mandag 8. september 2014

ብኵርና በቀይ ወጥ እንደዘበት !

ብኵርና በቀይ ወጥ እንደዘበት !

Sept 7, 2014

 ይድነቃቸው ከበደ

ኤሳው ከእናቱ መኋፀን ቀድሞ በመወለዱ ብቻ ሣይሆን ከፈጣሪው የተሰጠው ልዩ ፀጋ ነበረው፡፡ግን ኤሳው ለጢቂት ጊዜ ቢርበውም መታገስ አቅቶት ለታናሽ ወንዱሙ ብኵርናውን በቀይ ወጥ ለወጠ፡፡ሆኖም ግን በልቶ ሲጠግብ ብኵርናውን ቢፈልጋት ከእርሱ ተለይታለች፡፡ኋላም ለንስሐ ህይወት እድል ሳያገኝ ሞተ፡፡ ዘፍ.25 ቁ 5-33 ፡፡ ብኵርና ወይም ታላቅነት የእድሜ ብቻ ሣይሆን የፀጋም ጭምር ነው፡፡ፀጋ ደግሞ እድሜ፣ ሀብት፣የሰው ፍቅር፣አርቆ አስታዋይነት እና የመሣሰሉት ሁሉ የሚያካትት ነው፡፡
ከላይ በጢቂቱ ተገልፆ የሚገኘው ከመፃህፍ ቅዱስ የተወሰድ ሃሳብ ነው፡፡ሆኖም ግን የአገራች ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ህዝባዊ አመኔታ ባጣው በገዥው በወያኔ መንግስት የህዝብ ፍቅር እና ዝና በቀይ ወጥ ስለሚለውጡ ታዋቂ ሰዎች በወፍ በረር ለመዳሰስ ነው፡፡እንደሚታወቀው አገራችን ኢትዮጵያ የታዋቂ ሰው ችግር አለባት ለማለት የሚያስችል ምንም አይነት አስተማማኝ መረጃም ሆነ ማስራጃ ማግኘት የማይቻል ነው ፡፡ ሆኖም ግን አሉን የምንላቸው ከራሣቸው ጥረት ባለፍ የፈጣሪ ፀጋ ታክሎበት በህዝብ ዘንድ እውቅናን ያተረፉ ለቁጥር ያልበዙ እውቅ ሰዎች ስለመኖራቸው ማንም የማይክደው ሃቅ ነው፡፡
በመሆኑም ከተገፋው ጋር እየተገፉ ለአገር እና ለወገን ቅድሚያ እየሰጡ በክብር ላይ ክብር እያገኙ በሰው ልብ ውስጥ በፍቅር የሚኖሩ ምርጥ ኢትዮጵያዊያን እውቅ ሰዎች አሉን፡፡ እነዚህ እውቅ ሰዎች እውቅና ያተረፉበት መንገድ እና ሙያ የተለያየ ቢሆንም አንድ የሚያደርጋቸው እውቅናቸውን በቀይ ወጥ አለመለወጣቸው ነው፡፡ቀይ ወጥ ደግሞ ሌላ ምንም አይደለም የለየለት አድር ባይነት ነው፡፡የአድር ባይነት መሠረቱ ደግሞ ሐሰት ነው፡፡አሉን የምንላቸው አዋቂ ሰዎች ግን ሐሰት ከሆነ ሣይሆን እውነት ከሆነው ጎኖ መቆማቸው ነው፡፡
እውነት የሆነው ነገር ደግሞ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤት የሚገኝ የውስጥ እግር ቁስል ነው፡፡ እሱም ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በመነሣት በመንግሰት የአስተዳደር ብሉሹነት ምክንያት እየደረሰብን ያለ በደል ነው፡፡በደሎ ደግሞ እራብ፣ስደት፣ስራ-አጥነት፣የመብራት እና የውሃ እጥረት፣የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብቶች መረገጠ፣ እና ከመኖሪያ ቦታ መፈናቀል እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ሌላው እና አሳሳቢው ነገር የአምልኮ ቦታዎች በልማት ስም ይፈርሳሉ፣ የእምነት አባቶች እና መምህራኖች  ይታሰራሉ እንዲሁም ይሰዳዳሉ፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ቤተ-ክርስቲን እና መስጂዶች የገዥው መንግሰት የፖለቲካ ማራመጃ ተቋም ሆኗአል፡፡
እነዚህን ችግሮች በመለየት እና በአግባቡ በመረዳት አማራጭ መፍትሔ ለማምጣት እና ብሉሹ የሆነው የመንግስት አስተዳደር ለመለወጥ ተደራጅቶ በፖለቲካ ፓርቲ መንቀሳቀስ አስቸጋሪ የሆነበት ወቅት ልይ ነው የምንገኘው፡፡ መንቀሳቀስ ሲባል ምርጫ ቦርድ እና መንግስት ቀለብ ሰፍሩላቸው የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችን የሚመለከት አይደለም፡፡በመሆኑም ቁጥሩ እየጨመር የሚሄድ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኛ መብዛቱ፣በታሳሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ እና በደል እጅግ በጣም የበዛ ነው፡፡
ስለዚህም እነዚህን እና መሰል ችግሮችን ለመጠቆም እና ለማወያየት እንዲሁም መፍትሔ ለማመላከት ነፃ ሚዲያ ያለው አስታውፆኦ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ይሁን እንጂ በአገራችን እንደነዚህ አይነት ጋዜጠኞች ይታሰራሉ ወይም እንዲሰደዱ ይደረጋል፡፡ መንግሰት ከፍተኛ ባጃት በመመደብ ጠንካራ የሚዲያ ተቋማትም በውጪ እንዲሁም በአገር ውስጥ ያሉ  እንዲፈርሱ ወይም እንዲታፈኑ ያደርጋል፡፡ይህ ነው እንግዲ የአገራችን ወቅታዊ እውነት የሆነው ነገር !
ይሁን እንጂ እነዚህ እና መሰል ግፍ እና በደሎችን በመንግስት ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ሆኖም ግን ይህን አይቶ እንዳላየ ማልፍ በራሱ አንድ ነገር ሆኖ እያለ፤ምንም ቢሆን ከመጠየቅ ባያድንም፡፡ ይበልጥ ግን የሚያስቆጨው እና የሚያንገበግበው ለእንዲህ አይነቱ መከራ እና ስቃይ የሚዳርገውን መንግስት መደገፍ እና ለመጥፎ ተግባሩ መስክር በመሆን ዘብ በመቆም አድር ባይ ሲኵሆን ማየት ምን የሚሉት እብደት ነው ! ብሎ ማለት ምኑ ላይ ነው ስህተቱ ?
ጥያቄው በራሱ ስእተት ባይሆንም በስእተት ሳይሆን በድፍረት ላዛውም እንደዘበት፡፡ የህዝብ ፍቅር እና ዝና በርካሽ ነገር አላፊ ጠፊ በሆነ፤ ስም እና ዝናቸውን እየለወጡ ፈራሽ የሆነውን መንግሰት በመተማመን በህዝብ ላይ የሚቀልዱ የታዋቂ ሰዎች የቁልቁለት ጉዞ በርክቷል፡፡ይሁን እንጂ እንዲህ አይነቱ አስተዛዛቢ ድርጊት ሣይፈፅሙ ወይም ሣይቃወሙ መኖራቸው በራሱ የሚያሳጣቸው ነገር የለም፡፡ይሁን እንጂ  ደሃ ከበዛበት የአገራችን ኑሮ መቶ እጥፍ እየኖሩ መቶ እጥፍ ከእነሱ አንሱ በሚገኝ በድሃ ህዝብ ላይ መከራውን ከሚያበዛው የህዝብ ውክልና ከሌለው፣ የመንግስትነትን ስም ይዞ ከሚንቀሳቀስ የአንድ አካባቢ ተወላጅ ስብስብ ጋር በማበር ከህዝብ ዘንድ ያገኙትን ብኵርና በቀይ ወጥ የለወጡ ስኖቶች ናቸው ?
ቀን አይለወጥ መስሏቸው ማንነታቸውን በርካሽ ነገር የለወጡ እና ለመለወጥ ያሰቡ የመመለሻቸው ጊዜ አሁን ነው፡፡እጅ የሰጡለት ወደቃዊ መንግሰት እጅ መንሳቱ አይቀሪ ነው፡፡እሱም ቢሆን ወዶ ሳይሆን በግዱ ነው! ያኔ ግን እንደዘበት ያጡት ብኵርና ከወዴትም አይገኝም፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar