mandag 30. juni 2014

አንጋፋው የነጻነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ግንቦት 7 ዛሬ አስታውቋል::

June 30, 2014
ግንቦት 7 ዛሬ ለጋዜጠኞች እና ለአባላቶቹ በላከው መግለጫ የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለስራ በሚንቀሳቀሱበት ሰአት ትራንዚት በአደረጉበት በየመን አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ በፀጥታ ሃይሎች መወሰዳቸውን አስታውቋል።
ginbot 7
ንቅናቄው የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን ለወያኔ አሳልፎ እንዳይሰጥ ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ የላከ ሲሆን ለሳምንት ያህል ውስጥ ለውስጥ ሲደረግ የነበረው ውይይትም በሁለቱ ወገኖች ሳይሳካ መቅረቱን በመግለጽ የመን ይህን ታሪካዊ ስህተት ብትፈጽም በወደፊቱ የሁለተዮሽ ሀገራት ግንኙነት ላይ የማይጠፋ ጠባሳ እና አስቸጋሪ ሁኔታ እንደሚፈጠር አስታውቋል፡፡
ድርጅታችን የሚያደርገውን የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ከቶ ለአንዳፍታም ቢሆን አያቆምም ያለው ድርጅቱ፤ አቶ አንዳርጋቸው ራሳቸውን አሳልፈው ለሚወዷት ሀገራቸው እማማ ኢትዮጵያ መሰዋእት ለመሆን የተዘጋጁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጅ መሆናቸውን እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ከጎናችን ሆኖ ትግሉን እንዲያጠናክርና  በየመን መንግስት ላይ ህዝቡ በያለበት ጫና እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
እንደሚታወቀው በአለፉት ወራቶች የኢትዮጵያ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ የመግደል ሙከራ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
ሙሉ መግለጫውን በሚቀጥለው  እናወጣለን።
በዚህ አጋጣሚ አባይ ሚዲያ በየመን መንግስት ያደረበትን ከፍተኛ ቅሬታ እየገለጸ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ለዚህ አንጋፋ የነጻነት ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ተላልፎ እንዳይሰጥ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በየመን እና በአለም አቀፍ የተባበሩት ቢሮዎች የተቃውሞ ድምጻችን እንድናሰማ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚደርሱንን ማናቸውም መልእክትና ጽሁፍ ቅድሚያ በመስጠት ድህረገጻችን ላይ እንለጥፋለን።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar