በቅርቡ ከ 8 አመት በኋላ በሰማያዊ ፓርቲ አነሳሽነት በከተማችን በአዱ -ገነት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ ይታወሳል።
መንግስት ተብዬዉ ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ የፈቀደዉ ፈልጎት አይደለም ተገዶ እንጂ!
መንግስት የህዝቡንና የፓርቲውን አመራሮች ቁርጠኝነት ስለተገነዘበ ሰልፉን ፈቅዷል።አለቀ-ደቀቀ!
ሆኖም በቅርቡ በፌስ ቡክ ላይ ዶ/ር መራራ ጉዲና “ቆይ ለእኛ እንቢ የተባለዉ ሰልፍ እንዴት ለሠማያዊ ፓርቲ ተፈቀደ?” ሲሉ ተደምጠዋል።
እኔ ዶ/ር መራራን የመሳደብ ሞራሉም ሆነ ድፍረቱ የለኝም። በትምህርትም፣ በእድሜም ሆነ በልምድ እጅግ ይበልጡኛል። ነገር ግን የትንሽነቴን ሁለት አስተያየቶቼን ልስጣቸዉ።
1ኛ-እየፈሩ ትግል የትም አያደርስም። ይልቁንስ ምስኪኑን ወገኔን ያስጨርሱታል። ስለሆነም ቆራጥ ይሁኑ እንደ ሠማያዊ ፓርቲ አመራሮች።
2ኛ-አብሮ ስለመስራት ያስቡ። ሠማያዊ ፓርቲ እንዴት ተፈቀደለት ብለዉ ከሚጨናነቁ ከ90 ቀን በኋላ ለሚኖረዉ ሰልፍ ተዘጋጁ፣ ተነጋገሩ!
በመጨረሻም ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳለዉ “ነፃነት በጨቋኞች መልካም ፈቃድ የሚሰጥ ሳይሆን በተጨቆኑ ህዝቦች ትግል የሚገኝ ዉጤት ነዉ!” እግዛብሔር ድፍረቱን ይስጥዎት አሜን።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar