቄ ተጽፎ ነገር ግን ያልታተመ ጽሁፍ ከላፕቶፑ
  9. የ1ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ(draft ሕገ መንግሰቱ ይከበር)
  10. የ4ኛው ዘመቻ ዕቅድ( ኑ ኢትዪጲያዊ ህልም አብረን እናልም)
  11. ጋዜጠኛ አስማማው ለድምፃችን ይሰማ የፌስቡክ ገጽ ያዘጋጀቸው ጥያቄዎችከኢሜሉ (ለአዲስ ጉዳይ መጽሄት)
  12. ስለ ዞን 9 ዘመቻዎች globalvoicseonline.org ላይ የታተሙጽሑፎች
  13. በናትናኤል በኩል ለርዕዮት ዓለሙ ቤተሰቦች ከ Article 19 የተላከ48,170.25(ብር) የዌስተርን ዩኒየን ኮፒ
  14.  “የተቃውሞሰልፉ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች” በሚል አዲስ ጉዳይ ላይ የታተመ ጽሁፍ (draft)
  15. ማሒ ስለ ርዕዮት ዓለሙ እና ስለ አዲስ ዘመን “አዝማሚያ ጥናት ” በቀልድየጻፈችው ጽሑፍ፡፡
  16. የዞን 9 ወደፊት ለመስራት የታቀዱ ሶስት ፕሮጄክት ፕሮፓዛሎች ( ምርጫ2007 ሪፓርት የማድረግ ስራ፣ የኢትዮጲያ የነጻነት ኢንዴክስ ማዘጋጃት ስራ ፣ ገጠሪቷ ኢትዮጲያ ላይ ለመስራት የታሰበ ዶክመንተሪእቅድ)
  17. እና ሌሎችም ትርኪሚርኪዎች (ለምሳሌ የዳንኤል ብርሃነ ጽሑፍ፣ የናቲ የ10ኛክፍል ግጥም)
     

በፖሊስ የተፈነከተችው ወይንሸት ሞላ እና አዚዛ መሐመድ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

ከዳዊት ሰለሞን
ወይንሸት ሞላ ቀጭኗ የጥንካሬ ምልክት
addisweyeneshet molla
ከሁለት ሳምንት በፊት በአንዋር መስጊድ በተፈጸመ ጥቁር ሽብር እጇንና ጭንቅላቷን ተጎድታ እስር ቤት የተወረወረችውን ወይንሸት ሞላን የጠዋቱን ብርድ እየተጋፋን ልንጠይቃት ከኤልያስ ገብሩ ጋር አምርተን ነበር፡፡ከፎቶግራፍ ጋዜጠኛዋ አዚዛ መሐመድ ጋር አንድ ክፍል የተጋራችው ወይንሸት ከጉዳቱ በኋላ የማይንቀሳቀስ ቀኝ እጇን የለበሰችው ቱታ ጃኬት ውስጥ ከትታ ከአዚዛ ጋር ወደ እኛ መጣች፡፡
አዚዛ ጉዳት ያልደረሰባት በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ወይንሸትን የምትንከባከበው እርሷ ናት፡፡ጭንቅላቷን በተፈነከተች ወቅት የፈሰሰው ደሟ ጸጉሯን በማጠባበቁ ማላቀቁ ትልቅ ስራዋ ሆኖ መሰንበቱን አዚዛ አወጋችን፡፡እጇን በማሸትም ከፎቶግራፍ አንሺነት ሞያዋ በተጨማሪ ጥሩ የወጌሻ ብቃት እንዳላት ማወቋን በፈገግታ ታጅባ ነገረችን፡፡
‹‹አዚዛን ባላገኝ ኖሮ እስሩ በጣም አስቸጋሪ ይሆንብኝ ነበር፡፡ነገር ግን አሁን እሷን በማግኘቴ የጭንቅላቴም ሆነ የእጄ ህመም አይሰማኝም››የምትለው ደግሞ ወይንሸት ናት፡፡
ወይንሸት እጅግ በጣም ቀጭን ከመሆኗም በላይ ሴት ናት፡፡ወታደሮቹ ግን ሁለቱም አልታያቸውም፡፡ድፍረትን ከስጋ ውፍረትና ከወንድነት ጋር የምናቆራኝ ሰዎችም ወይንሸትን ስናይና ከአንደበቷ የሚፈልቁትን የውስጣዊ ጥንካሬ መገለጫ የሆኑ ቃላትን ስናደምጥ የመጀመሪያው አስተሳሰባችንን እንለውጣለን፡፡
‹‹እንዲህ አይነት ነገር በመፈጠሩ ምንም አልተሰማኝም፡፡ቁስሎቹ የፈጠሩብኝ ስቃይም ተራ ነገር ነው፡፡ይህ እንደሚሆን በፊትም አውቃለሁ፡፡››በማለትም ከሰውነቷ ገዝፎ የሚታየውን ጥንካሬዋን ታሳያለች፡፡
ነገ አዚዛና ወይንሸት ሜክሲኮ የሚገኘው ፍርድ ቤት ማለዳ ይቀርባሉ።

Ethiopia, Protecting Yourself Online is a Crime

July 29, 2014
Six Ethiopian bloggers were formally charged with terrorism in Ethiopia
Six Ethiopian bloggers were formally charged with terrorism in Ethiopia’s Lideta High Court on July 17th, a move provoking deep concern for hackers and human rights activists in Ethiopia and around the world. Three journalists were also charged, and a seventh blogger, Soleyana Gebremicheal, was charged in absentia.
The seven members of the Zone 9 blogger collective, who sprung to international attention upon their arrest last April, stand accused of associating with outlawed political groups and of attending a digital security training, among other charges. The criminalization of digital security training generates particular alarm among human rights activists, including PEN, who often promote these trainings for bloggers in repressive societies as a preventative measure against exactly the kind government spying and twisting of information that can lead to bogus charges like associating with outlawed groups. The bloggers maintain that they were openly critical of the outlawed groups and not, in fact, allied with them in any way.
“It is terrible that all of the articles we have written for two consecutive years have been brought to court as ‘evidence’ to support the terrorism charges. It is insane,” said Endalkachew Michael, a Zone 9 blogger currently living in exile. “Thinking and reflecting on the realities of the country is literally impossible in Ethiopia today. I have seen the charge sheet and they brought the laptops of the bloggers as evidence against them, including attending a training on encryption tools. The government has also accused us of associating with two ideologically hostile opposition groups which are outlawed. The paradox is that we have been very critical of these outlawed political parties.”
The name “Zone 9” is derived from a section of Kality Prison in Addis Ababa where journalists are held, called Zone 8. According to the bloggers, Zone 9 represents the invisible prison that surrounds all the citizens of Ethiopia, who may be arrested at any time for speaking out. Their motto is simple: “We Blog Because We Care”. Those who can continue to blog in the face of government harassment, threats, surveillance, and intimidation to fill the silence created by the government’s ongoing crackdowns on free speech and dissent.
Ethiopia is among the greatest violators of the right to free expression, operating one of the most sophisticated Internet monitoring and filtering systems in the world with near total impunity. Journalists Eskinder Nega, winner of the 2012 PEN / Barbara Goldsmith Freedom to Write Award, and Reeyot Alemu continue to suffer in prison on lengthy sentences for exercising their right to free expression.