søndag 31. mars 2013

በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ


መግለጫ

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
የወያኔ መሪዎች እነ መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በ1967 ዓም ለትግል ደደቢት በረሀ እንዲገቡ ያነሳሳቸዉና ያሰባሰባቸዉ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያላቸው  ጥላቻና የበቀል ስሜት እንጂ
Ginbot 7 press release in Amharicየኢትዮጵያ ህዝብ በደልና እሮሮ አንገፍግፏቸዉ እንዳልሆነ በተለያዩ ግዜዎች ለህዝብ ይፋ የሆኑት የወያኔ  መግለጫዎችና ለረጂም ግዜ ወያኔን የመሩት መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በየአደባባዩ ላይ ያደረጓቸዉ ንግግሮች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ከወጣትነት ግዜያቸዉ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ጥርሳቸዉን የነከሱ የወያኔ  መስራቾች በለስ ቀንቷቸዉ አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላም ቢሆን ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለቻዉ ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም።
የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ያከበረዉ ወይም የኤኮኖሚና የፖለቲካ ጥቅሙን ያስጠበቀለት ብሔረሰብ ባይኖርም በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቡድን የወያኔ ዘረኞች የአማራን ህዝብ ከተቀሩት ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ  ነጥለዉ ለማጥቃትና የስነ ልቦና ዘይቤውን ለመስበር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። በአጠቃላይ የወያኔ ዘረኛ ባለስልጣኖች አማራውን በተከታታይ ሲዘልፉ ቆይተዋል፤አዋርደው  አስረዋል፤ ከአገር እንዲሰደድ አድረገዋል፤ አፈናቅለዋል ገድለዋል።  ለምሳሌ ወያኔ ስልጣን በያዘባቸዉ በመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት ዉስጥ ብቻ አሶሳ፤ በደኖና አርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል።
ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው  ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡና  እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። የወያኔ ባለስልጣኖችና በየአካባቢዉ የኮለኮሏቸዉ ምስለኔዎች አካባቢዉን በግድ እንዲለቅ የተደረገ ህግ አክባሪ ዜጋ የለም፤ የተባረሩት ህግ የጣሱ ግለሰቦች ብቻ ናቸው፣ በማለት አሳፋሪ ድርጊታቸዉን ለመደበቅ ሲሞክሩ ታይተዋል። ሆኖም ከጉራ ፈርዳና ከአካባቢዉ ተፈናቅለዉ ወደ መጣችሁበት አካባቢ ተመለሱ ተብለው በየሜዳው ያለምግብ፣ ውኃና፤መጠለያ የተበተኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ለወገኖቻቸውና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ የድረሱልን ጩኸት ሲያሰሙ መሰንበታቸዉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነዉ።
ወያኔ በዚህ በያዝነዉ አመት ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ  በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል። ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ አያሌ የአማራ ተወላጆች ያፈሩትን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ግዜ ሳይሰጣቸዉ የኔ ብለው ከሚጠሩት የመኖሪያ ቦታቸዉ እንደባዳ እየተገፉ እንዲወጡ ተደርገዋል። እዚህ ላይ አንድ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ቢኖር በገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ ዉስጥ  አማራን እወክላለሁ ባዩ ብአዴን ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ዝም ብሎ መመልከቱ ብቻ ሳይሆን ባለፈው አመት ከጉራ ፈርዳ ዘንድሮ ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባረሩ እየወጡ ባሉ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ባለው ወንጀል ላይ  ተባባሪ መሆኑን አሳይቷል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያደረሰውንና በማድረስ ላይ ያለውን ይህ ነዉ የማይባል ግፍና መከራ ከዚህ ቀደም እንዳደረገዉ ሁሉ አሁንም አጥብቆ ያወግዛል። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔ በዚህ በኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የትግል ምእራፍ ውስጥ በደም የተቀባ፣ የቀለመ አኩሪ ታሪክ ያለውን የአማራውን ህዝብ መልሶ መላልሶ የሚያጠቃውና ይህንን ታላቅ ህዝብ ከየቦታዉ የሚያፈናቅለው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከአማራዉ ህዝብ ጋር ብቻ በማያያዝ አገራችንን ለማዳከምና አንዱ ኢትዮጵያዊ በሌላዉ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰዉን ግፍና መከራ “ምን አገባኝ” ብሎ እንዲመለከት ለማድረግ ባለው እጅግ አደገኛ ዕቅድ መሠረት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብ በጥብቅ ያሳስባል።
ከዚህም በተጨማሪ በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ባለው እጅግ አስከፊ ወንጀል በግልም ሆነ በቡድን፣ የንጹሀንን ደም እያፈሰሳችሁ  ያላችሁ  ወንጀለኞችና ተባባሪዎች፣ ከያላችሁበት ታድናችሁ ለፍርድ እንድትቀርቡ ንቅናቂያችን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት   በግልጽ እንድታውቁት ይገባል።
በአማራው የደረሰው ጥቃት የሁሉም ኢትዮጵያውያን  ዜጎች ጥቃት ነው እንላለን።  ግንቦት ሰባት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በግለሰብ ደረጃ የምንደሰትበትን ነጻነት የምናስጠብቀው በህብረት ነውና ወያኔ በአሁኑ ግዜ በአማራው ወገናችን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ፤ መከራና መፈናቀል በእያንዳንዳችን ላይ እንደደረሰ በመቁጠር ይህንን ግፍ በመፈጸም የማይሰለቸውን ዘረኛ አገዛዝ በተባበረ ህዝባዊ ትግል ከአገራችን ለማስወገድ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ትግል ጥሪ ያስተላልፋል።

fredag 29. mars 2013

ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?


(ምንጭ፡ ፍኖተ ነጻነት)

የኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?
ግራዚያኒ በመርዝ ጋዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል፤ ከየካቲት 12 ጀምሮ ለቀናት በዘለቀው የበቀል ጭፍጨፋም በአካፋ ሳይቀር በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በግፍ ጨፍጭፏል፡፡ ግራዚያኒ በወቅቱ በሰጠው ትዕዛዝ የፋሺስት ወታደሮች ህይወት ያለውን ተንቀሳቃሽ ፍጥረትን ሁሉ ገድለዋል፡፡ ይህ እሩቅ በማይባል ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለእንዲህ አይነቱ ጨፍጫፊ የተገነባን ሀውልት ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የወሰዱት የእስር ተግባር እውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው? አስብሎናል፡፡ ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ በተደጋጋሚ ጥፋት ፈፅሟል፡፡ ሀገራችንን የባህር በር ማሳጣትን ጨምሮ ሀገራዊ ስሜትን አንኳሶ ጠባብ የብሔር ስሜት እንዲንሰራፋ አድርጓል፣ ታሪክን ለስልጣኑ መደላድል ሲል በራሱ መንገድ የሚያዘጋጀው የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያን ጠፍጥፎ እንደሰራት ሁሉ ደርግን ለመጣል ካደረገው ትግል ውጪ ያለውን የአርበኞች ተጋድሎ እውቅና ሲሰጥ አይታይም፡፡
መንግስት ለፋሽስቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተገነባውን ሀውልት በመቃወም የወሰደው እርምጃ አለመኖሩ ሳያንስ ግራዚያኒን ለማውገዝ የወጡ ዜጎችን በመደብደብና በማንገላታት ማሰሩ አሳፍሮናል፡፡ ለዜጎቻቸው እና ለሚመሯት ሀገር ክብር የማይሰጡ ይልቁንም የጦር ወንጀለኛና ፋሺስትን ለመቃወም የወጣን ዜጋ ማሰርራቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት ወገንተኝነታቸው ለዜጎቻቸው ነው ወይስ ለፋሺስት? የሚል ዘግናኝ ጥያቄ እንድንሰነዝር ያስገድደናል፡፡
በሰልፉ ላይ የተገኙት ሀገር ወዳድ ዜጎች በማን አለብኝነት ሲታሰሩ ድባደባ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የታሳሪዎቹን የኢሜይልና የማህበራዊ ገፅ የይለፍ ቃል (password) በግዳጅ የሚቀበሉ የደህንነት ሀይሎች ተልከውባቸዋል፡፡ ይህን ቅጥ ያጣ አንባገነናዊ ድርጊት የፈፀመው ወይም እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጠው አካል ማንነት ተጣርቶ የማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ በየምክንያቱ ዜጎችን ማሰር የለመደው አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ምን ያክል ኢትዮጵያዊነትን እየተዋጋ እንዳለም የሚያሳይ ድርጊት ነው፡፡ መሰረቱ ዜጎች በማንኛውም ጉዳይ ላይ የተቃውሞም ሆነ የድጋፍ ሰልፍ ማድረግ እንደሚችሉ ህገመንግስቱ ደንግጓል፡፡ ይህን መብት ዜጎች እንዳይጠቀሙ ያፈነው መንግስት፣ ኢህአዴግን የሚደግፉ አልያም በራሱ ከተጠሩ ሰልፎች ውጪ ዜጎች እንዳይሳተፉ በአሰራር ከልክሏል፡፡ ይህ የመብት ረገጣ ከመሆኑም በላይ በዜጎች መካከል 1ኛ ደረጃና 2ኛ ደረጃ ዜግነትን ያስቀመጠ ነው፡፡
የኢህአዴግን ባናውቅም፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በቅኝ ገዢዎች የተዋረደ ስነልቦና የለንም፡፡ ሆኖም የግል ጥቅማቸውን ለማደላደል ሲሉ ለቅኝ ገዢ ጠላቶቻችን ያደሩ ባንዳዎች እንደነበሩ ታሪክ በጥቁር መዝገቡ ሸክፎታል፡፡ ይህን አሳፋሪ ተግባር በጣሊያን ወረራ ወቅት የፈፀሙ ኢትዮጵያውያን ለልጅ ልጆቻቸው የሚያስተላልፉት አንገት ቀና የሚያደርግ ታሪክ አይኖርም፡፡
በዚህም ዘመን ተመሳሳይ ክህደት የሚፈፅሙ አካላት መኖራቸው አይጠረጠርም፡፡
የኢህአዴግ መንግስት በይፋ ለጦር ወንጀለኛውና ለፋሺሽቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተሰራውን ሀውልት በይፋ ካለማውገዝ ባለፈ ለተቃውሞ የወጡትን ኢትዮጵያውያን በግፍ የማሰሩን ምክንያት ስንመረምር አንድ መራራ እውነት እንረዳለን፤ ይኸውም ጣሊያን ለኢህአዴግ መንግስት ዋንኛዋ ለጋሽ ሀገር መሆኗ ነው፡፡ ይህ የኢህአዴግ መንግስት ተግባር በስልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያዊነት ላይ ከፈፀማቸው ክህደቶች እኩል በታሪክ ጥቁር መዝገብ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

mandag 25. mars 2013

UN Human Rights Council Adopted a Resolution on Human Rights Defenders


by Betre Yacob

As the authoritarian government in Ethiopia continues its violence against journalists and human right defenders, the United Nation Human Rights Council (UNHRC) adopted a new resolution on 21 March 2013 calling an end to the impunity and the protection of dissent.
In a statement issued on 21 March 2013, the council says that the resolution on “protecting human rights defenders (A/HRC/22/L.13)” is successfully adopted at its 22nd Session in Geneva having received the support of 62 states across 6 continents.
“We welcome the resolution as a significant statement by the UNHRC reaffirming the positive obligation upon States to facilitate the work of HRDs, and remove obstacles to their work, including legislation that illegitimately criminalises the exercise of the right to freedom of expression and information”, the statement explains.
The statement says that the new resolution can be seen as a timely response to the increasing challenges faced by human right defenders, and it strongly calls on States to ensure that it translates to real action on the ground.
“We call on all states to review their domestic laws and practices to ensure that they comply with the new resolution and with other international human rights standards in this area”, the statement adds.
According to the statement, the resolution supports the obligation upon governments (including the Ethiopian Tyrannical Regime) to: create a safe and enabling environment in which HRDs can operate free from hindrance and insecurity; ensure laws to protect national security are not misused to target HRDs and that counter-terrorism measures comply with international human rights standards; ensure HRDs can perform their important role in the context of peaceful protests; ensure that reporting requirements for civil society do not inhibit functional autonomy, and that no law criminalises or places discriminatory restrictions on funding sources; and protect the expression of dissenting views.

የመለስ ዜናዊ ራዕይና መተካካት ያልተንጸባረቀበት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስብሰባ ተጠናቀቀ


 

News, Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy.የመለስን ራዕይ ከግቡ ሳናደርስ እንቅልፍ አይወስደንም ብለዉ ሲዝቱ የከረሙትየኢህአዴግ አባል ድርጅቶች “መተካካት” የሚለዉን ዋናዉን የመለስ ፖሊሲ ወደ ጎን ትተዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባካሄዷቸው ስብሰባዎች በአብዛኛው ነባር አመራራቸዉንመርጠዉ ድህረ መለስ ጉዟቸዉን መጀመራቸዉን ዘጋቢዎቻችን ከአዲስ አበባ በላኩልን ዜና ገለጹ፡፡ በዚህ ባሳለፍዉ ሳምንት ዉስጥ አዋሳ፤ መቀሌ፤ አዳማና ባህርዳር ላይ በተካሄዱት የየፓርቲዉ ጉባኤዎች ላይ መለስ ዜናዊ መተካካት ብሎ የጀመረዉ ነባር የፓርቲ ሹማምንትን በአዲስ የመተከት ፖሊሰ እምብዛም በተግባር ባይዉልም አራቱም ድርጅቶች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አንዳንድ ነባር አባላቶቻቸዉን ከፓርቲዉ የስራ አስፈጻሚ ከሚቴ አስወግደዋቸዋል፤  በዚህም መሠረት ደአህዴን ተሾመ ቶጋን፤ ህወሀት ስዩም መስፍንን፤ብርሀኔ ገ/ክርስቶስንና አርከበ ዕቁባይን፤ኦህዴድ  አባዱላ ገመዳን፣ ግርማ ብሩንና ኩማ ደመቅሳን ብአዴን ደግሞ ብርሃን ኃይሉን ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት አሰናብተዋቸዋል።
ሟቹ መለስ ዜናዊ በቀየሰዉ ዕቅድ መሰረት መተካካት እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ ከ2007ቱ ምርጫ በሁዋላ ነባር የአመራር አባላት ሙሉ በሙሉ ይለቃሉ ተብሎ የተገመተ ቢሆንም በሰሞኑ የፓርቲዎች ስብሰባ እንደታየዉ ግን ነባር ታጋዮች ስልጣናቸዉን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ተደርፈጓል። በ2003 ዓ.ም በተደረገዉ የመተካካት ሹምሽር የኃላፊነት ቦታዉን አጥቶ የነበዉ የብአዴኑ አዲሱ ለገሰ ተመልሶ ወደ ስልጣን የመጣ ሲሆን በቅርቡ በወጣት መሪዎች ይተካሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ በረከት ስምኦን፤ ህላዊ ዮሴፍና፣አባይ ወልዱ ጭራሽ ስልጣናቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸዉ ታዉቋል።
በ2003 ዓም በተደረገዉ መተካካት የመንግስትና የፓርቲ ኃላፊነታቸውን የለቀቁት ስዩም መስፍንና ሌሎች ዘጠኝ የህወሃት አባላት ከጤና ጋር በተያያዘ በራሳቸው ፈቃድ  ድርጅቱን ለመልቀቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የተሰናበቱ ሲሆን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ግን የእነዚህን ሰዎች መሰናበት ከመተካካት ጋር አያይዞ ዘግቧል። በአጠቃላይ ብዙ ዉጣዉረድና ድራማ የታየበት የዘንድሮዉ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስብሰባ ሲጀመር የመለስ ዜናዉን ራዕይ ከግቡ እናደርሳለን በሚል መሪ ቃል የተጀመረ ሲሆን ሲፈጸም ግን በመርገጥ “መተካካት” የሚለዉን የድርጅቱን መስራች አላማና ራዕይ በሌላ ነገር በመተካት ተፈጽሟል።
ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማቅረባቸው አጋጣሚ ሳይሆን ከመለስ ህልፈት በሓላ በህወሃት ውስጥ ከተፈጠረው ልዩነት ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ምንጫችን ቢጠቅስም ይህን በተመለከተ ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ብዙዎች እንደሚገምቱት ከአርከበ እቁባይ ጋር ጤነኛ ግንኙነት ያልነበራት  አዜብ መስፍን በዚህ ጉባኤ በድል አድራጊነት ወጥታለች።
ከፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የሚካሄደው የኢህአዴግ ጉባዔ ኃይለማርያም ደሳለኝን በሊቀመንበርነት፣ ደመቀ መኮንን በምክትል ሊቀመንበርነት በድጋሚ ይመርጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
የወያኔ ኢህአዴግ ድርጅቶች ያደረጉትን ሹም ሽር በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የቀድሞ የሀወሀት ነባር ታጋይ ፡ ምርጫውን “ውሀ ቢወቅጡት ነው” ብለውታል። “ከእነዚህ ሰዎች ምንም የሚጠበቅ ነገር የለም፣ ምን አዲስ ነገር እንደማይፈጥሩም ይታወቃል። የአፈና ስርአቱ እንደሚቀጥል ጥሩ ማሳያ ነው” ብለዋል ታጋዩ።

onsdag 20. mars 2013

ቋንቋ የሕወሃት የጥፋት ሚዛን እና የመጭው ዘመን የኢትዮጵያዊያን ስጋት


መጋቢት 19 2013

ልቃቂት ነው ሂዎት፤ በእንዝርት ላይ እንደሚሽከረከረው የጥጥ ንድፍ ዘለላ እየተጠማዘዘ እየተሽመለመለ፣ እየጠበቀና እየላላ፣ እየተወጠረና እየረገበ የሚጠመጠም የሂዎት አንጓ። ያንዱ ሂዎት ዘርፍ በሌላው መሰረት ላይ እየተመጠነና እየተደረበ የሚከወን ኩነት። የስረኛው የላይኛውን ተሸክሞ፣ የላይኛውም በስረኛው ላይ ያለጭንቀት ተመቻችቶና ተንደላቆ የሚቀመጥበት ልቃቂት ነው ሂዎት። ደግሞም እንደ ታሪክ የሚመዘዝ፣ የሚተረክ እንደ ልቃቂት የፈትሉን ጫፍ ይዘው የሚተረትሩት የሚያወጉት፤ ክፉ ደጉን፣ ሳቅ ዋይታውን፣ የጀግንነት የፍቅር ወጉን፣ ያንን ዘመን ያን የጥንቱን፣ የነንቶኔን የነንቶኔን፣ ምርቃቱን ቱፍቱፍታውን፣ የልጅነት ያፍላነቱን፣ የሚያሳየን የሚያሞቀን፣ ወዲያው ደግሞ የሚያበርደን፣ አበሳጭቶ የሚያነደን፣ አስደስቶ የሚያነጥረን፣ ያው ሂዎት ነው ልቃቂቱ፣ የጥንት ያሁን ወደፊቱ፣ እናም እንዲህ እንዲህ ብሎ፣ ስቃያችን አበሳችን ፉከራችን በያይነቱ ተጠቅልሎ፣ አሁን እኛ ከለንበት እኔ ዛሬ ከማወራው፣ ታሪክ አንጓ እንኳ ለመድረስ 68 ዓመት ሞላው። ይችን ትንሽ የታሪክ ጫፍ፣ ይዘን ሽምጥ ስንከንፍ፣ ልክ ከ68 ዓመት ደጃፍ፣ ሆሎኮስት ነው የሚገዝፍ። ከምስራቅ ጫፍ ጃፓን ጠረፍ፣ እስከ አሜሪካ ዳር ድንበር ጽንፍ፣ ከሩሲያ ጀርመን ጓዳ፣ ሳውዝ አፍሪካ ድረስ የፈነዳ፣ የዓለምን ቅስም የሰበረ፣ ያማረረ ያሳረረ፣ አውራ ኩነት እኩይ ተግባር ይህ ነበረ። እኔም እንግዲህ ዛሬ፣ ከታሪክ አንጓ ቆንጥሬ፣ ከሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር እየቃኘሁ፣ ዝግጅቴን ያው ለእናንተ ብያለሁ።
ኩነቱ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በቅርብ ርቀት የተከወነ ቢሆንም ለወቅቱ ከፍተኛ የሚባል ዝግጅት ተደርጎበታል። ዓለምን በሁለት ጎራ አቧድኖ አቆራቁሷል አፋጅቷልም። እስከ አሁንም ድረስ ለማሰብ የሚያዳግቱ፣ ለማስታወስ የሚዘገንኑ፣ ለማየት የሚቀፉ በፍርሃት የሚያርዱ ድርጊቶች ተከውኖበታል። በወቅቱ የወደመውን ንብረት የጠፋውን ሃብት መጠን ለጊዜው እንተወውና ስድስት ሚሊዮን አውሮፓዊያን ይሁዲዎችን ጨምሮ ካስራ አንድ ሚሊዮን በላይ ንጹሃን ዜጎች ሂዎታቸውን ገብረውበታል- ሆሎኮስት ሁለተኛው የዓለም ጦርነት።
ዓላማዬ ስለ ሁለተኛው ዓለም ጦርነት መተረክ ወይም በወቅቱ ስለጠፋው የንብረትና የሂዎት ብዛት መዘርዘር አይደለም፤ ሆሎኮስት እየተባለ ስለሚታወቀውና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት አንድን ዘር ለይቶ የማዳከም፣ የማመናመንና የማጥፋት እኩይ ስራ በእኛም አገር የመከሰቱ አይቀሬነት ስላሰጋኝ አንዳንድ ለማለት እንጅ።
ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጀምሮ በጀርመን ፖለቲካ በአክራሪ ብሔርተኛ ጀርመኖች አማካኝነት በሰፊው ሲቀነቀን የነበረው ፓን ጅርመኒዝም ጀርመንኛና የጀርመን ተወራራሽ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ሀገሮችን ወደ አንድ ሀገርነት ለመቀየር ብዙ ስራ ሰርቷል። በመጨረሻም በአዶልፍ ሂትለር የሚመራ ቋንቋን ብሔርንና ዘርን መሰረት ያደረገ ናዚ ፓርቲን መስርቷል።
በሀገራችንም በሀገር አቀፍ ደረጃ በ1950ዎቹና 1960ዎቹ ሲቀነቀኑ ከነበሩት የዲሞክራሲ ጥያቄዎችና የብሄሮች እኩልነት ፍላጎቶች ባፈነገጠ መልኩ፤ የትግራይን ትንሽ ጎጥ ከኢትዮጵያ ነጥሎ በማየትና (ፓን ትግራያኒዝም ልንለው እንችላለን) የዚህን ክልል ፍላጎት ብቻ ለማሟላት የሚተጋ ሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) የተባለ ድርጅት በቀድሞው ጎጠኛ መሪ መለስ ዜናዊ አማካኝነት መስርቷል። ይህ ድርጅት ልክ እንደ ፓን ጀርመኖቹ ናዚ ፓርቲ ቋንቋን ብሔርንና ዘርን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት በመመስረት ባንዱ ወይም በሌላ ምክንያት ትግሪኛ የሚናገሩ አካባቢዎችን በሙሉ የትግራይ ክልል አካል ናቸው በማለት በራሱ የቅዠት ካርታ ውስጥ አካቷል። በዚህም ምክንያት ከወሎ፣ ከጎንደር እንዲሁም ከአፋር ሰፋፊ መሬቶችን ወደ ትግራይ ክልል ተካተዋል።
ሂትለርና ናዚ ፓርቲ ምክንያቱ እስካሁንም ድረስ በግልጽና በእርግጠኝነት ባይታወቅም በሃብት በልጠውናል፣ ከኛ ይልቅ እነሱ ከፍ ብለው ታዩ፣ ሃይማኖታቸውን ከመጥላትና ጀርመን ለአርያን ብቻ ከሚል እጅግ ጠባብ አስተሳሰብ በመነሳት በጀርመንና በደፍን አውሮፓ ይኖሩ የነበሩ ከስድስት ሚሊዮን በላይ አይሁዶችን በግፍ ጨፍጭፏል። ሕወሃትም በኢትዮጵያ ገና ከጅምሩ በ1968 ዓ/ም ካወጣው ጥበት ያጠበበው ማንፌስቶው ጀምሮ አማራ የሚባለውን ብሔር አምርሮ ጠልቷል። የትግራይ ሕዝብ እራሱን እንዲጠላ፣ በአካባቢውም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስራ እንዳያገኝ፣ በትምህርት በጤና በግብርና ወደ  ሗላ እንድንቀር፣ በትግራይ አካባቢ ኢንዱስትሪዎች እንዳይገነቡና ባጠቃላይ የአማራ ብሔር በትግራይ ብሔር ላይ ከፍተኛ የብሔር ጭቆና ታካሂዳለች ይላል ጥበት ያጠበበው ማኒፍሰቶ። ከዚህም እጅግ በከፋ መልኩ ልክ ናዚዎች የይሁዲዎችን ሃይማኖት እንዳራከሱት ሁሉ ሕወሃትም ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን የአማራው የግል ሃብት አድርጎ በመቁጠር የትምክህተኛውና የነፍጠኛው ዋሻ በማለት የብዙውን ኢትዮጵያዊ ሃይማኖት ሲያራክስ መቆየቱ ያደባባይ ሚስጥር ነው።
ናዚዎች ይሁዲዎች እንዲጠሉ፣ እንዲገለሉ፣ ስራ እንዳያገኙ፣ እንዲዋከቡ፣ ሃብታቸው እንዲወረስ፣ እንዲሰደዱና ሕዝባዊ ፖሊሶችንና ብሄራዊ ወታደሮችን ሳይቀር በማዝመት በግፍ እንዲገደሉ አድርገዋል። ሕወሃትም በኢትዮጵያ አማራው ቦታ እንዳይኖረው በርትቶ ሰርቷል። ስራ እንዳያገኝ የተለያዩ የተንጋደዱ መለኪያዎችን በመጠቀም አስወግዷል። በስራ ላይ የነበሩትንም ውጤት ተኮር፣ ቢ ፒ አርና የመሳሰሉትን ስልታዊ መመንጠሪያች በመጠቀም ከስራ አፈናቅሏል። በልማት ሰበብ አማራው ከይዞታ መሬቱ ከመኖሪያ ቤቱ እንዲፈናቀል አድርጓል። ከዚህም በባሰ መልኩ ሲጨቁናችሁ የኖረው አማራው ነው በማለትና የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ሕወሃት የራሱን ፖሊሶችና ወታደሮች በማዝመት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አማራው እንዲመነጠርና እንዲገደል ከማድረጉም በተጨማሪ ከነ ሂወቱ ወደ ገደል እንዲወረወር ማድረጉ የቅርብ ጊዜ አሳዛኝ ትዝታችን ነው።
ሂትለርና ናዚ ፓርቲው ጥላቻቸው እጅግ አይሎ ‘ጀርመን ለአርያን ዘር ብቻ ይሁዲዎች ወደ ሀገራቸው’ በማለት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ይሁዲዎችን ከጀርመንና ከአጎራባች የአውሮፓ አገሮች እንዲሰቃዩ፣ እንዲዋከቡና ሃብታቸው እየተወረሰ እንዲባረሩ አድርጓል። በመጨረሻም እስካሁንም ድረስ ሆሎኮስት በመባል የሚታወቀውን ዘግናኝ ግድያ ከስድስት ሚሊዮን በሚበልጡ ይሁዲዎች ላይ ፈጽሟል። ሕወሃትም በሀገራችን በአማራው ላይ ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸም ላይ ይገኛል። ሕወሃት ከናዚም እጅግ በከፋ መልኩ አማራውን ከራሱ ሀገር በማፈናቀል ሰርቶ የመኖር መብቱን አሳጥቶ በስማሰቃየት፣ በማዋከብና ሰርቶ ያፈራውን ሃብት በግፍ በመውረስ እያንከራተተው ይገኛል። ምናልባትም የቀረው ልክ እንደ ናዚ ጀርመን በማጎሪያ ካምፖች በማጠራቀም የህብረት ግድያ ማከናወን ብቻ ነው። ይህንንስ እንዳይከውን ሕወሃትን ምን የሚያግደው ሃይል አለ? ለሀገር አቀፍም ሆነ ዓለም አቀፍ ህግጋት የሚገዛ አይደለምና፤ አበቃሁ።

ከታሰሩት ሰልፈኞች አንደበት (ፎቶ እና የእስር ቤት ውሎ ዘጋባቸውን ይዘናል)


(በበፍቃዱ ኃይሉ)

EMF – መጋቢት 8/2005 የባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር እና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የኢትዮጵያውያን ጠላት የነበረው የፋሺስት ጣሊያን ጄኔራል ግራዚያኒን ኃውልት (በጣሊያን አገር፣ የትውልድ መንደሩ አካባቢ) መቆም በመቃወም የሰልፍ ጉዞ ከስድስት ኪሎ (የካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ኀውልት) እስከ ጣሊያን ኤምባሲ ድረስ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነበር፡፡ የሰልፉ ተሳታፊዎች ከጀርባው ላይ ‹‹ለግራዚያኒ ኀውልት ማሠራት አባቶቻችን የከፈሉትን መስዋዕትነት ማራከስ ነው›› የሚል ጽሑፍ የታተመበት ቀይ ቲ-ሸርት ለብሰው ነበር፡፡ የኢሕአዴግ ካድሬዎች ደግሞ ‹‹ይቺ ባቄላ…›› በሚል ምክንያት ነው መሰለኝ ‹‹የተቃውሞ ሰልፍ…›› የሚባለውን ነገር ለማስቆም ራሱ ግብግብ ፈጠረ፣ ወጣቷ ዓለምን የቀን አጋጣሚ ስድስት ኪሎ አካባቢ፣ በዕለተ እሁድ (መጋቢት 8/2005) አንቀዥቅዦ አመጣት፡፡ የለበሰችው የአዘቦት ቀይ ቲ-ሸርት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ለመዋል ምክንያት ይሆነኛል ብላ አልተገመተችም ነበር፡፡ ፌዴራል ፖሊስ ቀይ ለባሾቹን ማፈስ ሲጀምር ዓለምንም አብሮ አፍሶ አጋዛት፡፡
qeylebashፎቶ ላይ ከፖሊሶች ጋር ዓይን ለዓይን ተጋጠመ፡፡ እሱም ተይዞ ተከተላቸው፡፡ ይህ ድንገተኛ እስረኛ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ሆነ፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ለሥራ ጉዳይ ጓዙን ጠቅልሎ ወደአፋር ለመጓዝ እየጠበቁት ያሉ ባልደረቦቹን ለማግኘት በታክሲ ውስጥ ይጓዝ የነበረ አንድ ሰው ከስድስት ኪሎ ተነስቶ አምስት ኪሎ እስኪደርስ የተመለከተውን ሁካታ ዓይቶ ላለማለፍ ከታክሲ ይወርዳል፡፡ ፖሊሶች ከሰልፈኞቹ ውስጥ አሳደው የያዙትን እያፈሱ መኪና ውስጥ ሲያጉሩ፣ ከፖሊሶች ዕይታ እየተሰወረ በሞባይሉ ፎቶ ለማንሳት ሲሞክር፣ አንድም የረባ ፎቶ ሳያነሳ በሦስተኛው ፎቶ ላይ ከፖሊሶች ጋር ዓይን ለዓይን ተጋጠመ፡፡ እሱም ተይዞ ተከተላቸው፡፡ ይህ ድንገተኛ እስረኛ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ሆነ፡፡
የታፈሱት ሰልፈኞች ሁሉ የታጎሩት በአራዳ ፖሊስ መምሪያ ጊቢ ውስጥ ነበር፡፡ ጊቢው ውስጥ እንደደረስኩ ከፊት ለፊቴ ደረጃው ላይ የተኮለኮሉትን ሰልፈኞች ተመለከትኩ፡፡ ወጣቶቹ ታፍሰው የገቡ ሳይሆን ወደው የተሰበሰቡ ይመስሉ ነበር፡፡ እንዲያውም በገባሁ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ጮክ ብለው ይዘፍኑ ጀመር፡-
‹‹… ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም፣ ባባቶቻችን ደም
እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም…››
በዚህ ጊዜ ከፖሊሶቹ አንዱ አብሮ ሲዘምር ይታይ ነበር፡፡ ፖሊሶቹ የተሻለ ትሁቶች ቢሆኑም፣ ሲቪል ለባሾቹ ግን ማመናጨቅ እና ማዋከብ ዋነኛ ሥራቸው ነበር፡፡ እኔን በመኪና ይዘውኝ ከመጡት ውስጥ አንዱ ‹‹ዴሞክራሲ በዛ…›› የሚለውን ቃል እየደጋገመ በቁጭት ይናገራል፡፡ ብዙዎቹ የመምሪያው ፖሊሶች ከየት እንደመጣ የማያውቁት ኮማንደር ግን የተቆጨው በመዘግየቱ ነው፤ ‹‹ይሄን ያክል እስኪሰባሰቡ መቆየት አልነበረብንም›› አለ – እኔው ጎን ቁጭ ብለው ሲነጋገሩ፡፡ በሬዲዮናቸው ሲለዋወጡ ከነበረው ውስጥም ‹‹ሱማሌ ተራ የተጎዳውን ሰውዬ የት ወሰዳችሁት?… ተክለሃይማኖት ሆስፒታል?…›› ይባባሉ ነበር፡፡ በዚሁ ጉዳይ ይሁን አይሁን ግን ‹‹መረጃም (ማስረጃም)›› አልነበረኝም፡፡
ጊቢው ውስጥ ከሌሎቹ እንዳልቀላቀልና ብቻዬን እንድቆይ አድርገውኛል፡፡ ባንድ በኩል ስልኬ ላይ ያሉትን ፎቶዎች አጥፍተው ይፈቱኛል፣ ጉዞዬም ይቀጥላል በሚል ደስ ብሎኛል፡፡ በሌላ በኩል በዓይን የማውቃቸውን እነዚያን ልጆች ቀረብ ብዬ አለማነጋገሬ ቆጭቶኛል፡፡ በዚህ መሐል ግን ሁሉም እየሄዱ ቃል ሲሰጡ ቆዩ (ቃል ሲባል ቃል እንዳይመስላችሁ፤ ከስም አንስቶ የኔ የምትሉትን ነገር በሙሉ ይጠይቋችኋል)፤ ከዚያም የኔም ተራ ደረሰና ቃል ሰጥቼ ሳበቃ እኔም በቀላሉ እንደማልሰናበት ሲያረዱኝ የጓዝ ኮተቴን ሁሉ አስመዝግቤ እዚያው ተጠቃለልኩ፡፡
ከዚያም ቃል የመስጠቱ ሥነ ስርዓት ቀጠለ፤ የመጣው ሁሉ በራሱ መንገድ ያንኑ ጥያቄ መልሶ፣ መላልሶ እያንዳንዱን ታሳሪ (ተጠርጣሪ ልበል ይሆን?) ይጠይቃል፤ እያንዳንዱም ተጠርጣሪ ይመልሳል፡፡ ሆኖም ብዙዎቹን መርማሪዎች የብስጭት መንስኤ የሚሆን ነገር ባለራዕዮቹ ወጣቶች ሳይናገሩ አይወጡም ነበር፡፡ ብሔር ሲባሉ ‹‹ኢትዮጵያዊ›› ይላሉ፡፡ ይህንን የሚሉት ‹‹ብሔር›› የሚለው ቃል ከግዕዝ የተወሰደ ሲሆን፣ ትርጉሙም ‹‹አገር›› መሆኑን እያጣቀሱ ነው፡፡ ታዲያ ይህ አባባል ለመርማሪዎቹ የሚያበሳጭ ድፍረት ነበር፡፡
ፖሊሶቹ የሆነችውን ሁሉ እየደወሉ፣ ለአለቆቻቸው ይናገራሉ፡፡ ከዚህ መሐል ከሰልፈኞቹ አንዱ ለብሶት የነበረው ባንዲራ ላይ በእስክርቢቶ የጻፈውን ደብዳቤ ከስልኩ ወዲያ ላለ ሰው በንባብ ሲያጽፉት ሰምቻለሁ፡፡ ጽሑፉ ባብዛኛው መንፈሳዊ ነው ቢባል ይቀላል፡፡ ‹‹ለእመቤታችን በአስራትነት የተሰጠችው አገራችን ኢትዮጵያ…›› ብሎ ነው የሚጀምረው፡፡
ምርመራው/ጥያቄው ቀጥሏል፤ ከጠያቂዎቹ መካከል የደኅንነት እና የኢንሳ ሰዎችም ነበሩበት፡፡ ከጥያቄዎቻቸውም ውስጥ የኢሜይል አድራሻ እና የይለፍ ቃል፣ የፌስቡክ አድራሻ እና የይለፍ ቃልም ይጠይቁ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ታሳሪ (ተጠርጣሪ አልልም) ስሙን በቪድዮ ካሜራ ፊት እንዲናገር ይገደድ ነበር፡፡ እንግዲህ ይህንኛው መጀመሪያ ላይ እያንዳንዱ ሰው ከተነሳው ፎቶ በተጨማሪ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ የጅምላ እስር ውስጥ ካስተዋልኳቸው ጉዳዮች ውስጥ የሴቶቻችንን ጀግንነት ነበር፡፡ ለምሳሌ፣ እኔ ያለምንም ማንገራገር ምስሌን አስቀርጬ ወደቃለመጠይቁ ሳልፍ የሰማያዊ ፓርቲዋ አመራር አባል ሐና ዋለልኝ ‹‹አልቀረጽም፣ አሻፈረኝ›› ብላ ስትሟገት ድምፅዋ ይሰማኝ ነበር፡፡
ሲመሽ ይፈቱን ይሆን? እዚሁ ያሳድሩን ይሆን? ሌላ ቦታ ይወስዱን ይሆን? ምን ብለው ይከሱን ይሆን? እየተባባልን የተሰባሰብንባት አንዲት በረንዳ መሳይ ክፍል ውስጥ፣ ኢቴቪ በቀጥታ የሚያስተላልፋቸውን የአዳማ እና የመቐለ የኦሕዴድ እና የሕወሓት ስብሰባዎች መኮምኮም ጀመርን፡፡ አሳሪዎቻችንም በስልክ አለቆቻቸውን እያነጋገሩ ሽር ጉዳቸውን አጧጡፈውታል፡፡ ኢቴቪም ብቻውን በዓሉን ማክበር አልቻለም፡፡ መብራቱ ብልጭ ድርግም አበዛ፡፡ ብልጭ ድርግም አልኩ እንጂ ያበዛውስ ድርግም ማለት ነው፤ አልፎ፣ አልፎ ግን ላፍታ ብልጭ እያለ ነበር፡፡ በጨለማው ውስጥ ራታችንን በጨለማ ተቋደስን፡፡ ሁላችንም ምሳ ያልበላን ቢሆንም አንዳንዶች ግን ቁርሳቸውንም አልበሉም፡፡
የመታሰራችን ዜና በማኅበራዊ አውታሮች በመጠኑ ቢስተገባም የብዙዎቻችን ቤተሰቦች ግን አልሰሙም፤ ደውሎ የማሳወቅ ዕድሉም አልተሰጠንም፡፡ እዚያው ጨለማ ውስጥ ከቆየን በኋላ ወደ 3፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ጃንሜዳ አካባቢ የሚገኝ ማረሚያ (እስር ቤት) በሁለት ዙር ተወሰድን ከ30 በላይ እስረኞች አንድ ላስቲክ ብቻ ወለሉ ላይ የተነጠፈበት ክፍል ውስጥ ብንታጎርም በእርስ በርሳችን ጫወታ ተጠምደን ነበር፡፡ (በነገራችን ላይ እኛ ወደዚህ እስር ቤት ስንዛወር ቀይ ለባሽዋ ዓለም ተለቅቃ ወደቤቷ ሄዳለች፡፡) የሄድንበት በሰልፉ ዋዜማ ሲቀሰቅሱ ከታሰሩ ሌሎች ጋር ተቀላቅለናል፡፡ የጅምላ እስሩ ጉዳይ በዋዜማው እንደተጀመረ ያወቅኩትም ያኔ ነው፡፡ ቀድመው ከታሰሩት ውስጥ ሁለቱ ክፉኛ ቡጢ እና ካልቾ ቀምሰው እንደሆነ ለማወቅ እስኪናገሩ መጠበቅ አያስፈልገንም ነበር፤ የአንደኛው ጃኬት የደረቀ ደም ከፊትለፊት ይታይበታል፡፡
ለአምስት ሰዓት ዐሥራ አምስት ደቂቃዎች ሲቀሩት ግን እንደገና እንድንንቀሳቀስ ተነገረን፡፡ ከኛ ቀደም ብለው ሴቶቹም ወደቀጨኔ (ችሎት መድኃኔዓለም ኮንዴሚኒዬም አጠገበ ያለ) ወረዳ 9 ማረሚያ ቤት እንደተወሰዱ እና ከኛም ውስጥ 12ቶቻችን መከተል እንዳለብን ተነገረን፡፡ እዚያ እንደደረስን ግን ምነው እዚያው በቀረን የሚያስብል ትዕይንት ገጠመን፡፡ እያንዳንዱ ክፍል እላይ በላይ ተደራርበው በተኙ እስረኞች ተጨናንቋል፡፡ ሌላው ቀርቶ ጫማ ማስቀመጫ ቦታ እንኳን በክፍሉ ውስጥ ስለሌለ ጫማዎቻችንን ውጪ እያስቀመጥን እንድንገባ ተገደድን፡፡ ሦስቱ (አራት ሜትር በአራት ሜትር የሚገመቱ) ክፍሎች ውስጥ አንዱ 37፣ አንዱ 34 እና ሌላኛው ውስጥ 30 እስረኞችን ይዟል፡፡
እንዳጋጣሚ 30 ሰዎች የያዘው ውስጥ ነበር እኔ የደረሰኝ፡፡ የኛ ክፍል ይሻላል ተብሎ ዶ/ር ያዕቆብንም አመጧቸው፡፡ ጉዳዩ በጣም አሳዛኝ ነበር፡፡ እኛስ ባልደከመ ጉልበታችን እንችለዋለን፤ ለርሳቸው ግን በጣም ፈታኝ እንደሚሆን መገመት ቀላል ነው፡፡ ክፍሉ በጣም ጥቅጥቅ ብሎ ከመሞላቱ የተነሳ ለኛ ቦታ ለማግኘት የቤቱ ካቦ ተነስቶ እያንዳንዱን እስረኛ እየቀሰቀሰ ማጠጋጋት ነበረበት፡፡ በቦታ ጥበት ምክንያት ደረቁ ወለል ላይ በአንድ ጎናችን እንድንተኛ ከመገደዳችን የተነሳ እኔ ይህን ጽሑፍ እስከምጽፍበት ሰዓት ድረስ ቁርቋሬው የፈጠረው ሕመም ጎኔን አያስነካኝም፡፡ ካቦው አጠጋግቶልን ሲጨርስ ሁላችንንም የገቢ ገንዘብ ተቀበለን እና ተኛን፡፡ እዚያ ክፍል ውስጥ መተኛት ማለት፣ መተኛት ማለት አይደለም፡፡ የክፍሉ መታፈን እና አስቀያሚ ጠረን፣ ሙቀት፣ በዚያ ላይ እየተቀባበሉ የሚያጨሱት ሲጃራ ጢስ፣ ከዚያ እና ከዚህ የሚተኮስ የፈስ ሽታ… ብቻ የአበሳ ናሙና ነበር፡፡ ሌሊቱን ሲዘንብ ማደሩ ግን በከፊልም ቢሆን የክፍሉን አየር አቀዝቅዞታል፤ ችግሩ ዝናቡ ውጪ ያስቀመጥነው ጫማ ውስጥ ውኃ መሙላቱ ብቻ ነበር፡፡
እንደምንም ነጋልንና ወደፍርድ ቤት እንደምንሄድ ተነግሮን ጥንድ ጥንድ እየተደረግ በካቴና ተቆላለፍን፡፡ ከመሐከላችን አንዱ የማኅበሩ አባል፣ ፀጉሩን አጎፍሮ ስለነበር (ለፍርድ ቤቱ ውበት አይመጥንም ብለው ይሆናል) ይቆረጥ አሉና መቀስ አንስተው ይከመክሙት ጀመር፡፡ ፀጉሩን ቆርጠው ሲጨርሱ አሰለፉንና ካቴናችንን ፈቱት፡፡ ‹‹ፍርድ ቤት መወሰዳችሁ ቀርቷል፣ ምናልባት ፖሊስ ጉዳዩን ይፈታዋል›› ተባልንና ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ወደጃንሜዳ ማረሚያ ቤት መልሰው ወሰዱን፡፡ እዚያ ስንደርስ ለፖሊስ ዋስ እያቀረብን እንድንፈታ ተፈቀደልን፡፡ ቀድሞውንም የታሰርነው ያለወንጀል በመሆኑ አስገራሚ ውለታ አልነበረም፡፡
የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስፈልገው ቅድመ ሁኔታ ለመስተዳድሩ ማሳወቅ ሲሆን፣ መስተዳድሩ ደግሞ በ24 ሰዓት ውስጥ ‹‹አይሆንም›› የሚል ደብዳቤ ካልጻፈ እንደተፈቀደ ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ ሰልፍ ማድረጉ ሕጋዊ ስህተት የለበትም፣ ጉዳዩ ባንድ ጀምበር የተወለደ ሳይሆን ጋዜጦች ዜና የሰሩለት፣ ቁጥቦቹ ሬድዮዎች ሳይቀሩ ያወሩለት ጉዳይ ስለሆነ ወንጀል ነው ፍርድ ቤት ሊያቀርቡት አይችሉም/አይገባቸውምም፡፡ ነገር ግን ‹‹…ካፈርኩ አይመልሰኝ…›› ይመስላል በዋስትና እንድንፈታ ፈቅደው ያገቱብንን ንብረቶቻችንን እየመለሱ መጋቢት 9/2005 እኩለ ቀን ላይ አሰናበቱን፡፡

søndag 17. mars 2013

የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው! ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡ እንዲሁም በትላንትናው እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን አስረዋል፡፡ በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ የሚገኙት እና ስማቸው የተገኘ 1. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም 2. አቶ ታዲዎስ ታንቱ 3. አቶ ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ሊቀመንበር) 4. ስለሺ ፈይሳ (የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር) 5. ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ የህግ ጉዳይ ሀላፊ) 6. ሀና ዋለልኝ (የሰማያዊ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ) 7. ጌታነህ ባልቻ (የሰማያዊ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ) 8. ብርሀኑ ተክለያሬድ (የባለራዕይ ወጣቶች ተ/ምክትል ሊቀመንበር) 9. ያሬድ አማረ (የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ጸሀፊ) 10. ኤልሳቤጥ ወሰኔ 11. ሰለሞን ወዳጅ 12. ወይንሸት ንጉሴ 13. እየሩሳሌም ተስፋው 14. ለገሰ ማሞ 15. ትዕግስት ተገኝ 16. አማኑኤል ጊዲና 17. አለማየሁ ዘለቀ 18. አገኘሁ አሰገድ 19. ሻሚል ከድር 20. አሸብር ኪያር 21. ጌታቸው ሽፈራው 22. ግሩም አበራ 23. አቤል ሙሉ 24. ዩሀንስ ጌታቸው 25. ስማቸው ተበጀ 26. ፍቃዱ ወንዳፍራው 27. ባህረን እሸቱ 28. ሄኖክ መሀመድ 29. እንቢበል ሰርጓለም 30. አለማየሁ በቀለ 31. ዩናስ 32. የመኪናው ሹፌር 33. ዮዲት አገዘ 34. ጥላዬ ታረቀኝ


ሰማያዊ ፓርቲ

ዛሬ መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!
እንዲሁም በትላንትናው እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን አስረዋል፡፡
በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ የሚገኙት እና ስማቸው የተገኘ
1. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም
2. አቶ ታዲዎስ ታንቱ
3. አቶ ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ሊቀመንበር)
4. ስለሺ ፈይሳ (የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር)
5. ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
6. ሀና ዋለልኝ (የሰማያዊ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ)
7. ጌታነህ ባልቻ (የሰማያዊ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ)
8. ብርሀኑ ተክለያሬድ (የባለራዕይ ወጣቶች ተ/ምክትል ሊቀመንበር)
9. ያሬድ አማረ (የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ጸሀፊ)
10. ኤልሳቤጥ ወሰኔ
11. ሰለሞን ወዳጅ
12. ወይንሸት ንጉሴ
13. እየሩሳሌም ተስፋው
14. ለገሰ ማሞ
15. ትዕግስት ተገኝ
16. አማኑኤል ጊዲና
17. አለማየሁ ዘለቀ
18. አገኘሁ አሰገድ
19. ሻሚል ከድር
20. አሸብር ኪያር
21. ጌታቸው ሽፈራው
22. ግሩም አበራ
23. አቤል ሙሉ
24. ዩሀንስ ጌታቸው
25. ስማቸው ተበጀ
26. ፍቃዱ ወንዳፍራው
27. ባህረን እሸቱ
28. ሄኖክ መሀመድ
29. እንቢበል ሰርጓለም
30. አለማየሁ በቀለ
31. ዩናስ
32. የመኪናው ሹፌር
33. ዮዲት አገዘ
34. ጥላዬ ታረቀኝ

lørdag 16. mars 2013

ሰላማዊ ትግል እንደ እስላማዊ ትግል…!


የልጅነት ወዳጄ ሁሴን ከድር እንደነገረኝ “እስላም” የሚለው ስም ራሱ የመጣው ሰላም ከሚለው ነው፡፡ ሁሴን የነገረኝ ሀሰት እንደሌለው ያረጋገጥኩት፤ ያኔውኑ የእርሱን ሰላማዊነት ስመለከት ነበር፡፡ ሁሴን እጅግ ሰላማዊ ሙስሊም ወዳጃችን ነው!

እስላም ማለት ሰላም ማለት ነው… የሚለውን በደንብ ለማስረገጥ ከፈለጉ ደግሞ ከድፍን አንድ አመት ሞልቶ የፈሰሰውን ሰላማዊ ትግል አይቶ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህንን መረዳት ካልተቻለ የህክምና እርዳታ ያስፈልገናል ማለት ነው፡፡ሰላማዊ ትግል እንደ እስላማዊ ትግል…!
ሁሌ ክበር የሚሉት አላህ ብርታቱን የሰጣቸው ሰላማዊ ሙስሊም ታጋዮች በተለያየ ጊዜ መንግስታችን ስም ማውጣት ብርቁ ስላልሆነ አንዴ አሸባሪ አንዴ አክራሪ ቢላቸውም እነርሱ ግን ከአመት በላይ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተሞላበት ፍፁም ሰላማዊ ትግል እያከናወኑ መንግስታችንን ኩም አድርገውታል፡፡
ችግሩ መንግስት “ኩም” ሲያደርጉት ምንም ሳይነካ እሪ… ብሎ እየጮኸ በድምሩ “እሪ… ኩም” እያለ ዘፈን አይሉት ልቅሶ ሲያሰማ ነገሩ እጅግ አስቂኝ ሆኖ ከርሟል፡፡ ይሄኔ እኛም “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል” የሚለው ተረት ስለተያዘብን እንደ አቅማችን አዲስ ተረት ተርተንለታል “መንግስታችን ራሱ በጥፊ ተማትቶ ራሱ ጯ! ብሎ ይጮሃል!”
ለማንኛውም ለመረጃ ያህል በዛሬው ጁምአ በመላው ሀገሪቱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለአላህ ተማፅኗቸውን ለመንግስት ደግሞ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ይቀጥላሉ! መንግስት የሚሰማ አይመስለንም ለራሱ ጮክ ብሎ እየጮኸ ስለሆነ ሌሎችን ለመስማት መቻሉን እንጃ…! አላህ ግን ይሰማል! መልሱም ያለው እርሱ ዘንድ ነው!
እኔ የምለው ግን በሀገር ቤት የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎቻችን ሰላማዊ ትግልን ከእስላማዊ ትግሉ ቢኮርጁ ማርክ የሚቀንስባቸው ማነው…! የምሬን እኮ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያለኝ አክብሮት ከፍ ያለ ነው፡፡ ተቃዋሚዎቻችን ሁልግዜም ያቺኑ ምርጫ ጠብቀው በአይሱዙ እና በሚኒባስ “ጃ ያስተሰርያል!” የምትለዋን ዘፈን እያዘፈኑ ምረጡን ብለው ሲቀሰቅሱ ስሰማ ደስ ለኛል፡፡ እርግጥ ነው ይሄ አዝናኝም አስደሳችም የሆነ ሰላማዊ ትግል ነው፡፡ ነገር ግን ዘጠና ሚሊዮን ለደረሰው ህዝብ እና ከዘጠና ሚሊዮን በላይ ለሆነው ጉስቁልናችን በቂ ትግል አይደለም፡፡
እና… እናማ ሰላማዊ ትግሉ እንደ እስላማዊ ትግሉ አይነት ነገር ይጨመርበት! ቢቻል ከዛም ተጨማሪ ነገር ጨመርመር ማድረግ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ተፈቀደም አልተፈቀደም ሰልፍ መውጣት፣ አደባባይ መዋል፣ ጩኸት ማሰማት እና ወዘተ መወዘት… ሰላማዊ ታጋይ የሚያስብለው ዋናው ሰላማዊ ሆኖ መገኘት ነው እንጂ የተፈቀደ ያልተፈቀደ እያሉ በትግል ላይ መሽኮርመም አግባብ አልመስልህ ብሎኛል! ምንም ማድረግ አይቻልም…
ከመሰለኝ እንግዲህ መተንፈስ ነው! ታፍኜ አልሞትም! (ተቃዋሚዎች ሰምታችኋል!)
የልጅነት ወዳጄ ሁሴን ከድር እንደነገረኝ “እስላም” የሚለው ስም ራሱ የመጣው ሰላም ከሚለው ነው፡፡ ሁሴን የነገረኝ ሀሰት እንደሌለው ያረጋገጥኩት፤ ያኔውኑ የእርሱን ሰላማዊነት ስመለከት ነበር፡፡ ሁሴን እጅግ ሰላማዊ ሙስሊም ወዳጃችን ነው!
እስላም ማለት ሰላም ማለት ነው… የሚለውን በደንብ ለማስረገጥ ከፈለጉ ደግሞ ከድፍን አንድ አመት ሞልቶ የፈሰሰውን ሰላማዊ ትግል አይቶ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህንን መረዳት ካልተቻለ የህክምና እርዳታ ያስፈልገናል ማለት ነው፡፡
ሁሌ ክበር የሚሉት አላህ ብርታቱን የሰጣቸው ሰላማዊ ሙስሊም ታጋዮች በተለያየ ጊዜ መንግስታችን ስም ማውጣት ብርቁ ስላልሆነ አንዴ አሸባሪ አንዴ አክራሪ ቢላቸውም እነርሱ ግን ከአመት በላይ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተሞላበት ፍፁም ሰላማዊ ትግል እያከናወኑ መንግስታችንን ኩም አድርገውታል፡፡
ችግሩ መንግስት “ኩም” ሲያደርጉት ምንም ሳይነካ እሪ… ብሎ እየጮኸ በድምሩ “እሪ… ኩም” እያለ ዘፈን አይሉት ልቅሶ ሲያሰማ ነገሩ እጅግ አስቂኝ ሆኖ ከርሟል፡፡ ይሄኔ እኛም “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል” የሚለው ተረት ስለተያዘብን እንደ አቅማችን አዲስ ተረት ተርተንለታል “መንግስታችን ራሱ በጥፊ ተማትቶ ራሱ ጯ! ብሎ ይጮሃል!”
ለማንኛውም ለመረጃ ያህል በዛሬው ጁምአ በመላው ሀገሪቱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለአላህ ተማፅኗቸውን ለመንግስት ደግሞ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ይቀጥላሉ! መንግስት የሚሰማ አይመስለንም ለራሱ ጮክ ብሎ እየጮኸ ስለሆነ ሌሎችን ለመስማት መቻሉን እንጃ…! አላህ ግን ይሰማል! መልሱም ያለው እርሱ ዘንድ ነው!
እኔ የምለው ግን በሀገር ቤት የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎቻችን ሰላማዊ ትግልን ከእስላማዊ ትግሉ ቢኮርጁ ማርክ የሚቀንስባቸው ማነው…! የምሬን እኮ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያለኝ አክብሮት ከፍ ያለ ነው፡፡ ተቃዋሚዎቻችን ሁልግዜም ያቺኑ ምርጫ ጠብቀው በአይሱዙ እና በሚኒባስ “ጃ ያስተሰርያል!” የምትለዋን ዘፈን እያዘፈኑ ምረጡን ብለው ሲቀሰቅሱ ስሰማ ደስ ለኛል፡፡ እርግጥ ነው ይሄ አዝናኝም አስደሳችም የሆነ ሰላማዊ ትግል ነው፡፡ ነገር ግን ዘጠና ሚሊዮን ለደረሰው ህዝብ እና ከዘጠና ሚሊዮን በላይ ለሆነው ጉስቁልናችን በቂ ትግል አይደለም፡፡
እና… እናማ ሰላማዊ ትግሉ እንደ እስላማዊ ትግሉ አይነት ነገር ይጨመርበት! ቢቻል ከዛም ተጨማሪ ነገር ጨመርመር ማድረግ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ተፈቀደም አልተፈቀደም ሰልፍ መውጣት፣ አደባባይ መዋል፣ ጩኸት ማሰማት እና ወዘተ መወዘት… ሰላማዊ ታጋይ የሚያስብለው ዋናው ሰላማዊ ሆኖ መገኘት ነው እንጂ የተፈቀደ ያልተፈቀደ እያሉ በትግል ላይ መሽኮርመም አግባብ አልመስልህ ብሎኛል! ምንም ማድረግ አይቻልም…
ከመሰለኝ እንግዲህ መተንፈስ ነው! ታፍኜ አልሞትም! (ተቃዋሚዎች ሰምታችኋል!)

በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች


በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች

የጋምቤላ “አኬልዳማ” እየተደረሰ ነው
በጋምቤላ የመከላከያ ሰራዊት ከጨፈጨፋቸው ሰዎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው አቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ ለማጣራት ከአሜሪካ መንግስት የተላኩት የፎረንሲክ (ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉ) ባለሙያዎችን ጋምቤላ ገብተው የማጣራት ሥራ ጀምረዋል። “የጋምቤላ አኬልዳማ” እየተዘጋጀ እንደሆነም ተሰማ።በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች
የጎልጉል የጋምቤላ መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ጋምቤላ የደረሱት የአሜሪካ ዜጎች የሄዱበትን ጉዳይ ለማከናወን ከክልሉና ከመከላከያ ሰራዊት ባለስልጣናት ዘንድ እክል ገጥሟቸው ነበር።
የፎረንሲክ ባለሙያዎቹ የዜጋቸውን አሟሟት መንስኤና የጉዳት መጠን ለማጣራት ጋምቤላ እንደደረሱ አስከሬኑ በስውር የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ እንደሚፈልጉ፣ አስከሬኑ ላይ የዲኤንኤ ምርመራ በማካሄድ የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ፣ የጉዳቱን መጠንና በምን ያህል ጥይት እንደተደበደበ ለማጣራት፣ ከዚያም በላይ ለምርመራ ስራቸው ይረዳቸው ዘንድ የሚፈልጉትን መረጃ ለመሰብሰብ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ መሄድ እንደሚፈልጉ ጠይቀው እንደነበር ለክልሉ መንግስት ቅርብ የሆኑ ለጎልጉል ገልጸዋል።
ጥያቄውን መቀበል የተሳናቸው የመከላከያና የክልሉ ባለስልጣናት አስከሬኑ መመርመር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን፣ ከተቀበረ የቆየ በመሆኑ ለማውጣት አስቸጋሪ እንደሆነና እንደማይቻል ለመርማሪዎቹ ገልጸው ነበር። “ስራው የኛ ነው” ያሉት መርማሪዎቹ አስከሬኑ በየትኛውም ደረጃ ላይ ቢገኝም ማየት እንደሚፈልጉ፣ ይህ አቋም እንደማይቀየር መሆኑን አመልክተው አስከሬኑ የተቀበረበት ቦታ ደርሰው የሚፈልጉትን ምርመራ ማድረጋቸው ታውቋል። አከራካሪ የነበረውና ግድያው የተፈጸመበት ቦታ የመጓዙ ጉዳይ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጭ፣ የቀረበው መልስ አስገራሚ እንደነበር ይገልጻሉ።
“ቦታው ላይ ደም የለም፣ ማንንም አታገኙም፣ ምን ያደርግላችኋል?” የሚሉ መከራከሪያዎችን ባለሥልጣናቱ ቢያቀርቡም ተቀባይነት ማግኘት አልቻሉም። አጣሪዎቹ ወደ ስፍራው ከመሄዳቸው በፊት ካድሬዎች ሽማግሌዎችንና ያካባቢው ነዋሪዎችን በማባበል የቅስቀሳና ፊልም የማዘጋጀት ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የጎልጉል ምንጮች አመልክተዋል።
ምንጮቹ እንዳሉት የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማባበል አሳ አስጋሪዎቹ ሲጨፈጨፉ የታሰሩት የቀበሌ ሊቀመንበር ከልጆቻቸው ጋር ከእስር እንዲፈቱ ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ አንድ ወጣት ከእስር ነጻ እንዲሆን በተላለፈ ውሳኔ መሰረት ተለቅቋል። ይህ ሁሉ የሚደረገው የአካባቢውን ሽማግሌዎች ለማባበልና “የጋምቤላ አኬልዳማ” በማለት የሚሳለቁበት ዘጋቢ ፊልም በተሳካ ሁኔታ እንዲሰራ ለመቀስቀሻነት ነው።
በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን በማምራት የበጋውን ደረቅ ወቅት ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባ አካሂዶ ተኩስ በመክፈት አስራ ሁለት የሚጠጉ ንጹሃንን መግደሉን መዘገባችን ይታወሳል። እዚህ ቦታ ደርሶ ማጣራት ማካሄድ የሚፈልጉት የፎረንሲክ ባለሙያዎች ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ወደ ስፍራው አልተነቃነቁም።
አጣሪዎቹ አቶ ኡሞት ከአሜሪካ መቼ ወደ ጋምቤላ እንዳመሩ የሚያረጋግጥ መረጃ አላቸው። ጥርሳቸውን ሲታከሙ ከነበረበት ክሊኒክ የዲኤንኤ መለያቸውን አግኝተዋል። ተጨማሪ አስፈላጊ መረጃዎችም አሏቸው። ስማቸውን የማንጠቅሳቸው ዲፕሎማት እንዳሉት ኢህአዴግ ለመዋሸት የሚችልበት ዕድል የጠበበ ነው።
ሪፖርተር ማርች 6 ቀን 2013 “በጋምቤላ ክልል 29 ሰዎች ግድያ የሚጠረጠረው ግለሰብ ተገደለ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ዜና የፍርድ ቤት ስራ መስራቱ ብዙዎችን እንዳስገረመ የጎልጉል የአሜሪካ ዘጋቢ አስታውቋል፡፡ ስለ ህግና የህግ የበላይነት እከራከራለሁ የሚለው ሪፖርተር ያለ አንዳች የፍርድ ሂደትና ማስረጃ አቶ ኡሞትን አሸባሪ ሰፈር ማሰለፉ የሟቾችን ቤተሰቦች ቅር እንዳሰኘም ታውቋል።
የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት “Anuak Justice Council – AJC” በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከዘጠኝ ዓመት በፊት ለ424 የአኙዋክ ተወላጆች ጭፍጨፋ ተጠያቂ የሆኑትን የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ለፍርድ ለማቅረብ የሚሠራ ድርጅትና አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው የክልሉ ተወላጆችና ፍትህ ወዳዶች አሜሪካ ለዜጎቿ የምትሰጠውን ክብር ያለማዳላት ለአቶ ኡሞት እንድትሰጥ በ11 የአሜሪካ ጠቅላይግዛቶች ተወካይ የሆኑ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት አባላትን (ሴናተሮችን) በማነጋገር ግፊታቸውን ቀጥለዋል። እነዚህ ክፍሎች አቶ ኡሞትን ብቻ ሳይሆን ደረቁን የበጋ ወቅት ለማሳለፍ ወደ ወንዝ የወረዱ ንጹሃን በግፍ የተጨፈጨፉበት ምክንያት እንዲጣራ እየጠየቁ እንደሆነም ዘጋቢያችን አመልክቷል።
የማጣራቱ ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ ስለሚደረገው ቀጣይ ተግባርና ራሱ የምርመራው ውጤት ምን እንደሚሆን በቀጣይ ምንጮቻችን እንዳደረሱን እንዘግባለን።

tirsdag 12. mars 2013

መንግስት ታላቁን የአፋር ኡለማ ሊያስር ነው!


ድምፃችን ይሰማ

አፋሮች ትግሉን መቀላቀላቸው ተከትሎ ታላቁ የሀይማኖት መሪ ሸህ መሀመድ አወል ሃይታንን ለማሰር ፌዴራል ፖሊስ እየተጠራ እንደሆነ ታወቀ::
በአፋር ህዝብ ዘንድ እንደ አባት የሚታዩትን ታላቁን ዐሊም ሸህ መሀመድ አወል ሀይታንን ለማሰር መንግስት እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ ታወቀ፡፡ መንግስት ይህን እርምጃ ሊወስድ ያሰበው ለወትሮውም ቢሆን ለዲኑ ቀናኢ መሆኑ የሚታወቀው የአፋር ህዝብ በአሁን ሰዐት በዲኑ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን መቃወም በመጀመሩ ነው፡፡ ሆኖም ግን የአፋር ነዋሪዎች እንደሚሉት የአፋር ህዝብ ስለ ዲኑና ስለ ማንነቱ ጠንቅቆ ያወቀበት ደረጃ ላይ በመድረሱ የትኛውንም አይነት ጭቆና ለመቀበል ፍቃደኛ አይደለም፤ ለዚህም ተቃውሞውን ተቀላቅሏል፡፡ የአፋር ህዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ መንቃቱ ያሰጋው መንግስት በበኩሉ በህዝብ ዘንድ ትልቅ ክብር ያላቸውን ሸህ ለማሰር እንደወሰነ፣ ይህ ደግሞ ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እየተነገረ ነው፡፡መንግስት ታላቁን የአፋር ኡለማ ሊያስር ነው!
ሸህ መሀመድ አወል ሀይታን በሎጊያና በሰመራ በአፋርኛ የቁርዐን ተፍሲርና ሃዲስ ህዝቡን ከማስተማራቸውም በላይ ህዝቡ እርስ በእርሱ እንዲቀራረብ ፣ እንዲከባበር፣ እንዲዋደድና ከሌላው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋርም እንዴት ተቻችሎ መኖር እንደላለበት የሰበኩ ታላቅ የሃይማኖት አባት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የህዝቦች መቀራረብና ሰላም መሆን ምቾት ለማይሰጣቸው የመንግስት አካላት ግን ጉዳዩ ፍርሃት ስለለቀቀባቸው ሸሁን ማሰር አማራጭ አድርገው እንደያዙት ታውቋል፡፡ ሸህ መሀመድ እንዲታሰሩ ለመንግስት ያማከሩ ግለሰቦችና ምክሩንም ተቀብለው ተግባራዊ ያደረጉ ባለስልጣናት የመንግስትን ውድቀት የሚሹ እንደሆኑ የጠቆሙት ምንጮቻችን ቁርዐንና ሃዲስ ለምን አወራህ፣ ህዝብ እንዲከባበርና አንድ እንዲሆን ለምን መከርክ በሚል ሰበብ ሸሁ እዲታሰሩ ሲወስኑ የአፋር ህዝብን በሙሉ ሰብስቦ እስር ቤት እንደማስገባት አድርገው ሊቆጥሩ እንደሚገባና ይህም ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍላቸው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፋር ህዝብ ሀይማኖቱን የሚጨቁኑበትንና የሀይማኖት አባቶቹን ወደ እስር ቤት የሚልኩበትን አካላት በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም ከምንግዜውም በላይ እንደተዘጋጀ ታውቋል፡፡ መንግስት ሸህ መሀመድ አወል ሀይታንን ለማሰር በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑ እንደታወቀ የአካባቢው ሰዎች እንደገለፁት ‹‹መንግስት ህዝብን ማዳመጥ አለበት፣ ህዝብ ያልፈለገውን ነገር በግድ ለመጫን መሞከር ከመንግስት አይጠበቅም፡፡ መንግስት ለሀገርና ህዝብ ደህንነት ያስባል በሚል አመት ሙሉ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊ ጥሪ ላይ ቢገኝም አንዳንድ የመንግስት ፅንፈኛ ባለስልጣናት ከታሪክ መማር ባለቻላቸው ለሀገሪቷ የማይጠቅም ውሳኔ ውስጥ እየገቡ ነው ›› ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ አያይዘውም ‹‹የህዝብ ሙስሊሙ ጥያዌ ምላሽ ያገኛል በሚል ተስፋ ላይ እያለን ጭራሽ በክልላችን እንደ አባት የምናያቸውን ታላቁን ዐሊማችንን ለማሰር መወሰኑ የአፋርን ህዝብ ከምንግዜውም በላይ ድምፁን እንዲያሰማ ያደርገዋል እንጂ ወደ ኋላ አይጎትተውም›› ብለዋል፡፡
አላሁ አክበር!

Tamagne Beyene: Ethiopian Hero


Artist Tamagne Beyene Ethiopian Hero
The thing about a hero, is even when it doesn’t look like there’s a light at the end of the tunnel, he’s going to keep digging, he’s going to keep trying to do right and make up for what’s gone before, just because that’s who he is.
Joss Whedon
A hero is a defender. A hero is a protector. A hero is a rescuer. The legendary Ethiopian writer Dr. Haddis Alemayehu (1902 – 2003) portrayed Gudu Kassa as a ‘hero’ in his classical work Fiqir Iske Meqabir (Love Unto Grave’. Gudu Kassa (Kassa Damte) was a nobleman by birth but refused all for the sake of his progressive ideas. He fought for individual liberty and freedom. He became a defender of his people, not his class, nor his race, nor his family power. He fell in love and married a working class woman while he was a noble because he saw love in her, nothing else. To him and so many millions of Ethiopians, love is the essence of life and the root of every particle, motion, foundation, liberty, freedom and expression. Love is our Ethiopian culture and our norm. And now these three remain; faith, hope, and love. But the greatest of these is love (1 Corinthians 13:13).
In our times too, we have several heroes who believe in such love, liberty, faith, and peace. They are crying for our liberty. They are crying for our believed country: Ethiopia. They cry for love, equality, and fairness. Tamagne Beyene is one among many. Tamagne was born in Ethiopia; grow up in Ethiopia, and becoming Ethiopia. His entire families were from Ethiopia. They all love their country and understand the beauty of love, kindness, respect, and compassion. They are the true faces of Ethiopia.
On the other hand, we have brothers and sisters who decided to be dark and evil. They want us to go back. They want us to count our bones. They want us to be divided in terms of race, power, province, and religion. I tell you such are not from God but evil. ‘Turn from evil; do good; seek peace and pursue it (Psalms 34:14). I tell you again anyone who purposefully tries to deprive our liberty, unity, and one nation for the sake of security are wrong and from evil. Benjamin Franklin stated any society that would give up a little liberty to a gain a little security will deserve neither and lose both.’
Lord Acton wrote, “Liberty and good government do not exclude each other, and there are excellent reasons why they should go together. Liberty is not a means to a higher political end. It is itself the highest political end. It is not for the sake of a good public administration that it is required, but for the security in the pursuit of the highest objects of civil society, and of private life.”
Long live mother Ethiopia.
God be with us.

mandag 11. mars 2013

ለኢትዮጵያ እንድረስላት ይህን ሳናደርግ የቀረን እንደሆነ ግን ህሊና ቢስ ነን ፍሬ ቢስ ነን ወይም ደግሞ ከሃዲ ነን


በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁናቴ ህዝቡ ዕድሉን አግኝቶ ወደውጭ የወጣ እንደሆነ ወደ ዓገር ቤት ተመልሶ ቢገባ የጭንቅላት በሽተኛ ወይም እንደ እብድ አልያም እንደ ሞተ

autor yared elias Brehane
ያሬድ ኤልያስ
ሰው ተቆጥሮ የህድር ጡሩንባ ተለፍፎ ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ የሚላቀስበት አልያም ደግሞ ከቤተሰብ ትዳር አንስቶ የሰፈር ሰው ትንሽ ትልቁ የስራ ባልደረባ ከታክሲ ሹፌር እስከ ዶክተር እስከ ትልቁ የወያኔ አገዛዝ ሚኒስቴር ድረስ እንደዘመኑ በሽታ ታይቶ የምትገለልበት ወሬው ሁሉ እንትና ደቡብ አፍሪካ ጠፋ በሞያሌ በሱዳን ሊቢያ  እየተባለ ስንቱ  ተስፋ ቆርጦ የሱሰኛ ተገዢ የሚደረግበትዘመን። ሌላው ይቅርና  እትብቱ ወደተቀበረበት ሃገር ለመመለስ እንኳን የወያኔ ገዢ ፓርቲ 10 ግዜ እንድናስብ የሚነግረን ወቅት  እንደነገሩ ተበልቶ አንዲት ለስላሳ ለመጠጣት 20 ግዜ የሚታሰብበት ቢራ ለመጠጣት ዱቤ ለመጠየቅ 40 ግዜ የሚታሰብበት ሃገር።  ስለ እውነት ስለነጻነት ቢጠየቅ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችል መልሱን ? ..ለነሱ………የሚባለበት ግዜ ።
መቼስ አገሩ ላይ መኖር የሚጠላ ስው ያለ አይመስለኝም ግና ገና አካሉ አገሩ ላይ ቍጭ ብሎ መንፈሱ ውጭ አገር ያለውን ስንቱ ይቍጠረው። በውጭ ሃገር የሚኖረውማ  ወደ ሃገሩ ተመልሶ ሃገሩ ላይ ሃገሩን ወገኑን ለማገልገል የፈለገ ሰው ሃገሪቷ ላይ መኖር የማይችልበትን የጥቂት ዘረኛ ወያኔ አገዛዝ መንግስት የሚኖርባት በመሆኑ ለማድረግ አይችልም። በዛ ላይ ሰሞኑን ያየሁት የሰለሞን ቦጋለ እና ሳምሶን ቤቢ ፊልም በጣም ሲከነክነኝ ነው የዋለው አዎ የዚህ ደራሲ በፈለገው መልኩ ይጻፈው እኔ በተረዳውት ግን ለዚያች አገር ለዛ ህብረተሰብ ነጻነት ያስፈልገዋል ። መልዕክቱን በፈለጉት መልኩ ያስተላልፉት ግን በደንብ የሚታይ ነገር ነበረበት ስለነጻነት ብሩህ ተስፋ ።
ለነገሩ ወያኔዎች አገራቸው አይደልም  የመጡበትን ዓላማ አሳክተዋል።  የስራውን ይስጠውና ሟቹ ስሙን ቄስ ይጥራውና አገሪቷን በዘር በዓይማኖት በብሄር ከፋፍሎ ሰዉ በጎሪጥ እንዲተያይ አድርጎት እሱ ወደማይቀረው ሄዷል ምን አለ የሱ ተከታዮችም ይሄ መኖሩን አውቀው ወደ ህዝቡ በተመለሱ። አገሪቷማ  ስንቱን አሳድጋ እንጡራ አብቷን አውጥታ ያስተማረችውን የተማረ ዓይል ስንት ድግሪ ፕሮፌሰር ያደረገችውን ሃገር እየተወ መመለሻም መቀበሪያም ላትሆነው ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተሰድዶ በአሁኑ ሰዓት በስደት ላይ ይኖራል ። እንዲህም ሆኖ ለሃገር የተቆረቆሩ የሚመስሉ ከሃዲ ሆዳም እነዚህን ሰዎች ባሉበት ቦታ እንኳን እንዲቀመጡ አያደርጓቸውም እንዲያውም ብለው ወያኔ ለሃገር እንደሚቆረቆር ያወራሉ  ለነገሩ የትኛው የወያኔ ሃገዛዝ መንግስት ነው ለሃገሩ የሚቆረቆረው በዛ በበረሃ የማንም ተኩስ መለማመጃ ሆነው እነደሻማ ቀልጠው ሲቀሩ ሴት እህቶቻችን ማንም ሳይደርስላቸው እንደበግ መሬት ለመሬት ሲጎተቱ ዝም ብሎ  በደፈናው ሃገር ሃገር ማለት መብራትና ውሃ በሌለበት ሰዉ በፈለገውና በሚታየው መልኩ የራሱን ሃሳብ መግለጽ የማይችልበት ከታክሲ ዳቦና ወዘተ የመሳሰሉት ሰልፍ በስተቀር 3 ሰው እንኳን አብሮ ቆሞ ማውራት የማይቻልበት ወያኔ ለህዝቡ ካልሰረቀና ሙስና ካልሰራ መሻሻል የማይቻልበት ሃገር ለዚች አገር ነው ተቆረቆረ የሚባለው። ውድ ወገኖች ስለዚህ ለዘመናት ባአባቶቻችን በጥረታቸው የተገነባች የገነቧትን ሃገር ወያኔ ደግሞ በግዴለሽነት በዘረኝነት እየፈራረሳት ይገኛል ። ህዝቡንም በትልቅ የሞራል እስር ቤት ውስጥ አስረውት ይገኛል ከዚህ እስር ቤት የሚያወጣው አንዳች አይል ያስፈልገዋል ። የኢትዮጵያን ህዝብ ክብር በማንኛውም መንገድ ማስመለስ ይኖርብናል ህዝቡ በእየለቱ በሚሰማው ነገር ልቡ  ሸፍቷል ከጥቂት ሆዳሞች በስተቀር ስለዚህ ይኼ የነገዋ ኢትዮዽያ ቀን ነዉ የኔ የእናንተ ብ ቻ ሳይሆን የመላዉ ኢትዮዽያ ጥያቄ ነዉ እንድረስላት ይህን ሳናደርግ የቀረን እንደሆነ ግን ህሊና ቢስ ነን ፍሬ ቢስ ነን ወይም ደግሞ ከሃዲ ነን
እግዚሃብሄር ኢትዮጵያንና ተከባብሮ የሚኖረውን በማንኛውም ዓይማኖት ላይያለውን ህዝብ ይባርክ
አሜን
ያሬድ ኤልያስ

እኛና እነሱ – የሁለት ሀገር ሰዎች ነን


ከሥርጉተ ሥላሴ 10.03.2013

እም! ብዬ እያማጥኩ ጀመርኩት።
eprdf leanders in ethiopia
(ፎቶ – ከኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ዲስከሽን ፎረም የተወሰደ)
እኛ ማነን? እኛ የተቀመምንበት ኢትዮጵያዊነት የሚያንገበግበን። ችግሯ – ችግራችን፤ ዕንባዋ – ዕንባችን፤ መከፈቷ – መከፈታችን፤ ጉስቁልናዋ – ጉስቁልናችን፤ አንገት መድፋቷ ሃዘናችን የሆነው በዬትኛውም ዓለም የምንገኝ ልጆቿ ነን። በወያኔ መዳፍ ውስጥ አሳሩን በማዬት የሚገኘው ከስሜን እስከ ደቡብ ጫፍ፤ – ከዱቡብ ጫፍ እስከ ምዕራብ ጫፍ፤ ከምዕራብ ጫፍ እስከ ምስራቅ ጫፍ የሚገኝ ህዝብ ለሀገሩ ልዩ መለዮችን የሆነው ሥጋና ደም ነን።
እነሱስ? „የደላው ገንፎ ያላምጣል“ እንዲሉ ከማህደረ – ኢትዮጵያዊነት ትንሽ ልቅላቂ ያልፈጠረላቸው፤ አለቶች … በዕንባ ላይ ይሾማሉ፤ ይሸለማሉ …. ልጆቻቸውን አንደላቅው ያሰተምራሉ፤ ሲሰኛቸው ውጬ ልከው ዶላር አፍሰው ያዝመነምናሉ።
ባይታዋሩ ወገናችን ደግሞ ዕጣ ፈንታው … ሥራ ፍለጋ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን፤ በውሃ ጥም፤ በመንገድ ጉዞ አቅም በማነስ፤ በውሃ ሙላት፤ በጾታ ጥቃት፤ በቀጣሪ ዳባ እንደተበተነ ያልቃል፤ እንዲሁም ካሰቡት ሳይደርሱ የአሞራ እራት ይሆናል። በስደቱ በእሳት የሚቀቀሉት፤ ከፎቅ ተከስከስሰው የሚሞቱት፤ በጭንቀት በሽታ አብደው አድራሻቸው ጠፍቶ የሚቀሩትንማ ስሌትም አይገታውም። እንደ ጣሊያን በመሳሰሉት ሀገሮችም መንገድ ላይ ተዳዳሪ ወገኖቻችን በሚመለከት — ቤቱ ይቁጠረው።
ሞተን እያዩ ወደ ሞት ፊት ለፊት የሚገሰግሱ፤ በልተን እንሙት ብለው ከሞት ጋር የሚፋጠጡት ሴተኛ አዳሪ እህቶቻችን ቁጥርም ከሌሎች የችግሩ ሰለባ ከሆኑት ወገኖቻችን ቁጥር
Ethiopian girl holding baby gott
(ፎቶ – ከኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ሆም ፔጅ – ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ከሰጠው መግለጫ ትርጉም – የተወሰደ)
ቢበልጥ እንጂ ከቶውንም አያንስም። ጧሪ ጠዋሪ አጥተው ቤት እንደ ተዘጋባቸው የሚያልፉት አዛውንታት በእርግማን ለወግ ሳናበቃቸው አፈር ራታቸው፤ ድንጋይ  ትራሳቸው ሆኗል። ሊለምኑ ያፈሩ አካሎቻችን ቁጥር የትዬለሌ ነው። ከመሬት የሚፈናቀሉ ወገኖቻችን ልጆቻቸውን ለመሸጥ ነፍሳቸው እንዲሰነብት ተሰልፈዋል …. ለመራራ ስንብት፤
የጥንተ – ጥዋቱ የአባት አደሩ ወግና ባህል ቀርቶ ዛሬ በገበሬው መንደር ሳይቀር ቡና እንኳን ብቻ – ለብቻ እንደ አውሮፓ የሚጠጣበት ዘመን ተድርሷል። ለቡናውም የቡና ቁርስ አሯል። እንግዲህ እኛ የዚህ እርቃኑን – መለመላውን ያለ፤ ለዕለት ጉርስና ከፈን ያልበቃ፤ መጠለያ የሌለው ወገንተኛ ነን፤ ቀኑ እራሱ የተጋጠ የተመለመለ ነው የማረተበት!
እነሱ ደግሞ ለአንድ የምክትል ጠ/ሚኒስተር ቦታ ሶስት – ከዋናው ጋር በድምሩ አራት ሰው ይሾማሉ … አዎን! እኛ የወያኔ ሱፍ ለባሾች ወገንተኛ አይደለነም። የእነኝህ እንጂ ….
እነሱ — ያላጋጥሉ! ….
ይማግጣሉ! ….
በህዝብ የዕንባ ጥሪት ይቀብጣሉ!
በማናለብኝነት ቀፎ ሰረገላ ይዝመነማናሉ!
በፈጣሪ አምላክም ይሳላቃሉ። በሚፈርስ ገላ ላይ ሆነው ይደልቃሉ። „በሬ ሆይ! ሳሩን አዬህ እንጂ …. „ እንዲሉ። ይህም ያልፋል። የማያልፍ ነገር ያልተፈጠረብቻ ነው። በተፈጥሮ
EPRDF leaders in Ethiopia
(ፎቶ – ከከረንት ሆም ፔጅ „መሳቂያው ፓርላማ – ከአቤ ቶኪቻው መጣጥፍ የተወሰደ)
ሂደት ይጨበረባራሉ … መፈረሳቸውን ስተው — ይደንሳሉ — ሙጃ!
… እኛና እነሱ የማንገናኝ፤ ልንቀራረብም ከቶውንም የማንችል ነን። …. በዬትኛውም ዘመን በዬትኛውም ጊዜ የማንገናኝ … የሁለት ሀገር ሰዎች ነን። ምን ግዜም አዎን ምንግዜም እኛ እና እነሱ በዚህ ሚዛኑን ባልጠበቀ ተፈጥሮ፤ ሚዛኑን ባልወሰነ ውስጥነት ስለማንገናኝ እስከ ህልፈት ድረስ፤ በታሪክም የማንገናኝ ሰዎች ነን። ብንሞትም አጥንታችን ከክህደት አጥንት ጋር ከቶውንም እርቀ ሰላም የለውም።  - ኃራም!
ታዲያ የተከበርክ ወገናችን ሆይ! ይህ የረመጥ ዘመን፤ ይህ ዘመነ ፅልመት እንዲያከትም ምን ትመክራልህ?! ምን ታስባለህ?! … እንደ ትናንቱም ዛሬ ወጥተህ ወያኔን ጠቅጥቀኝ፤ ተርትረኝ፤ እረሰኝ፤ በራህብ ጨርሰኝ … በስጋት ክተፈኝ ብለህ ድምጽህን ትሰጣለህን? ወይንስ በቃኝን በድርጊት አስጊጠህ – አሻም ብለህ – ትቆርጣለህ?
ድንቁ ወገናችን … ሆይ! የቱ ነው ምርጫህ እና ውሳኔህ? … እንሆ ነገ ያለ በእጅህ – በአንተ መዳፍ ወስጥ  ነውና ወስንለት! በውሳኔህንም እንክርዳዱን ከስንዴ ለይበት። ስንት ጊዜ ምርጫ አዬህ ….?! ምን ተለውጦ አገኘኽው?! ከቶ ከራህብህ፤ ከመገፋትህ፤ ከመረገጥህ፤ ከመታሰረህ፤ ከመሰደድህ፤ ከሞመትህ ድነኃልን?!
የሚጎሰምልህ የስጋት ነጋሪት፤ የሚታወጅልህ የመንፈስ እስረኝነት፤ የሚነገረህ ዕብለት ስለመሆኑስ ታስተውለዋለህን? ማግኘቱ፤ በሥልጣን ማደጉ፤ በኑሮ መድላቱ – ልማቱ ከቶ ለአንተ poor ethiopia mothers and daughterለራህብህ፤ እጥፍ ብሎ እህል እውሃ ለሚለምነህ አንጀትህ ፤ የዕለት ከፈን ለሚማጸንህ አካልህ፤ መጠጊያ አጥቶ የነፍሳ – የውጪ – ግቢ ህቅታ ድምጽ ለሚያስተጋበው  ጥግ አልባው ሰውነትህ  ምኑ ነው? በተደሞ እሰሰው፤ በአርምሞ መርምረው … አንተ ለእነሱ ለጥጋበኞች ምናቸውም አይደለህም። ልንገር እነሱ ከአንተ ይልቅ — ትቢያን ያከብራሉ ….
ይሄውልህ — እንደለመደው ወያኔ — አዲሱን ጨዋታ ይዞ ኮሶን በማር ለውሶ፤ ዓይኑን በጥሬጨው አሽቶ ለአዲስ ምርጫ ምረጠኝ እያለህ ነው። ቅድመ መሰናዶው እያዬህው ነው። … ውሳኔህ፤ ድምጽህ  ——— ለልደትህ ወይንስ ለቅብረትህ ….?! ለዳግም ሞትህ ወይንስ ለትንሳዬህ? ብይንህን ስጥ። የሚዛንህ አድሎ ለደም ዕንባህ ይሁን። ይህ ልግጫ እስከ መቼ በልና አፋጣቸው! … በተናጠል አይደለም – በህብረት!  … አንተ ዕልፍ – እነሱ እፉኝ ናቸው። ባህሪያቸውም እንደ እፉንኝት ነው። ሲጠነሰሱ አዳርን ገደሉ። ሲወለዱ ደግሞ እናታቸውን … በላ!  እንደ እስልምና እምነት ወገንህ አንተም …. የልብህን ለማደረስ ተሰናዳ! ቁረጥ! — ቁርጥ ያጠግባልና …..
መሽቶ ሲነጋ -
ነግቶ ሲመሽ  — ላይነጋ
ቀናቶች ሲከታተሉ  — እያወጉ
ወራቶች ሲደራረቡ — እዬተዋጉ
ዓመታት እኛን ትተው ሲነጉዱ
ምዕተ ዓመታታ እኛን – እረስተው – በድልቂያ – ተዥጎርጉረው ተዥጎደጎዱ።
ሰማዩም በአርምሞ ሲመክር …
ምድርም ጥቅጣቃው በዛብኝ ብላ — በሰቀቀን — ስትጣራ ….
የኢትዮጵያ መከራ ይከማራል፤ ይደረደራል በበቀል – ሰቤጠራ።
! … የሃርነት ትግራይ ትል ፍልቶ – አፈልቶባት ….
በመታበይ ሲደነፋባት ….
መራራት …. ጎመዘዛት እማ እናታለም ….
የትናንትናዋ ቀለማም – ለምልም -
ጠራች — እሙ —  ለነፃነትህ  ብላ/ – ትመም! – ትመም!
ሃብተ – ንብረቷ
ጥሪተ  - ቅርሷ፣
ባህለ – ልማዷ
እምን!  አርግዞ – ይሄው – ፤ ትውፊቷ በዕብሪት በሙጃ ሰርክ ይመነጠራል
ያራል – ይከስላል፤ – ከወገን ጋር ይደለቃል – በመታበይ ይደቆሳል።
ሞልቶ ተትረፎ
የአሳር ጎርፍ አጎርፎ
አደራ ይጣራል
ድረሱልኝ ይላል።
እሷማ —- አሮባታል
ተደፍቶባት —-
ቀኑ —- መክኖባት
ሰቀቅን ተከዝኖባት
እህህ! ከትሞባት፤
ሞት – ነግሶባት
እስራት – ቀስሶባት
እም! እያጠደፈ – ተጭኗት
ትጣራለች እናት ቀኑ ጨልሞባት
ኑ! ትላላች አማ ሁሌም – መሽቶባት።
ወገኔ ሆይ! ልደትህን ለማቅረብ ቁልፉ ያለ በእጅህ ላይ ነውና በቃኝን ተክለህ አጽድቀው!