fredag 4. juli 2014

የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለወያኔ ፋሽስቶች አሳልፋ መስጠቷን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

July 4, 2014
የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለወያኔ ፋሽስቶች አሳልፋ መስጠቷን በማስመልከት የወጣ መግለጫ
ሰኔ 27 ቀን 2006 ዓ.ም
የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቶ መቆየቱ ማስታወቃችን ይታወሳል።
የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቄዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል። በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።
የወያኔ ፋሽስቶች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰቃየት ትግላችንን ማቀዝቀዝ እንደማይችሉ ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን። እንዲያውም በግልባጩ ቁጣና እልሃችን በእጥፍ ድርብ በመጨመር ትግላችንን ያጦዘዋል። ወያኔ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በውንብድና ጠልፎ መውሰዱ የትግሉን ሜዳ አስፍቶታል፤ የትግሉንም ዓይነት አብዝቶታል። ይህ ደግሞ የወያኔ ፋሽስቶችን ከፍ ያለ ዋጋ ያስከፍላቸዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ህገ ወጥ እገታ ከተሰማ ዕለት ጀምሮ የፓለቲካ ልዩነት አጥር ሆኖ ሳይከልላችሁ ከጎናችን ለቆማችሁ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማኅበራትና ዜጎች ሁሉ ምሥጋናችንን እናቀርባለን። በወገናዊ ተግባራችሁ ልባችን ተነክቷል። ከዚህ በላይ ደግሞ ለቀጣዩ ወሳኝ ፍልሚያም እንደምንቆም እና የወያኔን እድሜ እንደምናሳጥር እምነታችን አጠንክሮልናል።
ከዛሬ ጀምሮ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳርጋቸው ጽጌን ሆኗል። ዛሬ ዘጠና ሚሊዮን አንዳርጋቸው ጽጌዎች በአንድነት ተነስተዋል። በአንድ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰው ጥቃት ሰበብ ሆኖ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣ የወያኔ ፋሽስቶችን ይጠራርጋል። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ለደረሰውና ለሚደርሰው ጥቃት እያንዳንዱ የወያኔ ሹም በግል ዋጋ ይከፍላል። ከእንግዲህ በምሬት የተነሳሳው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂው ራሱ ወያኔ መሆኑን እውን ሆኗል። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስር የክተት አዋጅ ታውጇል። ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለሀገር፣ ለእኩልነት ግድ ያለህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተነስ!!!
በመስዋዕትነት ድልን እንቀዳጃለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

torsdag 3. juli 2014

(ሰበር ዜና) ግንቦት 7 በአቶ አንዳርጋቸው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ከሰዓታት በኋላ መግለጫ ይሰጣል

በአቶ አንዳርጋቸው ዙሪያ በተለያዩ የመረጃ መረቦች ‘ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው ተሰጥተዋል’ እየተባለ በሰፊው እየተወራ ሲሆን ዘ-ሐበሻ ይህን ጉዳይ ለማረጋገጥ ወደ ግንቦት 7 አመራሮች ደውላ ነበር። ያነጋገርናቸው አመራሮች እንዳሉን ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ መንግስት ተሰጥቷል የሚባለውን እያጣራን ሲሆን ማምሻውን መግለጫ እንልካለን ብለዋል።
በሌላ በኩል አልጀዚራ የኢትዮጵያ መንግስት የመን አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ እንድትሰጥ መጠየቋን ዛሬ ዘግቧል።
መግለጫው እንደደረሰን ዘ-ሐበሻ ላይ እናቀርባለን።
andargachew

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ… ኤርትራ እና የመን ተፋጠዋል

መልእክተ ዜና – በዳዊት ከበደ ወየሳ
ኤርትራ የየመንን አየር መንገድ እንደምትዘጋ አሳወቀች (ምክንያቱ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር ነው)
Andargachew-Tsige
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ
(ኢ.ኤም.ኤፍ) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰና፣ የመን ውስጥ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ታፍኖ መታሰሩ ብሎም አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አለመታወቁ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ትራንዚት እያደረገ በነበረበት ወቅት ነበር በየመን ታጣቂዎች ታፍኖ የተወሰደው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በየቦታው ድምጻቸውን ለማሰማት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። ከ’ነዚያ ሁሉ ድምጾች ግን ጎልቶ የወጣው በኤርትራ በኩል የተላለፈው መግለጫ ነው። ይህን የኤርትራን መግለጫ መሰረት በማድረግ፤ ሌሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የራሳችንን ሃሳብ እንሰጣለን።
ኤርትራ ለየመን በላከችው መልዕክት መሰረት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ካልተፈታ፤ በኤርትራ አየር ላይ የሚሄዱትንም ሆነ፤ ምድር ላይ የሚያርፉት የየመን አውሮፕላኖች የሚታገዱ መሆኑን ገልጿል። ይህ ደግሞ እያደገ ለመጣው የየመን አየር መንገድ ትልቅ ኪሳራን የሚያስከትል ነው። ኤርትራ የጀርመኑን ሉፍታንዛ ካገደች ወዲህ፤ የየመን አየር መንገድ ሉፍታንዛን ተክቶ፤ አስመራ ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት ወደ አውሮፓ የሚሄዱም ሆኑ የሚመጡ አውሮፕላኖች በየመን በኩል አድርገው ማለፍ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። አሁን ኤርትራ የየመን አየር መንገድን እንደሉፍታንዛ የምታገድ ከሆነ፤ የየመን መንግስት የሚያገኘው ከፍተኛ ገቢ ሊቀንስበት ይችላል።
ከዚህ በፊት ባቀረብነው ዘገባ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ አገር ዜግነት ያለው እና የእንግሊዝን ፓስፖርት ይዞ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ስለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስናወራ፤ የ እንግሊዝንም መንግስት የጉዳዩ ባለቤት ማድረግ ያስፈልጋል። እንግሊዝ ዜጋዋ በየመን ታስሮ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይላክ በአውሮፓ ዲፕሎማሲያዊ ስራ መስራት ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ እና የመን እስረኛን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ቢኖራቸውም፤ የመን የ እንግሊዝ ዜግነት ያለውን ሰው አሳልፋ እንዳትሰጥ በዛቻ ሳይሆን፤ በህጋዊ መንገድ የመንን መሞገት ያስፈልጋል።
ከ እንግሊዝ በተጨማሪ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችም በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡ ማድረግ ሌላው ብልሃት ነው። አሜሪካ ከየመን ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት በመጠቀም አቶ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ በየመን የአሜሪካ ኢምባሲ ጥረት እንዲያደርግ ጫና መፍጠር ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት ግንቦት ሰባት የሚያወጣቸው የማስፈራሪያ መግለጫዎች ድምጸታቸውን በማስተካከል እንደአንድ በሳል የፖለቲካ ድርጅት የሚታይ ዲፕሎማሲያዊ ስራ በመስራት ለውጤት መብቃት አለባቸው። በመሆኑም ከማስፈራሪያ መግለጫዎች ይልቅ፤ ከዲፕሎማሲያዊው ዘመቻ ጎን ለጎን… ህጋዊ ጠበቃ በየመን አዘጋጅቶ፤ ጉዳዩ በኢሚግሬሽን እና በዋናው ፍርድ ቤት እንዲታይ በማድረግ፤ ቢያንስ አቶ አንዳርጋቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይላክ ጊዜ መግዛት ይቻላል።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው እንደመሆኑ መጠን ዲፕሎማሲያዊው ዘመቻ በእንግሊዛውያን ጭምር እንዲሰራ፤ ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎች የአገሪቱ ሚዲያዎች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ ተገቢ ነው። የምናወጣቸውም መግለጫዎች በአማርኛ ሳይሆን ሁሉም አገራት በሚረዱት እንግሊዘኛ ቋንቋ ሊሆን ይገባዋል። ከዚያ ውጪ ግን “አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባስቸኳይ ካልተፈታ በኢትዮጵያ እና በየመን ባለስልጣናት ላይ እርምጃ እንወስዳለን” አይነት መግለጫዎች፤ ወያኔ ኢህአዴግ “ግንቦት ሰባት የአሸባሪዎች ድርጅት ነው” የሚለውን አባባል ከማጠናከር ውጪ ብዙም ፋይዳ ላይሰጥ ይችላል።
ይህ ብቻም አይደለም። በማህበራዊ ድረ ገጾች እና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከዚህ በፊት ያደረጓቸው ንግግሮች እየተለጠፉ መሆኑን ታዝበናል። እንዲህ አይነቶቹ… ቀደም ሲል የተደረጉ ንግግሮችን አሁን ለእይታ ማቅረቡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስሩ እንዲጸናባቸው እንጂ፤ እንዲፈቱ ስለማይረዳቸው፤ በዚህ ረገድ ሌላ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በድጋሚ ለማሳሰብ ያህል… ግንቦት ሰባትም የማስፈራሪያ መግለጫዎችን ከማውጣት ይልቅ፤ በሌሎች ዜጎች እየተደረጉ ያለውን ጥረት ማስተባበር እና ዲፕሎማሲያዊ ይዘት እንዲኖራቸው ማድረግ አለበት። ኤርትራ ያደረገችውን ውሳኔ በማድነቅ፤ ሌሎች አገሮችም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ማበረታታት ከግንቦት ሰባት አመራሮች የሚጠበቅ ነው።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሌሉበት ሞት የተፈረደባቸው መሆኑን፣ ንብረታቸው በወያኔ ኢህአዴግ መወረሱን፣ ወላጅ አባታቸው እና ቤተሰባቸው በእስር መንገላታቱን አጉልቶ በማውጣት የወያኔ ኢህአዴግን አስከፊ ገጽታ ማሳየት ይቻላል። አሁንም የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ወደ ኢትዮጵያ ብትመልስ በወያኔ ኢህአዴግ ሊደርስባቸው የሚችለውን የግድያ ወንጀል ማሳወቅ እንጂ፤ “አቶ አንዳርጋቸው ካልተፈታ ወዮላቹህ!” የሚለው አይነት ማስፈራሪያ ህሊና ለሌላቸው የሁለቱም አገራት አምባገነን መሪዎች ላይሰራ ይችላል። ህዝብ እና አገር የሚመሩት በእውቀት እና በጥበብ ጭምር በመሆኑ፤ ህጋዊ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመከተል… ነገር ግን በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ አቶ አንዳርጋቸውን የማስፈታቱን ሂደት እንቀጥል – የዛሬው ዜና መልእክታችን ነው

onsdag 2. juli 2014

Yemen: Global Alliance Outraged by Mr. Andargachew Tsege’s Detention

July 2, 2014

Ethiopian-Americans are outraged by news of the illegal detention on June 23, 2014 of Mr. Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy while in transit at Sanaa International Airport in Yemen. Mr. Tsege was travelling with a United Kingdom passport at the time of his detention.Global alliance for the rights of Ethiopians
Mr. Tsege, a well-known pro-democracy and human rights activist in his ancestral homeland, Ethiopia, presents no threat to Yemen or to the Yemeni authorities. Mr. Tsege was imprisoned in Ethiopia for his political activities during the ill-fated election of 2005 and has escaped assassination attempts by the dictatorship in Ethiopia whose brutality, is well documented by international human rights groups and the United States State Department. He has been convicted and sentenced to death in absentia by the tyrannical regime in Ethiopia. We are particularly concerned that the continued illegal detention of Mr. Tsege, a renowned critic of the Ethiopian government is politically motivated and against international law.
It is now universally recognized that the Ethiopian regime subjects political opposition, human rights defenders, journalists and critics of the government in general, to persecution including threats, intimidation, arbitrary arrests and detentions, politically motivated trials, enforced disappearances and torture , extra-judicial killings.
Unconfirmed reports have come out from Ethiopia that the Ethiopian government has requested the extradition of Mr. Tsege to Ethiopia. The principle of non-refoulement is well established in customary international law, prohibiting states, in this case Yemen, from extraditing Mr.Tsege to Ethiopia where he will certainly face torture and even death by the brutal regime of Ethiopia.
It’s unconscionable that the Government of Yemen would hand Mr. Tsege over summarily to the security forces of the Ethiopian regime whose persecution of its critics at home and abroad is well documented.
We respectfully urge the Government of Yemen:
  • To release Mr. Tsege immediately and unconditionally;
  • To respect its solemn obligations under international law and release Mr Tesge immediately and unconditionally;
  • To immediately inform his family and loved ones of his whereabouts;
  • To allow ICRC representatives to visit him wherever he is being held;
  • To stop any illegal renditions the regime in Ethiopia may have requested.
We urge all human rights defenders and advocates to speak out against the illegal detention of Mr. Tsege and call on the government of Yemen for his unconditional and immediate release.
Ethiopian-Americans are outraged by news of the illegal detention of Mr. Andargachew Tsege

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ

Melaku-Fenta-and-Gebrewahid-Woldegiorgisየፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ፡፡ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር በሚገኙት በእነ አቶ መላኩ ላይ የኮሚሽኑ
ዓቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ሦስት የክስ መዝገቦች መካከል በመዝገብ ቁጥር 141356 ላይ ከቀረቡ 28 ክሶች መካከል 23 ክሶችን አሻሽሎ እንዲያቀርብ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15 ወንጀል ችሎት ብይን መስጠቱ ይታወሳል፡፡
የፍርድ ቤቱን ብይን የተቃወመው የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የክስ መዝገቡን ማሻሻል እንደሌለበት በመጥቀስ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ አቤቱታውንና ብይኑን መርምሮ የዓቃቤ ሕግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሥር ፍርድ ቤቱን ብይን አፅንቶታል፡፡
የሥር ፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ እንዲያሻሽል ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረው ዓቃቤ ሕግ በቡድን በቡድን ያቀረባቸው 23 ክሶችን ነጥሎ እንዲያቀርብ፣ ጊዜና ቀን ያልተጠቀሰባቸውን ክሶች ጠቅሶ እንዲያቀርብና ለክሶቹ ማስረጃነት ያቀረባቸው ሰነዶች ጥቅል በመሆናቸው የትኛው ማስረጃ ለየትኛው ክስ እንደሚያስረዳ ግልጽ ባለመሆኑ አስተካክሎ እንዲያቀርብ ብይን ሰጥቶ ነበር፡፡
ይህንን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት ያፀናው በመሆኑ፣ ዓቃቤ ሕግ ሰኔ 27 ቀን 2006 ዓ.ም. በችሎት ቀርቦ ክሶቹን አሻሽሎ የሚያቀርብበትን የጊዜ ትዕዛዝ ይቀበላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግስት ከታገቱ በሁዋላ የኢትዮጵያ ትምባሆ ድርጅት ለየመን ኩባንያ ተሰጠ

andargachew
በአሁኑ ወቅት የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግታ ባለችበት ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየመኑ ኩባንያ ሼባ ኢንቨስትመንት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 60 በመቶ ባለቤት እንዲሆን መወሰኑ በርካታ ፖለቲከኞችን እያነጋገረ ይገኛል;:
ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የ70 ዓመት ዕድሜ ባለቤት የሆነው ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት 22 በመቶ የሚሆነው አክሲዮን ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ በየመኑ ሼባ ኢንቨስትመንት ሲያዝ፣ ቀሪው 78 በመቶ አክሲዮን ደግሞ በመንግሥት የተያዘ ነበር፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወሰነው አዲስ ውሳኔ ሼባ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 38 በመቶ አክሲዮን ከመንግሥት ላይ እንዲገዛ የሚፈቅድ በመሆኑ፣ ሼባ ኢንቨስትመንት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ላይ አንበሳውን ድርሻ 60 በመቶ ሲይዝ፣ መንግሥት ደግሞ 40 በመቶ ድርሻ ይዞ ይቀጥላል፡፡
ሼባ ኢንቨስትመንት እንዲገዛ ለተፈቀደለት 38 በመቶ አክሲዮን 1.3 ቢሊዮን ብር መክፈል እንደሚጠበቅበት የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለሪፖርተር ገልጸው፣ ኩባንያው ይህንኑ ገንዘብ እንደከፈለ የስም ዝውውር እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
ብዙም ባልተመለመደ ሁኔታ የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አክሲዮን ሽያጭ ላይ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ ለመስጠት የተቸገረው በሁለት ምክንያቶች መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ የመጀመርያው ድርጅቱ በሲጋራ ላይ ብቸኛ መብት (ሞኖፖሊ ራይት) ያለው በመሆኑ፣ ይህ የብቸኝነት መብት የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ድርሻ በሚይዝበት ወቅት ምን መሆን አለበት? የሚለው ጉዳይ ላይ አቋም መያዝ ባለመቻሉ ነው፡፡ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ የታክስ ዓይነቶች በየዓመቱ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት የሚያስገባ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ትርፋማ ከሆኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ በመሆኑ፣ ለመንግሥት ግምጃ ቤት ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ የሚያደርግ ነው የሚለው ጉዳይ ቦርዱ በአክሲዮኑ ሽያጭ ላይ ለመወሰን እንዲቸገር ማድረጉ ነው፡፡
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ የሚመራው የፕራይቬታይዜሽን ቦርድ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የመንግሥትን አቅጣጫ በግልጽ ባለመረዳቱ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቅጣጫ እንዲሰጠው መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሁለቱም ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው የአክሲዮን ሽያጩ እንዲከናወን በማዘዙ፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተሰበሰበው የፕራይቬይታዜሽን ቦርድ የየመኑ ኩባንያ ከፍተኛ ባለድርሻ መሆን የሚያስችለውን ውሳኔ እንዲወስን ማድረጉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ትምባሆ ድርጅት በተለያዩ አካባቢዎች የትምባሆ ልማት የሚያካሂድባቸው የእርሻ መሬቶች ባለቤት ነው፡፡ የድርጅቱ መሥርያ ቤት ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳር ቤት በሚወስደው መንገድ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን፣ ለፀጥታ አመቺ አይደለም በሚል መሥርያ ቤቱ ከዚህ ቦታ ተነስቶ ወደ አቃቂ አካባቢ እንዲዛወር ተወስኗል፡፡ ምንጮቹ እንደገለጹት ድርጅቱ ቃሊቲ አካባቢ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተረከበው ቦታ ላይ የሚያካሂደውን ግንባታ ሲያጠናቅቅ፣ ለበርካታ ዓመታት ከነበረበት ቦታ ይነሳል ሲል ሪፖርተር ዘገባውን አጠናቁአል::
ውድ አንባቢያን በኢትዮጵያ አትራፊና ከፍተኛ ታክስ ከፋይ ከሆኑ ትላልቅ የመንግስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት አቶ አንዳርጋቸው ከታሰሩ ወዲህ ለየመኑ ኩባንያ በጠቅላይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንዲተላለፍ መደረጉ ዙሪያ ምን ትላላችሁ?

tirsdag 1. juli 2014

ግንቦት 7 – አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

ከግንቦት 7 አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ
ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም
Andargachew Tsigieየግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቷል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን የጉዞው መዳረሻ አልነበረም፤ ከየመን ጋርም የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ አልነበረውም። የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግቶ ለአንድ ሰዓት እንኳን ለማቆየት ምንም ምክንያት የለውም። በዚህም ምክንያት ያለአግባብ የታገተብን የንቅናቄያችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። እንዲያውም የየመን ባለስልጣናት አምባገኑን ወያኔ ለመርዳት ባለው ፍላጎት ሳቢያ መሪያችንን አሳልፎ ሊሰጠው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮብናል።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ጊዜውን፣ እውቀቱንና ጉልበቱን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ፤ ዝግጁነቱንም በተግባር ያሳየ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። የየመን መንግሥት ከዘረኛውና ፋሽስታዊው ወያኔ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ታጋይ መሪያችን ላይ እየፀመ ያለውን ደባ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ የንቅናቄዓችን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስኗል።
ትግላችን መስዋትነት እንደሚያስከፍል እናውቃለን። ከዚህ በፊትም ብዙ ጓዶቻችን መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ወደፊትም ብዙ መስዋዕትነት መከፈሉ የማይቀር ጉዳይ ነው። አሁን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰውና ወደፊትም ሊደርስ የሚችለው ጉዳት ምሬታችን በማብዛት፣ ቁጣችንና ዝግጁነታችን ከማጠንከር በስተቀር ቅንጣት ታክል እንኳን ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ እንደማያደርገን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለአባሎቻችንና ለደጋፊዎቻችን ሁሉ መግለጽ እንወዳለን።
መንግሥታት ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ። ኢትዮጵያና የመን ግን ጎረቤታሞች ሆነው መቆየታቸው የማይቀር ነው። የየመን መንግሥት የወያኔ እድሜ አጭር መሆኑ የተገነዘበ አይመስልም። በዚህም ምክንያት የየመን መንግሥት የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች የቆየ ወዳጅነት የሚያደፈርስ እርምጃ ወስዷል። የየመን መንግሥት የየመንን የወደፊት የረዥም ጊዜ ጥቅም እንዲያሰላና ያገተብንን መሪ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንመክራለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመሪያችን ላይ ጉዳት ቢደርስ ወይም ለወያኔ አሳልፎ ቢሰጥ የመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማይሽር ቂም ውስጥ የምትገባ መሆኑን የየመን መንግሥት አውቆ በጥብቅ እንዲያስብበት እናስጠነቅቃለን።
በየመን መንግሥት አልሰማ ባይነት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ ተላልፎ ቢሰጥ በአካሉና በሕይወቱ ለሚደርሰው ሁሉ የወያኔ ፋሽስቶችን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ ከአሁኑ እናስጠነቅቃለን። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስና ሕይወት ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ጥቃት ለነፃነታቸው ለመሰዋት ዝግጁ የሚሆኑ እልፍ አዕላፍ ታጋዮችን እንደሚፈጥር ጥርጥር የለንም። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስ እና ሕይወት ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ሁሉ በማንኛውም መንገድ በማንኛውም ቦታ የምንበቀል መሆኑንና ብዙ የወያኔ ሹማምንት ዋጋ የሚከፍሉበት እንደሚሆን እንዲያውቁት እናስጠነቅቃለን ።
በመስዋዕትነት ድልን እንቀዳጃለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!