“ከሰላሳ የማያንሱ የምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ ባጅላ ዳሌ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪዎች «ወደ ክልላችሁ ተመለሱ » ተብለው መሬታቸውን ለመነጠቅ መቃረባቸውን ለማመልከት አዲስ አበባ በመምጣት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተ/ብርሃንን ካናገሩ በኋላ አፈ ጉባኤው ‹‹ወደ ቀዬአችሁ ተመለሱ እኔ ችግሩ እንዲፈታላችሁ አደርጋለሁ››በማለታቸው ገበሬዎቹ ወደ አምቦ መመለሳቸው አይዘነጋም” ሲል የዘገበው ፍኖት፣ ወደ አምቦ የተመለሱትን ገበሬዎች በዞኑ ሃላፊዎችና የኦህዴድ ካድሬዎች ‹‹አዲስ አበባ በመሄድ ገመናችንን አጋለጣችሁ››በማለት በተከታታይ ዛቻ እንደደረሰባቸው የፍኖት ዘገባ አክሎ ያትታል።
«ከትናንት ጀምሮም የታጠቁ ሚሊሻዎችን በማስከተል የቀበሌ ገበሬ ማህበሩ አክራሪ አመራሮች፣ «ለቃችሁ ወደ መጣችሁበት ክልል ተመለሱ» በማለታቸውና፣ ገበሬዎቹ «አንለቅም ከዚህ ውጪ አገር የለንም» ቢሉም፣ በመሳሪያ ከፍተኛ ማስፈራራት ስለደረሰባቸው መኖሪያቸውን ለቀዉ ከአካባቢው እንዲርቁ በማድረግ፣ መሬቱን ለሚፈልጓቸው ሰዎች ማከፋፈላቸው፣ «ሊደበድቡንና ሊገድሉን ይችላሉ» ብለው የሰጉ ገበሬዎችም ልጆቻቸውንና ባለቤቶቻቸውን በመያዝ ጫካ መደበቃቸውን በስልክ ከስፍራው ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡» ሲል ፍኖት ዘግቧል።
በኢትዮጵያ ሕግ መንግስት እንደተደነገገው ኢትዮጵያ የዜጎቿ ወይንም የኢትዮጵያ መላዉ ሕዝብ ሳትሆን የ«ብሄር ብሄረሰቦች» እንደሆነች በመግለጽ፣ በየትም አገር የሌለ የአገር በለቤትነት አንቀጽ እንዳካተተ ይታወቃል። የክልል መስተዳደሮችም በፌደራል ሕገ መንግስቱ በተደነገገላቸው መብት መሰረት፣ «የኦሮሞያ ባለቤት ኦሮሞዉ ነው»፣ «የሶማሌ ክልል ባለቤት ሶማሌው ነው» እያሉ ክልሎች የሁሉም ኢትዮጵያዉያን ሳይሆን፣ የአንድ ጎሳ ወይንም ብሄረሰብ ክልል ብቻ እንደሆነ፣ ከብሄረሰቡ ዉጭ ያሉት የክልሎ ባለቤትነት ስልጣን እንደሌላቸውና እንደ እንግዶች እንደሚቆጠሩ በመግለጽ፣ የክልል ሕገ መንግስታቸዉን፣ በአምቦ የተፈጠረዉን አይነት ግፍ ሕጋዊ ሽፋን የሚሰጥና የሚያበረታታ እንዲሆን አደርገው እንደቀረጹት የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው።
በአምቦ የደረሰው ዜጎችን ከአንድ ብሄረሰብ ስለሆኑ የማፈናቀል ወይንም የዘር ማጽዳት ወንጀል የመጀመሪያዉ እንዳለሆነ የገለጹት በጉዳዩ ላይ ያናጋገርናቸው የፖለቲካ ተንትበቅርብ ጊዜያት ዉስጥ ብቻ ከደቡብ ክልል፣ ከቤኔሻንጉል ክልል፣ አማርኛ ተናጋሪዎች በግፍ እንዲባረሩ የተደረገበት ሁኔታ እንደነበረም ይታወቃል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar