በተመሳሳይ ከወራት በፊት መርካቶ አካባቢ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች ‹‹ኢሳትን ለህዝቡ እያሳያችሁ ነው›› ተብለው በፖሊስ ተይዘው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ ያም ሆኖ ግን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ኢሳትን እንደሚገጥሙ የሚያሳዩ የዲሽ ማስታወቂያዎች ይታያሉ፡፡ ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ
mandag 8. september 2014
በአዲስ አበባ በየሰፈሩ ዲሽ የሚገጥሙ ወጣቶች “ኢሳትን እየቀጠላችሁ ነው በሚል ወከባ ይደርስባናል” አሉ
ብኵርና በቀይ ወጥ እንደዘበት !
Sept 7, 2014
ይድነቃቸው ከበደ
ኤሳው ከእናቱ መኋፀን ቀድሞ በመወለዱ ብቻ ሣይሆን ከፈጣሪው የተሰጠው ልዩ ፀጋ ነበረው፡፡ግን ኤሳው ለጢቂት ጊዜ ቢርበውም መታገስ አቅቶት ለታናሽ ወንዱሙ ብኵርናውን በቀይ ወጥ ለወጠ፡፡ሆኖም ግን በልቶ ሲጠግብ ብኵርናውን ቢፈልጋት ከእርሱ ተለይታለች፡፡ኋላም ለንስሐ ህይወት እድል ሳያገኝ ሞተ፡፡ ዘፍ.25 ቁ 5-33 ፡፡ ብኵርና ወይም ታላቅነት የእድሜ ብቻ ሣይሆን የፀጋም ጭምር ነው፡፡ፀጋ ደግሞ እድሜ፣ ሀብት፣የሰው ፍቅር፣አርቆ አስታዋይነት እና የመሣሰሉት ሁሉ የሚያካትት ነው፡፡
ከላይ በጢቂቱ ተገልፆ የሚገኘው ከመፃህፍ ቅዱስ የተወሰድ ሃሳብ ነው፡፡ሆኖም ግን የአገራች ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ህዝባዊ አመኔታ ባጣው በገዥው በወያኔ መንግስት የህዝብ ፍቅር እና ዝና በቀይ ወጥ ስለሚለውጡ ታዋቂ ሰዎች በወፍ በረር ለመዳሰስ ነው፡፡እንደሚታወቀው አገራችን ኢትዮጵያ የታዋቂ ሰው ችግር አለባት ለማለት የሚያስችል ምንም አይነት አስተማማኝ መረጃም ሆነ ማስራጃ ማግኘት የማይቻል ነው ፡፡ ሆኖም ግን አሉን የምንላቸው ከራሣቸው ጥረት ባለፍ የፈጣሪ ፀጋ ታክሎበት በህዝብ ዘንድ እውቅናን ያተረፉ ለቁጥር ያልበዙ እውቅ ሰዎች ስለመኖራቸው ማንም የማይክደው ሃቅ ነው፡፡
በመሆኑም ከተገፋው ጋር እየተገፉ ለአገር እና ለወገን ቅድሚያ እየሰጡ በክብር ላይ ክብር እያገኙ በሰው ልብ ውስጥ በፍቅር የሚኖሩ ምርጥ ኢትዮጵያዊያን እውቅ ሰዎች አሉን፡፡ እነዚህ እውቅ ሰዎች እውቅና ያተረፉበት መንገድ እና ሙያ የተለያየ ቢሆንም አንድ የሚያደርጋቸው እውቅናቸውን በቀይ ወጥ አለመለወጣቸው ነው፡፡ቀይ ወጥ ደግሞ ሌላ ምንም አይደለም የለየለት አድር ባይነት ነው፡፡የአድር ባይነት መሠረቱ ደግሞ ሐሰት ነው፡፡አሉን የምንላቸው አዋቂ ሰዎች ግን ሐሰት ከሆነ ሣይሆን እውነት ከሆነው ጎኖ መቆማቸው ነው፡፡
እውነት የሆነው ነገር ደግሞ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤት የሚገኝ የውስጥ እግር ቁስል ነው፡፡ እሱም ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በመነሣት በመንግሰት የአስተዳደር ብሉሹነት ምክንያት እየደረሰብን ያለ በደል ነው፡፡በደሎ ደግሞ እራብ፣ስደት፣ስራ-አጥነት፣የመብራት እና የውሃ እጥረት፣የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብቶች መረገጠ፣ እና ከመኖሪያ ቦታ መፈናቀል እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ሌላው እና አሳሳቢው ነገር የአምልኮ ቦታዎች በልማት ስም ይፈርሳሉ፣ የእምነት አባቶች እና መምህራኖች ይታሰራሉ እንዲሁም ይሰዳዳሉ፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ቤተ-ክርስቲን እና መስጂዶች የገዥው መንግሰት የፖለቲካ ማራመጃ ተቋም ሆኗአል፡፡
እነዚህን ችግሮች በመለየት እና በአግባቡ በመረዳት አማራጭ መፍትሔ ለማምጣት እና ብሉሹ የሆነው የመንግስት አስተዳደር ለመለወጥ ተደራጅቶ በፖለቲካ ፓርቲ መንቀሳቀስ አስቸጋሪ የሆነበት ወቅት ልይ ነው የምንገኘው፡፡ መንቀሳቀስ ሲባል ምርጫ ቦርድ እና መንግስት ቀለብ ሰፍሩላቸው የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችን የሚመለከት አይደለም፡፡በመሆኑም ቁጥሩ እየጨመር የሚሄድ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኛ መብዛቱ፣በታሳሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ እና በደል እጅግ በጣም የበዛ ነው፡፡
ስለዚህም እነዚህን እና መሰል ችግሮችን ለመጠቆም እና ለማወያየት እንዲሁም መፍትሔ ለማመላከት ነፃ ሚዲያ ያለው አስታውፆኦ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ይሁን እንጂ በአገራችን እንደነዚህ አይነት ጋዜጠኞች ይታሰራሉ ወይም እንዲሰደዱ ይደረጋል፡፡ መንግሰት ከፍተኛ ባጃት በመመደብ ጠንካራ የሚዲያ ተቋማትም በውጪ እንዲሁም በአገር ውስጥ ያሉ እንዲፈርሱ ወይም እንዲታፈኑ ያደርጋል፡፡ይህ ነው እንግዲ የአገራችን ወቅታዊ እውነት የሆነው ነገር !
ይሁን እንጂ እነዚህ እና መሰል ግፍ እና በደሎችን በመንግስት ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ሆኖም ግን ይህን አይቶ እንዳላየ ማልፍ በራሱ አንድ ነገር ሆኖ እያለ፤ምንም ቢሆን ከመጠየቅ ባያድንም፡፡ ይበልጥ ግን የሚያስቆጨው እና የሚያንገበግበው ለእንዲህ አይነቱ መከራ እና ስቃይ የሚዳርገውን መንግስት መደገፍ እና ለመጥፎ ተግባሩ መስክር በመሆን ዘብ በመቆም አድር ባይ ሲኵሆን ማየት ምን የሚሉት እብደት ነው ! ብሎ ማለት ምኑ ላይ ነው ስህተቱ ?
ጥያቄው በራሱ ስእተት ባይሆንም በስእተት ሳይሆን በድፍረት ላዛውም እንደዘበት፡፡ የህዝብ ፍቅር እና ዝና በርካሽ ነገር አላፊ ጠፊ በሆነ፤ ስም እና ዝናቸውን እየለወጡ ፈራሽ የሆነውን መንግሰት በመተማመን በህዝብ ላይ የሚቀልዱ የታዋቂ ሰዎች የቁልቁለት ጉዞ በርክቷል፡፡ይሁን እንጂ እንዲህ አይነቱ አስተዛዛቢ ድርጊት ሣይፈፅሙ ወይም ሣይቃወሙ መኖራቸው በራሱ የሚያሳጣቸው ነገር የለም፡፡ይሁን እንጂ ደሃ ከበዛበት የአገራችን ኑሮ መቶ እጥፍ እየኖሩ መቶ እጥፍ ከእነሱ አንሱ በሚገኝ በድሃ ህዝብ ላይ መከራውን ከሚያበዛው የህዝብ ውክልና ከሌለው፣ የመንግስትነትን ስም ይዞ ከሚንቀሳቀስ የአንድ አካባቢ ተወላጅ ስብስብ ጋር በማበር ከህዝብ ዘንድ ያገኙትን ብኵርና በቀይ ወጥ የለወጡ ስኖቶች ናቸው ?
ቀን አይለወጥ መስሏቸው ማንነታቸውን በርካሽ ነገር የለወጡ እና ለመለወጥ ያሰቡ የመመለሻቸው ጊዜ አሁን ነው፡፡እጅ የሰጡለት ወደቃዊ መንግሰት እጅ መንሳቱ አይቀሪ ነው፡፡እሱም ቢሆን ወዶ ሳይሆን በግዱ ነው! ያኔ ግን እንደዘበት ያጡት ብኵርና ከወዴትም አይገኝም፡፡
søndag 7. september 2014
የለውጡ አካል መሆኛው ግዜው አሁን ነው
በኢትዮጵያችን ፍትህ ከጠፋ ብዙ ዘመን ሁኖታል። ከሁሉም ዘመን የህወሃቶች ዘመን ግን የተለየ ነው። ህወሃቶች ህግን ዜጎችን የማጥቂያ መሣሪያ አድርገው መጠቀማቸው ከሌሎች እንዲለዩ ያደርጋቸዋል። እነዚህ ቡድኖች ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ቂም መወጣጪያ ህጎችን አውጥተዋል። እንዲህ በማድርጋቸውም ሠላም እናገኛለን ብለው ያስባሉ። የህወሃቶች አስተሳሰብ ደካማና እርባና ቢስ መሆኑን ከሚያሳዩ ተግባሮቻቸው መካከል አንዱ ይሄው በፍትህ ሳይሆን በህግ ብዛት ሠላም እናገኛለን ብለው ተስፋ ማድረጋቸው ነው። የህግ ብዛት ሠላምን አያስገኝም፤ ፍትህንም ማስፈን አይችልም። እንዲያውም ህግ በበዛ ቁጥር ፍትህ እየጎደለች እንደምትሄድ የህወሃቶች ድርጊት ደህና ምስክር ነው። እነርሱ ዜጎችን ለመበቀያ ብለው የሚያወጧቸው ጥቃቅን ህጎች እነርሱ “ህገ መንግስት” ብለው የሚጠሩትን የሚንዱ እና ፍትህን ዋጋ የሚያሳጡ ሁነው እያየናቸው ነው። የፀረ ሽብር ህጉ በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን የዜጎችን የመናገር የመደራጀትና በሰላማዊ መንገድ የመንግስትን እኩይ ተግባራት የመቃወምን መብት የገፈፈ ነው። የፀረ ሙስና ህጉም ቢሆን እንዲሁ ነው። በፀረ ሙስና ህጉ የሚጠየቁ በህወሃት የተጠሉ ብቻ ስለመሆናቸው በሙስና የተጨማለቁት የህወሃት ሹማምንት ህያው ምስክሮች ናቸው። በህወሃቶች ህግ ሁሉም ዜጎች እኩል አይደሉም። ህወሃቶች ከሌሎች ይበልጣሉ። የህወሃቶች ምኞት እነርሱ ከህግ በላይ፤ ሌላው ህዝብ ከህግ በታች ሁነው ህወሃትን ተሸክመው እንዲኖሩ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ኢ-ፍትሃዊነት መታገል ግዜው የሚጠይቀው ታሪካዊ ግዴታ ነው። መሪያችን አንዳርጋቸው ፅጌ የተነሳውም ህወሃቶች መሣቂያ መሳለቂያ ያደረጓትን ፍትህ ወደ ሚገባት ክብር ለመመለስ ነው። በአገራችን የህግ የበላይነት ሠፍኖ ጥቂቱ ብዙሃኑን ሳይጫን፤ ማንም ማንንም ሳይሸከም ሁሉም በህግ እና በፍትህ እኩል ሁኖ የሚኖሩባት ሠላም የበዛላት ሥፍራ እንድትሆን የመሪያችን የአንዳርጋቸው ምኞት ነው። ይሄን ምኞት ሚሊየኖች አንግበው ተነስተዋል።
ህወሃቶች አገራችንን አደጋ ላይ ከጣሉባቸው አንኳር ድርጊቶቻቸው መካከል አንዱ በዜጎች መካከል እየፈጠሩ ያሉት ግልፅ ልዩነት ነው። ህወሃቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር እኩል ነን የሚል እምነት የላቸውም። የህወሃቶች ዕምነት እነርሱ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ከፍ እንደሚሉና በዚያች አገር ውስጥ የተለየ መብት እንዳላቸው ነው። ለመገድልም፤ ለመዝረፍም፤ዜጎችን ለማሳቃየት እና ከአገር ለማባረርም መብቱ የእኛ ነው የሚል ጅላጅል እምነት አላቸው። ይህ የሞኝ እምነታቸው በዜጎች መካከል ቂመ በቀል ሊያተርፍ የሚችል አድሎዎ እንዲፈጥሩ አድርጓቸዋል። አድሎአቸውንም ይበልጥ የከፋ የሚያደርገው ህወሃቶች ሁሉን አድራጊ እኛ ነን ብለው ሲያበቁ የህወሃት የበላይነት የለም ብላችሁ እምኑ ብለው ዜጎችን መጫናቸው ነው። ይህ ድርጊታቸው ብዙ ዜጎችን አስቆጥቷል። ህወሃቶች ግን የዜጎችን ቁጣ የሚያይ ዓይን፤ የሚያስተውል ሂሊና ርቋቸዋል። በኢትዮጵያችን በህወሃቶች አማካኝነት እየተፈጠረ ያለው ግልፅ አድልዖ ለአገራችን ህልውና ከፍተኛ አደጋ ነው። በህዝብ መካከል አድልዖ መፈፀም እና ቂምና በቀልን መትከል የህወሃቶች የመኖሪያ ድንኳናቸው ሁኗል። መከፋፈልና አድልዖ ባለበት አገር ውስጥ ሠላም ይኖራል ማለት አይቻልም። አድልዎ የታላላቅ ግጭቶችና ለውጦች ጥሩ ምክንያት መሆኑን መርሳት አይገባንም።መሪያችን አንዳርጋቸውም ሆነ ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የተነሳው እንዲህ በዜጎች መካከል የሚፈፀመውን አድልዖ ለማስቆምና ዜጎች በገዛ አገራቸው በእኩልነት የሚኖሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው። ይህ የእኩልነት ጥያቄ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጎች ጥያቄ ሁኖ ከኢትዮጵያ እስከ ውጪ አገራት ድረስ እያሰተጋባ ነው።
ሌላው ህወሃቶች አገሪቷን እያዋረዱ ካሉበት ነገሮች መካከል አንዱ የነፃነት ጥያቄ ነው። እኛ ከመጣን በኋላ በኢትዮጵያ ነፃነት ሰፈነ እያሉ ያላዝናሉ። ህወሃቶች ከነፃነት ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለውን ኃላፊነት ለመረዳትና ለመሸከም ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ድክመት አለባቸው። ከነፃነት ጋር የሚመጣውን ኃላፊነት ለመሸከም ብቻ ሳይሆን የነፃነትንም ትርጉም ለመረዳት ከፍተኛ የሆነ የእውቀት ማነስ ችግር ያለባቸው መሆኑም ይታወቃል። ራሳቸውን ከታሰሩበት የድንቁርና ሰንሰለት ማስፈታት ሳይችሉ ከሰሞኑ የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎችን ሰብስብው የእኛን አብዮታዊ ዲሞክራሲ ካልስተማርናችሁ ትምህርታችሁን አትቀጥሉም ሲሉ ማሰብ ማቆማቸውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየን አንድ እውነት ሁኖ አግኝተነዋል። ማሰብ የሚችሉ ቢሆኑማ ኑሮ ነፃነት ማለት ‘የእናንተን አብዮታዊ ዲሞክራሲ መስማት አልፈልግም ማለትን’ እንደሚጨምር ያውቁ ነበር። ነፃነትን የማያውቁት ነፃ አውጪዎች ነን ባዮቹ ህወሃቶች ግን ተማሪው መስማት የማይፈልገውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ አስገድደው እየጋቱት ይገኛሉ። ለሚቀጥለውም አርባና ሃምሳ ዓመት ስልጣኑን ለማንም አሳልፈን የምንሰጥ አይደለንም ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል። የዚህ ሁሉ ድፍረት ምንጭ ህወሃቶችን የተፀናወታቸው እኔ ብቻ ከሚል ከንቱ አስተሳሰብ የመነጨው ስግብግብነታቸው መሆኑን መገነዘብ ያስፈልጋል።
እንግዲህ ፍትህ መቀለጃ ሁናለች፤ እኩልነት ተጓድሏል፤ ነፃነት ጠፍቷል የሚሉ ዜጎች ከሁሉም አቅጣጫዎች ድምፃቸውን እያሰሙ ነው። የህዝቡ ብሶትም ፅዋውን ሞልቶ እየፈሰሰ ነው፤ ቁጭቱም ከመቸውም ግዜ በላይ ግሏል። ከሰሞኑ በሃያ ስድስት ታላላቅ ከተሞች የተደረጉት ውይይቶችም ያሳዩን አንድ እውነት ህዝቡ ይበልጥ መቆጣቱን ነው። ቁጣውም የተገለፀበት መንገድም ሌላው አስደማሚ ጉዳይ ነው።“እኛም አንዳርጋቸው ነን” ሲሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል። ከእንግዲህ ፍርሃት ሆይ መወጊያህ ወዴት አለ የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ፤ ላንቺ ነው ኢትዮጵያ እያሉ ዘምረዋል። ይሄ ለፍትህ፤ ለእኩልነትና ለነፃነት ለሚታገሉ ታጋዮች ተስፋ ሰጪ ምልክት ነው።
ህወሃቶች በሠላማዊ መንገድ ለሚደረገው ትግል መንገዱን ሲያደናቅፉ እሰከ ዛሬ ዘልቀዋል። አሁን ጭራሹን ገና ሃምሳ የመከራ ዘመን እየተመኙልን ነው። ይሄ ምኞታቸው ቅዥት ሁኖ እንደሚቀር እኛ ልናስታውሳቸው እንፈልጋለን። በዚያች አገር ለውጥ መምጣት አለበት። ለውጡ በዛፍ ላይ የተንጠለጠለ የጎመራ ፓፓያ አይደለም በራሱ ወደ ምድር የሚወርድ፤እኛ ራሳችን ልናወርደው የሚገባን እንጂ። ተፈላጊውን ለውጥ ለማምጣት እያንዳንዱ ዜጋ በቻለው መሣሪያና ባለው አቅም ሁሉ ለልውጡ ሳያቅማማ መታገል ይኖርበታል። ህወሃቶች ነፃነታችንን አይሰጡንም፤ ፍትህም ከእነርሱ እጅ የምትገኝ አይደለችም፤ እኩልነትንም የሚያውቁ አይደሉም እነዚህ ወርቃማ እሴቶች በትግል የሚገኙ ናቸው። እነዚህን ክቡር ስጦታዎች አስነጥቆ ዝም ያለ ወደ መታረጃው ሥፍራ የሚነዳ ከብትን ይመስላል። ብዙ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ መሆንን የሚምርጡ አይደሉም። በየከተሞቹ በተደረገው ውይይት ከተገነዘብናቸው እውነቶች መካከል አንዱ ዜጎች ለፍትህ፤ለእኩልነት እና ለነፃነት አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ነው።
በህወሃት ዘመነ መንግስት የመከራ እንባችሁን በመዳፋችሁ የምታፍሱ፤ ህወሃት በአገሪቷ ላይ እያደረሰ ያለው የጥፋት ድርጊት የሚያነገበግባችሁ እና ምን እናድርግ መሪ አጣን የምትሉ ስሙን! መሪ ካጣችሁ እንዲህ አድርጉ “ራሳችሁ ተነሱና መሪ ሁኑ!”። ከምታምኗቸው ጥቂት ወዳጆቻችሁ ጋር ሁናችሁ ተደራጁ፤ አንዳችሁ አንዳችሁን አድምጡ፤ ጥሩ ተመሪ መሆን ከቻላችሁ ጥሩ መሪ ወጥቷችኋል ማለት ነው። የአገራችን ፈርጀ ብዙ ችግር በጥቂት ዜጎች ብቻ የሚቀረፍ አይደለም።የሁሉንም ቁርጠኛ ዜጎች ትግል የሚጠይቅ ነውና በየመንደራችሁ ተደራጅታችሁ የጎበዝ አለቃ መርጣችሁ ዘረኞችን፤ ዘራፊዎችንና አድሎዋዊ ሥርዓት የዘረጉባችሁን ታገሏቸው። እንዲህ ካደረጋችሁ ከእኛ ጋር ለመገናኘት መንገዱ ቀላል ይሆናል።
የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጥያቄ አጭርና ግልፅ ነው። ፍትህ፤ ነፃነትና እኩልነት በኢትዮጵያችን ይሰፈን ነው። የህወሃትን ዘረኝነትና አምባገነንነት የሚፀየፍ ሁሉ የንቅናቄያችን ደጋፊ ነው። እነዚህን ነገሮች በኢትዮጵያ ለማስፈን በሚችለው ሁሉ ርምጃ መውሰድ የጀመረ የንቅናቄያችን አካል ነው። እኛም ከጎኑ አለን። እንዲህ በማድረግ የማይቀረውን ለውጥ አናመጣለን። ለውጡ ይመጣል አንድም የተፈጥሮ ህግ ስለሆነ፤ አንድም ደግሞ እኛ ሳናቅማማ የፈለግነውን ለውጥ ለማምጣት ስለተነሳን።
ህወሃቶች መስልጠን የማይችሉ፤ ከአዲስ አስተሳሰብ ጋር ራሳቸውን ማዋሃድ የማይሆንላቸው ፍፁም ግትሮች መሆናቸውን በተዳዳጋሚ አይተናል። ይሄን ግትርነታቸውን እንደ ጀግንነት ይቆጥሩታል። በአገራችን ደህና አባባል አለች እንዲህ የምትል “ሞኝ አሸነፈ ምን ብሎ? እምቢ ብሎ” ይባላል። ህወሃቶችን በዚህ አባባል መግለፅ ሞኝ ያስመስላቸዋል እነርሱ ግን ሞኞች አይደሉም ጨካኞች እንጂ። የጭካኔያቸው ምንጭ ደግሞ በራሳቸው የማይተማመኑ ደካሞች መሆናቸው ነው። እነርሱ ከዛሬ ሠላሳ ዓመት በፊት በመስታወት ውስጥ ያዩትን የራሳቸውን ምሥል ዛሬም መልሰው ያንኑ ምሥል እያዩት ነው። ከሠላሳ ዓመት በኋላም ሊቀየሩ አልቻሉም። ከዚያ ካረጀው ምሥላቸው ላይ ዓይናቸውን ነቅለው ግዜው እና ሁኔታው የፈጠረውን በአካባቢያቸው ያለውን አዲስ ምሥል ለማየት አቅቷቸውል። ስለዚህ ህወሃቶችን ማስወገድ ግድ ነውና ሁሉም በያለበት ለሚመጣው ለውጥ ራሱን ያዘጋጅ፤ የለውጡም አካል ይሁን እንላለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
ሶስት ጋዜጠኞች አገር ለቀው ወጡ
የወያኔው መንግስት አላሰራ ያላቸው እና ጫናውን ያሳረፈባቸው ሶስት ጋዜጠኞች አገር ለቀው መውጣታቸው ታውቋል።
በዚህም መሰረት
በዚህም መሰረት
1ኛ/ ሚሊዮን ሹሩቤ – የማራኪ መጽሄት ባለቤት እና አዘጋጅ
2ኛ/ ኤሊያስ ጉዲሳ – የቃልኪዳን መጽሄት ባለቤት እና አዘጋጅ
3ኛ/ መድሃኒት ረዳ – የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ሪፖርተር
በገዛ አገራችው መስራት ስላልቻሉ እናት አገራቸውን ኢትዮጵያን ለቀው ተሰደዋል። የወያኒው መንግስት ከምርጫ 2007 ቀደም ብሎ ነጻ ፕሬሶችን በማጥፈታ በራሱ አምሳል አዳዲስ ፕሬሶችን በመቅረጽ በ97 የደረሰበትን ሽንፈት አሁን እንዳይደርስበት በስፋት እየሰራ ሲሆን ሕዝብ የመረጃ ደሃ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት በዚህ አመት ብቻ ወደ 30 የሚጠጉ ጋዜጠኞች እንዲሰደዱ ሌሎችን ደሞ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ አድርጓል።
2ኛ/ ኤሊያስ ጉዲሳ – የቃልኪዳን መጽሄት ባለቤት እና አዘጋጅ
3ኛ/ መድሃኒት ረዳ – የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ሪፖርተር
በገዛ አገራችው መስራት ስላልቻሉ እናት አገራቸውን ኢትዮጵያን ለቀው ተሰደዋል። የወያኒው መንግስት ከምርጫ 2007 ቀደም ብሎ ነጻ ፕሬሶችን በማጥፈታ በራሱ አምሳል አዳዲስ ፕሬሶችን በመቅረጽ በ97 የደረሰበትን ሽንፈት አሁን እንዳይደርስበት በስፋት እየሰራ ሲሆን ሕዝብ የመረጃ ደሃ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት በዚህ አመት ብቻ ወደ 30 የሚጠጉ ጋዜጠኞች እንዲሰደዱ ሌሎችን ደሞ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ አድርጓል።
fredag 5. september 2014
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ካድሬ ለማድረግ የተጠራው ስልጠና በማስፈራራት ተጠናቀቀ
አኩ ኢብን አፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
በአፋር ክልል በረእሰ መዲናው በሰመራ የሚገኘው ብቸኛው ዩኒቨርሲቲ ለ10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የተማሪዎች ሰልጠና ባለፈው ሰኞ ተጠናቀቋል። በስልጠናው የክልሉ የፓለቲካ መሪዎች የተገኙ ሲሆን በአጣቃላይ ሰለ መጭው ምርጫ ቅስቀሳ እንደነበረ ምንጮችን ገልፆል።

እንደ ምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ ለመጪውው ምርጫ ኢህአዴግን ምረጡ ካልመረጣቹሁ ግን ስራ አታገኙም በሚል ብዙ ማሰፈራራት የበዛበት ስልጠና እንደነበረ ታውቋል፡
እንደ ምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ ለመጪውው ምርጫ ኢህአዴግን ምረጡ ካልመረጣቹሁ ግን ስራ አታገኙም በሚል ብዙ ማሰፈራራት የበዛበት ስልጠና እንደነበረ ታውቋል፡
በዚህ አመት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ተማሪዎች በሰልጠናው የተገኙ ሲሆን በተማሪዎች በኩል ለሚነሱ ወቅተዊ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ማስፈራራትና ማስጠንቀቅ እንደነበረ ታይቷል።
በመጪው ምርጫ ኢህአዴግ እና የክልሉ ፓርቲ አብዴፓ በዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ላይ ያላቸው ድፍራቻ በግልፅ በታየበት በዚህ ስልጠና በክልሉ በግልፅ ስለሚታዩ ችግሮች ላይ የሚናገሩ ተማሪዎች ስማቸው እየተመዘገበ እንደነበረ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በዘንድሮው ምርጫ በመላው ኢትዮጵያ ሊነሳ ስለሚችለው ሁከት ተማሪዎችን ከወዲሁ የማስጠንቀቅ ስልጣና ይመስላል ሲሉ አሰተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ ከሚገኙ 9 ክልሎች እስከ አሁን ብዙዎቹም የሚገባቸውን ያህል ባይሆኑም በትምህርት አመስፋፋት ኋላ በመቅረት አፋር ክልል መሪነቱን ይይዛል።
torsdag 4. september 2014
ወጣቱን ለማደንቆር ያለመው ስልጠና ህወሓትን ለመቅበሪያነት ይዋል!
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በዚህ ሥልጠና ላይ ያለውን እይታ በነሐሴ 16 ቀን 2006 ዓም ቁጥር 328 ርዕሰ አንቀጹ መግለጹ ይታወሳል። ግንቦት 7 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በወያኔ ስልጠናዎች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት መድፈራቸው ወጣቱ ለለውጥ የተዘጋጀ እንደሆነ አመላካች መሆኑን ተገንዝቦ ይህ የለውጥ ፍላጎት በድርጅት እንዲታገዝ ወጣቱ በትናንሽ ሕዋሶች ራሱን እንዲያደራጅ መክሯል። ሆኖም ግን ህወሓት ለስልጠናው የሰጠው ትኩረት ቀድሞ ከታሰበው በላይ በመሆኑ ንቅናቄዓችን በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንደገና ሊመለስበት ወስኗል።
ህወሓት፣ ይህንን ያህል መጠነ ሰፊ ስልጠና ማድረግ ለምን አስፈለገው? የዲሞክራሲ ኃይሎችስ ይህንን ስልጠና እንዴት ለራሳቸው ጥቅም ሊያውሉት ይችላሉ?
ህወሓት ይህንን ትርጉም የለሽ ስልጠና በአሁኑ ሰዓት ለመስጠት የፈለገበትን በርካታ ምክንያቶች ማቅረብ ቢቻልም የሚከተሉት ሁለቱ ግን ዋነኛዎቹ ናቸው ብለን እናምናለን።
አንደኛውና ዋነኛው ምክንያት ህወሓት የተከታዮች ድርቅ የደረሰበት መሆኑ አድርባይ መሪዎቹን ማሳሰቡ ነው። በሚሊዮን ይቆጠራሉ የሚባሉት የኢህአዴግ አባላት ልባቸው ከህወሓት ጋር አለመሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። በተለይ ደግሞ በተላላኪዎቹ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደህዴግ የተሰባሰቡ አባላት በግልጽ ህወሓትን መቃወም እየጀመሩ ነው። ህወሓት የራሱን መጥፊያ እያደራጀ መሆኑ የተሰማው በመሆኑ አዳዲስ “ምዕመናንን” ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ መመልመል ይፈልጋል። የመንግሥት ንብረትና መዋቅር ለፓርቲ ስልጠና የሚጠቀም በመሆኑ ከብዛት የሚገኝ ትንሽም ቢሆን ጥቅም የሚያገኝ ከሆነ የወጭው ጉዳይ ህወሓትን አያሳስበውም። ስለሆነም ይህ ስልጠና በተቻለ መጠን ብዛት ያላቸዉን የተማተሩ ወጣቶች በአድርባይነት ለህወሓት ማሰለፍን አላማዉ አድርጎ የተነሳ ስልጠና ነዉ።
ሁለተኛው አቢይ ምክንያት ደግሞ ህወሓት ለኢትዮጵያ ወጣት ለማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ወደ እያንዳንዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ጆሮ መድረሱን ማረጋገጥ መፈለጉ ነው። መልዕክቱም “ሜዳ ውስጥ ያለሁት ተጫዋች እኔ ብቻ ነኝ። ለሚቀጥሉት አርባና አምሳ ዓመታትም እኔን የሚገዳደረኝ አይኖርም፤ ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ ለለውጥ ያለህ ተስፋ ከንቱ ነው። አርፈህ ቁጭ ብለህ ተገዛ” የሚል መልክት ነው።
ስልጠናዎቹ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት ዓላማዎችን በሚገባ ማስፈፀም ይችላሉ ብሎ መገመት ከባድ ነው። የስልጠናው ይዘት እጅግ የወረደ እና የሰልጣኞቹን ብስለት ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑ ስልጠናውን ምፀት የበዛበት አድርጎታል፤ አሰልጣኞቹንም ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል። የስልጠናዎቹ ጽሁፎች (ማንዋሎች) ይዘት ደግሞ የአዘጋጆቹ የእውቀት ማነስ ምን ያህል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑ ለተማሪዎቹ ተጨባጭ ማስረጃዎች ሆነውላቸዋል። በአጠቃላይ ስልጠናው ለአሰልጣኝ ካድሬዎች ያልተዘጋጁበት ፈተና ደቅኖባቸዋል። የኢትዮጵያ ወጣት ሲሞሉት የሚሞላ ባዶ ጋን አለመሆኑን እያዩት ነው። ወጣቶች ጠጣር ጥያቄዎችን ያነሱባቸዋል፤ አሰልጣኖች እነዚህ ጥያቄዎች እንዴት መመለስ እንዳለባቸው ስለማያውቁ ይደናበራሉ። መልስ ሲጠፋ ቁጣ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ ይከተላል።
ይህም ሆኖ እነዚህ ስልጠናዎች ለህወሓት ምንም ውጤት አያስገኙም ብሎ ማለፍ አይቻልም። የስልጠናዎቹ ውጤት የሚወሰነው ግን የኢትዮጵያ ወጣት ከህወሓት ውጭ ለሚመጣ መረጃ ባለው ቅርበት መጠን ነው። ሁሉም የመረጃ ምንጮች ተዘግተውበት የህወሓትን የእድገትና የሰላም መዝሙር ሲሰማ ለኖረ ሰው በስልጠናው የሚሰጡ ባዶ ፕሮፖጋንዳዎችን የመቃወሚያ ምክንያት አይኖረውም። ለተለያዩ የመረጃ ምንጮች ቅርበት ያለው ወጣት ግን የህወሓት መዝሙር ከግራዚያኒ የእድገትና የሰላም መዝሙር የተለየ አለመሆኑን ይረዳል። በፋሺስት ወረራ ወቅት ግራዚያኒም ኢትዮጵያን በመንገድና በህንፃ እየገነባሁ ነው፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ አውሮፓ የደረሰችበት ደረጃ ላይ አደርሳታለሁ ይል እንደነበር ይታወሳል።
የህወሓትን ኢትዮጵያን ለአርባና አምሳ ዓመታት የመግዛት እቅድን ወጣቱ ምክንያታዊ ነው ብሎ ይቀበላል? የራሱን አፋኝ ህጎች አክብረው እየተፍጨረጨሩ ያሉ ተቀናቃኖቹን እንኳን በእንጭጩ እየደፈጠጠ ያለ ሥርዓት “ኃላፊነት የሚሸከም አጣሁ” የሚለው ሰበቡ በወጣቱ ዘንድ ምን ያህል ተቀባይነት ይኖረዋል? በግንቦት 7 እምነት ይኸኛው የስልጠና ዓላማ ሊሳካ የሚችለው በዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ድክመት ብቻ ነው። ዘረኛውንና ዘራፊውን ወያኔ መጣል ብቻ ሳይሆን ከወያኔ በኋላ ፍትህ፣ እኩልነትና ብልጽግና የሚሰፍኑበትን ስትራቴጄ ያዘጋጀና ለስትራቴጂዉ ክንዉንራሱን ያዘጋጀ ድርጅት መኖሩን የኢትዮጵያ ወጣት ማወቅ ይኖርበታል። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከሌሎች ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ወደ ነፃነት፣ እኩልነትና ብልጽግና ጎዳና ለማስገባት እየታገለ መሆኑን ሁሉም ወጣት ሊገነዘብ ይገባል። ይህ ግንዛቤ ካለ የኢትዮጵያ ወጣት ለእብርተኛው፣ ዘረኛው፣ ሙሰኛውና ከፋፋዩ ህወሓት ተገዢ አይሆንም።
በስልት ከተጠቀምንበት ህወሓት ብዙ ሚሊዮኖች የሕዝብ ገንዘብ አውጥቶበት ያዘጋጀው ስልጠና ለራሱ ከሚሰጠው ጥቅም በላይ ለዲሞክራሲያዊ ኃይሎች የሚሰጠው ጠቀሜታ ይበልጣል። ለምሳሌ፣ ግንቦት 7 እነዚህን ስልጠናዎች የኢትዮጵያን ወጣት ለትግል ያላቸውን ዝግጁነት ለመገምገም ተጠቅሞበታል። “የኢትዮጵያ ወጣት ለትግል ዝግጁ ነው – የቀረው ድርጅት ነው” ሲል የግምገማውን ውጤት አሳውቋል። በዚህም ርዕሰ አንቀጽ ይህንኑ መልዕክት ማስረጽ ይፈልጋል።
በአምባገነን ሥርዓቶች ውስጥ የሚኖሩ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ከተለመዱ አደረጃጀቾች መለየት አለባቸው። መደበኛ (Formal) አደረጃጀቶች አባላትን ለአደጋ ያጋልጣሉ። በዚህም ምክንያት ነው ግንቦት 7፣ ኢ-መደበኛ (Non Formal) አደረጃጀቶች የሚመርጠው። በእኛ ሁኔታ “ኢ-መደበኛ አደረጃጀት” ስንል አራት ይሁን አምስት የሚተማመኑ ወጣቶች የሚፈጥሩት የግንቦት 7 ሴል ነው። ይህንን ሴል የፈለጉትን ስም ሊሰጡት ይችላሉ – እድር፣ ክበብ፣ የሆነ ስፓርት ቡድን ደጋፊ የተመቻቸውን ስያሜ ይስጡት። የተቋቋመበት ዓላማ ግን ግልጽ ነው – ለፍትህና ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ማገዝ ነው። ይህ ኢ-መደበኛ ስብስብ ራሱን የግንቦት 7 አካል አድርጎ ይቁጠር። የግንቦት 7 ፕሮግራሞችንና ጽሁፎችን ያንብብ። ስብስቡ ለመረጃዎች ራሱን ቅርብ ያድርግ። መረጃዎችን ይለዋወጥ። በሂደት ቀጣዩ መንገድ ግልጽ እየሆነለት ይመጣል።
እየተካሄደ ያለው የህወሓት የጅምላ ስልጠና ለኢ-መደበኛ ድርጅቶች መስፋፋት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። የግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች እነዚህን ስልጠናዎች የግንቦት 7 ሴሎችን ለማደራጀት እንዲጠቀሙበት እንመክራለን። ግንቦት 7 በኢትዮጵያ ወጣት የፈጠራ ችሎታ ላይ እምነት አለው። የኢትዮጵያ ወጣት አደንቁሮ ሊቀብረው የመጣውን ስልጠና ህወሓትን ለመቅበሪያነት እንደሚጠቀምበት የግንቦት 7 እምነት ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
onsdag 3. september 2014
ግንቦት 7 ንቅንቄ ቅዳሜ ኦገስት 30, እሁድ ኦገስት 31, እና ሰኞ ሴፕቴምበር 1, 2014 በመላው አለም ያደረጋቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች ማሳካቱን ገለጸ።
ግንቦት 7 ንቅንቄ ቅዳሜ ኦገስት 30, እሁድ ኦገስት 31, እና ሰኞ ሴፕቴምበር 1, 2014 በመላው አለም ያደረጋቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች ማሳካቱን ገልጿል።
Sept 02, 2014
በአለም 26 ከተሞችና በኖርዝ አሜሪካ በሚገኙ 6 ታላላቅ ከተሞች የተደረጉት ውይይቶች በርካታ ኢትዮጵያኖች በቦታው በመገኘት ድጋፋቸውን ያሳዩበትና የገለጹበት ሲሆን፣ ዝግጅቱ በአትላንታ፣ ቦስተን፣ቴክሳስ፣ በዋሽንግተን ዲሲ እንዲሁም በካናዳ ቶሮንቶና ካልጋሪ ተካሂዷል።
በነዚህ ስብሰባዎች ሁሉ የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ የታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ስራዎች ሲታወሱና ሲዘከሩ ውለዋል። በሁሉም ስብሰባዎች ወያኔን ማስወገድ በሚቻልበት ስልቶችና ትብብሮች ላይ ሰፊ ውይይቶች ተደርጎባቸዋል። በታላላቁ ከተሞች ቁጥሩ በርካታ ህዝብ በተገኘበት በዚሁ ስብሰባ ማህበረሰቡ የተሰማውን ቁጭት በመለወጥ ትግሉን በማገዝና በመቀላቀል የወያኔን እድሜ ማሳጠር ወቅቱ የሚፈልገው ምላሽ መሆኑን ተሰብሳቢዎች አስምረውበታል።
Norway
ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ትግሉን ዳር ላይ አድርሶታል ከዚህ በኋላ ፍሬውን ማየት እንደሚፈልጉ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ሲገልጹ፣ ለዚህ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ ከአበው የወረሰውን የእምቢተኝነት እና አልገዛም ባይነትን በመድገም መሰዋእትነት በመሆን ኢትዮጵያን ከአምባገነኖች ነጻ ለማውጣት የነጻነት ሃይሉን በመቀላቀል ኢትዮጵያዊ ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል ሲሉ የመድረክ ተናጋሪዎች ተመሳሳይ የሆነ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በዚህ ላንቺ ነው ኢትዮጵያ በተባለው የግንቦት 7 ዘመቻ በርካታ የገንዘብ ድጋፍ የተሰበሰበ ሲሆን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአባላት ድጋፍ እና ትግሉን ለመቀላቀሉን የቆረጡ ምዝገባዎች መካሄዳቸውን አረጋግጠናል።
Abonner på:
Innlegg (Atom)