lørdag 10. mai 2014

የህውሃት/ወያኔ መሰሪ ስራ ለእኛ እንዳይተርፍ እንጠንቀቅ!!!

ከመሳይ በላይ !!!!
ህውሃት የሕዝቡን ሰምና መረጋጋት ለማግኘት፤ በሀገር ፀጥታና በብሔሮች ነፃ መውጣት ስም አምታትቶ፤ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በመንፈግና የመሪዎችን ኪስ በማሳበጥ፤ የውሸት ሀገራዊ ዕድገትን ለመሸፋፈን መሞከሩ የትም አላደረሰውም። ይልቁንም በሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ቁማር መጫወቱ ራሱን ዞሮ መቶታል። መሠረታዊ የሆነውን የመንግሥት ተልዕኮ ስቷል።
በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መንግሥት ማለት፤ የሕዝብ ተወካይ ማለት ነው። መንግሥት ማለት በሕዝብ ፍላጎት የቆመ ማለት ነው። መንግሥት ማለት በሕዝቡ መካከል እኩልነትን የሚጠብቅና የሚያሰጠብቅ ማለት ነው። መንግሥት ማለት ለሕዝብ ደኅንነት፣ ለሰላምና ለሀገር ዕድገት የቆም ማለት ነው። መንግሥት ማለት የሕዝብ አገልጋይ ማለት ነው። ህውሃት ከላይ የዘረዘርኳቸውን አንዳቸውንም አላሟላም።
የደርግን መንግሥት የኢትዮጵያ ሕዝብ የጠላበት ምክንያት፤ በአረመኔነቱ፣ ያለሕግ የፈለገዉን በማድረጉ፣ የግለሰቡ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ባለመከበራቸው፣ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ሠርቶ የማደርና የመበልፀግ በሩ በመዘጋቱ፣ የባለሥልጣኖች ወገን የሆኑ የሁሉም ነገር ፈላጭ ቆራጭ በመሆናቸው ነበር።
ታዲያ ህውሃት ግንባር መጥቶ የቀየረው ነገር ቢኖር፤ በደርግና በኢሠፓ ቦታ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሪዎችና ፓርቲ መተካታቸውን ብቻ ነው። ግድያው፣እስራቱና የሀገር ሀብት ዝርፊያው ብሷል። ጥቂቶቹ በሃብት መጨማለቃቸውና አብዛኛው በድኅነት መማቀቁ የዕለት እውነታ ሆኗል። ህውሃት መሪዎችና ሀብት ነጣቂ አባሪዎቻቸው፤ የሕዝቡን የነፃነት ፍላጎትና ሠርቶ የማደር ጉጉት በስግብግብ የግል ጥቅም ማካበት ሩጫቸው አመድ አስጋጡት። ሀገሪቱን በጣጠቋት። ደንበሯን ሸጡት። ለሙን መሬት ከባለቤቱ ነጥቀው ለራሳቸውና ለውጭ ከበርቴዎች በርካሽ ቸበቸቡት። ይህ የሕዝቡን ቁጣ አስነስቶ መቃብራቸውን እንዲቆፍር ገፍቶታል። ለሥልጣናቸው በር መክፈቻ የተዋቀረው የክልል ግዛት፤ እንዳቋቋመው ፌዴራላዊ ግዛት ውስጡ በስብሶ ንቅዘቱ ሕዝቡን ቀስቅሶታል። ይህን ማስተካከል አሁን የሕዝቡ ኃላፊነት ነው። የአንድ ቡድን ወይንም ፓርቲ ግዴታና ውዴታ አይደለም። በአንድነት መስራት የሁላችን ነው። ህውሃት በሌላ አንድ ፓርቲ ባሁኡ ሰዓት ለመለወጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት አይደለም። ሀገር አቀፍ የሆነ አንድነትንና ሰላምን ማግኘት ነው የሕዝብ ፍላጎት። እኛ ከብዛታችን፣ ከሀብታችን፣ ከዕውቀታችን፣ ከሀገር ወዳድነታችንና ለወገናችን ካለን ፍቅር የተነሳ፤ የበለጠ ማድረግ የምንችል ነን። የጎደለን ነገር ቢኖር፤ በአንድነት የመሰባሰቡ ጉዳይ ነው። አንድ ስንሆን፤ አይደለም የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ማስወገድ፤ ሀገራችን በብልፅግና ከዓለም ጎላ ብለው ከሚታዩት አንዷ መድረግ እንችላለን። የሚያሳዝነው ሀቅ ደግሞ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ብቻውን እስከቆመና እስከታገለ ድረስ፤ አቸነፈም አላቸነፈም ውጤቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን የዚያ ድርጅት ብቻ ነው። መነሻው ባሁኑ ሰዓት ሕዝቡን እኔ ብቻ እወክላለሁ የሚል አንድ ድርጅት የለምና ነው። የተለያዩ የነፃ አውጪ ግንባሮች ኢትዮጵያዊ ያልሆነ አጀንዳቸውን እያራመዱ ነው። የውይይቱን ይዘት እነሱው አሽከርካሪ ሆነዋል። በተደራቢ ደግሞ፤ ሥልጣን የቋመጡ ግለሰብና ቡድኖች አራጋቢ በመሆን ይኼንኑ እየገፉ ነው። ይኼ የነገን አይቀሬ ጠብ አድልቦታል። መለየት ያለበት፤ ይህ የኢትዮጵያዊያን ትግል ነው ወይንስ የሌሎች የሚለው ነው። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እምነት ያለን ማንኛችንም ታጋዮች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወሳኝነቱን ተቀብለን ባንድ ለመታገል ፍርሃት ሊኖረን አይገባም። ድርጅት የመታገያ መሣሪያ እስከሆነ ድረስ፤ አሁን የምንሻው ኢትዮጵያዊ የሆነ አንድ ድርጅት ነው። ህውሃት(ሕዝቡ በትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥት) የዕለት ተዕለት ፀረ-ኢትዮጵያ ተግባር ከቀን ወደ ቀን አንጀቱ እያረረ ነው። የመሪዎቹን ኪስ ማበጥ በዓይኑ እየተመለከተ ወገኖቹ በየመንገዱ እየተራቡ ማየቱ ዘግንኖታል። ሀገር እየተቆራረሰች ነው። በየክልሉ የተመደቡት ኩልኩል አገልጋዮች የክልላቸውን ሰዎች የግል ባሪያዎቻቸው እያደረጓቸው ነው። የውሸት ምርጫው ሕዝቡን እንደማያሳትፍ በተደጋጋሚ ታይቷል። የሚያጋልጡ ግለሰቦች ጥቃቱ በተደጋጋሚ ሕይወታቸው ማጣት ሆኗል። በትግሬዎቹ ነፃ አውጪ ግንባር ባለሀብቶችና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለው የኑሮ ልዩነት መለኪያ በሌለው ክፍተት ተራርቋል። ሥልጣንና ሀብት በተወሰኑት እጅ መካተቱ ትግሉን በጣም ለይቶ አውጥቶታል። በተደጋጋሚ ለገጠመው እድል በሩን ግጥም አድርጎ በመዝጋት፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ራሱን አግልሎ አስቀምጧል። ይህ ትግል፤ የጠራ ራዕይና አንድ ትክክለኛ ድርጅት እስካላበጀ ድረስ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድል በቀጠሮ ለወደፊቱ ተላለፈ ማለት ነው። እናም ደጋግመን ማንሰላሰል ያለብን፤ ጥረታችን የኢትዮጵያን ሕዝብ የትግል ግብ ገሀድ ለማድረግ እንጂ፤ ለመጪዎቹ ትግል ለማውረስ እንዳይሆን ነው። ሌባ ቀጪ አጥቶ ለሕዝብ አገልግሎት በሚውል ገንዘብ ደልቦ ሲንጎማለል ይውላል። ተጠቂው ሰፊው ሕዝብ አቧራ ለብሶ ለዕለት ጉርሱ ይማስናል። ፍትሕ የናፈቃት ዓለም። በየጥጋጥጉ ዲስኩር ብቻ ተለጥፎ ይነበባል!‹‹በመፈክር ውስጥ የተሸጎጡ በርካታ ውሸቶች አሉ፤›› “ነጻ ስለመሆን የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም። ሰው በሰውነቱ የሚከበርበትአገር እስከምንመሰርት ድረስ እንታገላለን። የብሶታችንና የትግላችን መነሻለናንተ ለኔ አዲስ ትግል አይደለም” መብታችን ይከበር ነው የምንለው፣ ነፃነት ያስፈልገናል፣ማንም እንዳሻው ተነስቶ ህወሃትን አምልኩ እንዲለን አንፈቅድም! ግን ለምንድን ነው እርስ በእርስ እየተሻኮትን ለወያኔ እድሜ የምንጨምርለት? ፖለቲከኞቹሰ ብንሆን የምንታገለው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ካልን ልዩነታችንን አጥበን አንድ ላይ ማበር ያልቻነው ለምንድን ነው? ህዝቡ አንድ በሆነበት ሰዓት በፖለቲካው ድርጅቶች ርዕዮተዓለም መከፋፈል ምክንያት ህዝቡን ከጨቋኝ ስርዓት መታደግ ያልተቻለበት ግዜ ላይ መሆናችንን አስተውለናል ካላስተዋልን እናስተውል እንጂ! ዛሬ በዚህ ወሳኝ ትግል ምዕራፍ በሆንበት ወቅት ላይ ሆነን አንድነታችን ካልታየ ነገ ደግሞ እንደፈራነው ስንታገል የነበርነው ድርጅት እራስ በራሳችን መሻኮት ልንጀምር ነው ማለት ነው ኧረ ጠንቀቅ እንበል!!
ከመሳይ በላይ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar