torsdag 26. juni 2014

የወያኔን የጥፋት ድግስ እናምክን! June 26, 2014

ኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና ህልውናቸው በበለጠ ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር።
ህወሃት በህዝቡ ውስጥ የኖረውን ልዩነት የጠብ፣ የግጭትና የመፈራራት መሰረት በማድረግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ካለው ምኞት የተነሳ በመደዴ ካድሬዎቹ አማካኝነት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ በማቃቃር እኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ ይገኛል።
ህወሃት ይህን የማጋጨት ስራ በተለይ በስልጣን የመቆየት ፍርሃት ባባነነው ቁጥር የሚጠቀምበት መሳሪያ አድርጎታል። በባህርዳር ላይ የብሄረሰቦች ኳስ ጭዋታ ውድድር ምክንያት አድርጎ፣ መደዴ ካድሬዎቹን አሰማርቶ ስታዲዮም ውስጥ ኦሮሞዎች እንዲሰደቡ ካደረገ በኋላ ነገሩን ከማረጋጋት ይልቅ በኦሮሞኛ የቴሌቪዥንና ሬድዮ፣ ኦሮሞዎች በአማራዎች ተሰደቡ ብሎ ያስነገረው ለምንድን ነው? ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ቁጣና ጠብ ለመቀስቀስ ብሎም በዚህ ጠብ ውስጥ ገላጋይ በመምሰል የአንዱ ብሄር ጠባቂ መስሎ ለመታየት ጉዳዩን ባልተረዱ የዋሆች ውስጥ ለመግባት ይፈልጋል። በአማራ ተወላጆች አካባቢ እኛ ከሌለን ኦሮሞ ይፈጇቹኋል፤ በኦሮምያም በሶማሊያም እንዲሁ በተዘጋ በር ውስጥ በተቃራኒው ዘረኝነትንና መከፋፈልን በመስበክ ንጹሃኑ ህዝብ ከፍርሃት ተነስቶ ተገዥ ደጋፊዎቹ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መሆኑንም ያልገባቸው የዋሆች ይኖራሉ። ህወሃትንና ባህርዩን በቅጡ ለምናውቀው ወገኖች ግን ይህ ተንኮሉ ትልቅ ሚስጥር አይደለም።
የጉጅሌው ቡድን የራሱን ስልጣንና የዝርፊያ ኢኮኖሚ ኮርቻ ለማደላደል እስከረዳው ወይም የሚረዳው መስሎ እስከታየው ድረስ ደሃ ገበሬዎችን ማፋጀትን፣ ህዝብን እርስበርስ ማናከስን፣ የቂም መርዝ መዝራትን የሚያየው እንደ ፖለቲካ ጥበብ ነው።
ጉጅሌው ብልጠት መስሎት የጎሰኝነትንና የማንነትን ደመነፍስ የሚነካ ፕሮፖጋንዳ በህዝቡ ውስጥ በመንዛት ሊያደርስ የፈለገው ጥፋት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስላልሰራለት የራሱን ሎሌዎችና ተካፋይ መደዴ ካድሬዎችን በማሰማራት የጭካኔ ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኑን በብዙ መረጃዎች አረገጋግጠናል። በአሁኑ ወቅት በየቦታው የሚካሄደውን የህዝብ ማፈናቀልና ግጭት የሚመራው ራሱ ህወሃት ያሰማራቸው ካድሬዎች እንጂ በራሱ በህዝቡ ተነሳሽነት እንዳልሆነ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል። በዚህ ሳይጣናዊ አካሄድ ለምትደርሰው ለያንዳንዷ ጉዳት ሀላፊነት የሚወስደውም ራሱ ህወሃት መሆኑን ግንቦት 7 አጥብቆ ያምናል።
ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ የሚደግስልንን የጥፋት ድግስ ለማምከን የየብሄረሰቡ ልሂቃን ሁሉ አንድ ላይ ሆነን ህዝባችንን እንድንታደግ ግንቦት 7 ለሁሉም የነጻነት ሃይሎች ጥሪውን ያቀርባል።
ግንቦት 7 በዚህ የህወሃት የጨለማ መንገድ ላይ የሚያበራውን የብርሃን ችቦ ይበልጥ በማብራት ላይ ይገኛል። ሁላችንም በምናገኘው የብርሃን ሃይል ጨለማው ላይ እያበራን ከማሳየት አልፈን ወደ መቃብሩ ልንገፋው ይገባል።
ግንቦት 7 በኢትዮጵያ የማንነትና የብሄር ብሄረሰብ ጉዳዮች በሰለጠነ መንገድ እና በመደማመጥ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደረግ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ያምናል። ይልቁንም የወደፊቱ የህዝባችንና የሀገራችን ጥቅም ይበልጥ የሚከበረው በስብጥርነታችን ላይ በምንገነባው አንድነት መሆኑን ያምናል።
የተከበራችሁ የአገራችን ዜጎች የነጻነታችን ጊዜ ቅርብ ነው። ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ ያዘጋጀልንን የጥፋት ድግስ፣ ሀገራችን የጋራ ጠላት በመጣባት ጊዜ ሁሉ እንደምታደርገው በአንድ ላይ ታግለን የጋራ ታሪክ እንሰራ ዘንድ የዘወትር ጥሪያችን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

የፊታችን ቅዳሜ በመቐለ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ይካሄዳል

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ
ዓረና መድረክ ቅዳሜ ሰኔ 21, 2006 ዓም በመቐለ ከተማ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ያካሂዳል። ለሰልፉ የሚሆን ሙሉ ዝግጅት ተጠናቋል። የመቐለ ህዝብ በሰልፉ ለመሳተፍ ተዘጋጅቷል። ቅዳሜ ጥዋት ከአምስት ሺ በላይ ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል ሰልፉ የጠራንበት ዋነኛ አጀንዳ መድረክ በአዲስ አበባና በክልሎች ዋና ከተሞች እያደረገው ካለው የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ አካል ሲሆን የሰልፉ ዋነኛ አጀንዳዎች ደግሞ የፍትህ እጦት፣ የነፃነት እጦት፣ የዉሃ ችግር፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የመሬት ጉዳይ፣ የግብር ጉዳይ፣ የማዳበርያ ጉዳይ ወዘተ ናቸው።
ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትም ሰለማዊ ሰልፍ በማድረግ ይረጋገጣል። የትግራይ ህዝብ እስካሁን ድረስ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፍጎ ይገኛል። በአላማጣ፣ ኲሓ፣ አይናለም፣ መቐለ (ገፊሕ ገረብ)፣ ሓውዜን፣ ዓዲግራት ወዘተ ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ መክረው በፌደራል ፖሊስ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተገድለዋል። ስለዚህ ቅዳሜ ጥዋት ሰለማዊ ሰልፍ የሚጀመርበት ታሪካዊ ቀን ይሆናል። በመቐለ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የተፈቀደ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ይደረጋል ማለት ነው።
ስለዚህ የመቐለው የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ከዉሃ ጥያቄ የዘለለ ነው። የዉሃ ጥያቄ አንድ መሰረታዊ ጉዳይ ሁኖ ሌሎች አስቸኳይ መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ። ሰዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እየተገደሉ ነው። በሌሎች ክልሎችም እየተገደሉብን ነው። ንፁሃን ዜጎች ያለ ፍርድ እየታሰሩ፣ በድንጋይ እየተወገሩ፣ በፖሊስ እየተደበደቡ፣ በመርማሪዎች እየተገረፉ፣ ያለ ምንም ወንጀል በሽብር እየተከሰሱ ነው። ከዚህ በላይ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ የሚጠይቅ ጉዳይ የለም።
ከሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ከመገረፍ፣ ከመታሰር፣ ከመገደል በላይ ምን ሊያደርጉን ይችላሉ? በሌሎችስ ከዚህ በላይ ምን ተደረገ? ስለዚህ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ በቂ ምክንያት አለን። የመቐለ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ በሰለማዊ ሰልፍ ማክበር አለበት። የመቐለ ህዝብ እንደነ አዲስ አበባዎች፣ ባህርዳሮች፣ ደሴዎችና ሀዋሳዎች የተቃውሞ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ሊከበርለት ይገባል።
የመቐለ ህዝብ ነፃነት ይፈልጋል። ስለዚህ ይሰለፋል። የቅዳሜ ሰልፍ በገዥው መደብ ካልተስተጓሆለ በቀር ኃይለኛ ሰልፍ ይደረጋል። በአደባባይ ስለሚደረግም ማንም ሰው አይቶ ይመሰክራል። የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ እንዳልሆነ ያስመሰክራል። ፎቶዎችና ቪድዮች እንቀርፃለን። ትመለከታላቹ።
ሰልፉ ቅዳሜ ጥዋት በ3:00 ሰዓት ከአደባባይ ዘስላሴ (ባዛር) ተነስቶ በሓውዜን አደባባይ አልፎ ሮማናት አደባባይ አቋርጦ አብርሃ ካስትል ሆቴል ከደረሰ በኋላ ወደ ናሽናል ሆቴል ታጥፎ በጤና ጣብያ በኩል ላዕለዋይ ፍርድቤት ደርሶ ሮማናት አደባባይ ላይ ይጨረሳል። የመድረክ መሪዎች ንግግር ያደርጋሉ። በ6:00 ሰዓት ይጠናቀቃል።
ህወሓት የሀዋሳውን፣ የባህርዳሩን፣ የአዲስ አበባውን ወይ የደሴውን ያህል ከፈቀደልን የቅዳሜ ሰልፍ በእርግጠኝነት የተዋጣለት ይሆናል። እስቲ ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ሰልፍ ከፈቀደ እንይ። መቐለ ሰልፍ ልትጀምር ነው። ህዝብ ዓረና መድረክ ያለውን ድጋፍ ባደባባይ የሚገልፅበት ቀን: ቅዳሜ።
ህወሓት ሰልፉ እስኪጠናንቀቅ ድረስ ፀጥታ ካስከበረ ህወሓትን በፅሑፍ ነው የምናመሰግነው። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ እንደሌላው ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ አስከብሮለታል ማለት ነውና። ሰለማዊ ሰልፍ መፍቀድ በራሱ ጥሩ ነገር ነው። ሰልፍ ለትግራይ ህዝብ ተአምር ነውና። ምክንያቱም ተፈቅዶልን አያውቅም።
እስቲ ህወሓት ትፈተን። እስቲ ህወሓት የህዝብ ድጋፍ አለኝ ብሎ የሚተማመን ከሆነ ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሰልፉን ለማየት ዝግጁ ይሁን።mekele
ለማንኛውም ቅዳሜ እንገናኝ። የዉስጥ ለውስጥ ቅስቀሳው አልቋል። ነገ ዓርብ ፎርማል ቅስቀሳ ይደረጋል። በህዝብ ያለን ድጋፍ ለማወቅ ተከታተሉን።     

onsdag 25. juni 2014

በዓለም አቀፉ የሠላም ደረጃ ኢትዮጵያ ከ162 ሀገራት 139ኛ ደረጃን ያዘች

በየዓመቱ የየሀገራትን የሠላም ይዞታ በማጥናት ደረጃን የሚያወጣው ኢኒስቲትዩት ፎር ኢኮኖሚክስ ኤንድ ፒስ የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም የ2014 የዓለም ሀገራት የሰላም ደረጃ ከሰሞኑ የለቀቀ ሲሆን በዚህም ጥናቱ ከ162 ሀገራት ኢትዮጵያን በ139ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧል። ተቋሙ የአንድን ሀገር የሠላም ደረጃ ለማውጣት በርካታ የስኬት ማሳያዎች (Indicators) ግምት ውስጥ ያስገባል። ለዚሁ ልኬት ግብዓትነት ከሚውሉት መመዘኛዎች መካከል የውስጥና የውጭ ግጭቶች፣ አንድ ሀገር ከጎሬበቶቹ ጋር ያለው የግንኙነት ሁኔታ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የሽብር ተጋላጭነት፣ የወንጀል መስፋፋት እንዲሁም በእያንዳንድ አንድ መቶ ሺ ሰው በአንድ ሀገር ውስጥ ያለውን የእስረኛ ብዛትንም በመውሰድ ደረጃውን ለማውጣት በልኬትነት ይጠቀማል። ከዚህም በተጨማሪ ከአጠቃላይ ብሄራዊው ምርት አንፃር ለሚሊተሪው ዘርፍ የሚወጣውንም የገንዘብ መጠን ታሳቢ ያደርጋል። እነዚህንና ሌሎች ተጨማሪ ግብዓቶችን በማካተት ነው መረጃዎቹ ተተንትነው ደረጃ ወደ ማውጣቱ ስራ የሚካሄደው።
የየሀገራቱ ደረጃ ወጥቶ በድርጅቱ ድረገፅ እንዲሁም በዘ ኢኮኖሚስት መፅሄት ለህትመት የሚበቃ ሲሆን የዘንድሮውም ሪፖርት የ162 ሀገራትን መረጃ በመውሰድ ሰፊ ትንታኔ ከሰጠ በኋላ ኢትዮጵያ በ139ኛ ደረጃ አስቀምጧል። ተቋሙ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምም ሆነ ጦርነት የሌለበት ሁኔታ በመግለፅም በይደር የተቀመጠ ጉዳይ መሆኑንም አመልክቷል። ኢትዮጵያ ከፀጥታ ጋር በተያያዘም ከፍተኛ ገንዘብ የምታወጣ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አመልክቷል። በዚህ የሀገራት የሰላም ደረጃ አይስላንድ የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ በዓለም እጅግ ሰላም የሰፈነባት ሀገር ተብላለች። ዴንማርክ ሁለተኛ ስትሆን ኦስትሪያ የሶስተኝነትን ደረጃን ይዛለች።
ከ162ቱ ሀገራት 162ኛን ደረጃ በመያዝ በደረጃው ግርጌ ላይ የተቀመጠችው ሶርያ ናት። አፍጋስታን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኢራቅ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎም በደረጃው የመጨረሻ ግርጌ ላይ የተቀመጡ ሀገራት ናቸው። ግብፅ 148ኛ ደረጃን ይዛለች።
ዓለም አቀፍ የሀገራት የሠላም ስኬት ደረጃ (Global peace Index) በኢንስቲትዩት ፎር ኢኮኖሚክስ ኤንድ ፒስ ተቋም በየዓመቱ ይፋ የሚሆን ሲሆን መረጃውን በማሰባሰቡ በኩል በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሰፊ ትብብርና ተሳትፎን ያደርጋሉ። ከዓለም አቀፍ ተቋማቱ መካከል የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት አካላትም ይገኙበታል። እንደ ኮፊ አናን እና ሊቀጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱን የመሳሰሉና በተለያዩ ጊዜያት ሀገራትን ከመሩ በኋላ የስልጣን ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ መሪዎችም የሙያ አስተዋፅዖችን የሚያበረክቱበት ተቋም ነው። ተቋሙ የሀገራትን የሠላም ደረጃ የሚያወጣው 22 መስፈርቶችን አስቀምጦ በዚያ ልኬት መሰረት ነው።
ምንጭ – ሰንደቅ ጋዜጣ (በአዲስ አበባ የሚታተም)

የመጨረሻዉ መጀመሪያ

በቅርቡ በተከታታይ አገር ቤት ዉስጥ ቅርጽና ይዘት እየያዙ የምናያቸዉና ማንም አሌ የማይላቸዉ ግዙፍ እዉነታዎች ሁሉም በአንድነት የሚጠቁሙት አይቀሬዉ የወያኔ መጨረሻ መጀመሩን ነዉ። ከዚህ ቀደም በግልጽ እንዳየነዉ ወያኔ አንድ ቦታ ሲሸነፍ ሌላ ቦታ እያሸነፈ በጉልበትም በተንኮልም የፖለቲካ የበላይነቱን እንደያዘ ከሃያ ሁለት አመት በላይ ቆይቷል። ወያኔ ለአመታት ህዝብን ያታለለባቸዉ የዉሸት ክምሮችና ህዝባዊዉን ትግል ወደ ኋላ ለመጎተት የተጠቀመባቸዉ ስልቶች ዛሬ ሁሉም ሙጥጥ ብለዉ አልቀዉበት ዬኔ ነዉ ብሎ በሚመካበት ትግራይ ዉስጥ ጭምር መግቢያና መዉጪያዉ የጠፋዉ የተከበበ አዉሬ መስሏል። በያዝነዉ የ2006 ዓም ሁለተኛዉ አጋማሽ ወያኔ ጨካኙን የአግአዚ ኃይል እዚህም እዚያም አሰማርቶ ከሚቆጣጠራቸዉ ጥቂት አደባባዮች ዉጭ እንደቀድሞዉ በግልጽ ወጥቶ ወያኔን የሚያሞግስ ወይም የወያኔን የሌለ ገድል የሚናገር ሰዉ የለም። በሌላ በኩል ደግሞ በተለያዩ የትግል ስልቶች ወያኔን የሚታገሉ ኃይሎች አገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ ኃይላቸዉና ቁርጠኝነታቸዉ እየጨመረ መጥቶ ወያኔ ያንን የተለመደ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃዉን እዲወስድና የራሱን የመጨረሻ እሱ እራሱ ሳይወድ በግዱ እንዲያፋጥነዉ እያደረጉት ነዉ።
የአገራችንን አንድነት ሊያላሉና ኢትዮጵያ የሚለዉን ታሪካዊ ስም ከታሪክ ዉጭ ማድረግ ከሚችሉ አደገኛ የወያኔ ባህሪዮች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ዘረኝነቱና ለአገር አንድነትና ዳር ድንበር መከበር ያለዉ የግድየለሽነት ባህሪይ ነዉ። ዛሬ ወያኔ በአራቱም ማዕዘን በየቀኑ አየጨመረና እያየለ የሚሄደዉን የህዝብ ቁጣ ለማብረድና አፋፍ ላይ ለደረሰዉ ስርዐቱ ተጨማሪ ግዜ ለመግዛት የሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ከዚሁ ከዘረኝነት ባህሪይዉ የሚመነጪ እርምጃዎች ናቸዉ። ወያኔ ዕድሜዉ ሊበረክት የሚችለዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ኃይሎች መግባባት ሲያቅታቸዉ መሆኑን ያዉቃል፤ ስለዚህም በተቻለዉ መጠን ኢትዮጵያዉያንን የሚለያዩና ግጭት ዉስጥ የሚከትቱ አጀንዳዎችን አየፈጠረ ይወረዉርልናል። ከእነዚህ አገር አጥፊ የወያኔ አጀንዳዎች ዉስጥ አንዱ ህዝብን በዘር ከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዲጋጭ ማድረግ ነዉ። ለምሳሌ በቅርቡ ደቡብ ኢትዮጵያ ዲላ ከተማ ዉስጥ በንግዱ ህብረተሰብ ላይ የነጋዴዎችን አቅምና ትርፍ ያላገናዘበ ግብር በመጫን በአንድ በኩል ነጋዴዎቹ በዞኑ አስተዳዳሪዎች ላይ እንዲነሱ በማድረግ በሌላ በኩል ደግሞ የዞኑ አስተዳዳሪዎች ነጋዴዎቹን የምትሰሙን ከሆነ ስሙን አለዚያ ክልሉን ለቅቃችሁ ሂዱ የሚል አስነዋሪና የዜግነት መብትን የሚጋፋ መልስ እንዲሰጡ በመገፋፋት በጌዲኦ ብሄረሰብና በዲላና አካባቢዉ በብዛት በንግድ ስራ ላይ በተሰማራዉ የጉራጌ ማህበረሰብ መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ ለማድረግ ሞክሯል። ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥም እንደዚሁ የጋምቤላ ህዝብ ከጋምቤላ ዉጭ ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡትን ኢትዮጵያዉያን ክልሉ የእናንተ አይደለምና ለቅቃችሁ ዉጡ ብሎ እንዲያሰገድድ በመገፋፋት በኢትዮጵያዉያን መካከል ቂምና ጥላቻ እንዲፈጠር አድርጓል። ባለፉት አምስት አመታት ወያኔ ጋምቤላ ዉስጥ ገበሬዉን እያፈናቀለ መሬቱን ለዉጭና ለአገር ዉስጥ በተለይ ለትግራይ ባለኃብቶች በርካሽ ዋጋ ማስረከቡ የሚታወስ ነዉ። ይህ ባዕዳንን ጋምቤላ ላይ እያሰፈረ ኑና እረሱ እያለ የሚለምን ነዉረኛ አገዛዝ ነዉ ዛሬ ኢትዮጵያዉያንን ከጋምቤላ ዉጡ እያለ የሚያሰገድደዉ።
ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ደቡብ ኢትዮጵያ ዉስጥ ምን ያክል እንደተጠላ ለማወቅ ባለፈዉ ቅዳሜ መድረክ አዋሳ ዉስጥ የጠራዉን የተቃዉሞ ሰልፍ መመልከቱ ይበቃል። የአዋሳና የአካባቢዉ ህዝብ በዚህ መድረክ በጠራዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ የተገኘዉ ፌዴራል ፖሊስ፤ የክልሉ ፖሊስና የአገዛዙ ካድሬዎች በእያንዳንዱ ሰላማዊ ሰልፍኛ ላይ ያወርዱት የነበረዉን ዛቻ፤ ማስፌራሪያና ና የስድብ ናዳ ከምንም በለመቁጠር ነዉ። በዕለቱ የአካባቢዉን ሰላምና የሰልፈኛዉን ደህንነት አስጠብቃለሁ ብሎ በአዋሳ አደባባዮች ላይ የተሰማራዉ የወያኔ የፖሊስ ኃይል በህግ የተሰጠዉን ኃላፉነት ትቶ ፀረ ህዝብና ፀረ አገር እርምጃዎች ሲወስድ ታይቷል።
ወያኔ ብሶቱን አይቼ 17 ዐመት ታገልኩልት የሚለዉና ዛሬም እወክለዋለሁ ብሎ የሚነግረን ክልል ቢኖር የትግራይ ክልል ነዉ። ዛሬ ትግራይ ዉስጥም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሞቱት ለዚህ አይደለም ብለዉ ብረት አንስተዉ ወያኔን አምርረዉ የሚታገሉ የትግራይ ወጣቶች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነዉ። አስራ ሰባት አመት ሙሉ በወያኔ የማይጨበጥ ተስፋ ተታልሎ በከንቱ ህይወቱን የገበረዉ የትግራይ ወጣት ዛሬ እዉነቱ ገብቶት ወያኔን በትግራይ ህዝብ ስም መነገድህን አቁም እያለዉ ነዉ። በቅርቡ በመቀሌና በአካባቢዋ የታየዉ ከፍተኛ ፀረ ወያኔ እንቅስቃሴ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ወያኔ ለዚህ የሸተተ ስርአቱ ዕድሜ ለመግዛት ቢፍጨረጨርም “ከወደቁ በኋላ መራገጥ ለመላላጥ” ካልሆነ በቀር ካሁን በኋላ ወያኔዎች በስልጣን ላይ መቆየት ቀርቶ የዘረፉትን ኃብት የሚያሸሹበት ግዜም ልንሰጣቸዉ አይገባም።
የወያኔ ጠመንጃና የሚቆጣጠራቸዉ የአፈና ተቋሞች አላናግር ወይም አላስተነፍስ እያሉት እንደ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር ስለተገደደ ነዉ እንጂ አመጸኞቹ የወያኔ መሪዎች ለተቀረዉ የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ታገልንለት ብለዉ በስሙ ለሚነግዱት የትግራይ ህዝብ በፍጹም የማይበጁ ፀረ አገር ኃይሎች መሆናቸዉን የትግራይ ህዝብ ካወቀ ቆይቷል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የትግራይ ህዝብም በቃ በስሜም አትነግዱ ወንድሞቼንና እህቶቼንም አትበድሉ ብሎ ደጋግሞ እየነገራቸዉ ነዉ። ዛሬ ብዙ የትግራይ ወጣቶች እዚያ የዛሬ ሰላሳና ሰላሳ አምስት አመት አባቶቻቸዉ የታገሉበት ጫካ ዉስጥ ገብተዉ እነሱም በተራቸዉ የዛሬዉን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ በጠመንጃ ጭምር በመፋለም ላይ ይገኛሉ። ወያኔ የመጨረሻ መደበቂያዬ ይሆነኛል ብሎ ይተማመንበት የነበረዉ የትግራይ ክልል ዛሬ ግልጽ በሆነ መልኩ የወያኔን መጨረሻ ለማየት የሚቸኩሉ ጀግኖች ክልል እየሆነ ነዉ።
የትግራይ ጫካዎችን ጨምሮ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች “ጨርቅ” ብለዉ ያንኳሰሱትን የኢትዮጵያ ባንዲራ በክብር አንግበዉ ከቋጥኝ ቋጥኝ የሚዘልሉት የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አርበኞች ወገንን የሚያኮሩ ዘረኞቹን የወያኔ መሪዎች ደግሞ ምነዉ ባልጀመርነዉ የሚያሰኙ የአገርና የወገን አለኝታ ሆነዋል። ዛሬ ወያኔ የትግራይን ምድር የእግር መረማመጃ እስኪጠፋ ድረስ በወታደርና በታንክ ያጠረዉ ይህንኑ በትግራይ ወጣቶች የተገነባ ህዝባዊ የነጻነት ኃይል ስለፈራ ነዉ። አምባገነኖቸ በደም የሚቀባበሉት የተፈጥሮ ባህሪያቸዉ ሆኖ ነዉ እንጂ የታንክና የወታደር ጋጋታ ህዝባዊ ኃይልን የሚያቆም ቢሆን ኖሮ እነሱ ዛሬ ሚኒልክ ቤ/መንግስት ዉስጥ ገብተዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ሊረግጡ ቀርቶ ከተፈጠሩበት ደደቢት በረሃ ስንዝር ሳይራመዱ የእሳት እራት ሆነዉ ይቀሩ ነበር። ወያኔ ዛሬ በምድርና በአየር የታጠቀዉ መሰሪያና ሰራዊት ደርግ ከታጠቀዉ መሳሪያና ከነበረዉ ወታደራዊ ብቃት ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፤ ሆኖም ለነጻነቱ ቆርጦ የቆመን ህዝብ የሚገታ ምንም አይነት ምድራዊ ኃይል ሰለሌለ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ድጋፍ አግኝቶ ደርግን መደምሰስ ችሏል። የዛሬዉ አምባገነን ወያኔም ዕድል ከደርግ የተለየ አይደለም። ወያኔ ያሰኘዉን ያክል ቢታጠቅ፤ ያሻዉን ያክል የድንበር አካባቢዎችን በታንክና በወታደር ብዛት ቢያጥር . . . . ደፋርና ጭስ መዉጪያ አያጣምና የወያኔ መሸነፍና መደምሰስ ጉዳይ ቀን እስኪያልፍ ያለፋል ካልሆነ በቀር ያለቀለት ጉዳይ ነዉ።
ደርግ ስልጣን በያዘባቸዉ የመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት ዉስጥ ወታደራዊ አገዛዝ አንቀበልም ብለዉ ደርግን መግቢያና መዉጪያ ካሳጡት የህብረተሰብ ክፍሎች ዉስጥ ትልቁን ሚና የተጫዉተዉ ወጣቱ ትዉልድ ነበር። ይህ ወጣት ትዉልድ በኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ ትግል ዉስጥ ምን ግዜም ቢሆን ትዝታዉ የማይደበዝዝ አኩሪ የመስዋዕትነት ትግል ያካሄደና ያለምንም ፍርሃት ዉድ ህይወቱን ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነጻነት መከበር አሳልፎ የሰጠ ጀግና ትዉልድ ነዉ። ዛሬም አዲስ አበባ፤ አዋሳ፤ ባህርዳር፤ ጅማ፤ አምቦ ጊምቢና በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተማዎች የሚኖረዉ ወጣት እኔም አገሬም አብረን ከምንጠፋ እኔ ሞቼ አገሬን አኖራለሁ በሚል ኢትዮጵያዊ እልህ ተነሳስቶ የወያኔን የመጨረሻ እያፋጠነ ነዉ። የወያኔን እገድልሃለሁና አጅ እቆርጣለሁ የሚል ዛቻ ከመጤፍ ሳይቆጥሩ በብዕራቸዉ ህዝብን እያስተማሩ ቃሊቲ ከገቡት ጀግኖች ጀምሮ ከተማ ዉስጥ ከወያኔ ጋር መኖር በቃኝ ብለዉ ጠመንጃቸዉን ተሸክመዉ ጫካ እስከገቡት ቆራጥ አርበኞች ድረስ ኢትዮጵያ ዳግም ትንሳኤዋን ለማብሰር የተዘጋጁ እልፍ አዕላፋት ጀግኖች አሏት።
በገጠሪቱ ኢትዮጵያም መሬቱን ተቀምቶ የተሰደደዉ ወጣት ልክ እንደ ከተማዉ ወጣት በወያኔ ላይ አምርሮ ዱር ቤቴ ብሎ ጫካ ከገባ ቆይቷል። አባቶቹና አያቶቹ ያቆዩለትን መሬት በወያኔ የተቀማዉ የጋምቤላ ገበሬ መሬቴን አለዚያም ህይወቴን ብሎ ወያኔን ማንቀጥቀጥ ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። የሰሊጥ ማዕከል የሆነዉን ለምለም መሬቱን በወያኔ የተቀማዉና ዛሬም የአባቶቹን አጽም የተሸከመዉን መሬት ለባዕዳን ለመስጠት የሚዶለትበት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በወያኔ ላይ ጥርስ ከመንከስ አልፎ ቃታ መሳብ ጀምሯል። እነዚህ ከትግራይ እስከ ጋምቤላ ከጋምቤላ እስከ ጎንደር በአራቱም ማዕዘናት የሚታዩ ህዝባዊ አመጾች የሚያሳዩን አንድ ትልቅ ነገር አለ፤እሱም ወያኔ በህዝብ የተጠላ ብቻ ሳይሆን ህዝብ አንቅሮ የተፋዉ ከቆሻሻም ቆሻሻ መሆኑን ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘረኝነት በጉልህ ከሚታይባቸዉና በዘረኝነት ፖሊሲ ላይ ተመስርተዉ ከተዋቀሩ አገራዊ ተቋሞች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ የመከላከያ ተቋም ነዉ። የኢዮጵያ መከላከያ ተቋም በተለይ ዋናዉን የዉግያና አገርን የመከላከል ስራ የሚሰራዉ የሰራዊቱ ክፍል የተሰባሰበዉ ከመላዉ የአገሪቱ ክፍሎች ቢሆንም ይህ ተቋም ሁለት ፀረ ኢትዮጵያ የሆኑና ሆን ተብለዉ የጎደሉ ጉድለቶች አሉበት።አንደኛዉ ጉድለት ሠራዊቱን በተለያየ ደረጃ ከሚመሩና ከሚያዝዙ ወታደራዊ መኮንኖች ዉስጥ ከ95% በላይ የአንድ ዘር ተወላጆች መሆናቸዉ ሲሆን ሁለተኛዉ ትልቅ ጉድለት ደግሞ በኢትዮጵያ ሠራዊት ዉስጥ አግአዚ የሚባል የአዉሬዎች ክምችት የሚገኝበት አንድ ቋንቋ ብቻ የሚናገሩና ከአንድ ክልል የመጡ ተዋጊዎች ያሉበት ሠራዊት መኖሩ ነዉ። የአገሬን አንድነትና ዳር ድንበር አስከብራለሁ ብሎ ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰበዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት በዘር ተከፋፍሎ የወያኔ መጠቀሚያ መሆን ሰልችቶታል።በተለይ ይህ ሰራዊት ብዛቱን በሚመጥን ቁጥር የመሪነትና የአዛዥነት ቦታ ስለማይሰጠዉ ሁል ግዜ በሚንቁትና በሚያንቋሽሹት የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች መመራት አንገሽግሾታል። ዛሬ በየበረሃዉ ለሚገኙት የነጻነት አርበኞች እባካችሁ እንገናኝና አገራችንን አንድ ላይ ሆነን ነጻ እናዉጣ የሚል የትግል ጥሪ በተደጋጋሚ የሚመጣዉ ከዚሁ በዘረኝነት አለንጋ ከሚገረፈዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ነዉ። ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ በተለይ ባለፉትሦስት አመታት በኢትዮጵያ ሠራዊት ዉስጥ ትልቁ የመወያያ አርዕስት አንዴት አድርገን የነጻነት እበኞችን እንቀላቀል የሚለዉ ጥያቄ ነዉ። በሠራዊቱ ዉስጥ ሆኖ በዚህ አርዕስት ላይ የማይወያይ የሰራዊቱ አባል ቢኖር እንደ ዘይትና ዉኃ ቅልቅል በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ ባዕድ አካል ሆኖ የሚታየዉ አዉሬዉ የአግአዚ ሠራዊት ብቻ ነዉ። አግአዚ ደግሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት ሳይሆን በኢትዮጵያ ሰራዊት ዉስጥ እንደ እንክርዳድ የበቀለ ፍጹም ባዕድና ጨካኝ የሆነ የወያኔ መገልገያ ነዉ።
ከዚህ በላይ ለመጥቀስ እንደሞከርነዉ ወጣቱ፤ ገበሬዉ፤ ነጋዴዉ፤ ከተሜዉና ወታደሩ ሁሉም ወያኔን የሚቃወም ብቻ ሳይሆን ወያኔንና ዘረኛ ስርዐቱን ለመደምሰስ የተዘጋጁ `ኃይሎች ናቸዉ። ባለፈዉ ግንቦት ወር ወያኔ ዘረኝነትንና ሙሰኝነትን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተከለበትን ሃያ ሦስተኛ አመት ሲያከብር የኢትዮጵያ ህዝብ የተዋርድንበትን ቀን አናከብርም ብሎ ወያኔ የራሱን በዐል ብቻዉን አክብሮ ዉሏል። ከዚህ በተጨማሪ እጅግ በጣም ብዙ ኢትዮጵያዉያን ይህንን የባርነት ቀን እንደገና ሲከበር ማየት አንደማይፈልጉ በይፋ ተናግረዋል። በእርግጥም ካሁን በኋላ ወያኔ ግንቦት ሃያን ብቻዉንም ቢሆን እንዲያከብር መፍቀድ የለብንም። ደግሞም ወደድንም ጠላን ወይም አወቅን አላወቅን ወያኔ ግንቦት ሃያን የሚያከብረዉ ብቻ ሳይሆን እንዳሰኘዉ ረግጦ የሚገዛን እኛ አሜን ብለን ስለፈቀድንለት ብቻ ነዉ። ህዝብ በአንድ ድምጽ አልገዛም ብሎ አለመገዛቱን የሚያሳይ እርምጃ መዉሰድ ቢጀምር አይደለም በዐል ማክበር ወያኔዎች ሰኞ ያደሩበት ሚኒልክ ቤ/መንግስት ዉስጥ ማክሰኞ ማምሸትም አይችሉም ነበር።
መሬት አልባዉ የኢትዮጵያ ገበሬ ወያኔ እስካለ ድረስ ልጆቼን ብሎ ስለወደፊቱ ማሰብ ቀርቶ የዕለት ጉርሱን የማግኘት ዋስትናም የለዉም። ነጋዴዉም እንደዚሁ ነዉ። ለወያኔ ሙሰኞች ካላጎበደደና ግማሽ ትርፉን ለእነሱ ካልገበረ ነግዶ መኖር ቀርቶ በልቶ ማደር የማይችልበት ግዜ እየመጣ ነዉ። ከተሜዉ ኢትዮጵያዊስ ቢሆን እስከመቼ ነዉ ሰላማዊ ልጆቹ ከጉያዉ እየተጎተቱ ሽብርተኞች ተብለዉ ዕድሜ ልክ ተፈርዶባቸዉ ቃሊቲ ሲገቡ የሚመለከተዉ? እስከመቼ ነዉ ዬት ገቡ ተብለዉ አድራሻቸዉ የጠፋ ልጆቹ መንገድና ህንጻ ሲሰራ የጅምላ መቃብራቸዉ በግሬደር እየተቆፈረ ሲወጣ የሚመለከተዉ? ከኢትዮጵያ ህዝብ አብራክ የወጡት የመከላከያና ፖሊስ ሠራዊት አባላት እስከመቼ ነዉ እነሱ እራሳቸዉ በወያኔ ዘረኝነት እየተለበለቡ ለወያኔ ዕድሜ መራዘም ሲሉ ወንድሞቻቸዉንናነ እህቶቻቸዉን የሚገርፉትና የሚያዋርዱት?
ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ገዳማትን የእርሻ ቦታ አድርጓቸዋል፤ የእምነት ተቋሞችን የክፋቱ መሠረት አድርጓቸዋል፡ ምሁራንን ደግሞ አገራቸዉን ጥለዉ እንዲሰደዱ አድርጓል። ባጠቃላይ ወያኔ ያልበደለዉ፤ ያላሳቀቀዉ ወይም ተስፋዉን ያላጨለመበት የህብረተስብ ክፍል የለም። የገበሬዉ፤ የከተሜዉ፤ የነጋዴዉ፤ የወታደሩ ፤ የወጣቱና የምሁሩ ጠላት ወያኔ መሆኑን ካወቅን ዉለን አድረናል፤ ታዲያ ለምንድነዉ ይህንን የጋራ ጠላት በገራ የማናስወግደዉ? ከዛሬ በኋላ ወያኔ ስልጣን እንደያዘ በሚቆይባት በእያንዳንዷ ቀን የእኛ ስቃይና መከራ መብዛቱ ብቻ ሳይሆን ጥፋቱም የኛ መሆኑን አጥብቀን ልንረዳ ይገባል። ወያኔ እንደሆነ ቀንበር ለመሸከም የተመቻቸ ትከሻ ካገኘ ምን ግዜም ቢሆን ከመግዛት፤ ከማሰርና ከመግደል ወደ ኋላ አይልም። አልገዛም፤ አልታሰርም ወይም አትገድሉኝም ብሎ በወያኔ ላይ መነሳት የዚህ ትዉልድ ኢትዮጵያዉያን ሀላፊነት ነዉ፤ ይህ ሀላፊነት ደግም በህብረት ቆመን ለአንድ አላማ በአንድነት ከታገልን በቀላሉ ልንወጣዉ የምንችለዉ ሀላፊነት ነዉ። ሰለዚህ የዛሬም ጥሪ እንደትናንቱ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወያኔን ለማስወገድ ሀላፊነቱን ይወጣ የሚል ነዉ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

tirsdag 24. juni 2014

ሰበር ዜና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ አንዲት ኢትየጵያዊት በጁዳ ቆንስል ግቢ ታንቃ ተገኘች

unnamed (1)በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ግዜያዊ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ እንዲት ኢትዮጵያዊት ታንቃ መገኘቷ የአካቢውን ማህበረሰብ ደረት ሲያስደቃ መዋሉን ቦታው ላይ የነበሩ የአይን እማኞች አረጋግጠዋል። ዛሬ በኢትዮጵያ ሰአት አቋ ጣጠር ከቀኑ 10 ሰአት ቆንስላው ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ታንቃ የተገኘቸው ወጣት በ 20 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ መሆኗን የሚናገሩ እማኞች በኮንተራት ለስራ መጥታ ከአሰሪዎቾ ባለመስማቷ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ግዜያዊ መጠለያ ኮንቴነር ውስጥ ለረዥም ወራት ስትሰቃይ የኖረች ሳትሆን እንደማትቀር ይናገራሉ ; ፡ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ዛሬ ከቀኑ 10 አካባቢ እዚህ ቆንስላ ግቢ ውስጥ የታነቀቸውን ወጣት በአይናቸው ለማየት እድል ያገኙ እማኞች ወጣቷ እራሷን አንቃ ለመግደል ስትወራጭ አንገቷ ውስጥ የገባው ገመድ መስል ነገር ጉሮሮዋን ቆርጧ ወዲያው ሳይገድላት እንዳልቀረ ይገልጻሉ።

ይህ ዜና እስከ ተጠናከረበት ግዜ ድረስ የወጣቷ ሬሳ አለመንሳቱን የሚናገሩ ምንጮች በአካባቢው የፓስፖርተ እድሳት እና መስል ተዘማጅ ጉዳዩቹን ለማስፈጸም የቆንስላ ግቢውን አጨናነቀው እምባ ሲራጭ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ከቆንስላው ጽ/ቤት እንዲወጡ መደረጋቸውን የአይን እማኞቹ አክለው ገልጸዋል ። ይህ በዚህ እንዳለ የሬሳ ጉዳይ የሚከታተለው እና የቀድሞ የኮሚኒቲ አመራር አቶ መሃመድ ሸህ ተፈቅዶለት ወደ ግቢው ሲገባ ያዩ ምንጮች ቦታው ላይ የሳውዲ ፖሊሶች እና ዲፕሎማቶች መገኘታቸውን አረጋግጠዋል ። የጅዳ ቆንስ ጽ/ቤት የእህቶቻችንን አስከሬን ሲያስተናገድ የመጀመሪያ ግዜው እንዳለሆነ የሚናገሩ ወገኖች በዲፕሎማቱ የአሰራር ድክመት በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ለሁለተኛ ግዜ ታንቃ ህይወቷ ባለፈው ወጣት ተደናግጠው ሲጮጮሁ በነበሩ ኢትዮጵያውያን የቆንስላው ጽ/ቤት ድባብ ወደ መቃብር ስፍራ ነት ተለውጦ ማምሸቱን ይናገራሉ ።

በአሁኑ ግዜ በዚህ የቆንስላ ቅጥር ግቢውስጥ ከ 40 የሚበልጡ ተፈናቃይ የኮንተራት ሰራተኞች ከሰው እይታ ተገለው ይሚገኙ ሲሆን ባዶ ክፍሉ ውስጥ ያለምንም እርዳታ ሃገር ትገባላቹ በሚል ተስፋ መጋዘን ተቆልፎባቸው ለበለጠ ስቃይ እና መከራ እይተዳረጉ ከሚገኙ እህቶቻን መሃከል አብዛኛዎቹ የፈላ ውሃ በአሰሪዎቻቸው የተደፋባቸው የተድፈሩ እና ደሞዛቸው የተነጠቀ መሆኑ ይነገራል።፡፤ የወገኖቻችን ሞት ከሚፈበረከበት ሁለተኛው ማዕከል ጅዳ ከሆነው የ ቆንስላ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በአንድ ወቅት አንድ የውሃ ጉድ ጓድ ውስጥ ሬሳዎ በተገኘ ኢትዮጵያዊት ጉዳይ የህ.ወ.ህ.ቱ አባል አቶ ገሬ ለወራት ወህኒ ቢወርዱም የሞቾ ምስኪን ጉዳይ ተድበስብሷ ሲቀር አቶ ገሬ ከወራት እስራት በኋላ በወጭ ጉዳይ ግፊት መፈታታቸው በህዝብ ዘንድ ተቃውሞ ማስነሳቱ አይዘነጋም።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

በሀዋሳ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ዛሬም የረሀብ አድማ ላይ ናቸው!! በሀዋሳ ሰ.መ.ጉ እስረኞችን እንዳይጎበኝ ተከለከለ – የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)ባሳለፍነው ሳምንት ሰኔ 15 ቀን 2006ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ‹‹ፍትህን ተነፍገን ትግላችን አይቆምም ››በማለት ዛሬም ለ4ኛ ቀን በርሀብ አድማ ላይ ናቸው፡፡አባላቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ቅዳሜ እለት ጀምሮ በረሀብ አድማ ላይ ሲሆኑ በትላንትናው እለት ሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው በኢ/ፌ/ዲ/ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27(1-ሀ)32/1-ሀ/እና 257 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በሚል የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ዐ/ሕግ ክስ ተመስርቶባቸው የዋስትና መብታቸው ተነፍጎ በእስር እንዲቆዩና ዓቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለሰኔ 20 ቀን 2006 እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በማስተላለፉ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
በተያያዘም ዜና ሰ.መ.ጉ በሃዋሳ ከተማ በእስር ላይ የሚገኙትን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላትን ሁኔታ ለመመልከት ወደ ወደ ሃዋሳ እስር ቤቶች ያመሩት የሰብዓዊ መብት ጉባዔ ሀላፊዎች እስረኞቹን ለማግኘት እንደማይችሉና ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ትዕዛዝ በመተላለፉ ምክንያት ታሳሪዎቹን ማግኘት እንዳልተቻለና የጣቢያ ሀላፊዎቹን ለማናገር የተደረገውም ጥረት እንዳልተሳካ አስረድተዋል፡፡10448208_657204214364516_9050720156707149922_n
10450753_657204294364508_6267425299544943631_n

søndag 22. juni 2014

የ2007 የመንግሰት በጀት ሚስጥር

ግርማ ሰይፉ ማርይ
(የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል)

የኢትዮጵያ በጀት በደንብ አድርጎ ለመረመረው ሀገሪቱ ያለችበትን ፖለቲካ ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም ማለት በበጀቱ ውስጥ የቻይና፣ ምዕራባዊያን ሀገሮች እንዲሁም የምዕራብ ሀገሮች ይዞታ የሚባሉት አለም አቀፍ ባንኮች እጅ በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ እንደምታውቁት መንግሰት ለ2007 ዓመተ ምህረት ያቀረበው በጀት ብር 178.6 ቢሊዮን ነው፡፡ ዘጠኝ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ማለት ነው፡፡ መደበኛው ወጪ እና የክልሎች ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የሚሸፈን ሲሆን ዋና ዋና የካፒታል በጀት ደግሞ ከመደበኛ ወጪ እና ክልሎች ድጋፍ ከሚተርፈው አነሰተኛ የሀገር ውስጥ ገቢ እና ለበጀት ጉድለት ለመሸፈን ከታሰበው ከሀገር ውስጥ ባንኮች ብድር ይሸፈናል ተብሎ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከአጠቃላይ በጀቱ 19.2 በመቶ ከእርዳታና ብድር ይሸፈናል በዝርዝር ሲታይ ግን የመደበኛ በጀቱ 21.8 ከመቶ፣ የካፒታል በጀቱ ደግሞ 36.5 ከመቶ የሚሸፈነው ከብድርና እርዳታ ነው፡፡
ስንት ሰው እንደሚያስታውስ ባላውቅም የቀድሞ አዲስ ጉዳይ ጋዜጣ (ሁሌም ጋዜጣ ሳስብ የሚናፍቀኝ) በአንድ ወቅት የቀረበን በጀት ይህ በጀት ኢትዮጵያዊ በጀት ነው ወይ? የሚል ጥያቄ አንሰቶ ነበር፡፡ የበጀትን ዜግነት የጠየቀበት ገፊ ምክንያት በዚያን ሰሞን መወያያ፤ በአሁኑ ጊዜ ጠርናፊ ህግ የሆነውን የሲቪል ማህበራት ህግ ነበር፡፡ ይህ አፋኝ ህግ ማነኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሰቪል ማህበር በጀቱ ከአስር በመቶ በላይ ከውጭ ከሆነ ኢትዮጵያዊ አይደለም ነው የሚለው፡፡ አሁን በሀገራችን የሚንቀሳቀሱት ብዙዎች መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተመዘገቡት በኢትዮጵያዊነት ሳይሆን “ረዚደንት” በሚል ቅፅል ነው፡፡ አዲስ ጉዳይ ጋዜጣ ይህን በጠየቀበት ወቅት የሀገሪቱ በጀት ከ40 በመቶ በላይ ከውጭ እርዳታ ሰለነበር ይህ መንግሰት ይህን ያህል ከውጭ የሚያገኝ ከሆነ ኢትዮጵያዊ አይደለም የሚል መከራከሪያ ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡ ይህን ሰፋ አድርገው በመተርጎም አንድ አንድ ሰዎች የገቢ ምንጭ ዜግነት የሚወስን ከሆነ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ከውጭ ከሚኖሩ ዘመዶቻቸው በሚላክላቸው ገንዘብ የሚተዳደሩ ስለሆነ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ መሆን የለበትም ብለው ነበር፡፡ ስላቅ መሆኑ ነው፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ የሚልኩላቸው ዘመዶቻቸው ዜግነት ያልቀየሩ በመኖሪያ ፍቃድ (ረዚደንት) የሚኖሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ethiopia-parliament
የሰዎችን ወይም የድርጅቶችን ዜግነት ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ ለማድረግ የገቢ ምንጭ መስፈርት መሆን የለበትም የሚለውን መከራከሪያ መንግሰት በዋዛ ያለፈው እንዳይመስላችሁ፡፡ መፍትሔ ብሎ የያዘው በተቻለ መጠን መንግሰት በጀቱን በመከፋፈል እና የተወሰኑት ወደ ጎን በማድረግ የብድርና የእርዳታ ገንዘቡ እንዳይታይ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም ነው መንግሰት ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ከሚፈስባቸው የመሰረተ ልማቶች ውስጥ ዋና ዋና የሆኑትን ለምሳሌ እነ ቴሌ፣ መብራት ሀይል፣ ባቡር፣ የመሳሰሉት በሪፖርት ውሰጥ በስፋት እንደሰኬት ተካተው በበጀት ውስጥ ግን አይታዩም፡፡ ሉሎች ፋብሪካዎች ለምሳሌ ስኳር ፋብሪካ፣ ማዳበሪያ ፋብሪካ የመሳሰሉት ትልልቅ የመንግሰት ፕሮጀክቶቸ በበጀት ውስጥ የሉም፡፡ እነዚህ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ የፈሰሰላቸው የመንግሰት ኢንቨስትመንቶች ከበጀት ውሰጥ እንዲወጡ የተደረጉት ደግሞ ብዙዎች በብድር የሚሰሩ ናቸው፡፡ የእነዚህ ፕሮጀክቶች የብድር ሂሣብ በበጀት ውስጥ ቢደመር የመንግሰትን በጀት ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ላይሆን ነው ማለት ነው፡፡ ለነገሩ በሲቪል ማህበራት ትርጉም እነዚህ ሁሉ ተቀንሰው አሁን የቀረበው የመነግሰት በጀት ኢትዮጵያዊ በሚያደርገው ደረጃ ላይ አይለም፡፡ ምክንያቱም ከአጠቃላይ በጀቱ 19.2 በመቶ ከውጭ ብድርና እርዳታ የሚገኝ ስለሆነ ማለት ነው፡፡
መንግስት በበጀት ውስጥ ያካተታቸው በእርዳታና ብድር የተገኙ አብዘኞቹ የካፒታል ወጪዎች ለኤኮኖሚ ሴክተር መንገድ፣ ግብርና እና ውሃ ሲሆን፤ እርዳታው ደግሞ ለጤናው ሴክተር የተመደበ ነው፡፡ የእነዚህ ገንዘቦች ዋናኛ ምንጮች ደግሞ የኒዎ ሊብራል አራማጆች የሚባሉት መንግሰታት እና የእነዚሁ መንግሰታት ይዞታ ናቸው የሚባሉት ባንኮች የሰጧቸው ብድሮች ናቸው፡፡ እነዚህ መንግሰታት እና በቁጥጥራቸው ስር ያሉት የፋይናንስ ተቋማት ኢትዮጵያዊያን ጤናቸው እንዲጠበቅ የተሻለ መንገድ እንዲኖረን፣ ምርታማ ግብርና እንዲሁም ንፁህ ውሃ እንዲኖረን ዕርዳታና ብድር እየሰጡን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ብጥብጥ እንዲነሳ የቀለም አብዮት ይደግፋሉ ብሎ ስጋት ውስጥ መውደቅ አይቃረንም ወይ? ይህ በእውነት የአብዮታዊ ዲሚክራሲ ወይም የልማታዊ መንግሰት ቅዠት ይመስለኛል፡፡
በጣም የሚያስገርመው ደግሞ በዋነኝነት ከፍተኛ እርዳታ የሚሰጡን መንግሰታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በኩል አድርገው በቀለም አብዮት ሊያጠፉን ነው የሚባሉት የኒዎ ሊብራል አራማጅ ተብለው የተፈረጁት ሀገሮች መንግሰታት ናቸው፡፡ ከነዚህ ውሰጥ ቻይና እንደ መንግስት የምትሰጠን እርዳታ በሀገር ውስጥ ከውጭ ሀገር ዜጎች ምዝገባና የስራ ፈቃደ ከምናገኛው ያንሳል፡፡ ከሌሎቹ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ከአንድ መቶኛ ያነሰ ነው፡፡ ቻይና ሀገራችን በበጀት ውስጥ ከተካተተው ብድር ከ59 በመቶ በላይ ሰጥታናለች፡፡ ይህ ቻይና የሰጠችን ብድር ብዙ ስለሆነ ሳይሆን መንግሰታት ለኢትዮጵያ የሰጡት ብድር እጅግ ዝቅተኛ ከመሆኑ የመጣ ከፍተኛ የመቶኛ ድርሻ ነው፡፡ ቻይና በጀት ውስጥ ባልገባው ብድር ከፍተኛ አበዳሪያችን ነች፡፡ የቻይና ብድር በዋነኝነት በበጀት ውስጥ ባለተካተቱት ከፍተኛ የመንግሰት የመሰረተ ልማቶች እና የኤኮኖሚ ሴክተሮች ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ ከበጀት እንዲወጣ የተደረገውን የቴሌን ማስፋፊያ ብቻ ብንወሰድ ወደ 32 ቢሊዮን ብር ወይም 1.6 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር በ2007 በጀት ተብሎ የተያዘውን 18 ከመቶ ይሆናል፡፡ ይህ ገንዘብ በጀት ውስጥ ቢታይ እና የመንግሰትን የዜግነት መስፈርት ብንጠቀም መንግሰት ኢትዮጵያዊ ነው ለማለት ይቻላል ወይ? በጀት የመንግሰትን አቅም የሚያሳይ መለኪያ ነው በሚለው ልማዳዊ መለኪያ ለመጠቀም ለሚፈልግ ለቀጣይ ዓመት የቀረበው በጀት ትክክለኛውን የመንግስት ጡንቻ የሚያሳይ ነው ብለን ለመውሰድ እንቸገራለን፡፡
የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒሰትሩ አቶ ሶፊያ አህመድ በዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ በግንባር ቀደምነት የሚያነሱት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዕዝ ኢኮኖሚ በሚባለው በደርግም ጊዜ ቢሆን ሪፖርቱን በይፋ ያቀርባል አቶ ሶፊያ ግን ይህን እንዲያደርግ ያለበትን ዓለማ አቀፋዊ ጫና የምንረዳ አይመስላቸውም፡፡ ያለበለዚያ ቦይንግ መግዣ ገንዘብ ሊገኝ እንደማይችል ግልፅ ነው፡፡ አሁን እኛ የግልፅነት ችግር አለባቸው እያልን ያለነው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪን የሚባለው አስማተኛ ድርጅት የሚሰራው ሰራ የሚያገኘው ገቢና ወጪው በግልፅ አይታወቅም ነው፡፡ እጅግ ብዙ ሀብት ፈሶበትም የሚያመጣው ትርፍ ተመጣጣኝ አይደለም እያልን ነው፡፡ በቅርቡ ከመንግሰት ድርጅቶች ይገዛው የነበረውን የወዳደቁ ብረቶች ግዢ እንዲያቆም መታዘዙ ይታወቃል፡፡ ለምን? የፀረ ሙስና እና ሰነምግባር ኮሚሸን እነዚህ ተቋማት ለምዝበራ የተጋለጡ እንደሆነ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ለነገሩ ይህ ድርጅት ተጠሪነቱም ለመንግሰት የልማት ድርጅት አይደለም፡፡ ሌሎቹም ኮርፖሬሽኖች ለምሳሌ የሰኳር ኮርፖሬሽን ስር ነው የሚባለው ተንዳሆ የሰኳር ፕሮጀክት ያለበትን ጉድ የማያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡
በጀት ውስጥ የገባውን የመከላከያ በጀት ስንመለከት ደግሞ በየሳምንቱ እሁድ በሚያቀርበው የቴሌቪዥን ፕሮግራ በነፃ ገበያ ሰርዓት እየተወዳደረ መነገዱን ቢነግረንም፡፡ በግልፅና በሰውር የሚሰራቸው የገቢ ማስገኛ ገንዘቦች እንዳሉት እየታወቀ ከውስጥ ገቢ የሚባል አንድም የገቢ ርዕስ በጀቱ ላይ አይታይም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ የመከላከያ በጀት ይህ ብቻ ነው ብሎ ለመውሰድ አይቻልም፡፡ የመንግሰት ጡንቻ በመከላከያ በኩል ከዚህ እንደሚበልጥ ለማወቅ ደግሞ ልዩ እውቀት አይጠይቅም፡፡ ለዚህ ነው የመንግሰትን ትክክለኛ ቁመና የሚያሳይ በጀት አይደለም የምንለው፡፡
እነዚህ እርዳታ እየሰጡን ብድር የማይሰጡን መንግሰታት ምክንያታቸው ምንድነው? ብሎ መጠየቅም ተገቢ ይመሰለኛል፡፡ በኒዮ ሊብራል አሰተሳሰብ ተፈርጀው ሀገራችን ላይ የቀለም አብዮት ሊያመጡ ያሴራሉ የሚባሉት ሀገራት በዋና ዋና የንግድ እና ኢንቨስትምነት ውስጥ እጃቸውን ለማስገባት ወደኋላ ያሉት ለምንድነው? በተቃራኒው ደግሞ ቻይና በእነዚህ ወሳኝ የኤኮኖሚና የንግድ ኢንቨስትመንት ውስጥ እጇን በሰፊው የምትዘረጋው ለምንድነው? ብሎ መጠየቅ እና መልስ መሻት ግድ ይላል፡፡
በእኔ እምነት የምዕራባዊያን መንግሰታት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የኢኮኖሚ መስኮች ውስጥ ለመሳተፍ ውሳኔ የሚሰጡት መንግሰታት ሳይሆኑ በየሀገሮቻቸው ያሉት የግል ባለሀብቶች ናቸው፡፡ የመንግሰታት ድርሻ ለባለሀብቶች ትክክለኛ መረጃ እንዲደርሳቸው ማድረግ እና ተገቢውን ከለላ መስጠት ነው፡፡ የግል ባለሀብቶች ደግሞ መረጃ የሚያገኙት ከኢቲቪ አይደለም፡፡ በተለያየ መልኩ በሀገራችን ያለውን ሁኔታ አብጠርጥረው ያውቁታል፡፡ እንደ ምሳሌ በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተው ዓይነት ብሔርን መሰረት ያደረገ ብጥብጥ ከፍተኛ ትርጉም አለው፡፡ አንድ አንዶች እንደሚያስቡት በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች የተቀናጀ ማሰትር ፕላን ዝግጅት ነው ብለው አይወስዱትም፡፡ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችና የሰጋት ደረጃ የሚተነትኑ ድርጅቶች የሚያወጧቸው ሪፖርቶች ትርጉማቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ በሀገሪቱ ውሰጥ ያለው የዲሞክራሲያዊ ሰርዓት በተለይም በየምርጫ ወቀት የሚፈጠሩ ሰጋቶች፤ መንግሰት የሚያወጣቸው አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ተገማችነት፤ በአጠቃላይ ለኢንቨስትመንት ያለው ምቹ ሁኔታ ወሳኝ ግብዓቶች ናቸው፡፡ ዝም ብሎ በኢቲቪ የሚለፈፍ የገፅታ ግንባታ ፕሮፓጋንዳ ተጠቅመው የኢንቨስትምነት ውሳኔ አይሰጡም፡፡
በተቃራኒው የቻይና መንግሰት በከፍተኛ ደረጃ አፍሪካን ለመቆጣጠር ባለው ፍላጎት መነሻ እንዲሁም ውሳኔ የሚሰጡት የግል ባለሀብቶች ሳይሆን የቻይና መንግሰት በመሆኑ ውሳኔዎች በአብዛኛው ኤኮኖሚያዊ አዋጭነት ብቻ ሳይሆኑ የፖለቲካ ጭምር ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቻይና በዓለም ላይ ከፍተኛ ብድር ሰጪ ሀገር ነች፡፡ ለአማሪካ ጭምር፡፡ በቻይና የግል ሴክተሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢንቨስት ለማድረግ ገና አልደረሱም፡፡ ቻይና እንደ ሀገር ያላትን ከፍተኛ ቁጠባ በዓለም ላይ ኢንቨስት ለማድረግ እየተጠቀመችበት ነው፡፡ ቻይና በሙሉ በሚባል ደረጃ የምትሰጠንን ብድር የሚጠቀሙበት የቻይና ኩባንያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ያለውን ስጋት በሚያካክስ ደረጃ ትርፋቸውን በአጭር ጊዜ ለማግኘት ይገባሉ በአሁኑ ሰዓት ቴሌን የወሰዱት ሁለት የቻይና የመንግስ ኩባንያዎች ናቸው፡፡ በተለያየ ስም የሚሰሩ፡፡ ቻይና የምታስገርመው እነዚህ የመንግሰት ኩባንያዎች ጉቦ የመሰጠት ጭምር አቅም አላቸው፡፡
እንደ ማጠቃለያ ለኢትዮጵያ የተበጀተው በጀት ብር 178.6 ቢሊዮን በጀት እንደ ሀገር ሲታይ አጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ ኢትዮጵያ 90 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት ከመሆኗ አንፃር እና በቅርቡ ደግሞ ዓመታዊ የነብስ ወከፍ ገቢያችን ብር 11 ሺ (550 የአሜሪካ ዶላር) ደርሶዋል ከተባልን ይህ በጀት ከእያንዳንዱ ሰው በወር የገቢውን 1.5 ከመቶ መዋጮ ሊሸፍነው የሚችለው ነው፡፡
ቸር ይግጠመን