tirsdag 8. oktober 2013

የምርትና የሕዝብ እድገት እሽቅድድም


መሬት የማነው? ክፍል ሁለት ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
farmer1
እአአ በ1798 (ከሁለት መቶ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት) መምሬ ቶማስ ሮበርት ማልቱስ የሚባል የ32 ዓመት የብሪታንያ ቄስ የዘመኑን የነገረ ንዋይ አስተሳሰብ የለወጠ አዲስ ሀሳብን የያዘ መጽሐፍ አሳተመ፤  ሀሳቡ በጣም ግልጽ ነበረ፤ የሰው ልጆች ቁጥር እድገት መጠኑ እያጠፈ የሚሄድ ነው፤  የሕዝብ ቁጥር 1፣ 2፣ 4፣ 8፣ 16፣ 32፣ 64፣ 128፣  እያለ የሚጨምር ነው፤ ከእርሻ የሚገኘው ምርት ደግሞ የእድገቱ መጠን አያጥፍም፤ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 8፣ 9፣ 10፣ እያለ የሚሄድ ነው፤  የመምሬ ማልቱስን ሀሳብ በሌላ መንገድ ካየነው የበላተኞች ቁጥር እያጠፈ ሲያድግ የምግቡ አቅርቦት የሚያድገው ግን በጣም በዝግተኛ ፍጥነት ነው፤ የሚል ነው፤  እንግዲህ የሕዝብ ቁጥርና የምርት አቅርቦት እኩል መጓዝ ሲገባቸው የሕዝቡ ቁጥር እየቀደመ ስለሚገኝ፣ መምሬ ማልቱስ የደረሰበት መደምደሚያ የሕዝቡን ቁጥር ለመቀነስ በሰው ልጆች መሀከል በሽታ፣ ችጋርና ጦርነት የማይቀሩ ይሆናሉ፤ ችጋር፣ ጦርነትና ሌሎችም አደጋዎች በሕዝቦች ላይ እየደረሱ የሕዝብ ቁጥርና የምርት እድገት በሚያደርጉት መሽቀዳደም መሀከል ሚዛንን ይጠብቃሉ።
መምሬ ማልቱስ በነበረበት ዘመን ላይ ሆኖ ከሃምሳና መቶ ዓመታት በኋላ እውቀትና (ሳይንስ) የእውቀት ጥበብ የሚያስከትሉትን መሠረታዊ የአስተሳሰብ፣ የአሠራርና የኑሮ ለውጥ ለመገንዘብ አልቻለም፤ እንዴት ብሎ? በመምሬ ማልቱስ ዘመን በአንድ ሄክታር መሬት ላይ የሚገኘው ምርት አምስት ኩንታል ብቻ ቢሆን በኋላ ግን በአንድ ሄክታር ላይ በእውቀትና በእውቀት ጥበብ ኃይል ምርቱን ከእጥፍም በላይ ማምረት የሚቻልበት ዘመን መጣ፤ ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የተለያዩ የእርሻ ዘዴዎች የእርሻውን ሥራ ቀልጣፋና ምርታማ አደረጉት፤ በዚህም ምክንያት የመምሬ ማልቱስን ሀሳብ ብዙ ሰዎች ይነቅፉት ጀመር፤ ሆኖም የመምሬ ማልቱስን ሀሳብ ዛሬም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ጊዜ አልሻረውም፡፡
ከመሠረት ለመጀመር — አንድ አገር መሬት አለው፤ ሕዝብ አለው፤ መሬትም ሆነ ሕዝብ በጥሬአቸው ከቆሙ የመምሬ ማልቱስ ትንተና መደምደሚያ መሬቱ ከሚችለው በላይ የሆነውን ሕዝብ ችጋር፣ በሽታና ጦርነት ያነሣዋል፤ መሬትና ሕዝብ ብቻ አገርን አያቆሙም፤ በሕዝብ መሀከል ያለውን ግንኙነት፣ እያንዳንዱ ሰው ከሌሎች ጋር ያለውን አብሮ የመኖር ትስስር ሕግና ሥርዓት እንዲኖረው ያስፈልጋል፤ የመሬትም ሀብት አጠቃቀም በእኩልነትና በፍትሐዊነት ዘዴ ለመደልደል ሕግና ሥርዓት ያስፈልጋል፤ እንግዲህ ሕዝቡ ኑሮውን በሕግና በሥርዓት ለመምራት አንድ መንግሥት የሚባል እንደእድር ያለ ድርጅትን ይፈጥራል፤ እያንዳንዱ ሰው በግሉ የኑሮ ጣጣ ተወጥሮ በሚራወጥበት ጊዜ መንግሥት የሚባለው ድርጅት ለጠቅላላው ማኅበረሰብ የሚበጀውን ይሠራል።
በእያንዳንዱ ሰው የኑሮ ግዴታ መሬቱ ያለማቋረጥ በጥቅም ላይ እየዋለ በግጦሽና በእርሻ፣ በሌሎችም ምክንያቶች እየተጎዳ ይሄዳል፤ በዚህም የተነሣ መሬቱ የሚሰጠው ጥቅም በያመቱ ይቀንሳል፤ የመሬቱ መደህየት ከሕዝብ መደህየት ቀድሞ ይመጣል ማለት ነው፤ እንግዲህ መንግሥቶች የሚቋቋሙት እንዲህ ያለ ሁኔታ እንዳይፈጠር፣ ከተፈጠረም ብዙ ጉዳት እንዳያደርስ አስፈላጊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ነው፤ በኢትዮጵያ ስለኢትዮጵያ የሚፈበረከው የአሐዝ መረጃ ወይም ስታቲስቲክስ አስተማማኝ ነው ባይባልም አማራጭ ባለመኖሩ ልንጠቀምበት እንገደዳለን፤ ለምሳሌ በ2004 ዓ.ም. የስታቲስቲክስ ጽ/ቤት ባወጣው መረጃ መሠረት የታረሰው መሬት 13 690 119 ሄክታር ነበር ይባላል፤ የስታቲስቲክስ መሥሪያ ቤት ገበሬዎች ሳይሆን ባለይዞታ የሚላቸው 14 747 439 ይሆናሉ፤ ይህንን ቁጥር በአምስት ስናባዛው (በአንድ የገጠር ቤተሰብ በአማካይ አባሎች) 73 737 195 ይሆናል፤ ይህንን ቁጥር ከ2007 የሕዝብ ቆጠራ ውጤት ጋር ማስተያየቱ ያስተምራል፤ ከዚያም በላይ አንዳንዶቹ ቁጥሮች በሌላ ቦታ አይደገሙም፤ ወይም መልካቸውን ለውጠው ይቀርባሉ።
ለጊዜው ግን ለያዝነው ርእስ የሚከተሉትን አሐዞች እንመልከት፤ በመጀመሪያው ሰንጠረጅ ባለይዞታ የተባሉት ገበሬዎችና የታረሰው መሬት (በሄክታር) በሦስት ዓመት ውስጥ ያሳዩትን ለውጥ ለማሳየት ይሞክራል፤ ሠንጠረጅ ሁለት ደግሞ የእርሻ ምርት (እህል፣ ጥራጥሬና የቅባት ዘር) ከገበሬው ቁጥር ጋር ለማነጻጸር ይሞክራል፤ ኢትዮጵያ የተአምር አገር መሆንዋን ተንተርሶ የስታቲስቲክስ ጽ/ቤት የእርሻ መሬቱንም በ2004 ዓ.ም. ትንሽ አሳድጎታል፤ አይቻልም ማለት አይደለም፤ በመስኖና በእርከን የእርሻውን መሬት መጨመር ይቻላል።
ሠንጠረጅ አንድ
የታረሰ መሬትና (በሄክታርየገበሬዎች ቁጥር 2002-2004 .
ዓ.ም.
ባለይዞታ
እድገት ከመቶ
መሬት (ሄክታር)
ካለፈው ዓመት እድገት ከመቶ
አማካይ ድርሻ
መሬት ለባለይዞታ(ሄክ)
2002
13439174
100.0
12953636
100.0
0.96
2003
14789071
110.0
13358883
103.13
0.90
2004
14747439
109.7
13690119
105.69
0.93
ምንጭ የስታቲስቲክስ ጽ/ቤት ድረ-ገጽ
ዋናው ነጥብ ግን የስታቲስቲክስ ጽ/ቤት የፈለገውን ያሀል ቢጠማዘዝም እውነቱን እምብዛም ሊለውጠው አልቻለም፤ የቁጥር ነገር ወዲያ ቢሉት አራት፣ ወዲህ ቢሉት አራት ሆነና በአማካይ የአንድ ገበሬ እርሻ አንድ ሄክታር እንደማይሞላ መሸሸግ አልተቻለም፤ በእርሻ መሬቱ ላይ ያለው ጭነት በጣም ከፍተኛ ነው፤ እውነተኛውን የሕዝብ ቁጥር ብናውቅ ደግሞ ጭነቱ ምን ያህል የበለጠ እንደሆነ እንረዳ ነበር፤ የዓለም ባንክና የአሜሪካው ዓለም-አቀፍ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) የኢትዮጵያን ሕዝብ ቀጥር በአሁኑ ጊዜ ከዘጠና ሚልዮን በላይ ያደርሱታል፤ በአገር ውስጥ የሚነገረው ቁጥር ግን በሰባና በሰማንያ መሀከል ነው፤ የዛሬ ሠላሳ አምስትና አርባ ዓመት ግድም በደቡብ (በተለይ በከምባታና ሀድያ፣ በወላይታና በሲዳሞ፣ በደራሳ) የሕዝብ ቁጥር የሚፈነዳ እንደሆነ ተናግሬ ነበር፤ በትግራይና በወሎም፣ በሰሜን ሸዋም በመሬቱ ላይ ያለው ጭነት ከባድ ነው።
ሠንጠረጅ ሁለት
የእርሻ ምርትና (አህል፣ጥራጥሬና የቅባት) የገበሬዎች ድርሻ
ዓ.ም.ምርት ኩንታል ካለፈው ዓመት እድገት ከመቶየባለይዞታ ቁጥርየባለይዞታ/የዓመት ድርሻ ኩንታልየአንድ ሰው የወር ድርሻ ኪሎ
2002
180758897
100.0
13439174
13.45
22.25
2003
203485288
112.57
14789071
13.76
22.92
2004
218569429
120.92
14747439
14.82
24.67
ባለይዞታ ምናልባት በአማካይ አምስት ሰዎችን ያካትታል፤ ነፍስወከፍ እያንዳንዱን ሰው ይመለከታል።
በእነዚህ ሁለት ሠንጠረጆች ላይ በግርድፍ (መረጃው ነው ግርድፍ!) የሚታየውን እውነት መሸሽግ አይቻልም፤ በወር 25 ኪሎ እህል ከችጋር  አለመውጣትን ያሳያል፤ መሬት ተትረፍርፎ ሠራተኛ ሕዝብ የጠፋበት አገር አንዳልሆነም ይታያል፤ ታዲያ ለህንድና ለቻይና፣ ለሌሎችም መሬት በችሮታም ሆነ በሽያጭ የምንሸጥበት ምክንያት ዕብሪት ከወለደው እብደት ሌላ ምን ሊኖር ይችላል?
መሬት የማን ነው? ክፍል አንድ – ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

lørdag 5. oktober 2013

የማለዳ ወግ ... በተስፋየ ገብረ አብ ላይ የቀረበው ክስ መረጃ አንድ እውነታ!


 ከሶስት ቀናት በፊት ቀትር ላይ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ ። አንድ እዚህ ጅዳ የሚገኝ ወዳጀ ነበር ። ይህ ወዳጀ በስደተኛ ዜጎቻችንና
በኮንትራት ሰራተኞች ላይ የከፋ ግፍ ሲፈጸም ፣ ዜጎች በራሳችን መንግስት ተወካዮች በጅዳና ሪያድ መጠለያዎች ፍዳቸውን ሲያዩ ፣
ኢትዮጵያውያን ሲያመን ህመሙ ዘልቆ ሲያመው እና የአረቡ መገናኛ ብዙሃን ስማችን አጉድፈው ክብራችን ቀንሰው መረጃ ሲያሰራጩ
በስጨት ብለው ከሚደውሉልኝ ወዳጆቸ መካከል ብርቱው ወዳጀ ነው። ብርቱው ወዳጀ የኢትዮጵያ ነገር አይሆንለትም ...

 ያኔ የማይረባ የባድመ ድንበር ጦርነት ተቆስቁሶ የሁለት ሃገራት አንድ ህዝቦችን ታዳጊ ወጣቶች ነፍስ ሲቀጠፍ አንዳንዶች ኢትዮጵያን
ተንኳሽ እያደረጉ በሳውዲ ጋዜጦች ጨለምተኛ ፕሮፖንጋዳቸውን በመንዛት የተጠመዱ እኩዮች ብቅ ብቅ ብለው ነበር ። በዚህ ጭንቅ
ሰአት በጣም ጥቂት የጅዳ ነዋሪዎች ለፕሮፓጋንዳው መልስ ይሰጡ የነበረ ሲሆን ይህ ወዳጀ ደግሞ ቀዳሚ መልስ ሰጭ እንደነበር
አውቃለሁ። እናም ለዚህ መሰል ሃገር ፍቅሩ ክብር አለኝ !

ይህ ብርቱ ወዳጀ ከደወለልኝ ሰንበትበት ቢልም ዛሬ ቁም ነገር ይዞ መደወሉን አላጣሁትም !

"የት ጥፋህ ባክህ! " ብሎ መልሴን ሳይጠብቅ ወደ ጉዳዩ ዘው ብሎ ገባ ... ልጆቸን ከትምህርት ቤት ለመመለስ ነበርኩና ጎረምሶች
እስኪመጡ አናት ከሚሰነጥቀው የቀትር ጸሃይ በመኪናየ ውስጥ ተከልየ ብርቱ ወዳጀን ማድመጤን ቀጥያለሁ ... ወዳጀ በጋዜጠኛና ደራሲ
ተስፋየ ገብረ አብ ዙሪያ የተጻፈውን ጽሁፍና የቀረበበትን መረጃ ከላይ እስከታች አንብቦ እንደጨረሰ ነበርና የደወለልኝ መሰሪ ባለው
የተስፋየ ኢትዮጵያን የማድማት እኩይ ስራ መበሳጨቱን አውግቶኝ ሊጨርስ ሲቃረብ ..."ወረቀት ካለህ ይህን ስልክ ጻፍና አጣራው? "
ሲል አንድ ቁጥር ሰጠኝ ... "ስሙ ኢብራሂም ነው! ይህ ሰው በተስፋየ የመጽሃፍ ስርጭት መረብ የተስፋየን መጽሃፍ የሚያከፋፍል ነወና
አጣራው! " ብሎ የምደርስበትን እንድነግረው ተማጽኖኝ ስልኩን ዘጋን ...

 ወዲያው ስልኩን እንደዘጋሁ ወደ ተባለው አካፋፋይ ወንድም በመደወል ማጣራቴን ያዝኩ ... ወዳጀ የሰጠኝ ስም ትክክል አለመሆኑን
እና አማን ኢብራሂም እንደሚባል በመጀመሪያው ዙር ማጣራት ደረስኩበት! ... የተስፋየን መጽሃፍ ለመግዛት ጠይቄም አፈላልጎ
እንደሚያመጣልኝ ቃል ተገብቶልኛል ...

 በተስፋየ ገብረአብ ዙሪያ በዳኛ ወልደ ሚካኤል መሸሻ የተጻፈው በድረ ገጾች በተለጠፈ ቅጽፈት ባየውም እንደቀደመው እሰጣ እገባ
ጽሁፍ መጻፉን ገመትኩ፣ ተስፋየ ኬንያ ላይ ይጠቀምበት የነበረ በኤርትራ መንግስት የተሰጠው መታወቂያ ጉዳይም ቢሆን ለወግ ማጣፈጫ
የተቀነባበረ እንዳይሆን በጥርጣሬ መመልከቴ አልቀረም ። እናም መጣጥፉን ከነመረጃውን መመልከት ግድ አለኝ ...

 ከተስፋየ ጋር በጉርብትና ይኖር ነበር ከተባለው ወጣት አክቲቪስት አለማየሁ መሰለ መረጃው ተገኘ ፣ ዳኛ ወልደ ሚካኤል መሸሻ
ይርዘም እንጅ በግሩም የመረጃ ግብአትን እያስዋቡ የአለማየሁን ውሃ የሚያነሳ ሰነድ አሳዩን ፣ አስነበቡን ! የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል ለሚል
መጣጥፉ ረጅም ቢሆንም ወግ በወግ የተሰናዳ በመሆኑ አይሰለችም ። በጉጉት ፣ በአግራሞት እና በአድናቆት አነበብኩት! ከላይ ከጅዳው
ብርቱ ወዳጀ የተሰጠኝም ስምም የተስፋየን መጽሃፍ ጅዳ ውስጥ የማከፋፈል ስራውን የሚያሂዱ ግለሰብ መሆናቸውን የሚጠቅሰውን ሰነድ
ኮፒ ገጽ 31 ላይ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል! እንዴት ነው ነገሩ ? አልኩ ! ! !

 ወዳጀ መነሻ ሆኖኝ በግል ዳስሸ ያገኘሁት ተጨባጭ እውነታ እና በቀረበው መጣጥፍ የቀረበው ሰነድ እውነታ በውስጤ ሌላ ስሜት
መፍጠር ያዘ ፣ ቀድሞውኑ ስል ተስፋየ ገብረአብ ተጽፎ ሳይ "በተስፋየም በተቃዋሚዎቹም የቀጠለው ስም የማጠልሸት እስጣ ገባ አለያም
የተስፋየ ገብረአብ ቀጣይ መጽሃፉን ለማሻሻጥ የተደረገ ረቂቅ የገበያ ፍለጋ ዘመቻ ነው !" የሚለውን ጥርጣሬ ነበረኝ! ከሰአታት በፊት
ያነጋገርኩት አከፋፋይ አና ከመጣጥፉ ጋር የቀረበው ሰነድ ግን አጉል ጥርጣሬየን ብንን አድርጎ አጠፋብኝ ... !

 በአለማየሁ በኩል ከጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋየ ገብረአብ ጉያ ተገኙ ከተባሉትን ሰነዶች መካከል ማረጋገጥ የቻልኩት ሰነድ ብዙ አርቆ
አሳሰበኝ ... በዚህ ዙሪያ ከራሴ ጋር ስሞግት ግራ የተጋባችው ባለቤቴ ቁርጠት የሚያጣድፋትን እርጥብ ልጃችን ማህሌትን ከደረቷ ላይ
ለጥፋ ከምታባብልበት ቀረብ አለችና " አብረን ማንበብ ጀመረን ብቻህን ጨረስከው አይደል? " ብላ ስትጠይቀኝ የሆነውን ሁሉ
አጫወትኳት ... "ምን ሆነሃል እኔም ደስ አላለኝም ፣ ይህ ነገር እውነት ሳይሆን አይቀርም ! የቡርቃ ዝምታን አንብበው እስኪ ?" በማለት
ከመጽሃፍ መደርደሪያው የተወሸቀውን የተስፋየ ገብረአብ የቡርቃ ዝምታ መጽሃፍ የት አንደገዛችው እና በጅዳና አካባቢው በሰፊው
የተከፋፈለበት መንገድ አወጋችኝ! ኢትዮጵያን ትወዳለችና የመረጃውን እውነታ የቀረበው ሰነድ ተጨባጭነት አጉልቶ እንዳሳሰባት
አጫዎተችኝ ... ወደዚህ አለም ከመጣች ገና አስራ አምስት ቀን የደፈነቸው ልጃችን ማህሌት ይህን ሶስት ቀን ንጭንጭ ብላ ታለቅሳለች!                                                                                                                                                           ከትናነት በስቲያ ሃኪሟ ዘንድ ሄጀ "አዲስ ለተወለዱ ህጻናት ይህ መሰል ቁርጠት ከወተት ጋር የሚመጣ የተለመደ ነው!" ብሎ ምክር ቢጤ
ስለሰጠኝ ብዙ አላሳሰበኝም አልልም ! ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአለማየሁ ተገኝቶ በዳኛ ወልደ ሚካኤል የቀረበው መረጃና ያጋጠመኝ
ግጥምጥም ጉዳይ ሳይሆን ቢቀር አሳስቦኛል! እናም ብርቱ ወዳጀን ያመመው ኢትዮጵያዊ ህመም አመመኝ ! ግን ለምን ተስፋየ ? አልኩ ...
ትንሿ እውነተኛ የመረጃ ፍንጭ ጠልቃ ብታደማኝ...

 ብዙም ሳልቆይ አንዳች ነገር ሰውነቴን ወረረው ! በግላጭ አግኝቸው በተጨባጭ ሳልይዘው ያለፍኩት መረጃ ትዝ አለኝና ከአልጋየ
ተስፈንጥሬ በመነሳት ወደ ተስፋየ ገብረአብ መጽሃፍ አከፋፋይ ስልክ ደወልኩ ... ስልኩ ተነሳ !

"ጤና ይስጥልኝ ? "
"ጤና ይስጥልኝ ! "
"እንደምን አደሩ !?" ቀጠልኩ
"አልሃምዲላህ ! " መለሰ

 ከዚህ ቀደም ያገኘሁት ወንድም ነው። የማወራው ከምፈልገው ሰው ጋር መሆኑን ለማረጋገጥ መስመር ውስጥ ያገኘሁትን ወንድም "አቶ
አማን ነወት? "በማለት ጠየቅኩት ፣ አማን መሆኑን ካረጋገጠልኝ በኋላ ማንነቴን ሲጠየቀኝ ።... ከሁለት ቀን በፊት የተስፋየ ገብረአብን
መጽሃፍ አፈልጌ ደውየ እንደነበር ስገልጽለት አስታወሰኝ ...በመቀጠልም . ..

"አዎ መጽሃፍ የሚሸጠውን ሰውየውን ፈልጌው ነበር አላገኘሁቱም ፣ የትኛውን መጽሃፍ ነው የምትፈልገው ? የ . ... የፈልግከው ? "ሲል
ጠየቀኝ ፣
አዲሱ መጽሃፍ ካለ መልካም ከሌለ ያለውን ባገኝ ቅር እንደማይልሰኝ ገለጽኩለት

"ያለው አይመስለኝም ድሮ ይህ ሰውየ ያመጣው የነበረው የጋዜጠኛው ማስታወሻ የሚል ነው ። " ሲለኝ አስከተልኩና "እሱስ አለህ ? "
ስል ጠየቅኩት...

"እሱ ካለ እጠይቀዋለሁ ! ሰውየውን አላገኘሁትም ይሸጠው የነበረው . ..ስንት ነው የፈለግከው ? " በማለት7በድጋሜ ሲጠይቀኝ መግዛት
የምፈልገውን መጽሃፍ ብዛት ደርዘን አድርሸ መለስኩለት አቶ አማን መለሰ " አገኘኋለሁ እና ቢጠፋ ቢጠፋ እሁድ አገኘዋለሁ !
እነግርሃለሁ ! " አለኝ

አቶ አማንን በማስከተል የአዲሱን መጽሃፍ መምጣት መረጃ አና ስለ አከፋፋዩ ጠየቅኩት

" I don't know ከእርሱ አዲስ ስለመኖሩ አላውቅም ፣ የበፊቱን ከእርሱ አግኝቸው ነበር ከዚህ በፊት . ... አንተ እንግዳ ነህ ለጅዳ ?"
በማለት አከታትሎ ጠያቂውን ያጠየቀ ጥያቄ ከወደ አቶ አማን ቀረበልኝ ፣ ለሃገሩ ባዳ ነኝ የሚል ነጭ ውሸት ዋሸሁት...

"የት ነው ያለህው ?"ከሚለው ጥያቄ ጀምሮ " ማነው ይህን ስልክ የሰጠህ ? " የሚለው ጥያቄ ከወደ አቶ አማን ተከታትሎ ቢቀርብልኝም
ለስራ ጉዳይ ጅዳ ብመጣም የምኖረው ራቅ ወዳለች አንዲት የሳውዲ የጠረፍ ከተማ መሆኑን በማስረዳት እዚያ ላሉ ኢትዮጵያውያን
መጽሃፉን ለማከፋፈል እንደምፈልግ ገለጽኩለት ፣በማከልም የእርሱን አድራሻ ያገኘሁት አውሮፓ ከሚኖር ወዳጀ መሆኑን አስረዳሁት ።
ከዚያም አቶ አማን ጥያቄዎቹን በመግታት መጽሃፉን ከአከፋፋይ ካለው ሊጥይቅልኝ ቃል ገብቶልኝ ስልኩን ዘግተን ተለያየን ...

 አዎ ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋየ ገብረ አብ ተወልዶ ያደገባትን ፣ ለወግ ማዕረግ አብቅታ ያስተማረችውን ሃገር የኢትዮጵያን ህዝብ የሚጎዳ
ስራ መስራቱን ለመቀበል ከባጀና ከከረመ አመታት ተቆጥረዋል። ተስፋየ እንደ ደራሲና ጋዜጠኛም ባይሆን እንደ ሰው ተፈጥሯዊ ሃሳብ
የመግለጽ የማይገሰስ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን አምናለሁ። ዳሩ ግን ተስፋየ እንደተባለው እስከ ጥግ በሚጠቀመው መብቱ እንደ ዘርን
ከዘር የሚያጋጭ መረጃን ማስተላለፉን አልቀበለውም። ተስፋየ ገብረአብ የኢህአዴግ ባለስልጣን እያለ ጀምሮ የጻፈውን ወደ ኋላ ዘወር
ብሎ ላስተዋለው ያሳዝናል። ተስፋየ ገብረ አብ በኢህአዴግ መንግስት ታማኝ ሆኖ እና በወሳኝ የሃገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር ከፍተኛ
ስልጣን ተቀምጦ የሚጎዳንን ፣ የሚለያየንን በቡርቃ ዝምታን መጽሃፉ ጀባ ብሎናል ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ብዙዎችን በልዩነት በደጋፊና
ተቃዋሞ ዙሪያ ያዘባራው ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋየ ገብረአብ በቡርቃ ዝምታ የተሰቀዘው የብዙዎች ልብ በቀጣይ ስራዎቹ ለማባበል
አልገደደውም ።

 እርግጥ ነው ተስፋየ በልዩ የአጻጻፍ ክህሎቱና አልፎ አልፎ በሚያነሳቸው "ጮማ " የፓለቲካ ወጎቹ እና በቀጣይ ባቀረባቸው ወጥ ልብ
አንጠልጣይ የድርሰት ስራዎቹ የተቃወሙ እና የሸሹት መልሶ ምርኮኛ ማድረግን የተካነ የጥበብ ሰው መሆኑን ላፍታ እንኳ መካድ          አይቻልም። ዛሬ ሌላ ቀን ቢሆንም የተስፋየ የጥበብ ትጋት እና እየጣለ የሚያነሳን ያልረጋው የሃገራችን ፖለቲካ ውጥንቅጥ ውስብስብ ባህሪ
ጋርዶብን የተስፋየ ገብረ አብ ድጋፍ ሰጭ የነበርን የተጎጅዋ ሃገር ዜጎች ቁጥር ቀላል አልነበረም !
 እርግጥ ነው ተስፋየ ገብረአብ ከተባለው ረቂቅ ሴራ በተጓዳኝ ጠቃሚ ጠቃሚ የሚባሉ መረጃዎችን ይፋ በማድረጉ ረገድ የሰራው
መልካም ስራ የሚዘነጋ አይደለም። በስልጣን በቆየባት ሃገር ለተሰራው ሁሉ እሱም ከተጠያቂነት ባያመልጥም በስልጣን ዘመኑ በሃገሬ
ምድር በአደባባይ እና በስውር ተሰርቶ ያየውን ባያጠግበንም ብዙ አካፍሎናል ። እማኝነቱን በሰጠባቸው የአንድ ቡድን የበላይነት የነገሰበት
ሃገር ፣ የመብት ገፈፋና የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ያቀበልን መረጃዎች የስነጽሁፍ ጥበቡን ጨምሮ ብዙ ትምህርት ማግኘታችን
የሚካድና የሚዘነጋ አይደለም። በተስፋየ ዙሪያ ዛሬ ሌላ ቀን ያባተ ይመስላል።

 ዛሬ ሌላ ቀን ሆነና በወጣቱ ሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ በአለማየሁ ትጋት በመረጃ ተደግፎ የተጋለጠው የተስፋየ የከራረመ ሴራ በዳኛ
ወልደ ሚካኤል መሸሻ ጥናታዊ ዘገባ በዝርዝር ይፋ ሆኗል። ይህንን መረጃ እያየሁም በተስፋየ ክህደት ዙሪያ እየተጠራጠርኩ ለማንበቤ
ከተስፋየ አንደበት የሰማኋቸው የጸና ኢትዮጵያዊነት የአቋም መግለጫዎቹ እንደሆኑ ውስጤ አሁንም ያምናል ! አንዲህ ሆኖም የቀድሞ
መከላከያ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ስየ አብርሃን ጨምሮ በአካባቢያቸው ያሉትን ሃገር ወዳድ ተቃዋሚዎች እና አዛውንቱ የቀድሞው
የሃገሪቱ ፕሬዚድንት ዶ/ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ሳይቀሩ በተስፋየ ዘራፍ ብዕር ተወርፈዋል። ይህን ዘለፋውን ደጋግሜ ተምልክቸ ልቤ አልቀበል
እያለው ብቸገርም ከተራ ጥላቻ የዘለለ የለመድነው የመቦጫጨቅ ፖለቲካ ነው በማለት ችላ እለው ነበር ። ዛሬ ግን ያ ሁሉ በትር
ያዘነበባቸውን ወገኖች የማጥቃት አለማ አውጥቸ አውርጀ እመዝነው ዘንድ ግድ ይለኛል! ዛሬ የቀረበልን ጭብጥ ሰነድ ቢያንስ ተስፋየን እና
ይጠላቸው የነበሩትን ሁሉ ሳይሆን ይወዳቸው የነበሩትንም ፖለቲከኞቻችን መላለሰሸ እገመግማቸው ዘንድ ተገድጃለሁ! ዛሬ ቢያንስ በግል
በተስፋየ እጅ የተጻፉ ሰነዶች ጋር ለቀረበውን ቅንጣቢ መረጃ ማረጋገጫ ካጋገኘሁ ወዲህ ቢያንስ በተስፋየ ላይ ስለሚሰነዘረው ውንጀላ
የጥርጣሬ ግርዶሹ ተገፎልኛል !

 የማለዳ ወጌን ለመደምደም ዳኛ ወልደ ሚካኤል መሸሻ በቀረበው 44 ገጽ ጥናታዊ ጽሁፍ በገጽ 31 ላይ እዚህ ጅዳ በአከፋፋይት
የተጠቀሱትን ወንድም ካነጋገርኩ በኋላ በሰነዱ ጎን የሰፈረው መግለጫ አስታወስኩ ... አንዲህ ይላል "...ከዚህ በላይ በሻጭነት
የተመለከቱትን ምናልባትም በየአገራቱ ከምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ቢያንስ አንዳችሁ አንዱን ታውቁ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። እናም፣
ከእንግዲህ ልብ ልንል ይገባል። ባለማወቃችን፣ ባለማስተዋላችን ተታልለናል። ካወቅን በኋላ ደግሞ እንነቃለን። በቃህ! ወደዚያ! እንላለን።
ኢትዮጵያዊነት ኩራት መሆኑን እንነግራቸዋለን ማለት ነው!" ይላል! እርግጥ ነው ከተለቀቀው መረጃ ውስጥ የተጠቀሰውን አንድ መረጃ
መረጋገጥ በመቻሌ እኔም በመልካም ጥበብ ተደቁሶ የተቀመመውን መርዝ ላለመጋት "በቃ!" ብያለሁ ! አዎ ! አትዮጵያዊነት ከጥበብ ሁሉ
የላቀ ጥበብና ኩራት መሆኑን እነግራቸዋለሁ !

በቃ ይህን ነው የምለው . . . ኢትዮጵያ ለዘልአለም ትኑር !

 ነቢዩ ሲራክ

fredag 4. oktober 2013

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች በግድ ዩኒቨርሲቲው እንዲለቁ ተደረገ

ዘ-ህበሻ | October 3rd, 2013
tem
(ዘ-ሐበሻ) በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የሳይንስና ቴክኖሊጂ ተማሪዎች አስተዳደሩ COC (ፈተና) እንዲወስዱ በማስገደዱና ተማሪዎቹም ካለምንም ዝግጅት አንፈተንም፤ ጊዜ ሊሰጠን ይገባን በሚል ያነሱት አለመግባባት እየተካረረ ሄዶ ተማሪዎቹ በግድ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ።
ተማሪዎቹ ካለምንም

torsdag 3. oktober 2013

ምን ነካን?!

September 25, 2013


ገረመው ዘመኑ
ወያኔ ደርግን ፋሺስት ይበል እንጅ ደርግ የሠራውን አንዱንም ትክክል አይደለም ብሎ ለመለወጥ ወይም ለማረም ሲሞክር ማናችንም አላየንም። እንዲያውም የሕልውናው መሠረት እይደረገው እንጂ።
ለምሣሌ መሬትን ለሕዝብ ያደረገውን አዋጅ ወያኔ አንድም ቃል ሣይለውጥ እንዳለ ገልብጦ በከፍተኛ ደረጃ በገንዘብ ማምረቻነትና በፖለቲካ መሣሪያነት እየተገለገለበት እንደሆነ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምሥጢር አይደለም። ይህ ብቻም አይደለም። ወያኔ ሕዝብን እጅግ በጣም በመናቁ ደግሞ፣ ለፈረንጅ፣ ለሕንድና ለዓረብ መሬቱን፣ ደኑንና ውሃውን በሣንቲም ሲሸጥ የመሬቱ ባለቤት ለሆነው ኢትዮጵያዊ የሚሸጠው ግን መሬት ለንደን፣ ኒውዮርክና ዋሽንግተን ከሚሸጥበት በበለጠ ዋጋ ነው።
ለዚህ የወያኔ አገር ሺያጭ ዘመቻ ወገኖች ወርቃቸውን ተሸክመው ወገባቸው እስኪንቀጠቀጥ በየኤምባሲውና በየቀበሌው ቆመው መዋል – ማደራቸው ነው። የራሣቻውን መሬት ለመግዛት¡ [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ድሆችን ያፈናቀለው “ኢንቨስትመንት” ዕዳ ዋጠው

"እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልሸጥነው መሬት ነው" መለስ

DSCN0291
“መሬታችንን ለምን እንነጠቃለን?” በማለት የጠየቁ ተገድለዋል። ተገርፈዋል። ታስረዋል። አሁን ድረስ እስር ላይ የሚገኙ አሉ። ባዕድ እንኳን ባልሞከረው የከፋ ጭካኔ በከባድ መሳሪያ በተደገፈ የጦር ሃይል የተወለዱበትን መሬት እንዲለቁ የተገደዱ አዛውንቶች ላይ የተፈጸመው ግፍ እስከ ወዲያኛው የሚያሽር አይደለም። በሌሊት እርቃናቸውን ከሚያርፉበት ታዛ ስር ነፍጠኛ ሰራዊት እንዲከባቸው እየተደረገ የተፈጸመው አስነዋሪ ግፍ ጊዜ የሚጠብቅ እንደሆነ በየጊዜው የሚገለጽ ነው።
“የዘራሁትን ሳላነሳ በዶዘር ማሳዬን ጠረጉት፣ በዶዘር እርሻዬ ውስጥ ገብተው አረሱት፣ መሬቴን ለምን ትወስዳላችሁ? የት ልትወስዱኝ ነው? ያሸተውን በቆሎዬን መነጠሩት። ምን ላደርግ እችላለሁ። መሳሪያ የያዙ ወታደሮች ከበውኛል፣ ጠዋት ስነሳ ማሳዬ ባዶ ሆኖ አገኘሁት … ” ይህ ሁሉ የበደል ሰቆቃ ነው። በምስል ተደግፎ የቀረበ ህሊናን የሚሰብር መረጃዎች አሉ።
anuak man
(Photo: IC magazine)
አንድ የአካባቢው ነዋሪ “ሰላማዊ ህዝብ፣ በቅጡ የሚለብሰው እንኳን የሌለውን ህዝብ፣ አሮጊቶችን፣ አዛውንቶችንና ህጻናትን ሲገድሉና ሲያሰቃዩ የቆዩት ለዚህ ነው? ለዚህ ኢንቨስትመንት ነው ያ ሁሉ የተፈጥሮ ደን ወድሞ ከሰል እንዲሁን የተደረገው? ገንዘብ ሳይሆን የከሰል ጆንያ ይዘው ክልሉን እንዲቀራመቱ የሚፈቅዱት ክፍሎች ስለጊዜና ስለዘመን ለምን አያስቡም?” ሲል ይጠይቃል። በማያያዝም “70 ከመቶ የሚሆኑት ባለሃብቶች የትግራይ ሰዎች መሆናቸውን እናውቃለን። መረጃውም አለን። እባካችሁ የተጨቆናችሁ የትግራይ ወንድምና እህቶች እባካችሁን በስማችሁ እየተፈጸመብን ያለውን በደል ተቃወሙ” ሲል ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ አስረድቷል።
አዛውንቱ ጸሐይ ለመሞቅ ታዛ ስር ቁጭ ባሉበት (በፎቶው የሚታዩት አይደሉም) ከሙሉ ቤተሰባቸው ጋር የጥይት ራት የተደረጉበት ኢንቨስትመንት አስቀድሞ የተገለጸ ቢሆንም መጨረሻው ሌብነት እንደሆነ ኢህአዴግና ራሱ ድርጅቱ ማመናቸው ተሰማ። አቶ መለስ ሲጀነኑበት የነበረው ኢንቨስትመንት አውላላ ሜዳ ላይ የተደፋ ስለመሆኑ የተጠየቁት አቶ ኦባንግ ሜቶ “እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልተሸጠው መሬት ነው” በማለት አቶ መለስ የተናገሩትን በማስታወስ “ህዝብን የማይሰማ ድርጅት ዞሮ ዞሮ ከውርደት አይድንም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሰሙት ዜና የሚጠበቅ እንደሆነ ያመለከቱት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ “ሚዲያዎች በነካ እጃቸው ስለ ሰለባዎቹም ይተንፍሱ” ሲሉ ጠይቀዋል።
ኦገስት 31/ 2013 የታተመው የጎልጉል ዜና “የኢትዮጵያን ለም መሬት ከተቀራመቱት ኢንቨስተሮች መካካል አንዱ የሆነው የህንዱ ካሩቱሪ ከኢትዮጵያ ለቅቆ የሚወጣበት ጊዜ መቃረቡን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታወቁ። አበዳሪዎችና ባለ አክሲዮኖች ፊታቸውን እንዳዞሩበትም ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ባዶ ዋይታ የሚያሰማው ኢህአዴግ የያዘው አዲስ አቋም ድርጅቱንና ከድርጅቱ ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው የሚባሉትን ሃሳብ ላይ ጥሏል” ሲል መዘገቡ ይታወሳል።
በዚሁ ዘገባ ላይ በቦታው ኢህአዴግና ጭፍሮቹ መካከል ሆነው የተካሄደባቸውን የመሬት ነጠቃ በመቃወምና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ጀብድ ለሰሩት “… በቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም። ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችኋልና ክብር ይሁንላችሁ” ሲሉ አቶ አባንግ ያስተላለፉት መልክትም ከዜናው ጋር ተካትቶ ነበር።
“በእውቀት ላይ የተመረኮዘ፣ በእቅድ የተያዘ ትግል እያካሄድን እንደሆነ በገለጽኩበት ወቅት ካሩቱሪ በኪሳራ ከኢትዮጵያ ምድር እንደሚወጣ ተናግሬ ነበር። አሁን ጉዳዩ ያለው የኢትዮጵያን ድንግል መሬት በሳንቲም የቸበቸቡትና ያስቸበቸቡት የጥቅም ተጋሪዎችና ደላሎችን ለይቶ ለፍርድ የሚቀርቡበትን ስራ መስራቱ ላይ ነው። በህንድ ጥሪያችንን ሰምተው ትግላችንን የተቀላቀሉ ፍትህ ወዳድ እህትና ወንድሞች፣ ምስጋና ይገባቸዋል” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ስለ ካሩቱሪ የተሰማውን ዜና አስመልክተው ተናግረዋል።
ሰንደቅ የተሰኘው ጋዜጣ ዜና ባለስልጣኖችንና የካሩቱሪን ሃላፊ አነጋግሮ ይፋ ያደረገው ዜና ኢህአዴግን የሚያሳፍር ከመሆኑም በላይ ከዝርፊያው በስተጀርባ ያሉትን በሙሉ ያስደነገጠ ሆኗል። የጎልጉል ምንጭ እንደሚሉት የጋምቤላ ድንግል መሬት በሳንቲም ሲቸበቸብ ከጀርባ ሆነው ኮሚሽን የተቀበሉና የሚቀበሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ደላሎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የአገሪቱን ሃብት በዓይነት፣ ገንዘቧን በብድር፣ ወገኖቻቸውን በጥይት እያስደበደቡ ለባዕድ በመስጠት የፈጸሙት ወንጀል መጨረሻ በራሳቸው አንደበት ይፋ ተደርጓል።
የአክሲዮን ሽያጩና የብድር ምንጩ የደረቀበት ካሩቱሪ ንብረቱ ለሃራጅ እንዲቀርብ በዝግጅት ላይ ነው። ሰንደቅ ባይገልጸውም ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ሳዑዲ ስታር በሚባለው የግብርና ተቋማቸው ሰፊ መጠን ያለው መሬት በመውሰድ ህዝብ እንዲፈናቀል ካደረጉት ጋር እንደሚደመሩ በተለያየ ጊዜ የሚጠቆም ነው።
የሰንደቅ ዜና እንዲህ ይነበባል፡-

የህንድ ካራቱሪ ኩባንያ 62 ሚሊዮን ብር የንግድ ባንክን ዕዳን መክፈል አልቻለም

  • ኩባንያው የሠራተኞች ግብር፣ ጡረታ እንዲሁም የክልሉን የመሬት ግብር አልከፈለም
  • ከቀረጥ ነጻ ያስገባቸውን ማሽነሪዎች በማከራየትና በመሸጥ እየተከሰሰ ነው።
  • ከተረከበው 300 ሺ ሔክታር ያለማው 800 ሔክታር ብቻ ነው።
መሠረቱን በጋምቤላ ክልል ያደረገው የህንድ ካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክት ኀ/የተ/የግ/ማህበር በተሰጠው መሬት ላይ የልማት ሥራ ማከናወን አለመቻሉን እንዲሁም የባንክ ብድርና የግብር ግዴታዎቹን እየተወጣ አለመሆኑ ተገለፀ።
አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ የቢዝነስ ዴቭሎፕመንት የስራ ሒደት ባለቤት ስለጉዳዩ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንዳስረዱት “ካራቱሪ ከባንኩ እ.ኤ.አ በዲሴምበር 2011 ወደ 62 ሚሊየን ብር ብድር መውሰዱን አስታውሰው ነገር ግን መክፈል በሚገባው ጊዜ ሊከፍል አለመቻሉን፣ ብድሩንም ለማስታመም የተደረጉ ተጨማሪ ጥረቶች ባለመሳካታቸው ጉዳዩ ወደህግ ክፍል መመራቱን አስታውቀዋል። ባንኩ በአሁኑ ወቅት ይህ ብድር የተበላሸ ወይንም መመለስ የማይችል ነው በሚል ጉዳዩን ይዞት ለማስመለስ ወደ ሕጋዊ እርምጃ መግባቱን” ተናግረዋል።
በተያያዘም በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ከአራት ዓመት በፊት በጋምቤላ ክልል 300ሺ ሄክታር መሬት ለማልማት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር ተዋውሎ የገባው የህንዱ ኩባንያ ካራቱሪ ባለው ደካማ ማኔጅመንት ምክንያት ሥራውን ማከናወን ባለመቻሉ በአሁኑ ወቅት ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።
አቶ አለምሰገድ አያሌው የኩባንያው የምርት መሳሪዎች ዋና ክፍል ኃላፊና የሠራተኞች ተወካይ ለሰንደቅ ጋዜጣ በስልክ እንደገለጹት ኩባንያው 300ሺ ሄክታር ለማልማት ከግብርና ሚኒስቴር መሬት ተረክቦ የነበረ ቢሆንም ባለፉት አምስት አመታት ከ800 ሄክታር በላይ ለማልማት አልቻለም።
ግብርና ሚኒስቴር ይህንኑ ደካማ አፈጻጸም በማየት ከአንድ ዓመት በፊት 200ሺ ሄክታር መሬት የነጠቃቸው መሆኑን አቶ አለምሰገድ አስታውሰው ይህንንም ማልማት ባለመቻላቸው በአሁኑ ወቅት በእጃቸው የሚገኘው መሬት 10ሺ ሄክታር ብቻ ነው ብለዋል። ይህም ሆኖ በአሁኑ ወቅት በበቆሎ ሰብል የተሸፈነው 800 ሄክታር ገደማ ብቻ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
ድርጅቱ 150 ያህል ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዳሉት ያስታወሱት አቶ አለምሰገድ የሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ እስከ 45 ቀናት እንደሚዘገይ፣ ለጡረታና ለግብር ከሰራተኛው የሚሰበሰበው ክፍያ በአግባቡ ለሚመለከተው አካል እንደማይገባ ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል።
የኩባንያው አመራሮች በውጪ ምንዛሪ የሚያስገቡዋቸውን ዘርና ማዳበሪያ በአገር ውስጥ እንደሚሸጡ፣ ከቀረጥ ነጻ ያስገቡዋቸውን ማሽነሪዎች በማከራየትና ለሶስተኛ ወገን በመሸጥ ያልተገባ ጥቅም እንደሚያጋብሱ ተናግረዋል።
ይህንኑ አቤቱታቸውን ለጋምቤላ ክልል የሚመለከታቸው መ/ቤቶች በተደጋጋሚ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።
የጋምቤላ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ጆን ሾል ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው የካራቱሪ የስራ አፈጻጸም እጅግ ደካማ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኩባንያው በተጨማሪም ለወረዳ መክፈል ያለበትን የመሬት ግብር ጭምር እንዳልከፈለ የጠቆሙት አቶ ጆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክም የተበደረውን ባለመክፈሉ ባንኩ በመያዥነት የያዛቸውን ንብረቶች ወደማስከበር ስራ ፊቱን ማዞሩን ጠቁመዋል።
በቅርቡ ከፌዴራል መንግስት ባለሙያዎች ወደቦታው መጥተው ችግሩን አጥንተው መመለሳቸውን ጠቁመው በቅርቡ ኩባንያውን በተመለከተ የመጨረሻ መፍትሔ ሊገኝ እንደሚችል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክት ኃ.የተ.የግ.ማኅበር (ጋምቤላ ኤሊያ አካባቢ) የሥራ ኃላፊዎችን በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ድሆችን ያፈናቀለው “ኢንቨስትመንት” ዕዳ ዋጠው

"እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልሸጥነው መሬት ነው" መለስ
DSCN0291


“መሬታችንን ለምን እንነጠቃለን?” በማለት የጠየቁ ተገድለዋል። ተገርፈዋል። ታስረዋል። አሁን ድረስ እስር ላይ የሚገኙ አሉ። ባዕድ እንኳን ባልሞከረው የከፋ ጭካኔ በከባድ መሳሪያ በተደገፈ የጦር ሃይል የተወለዱበትን መሬት እንዲለቁ የተገደዱ አዛውንቶች ላይ የተፈጸመው ግፍ እስከ ወዲያኛው የሚያሽር አይደለም። በሌሊት እርቃናቸውን ከሚያርፉበት ታዛ ስር ነፍጠኛ ሰራዊት እንዲከባቸው እየተደረገ የተፈጸመው አስነዋሪ ግፍ ጊዜ የሚጠብቅ እንደሆነ በየጊዜው የሚገለጽ ነው።
“የዘራሁትን ሳላነሳ በዶዘር ማሳዬን ጠረጉት፣ በዶዘር እርሻዬ ውስጥ ገብተው አረሱት፣ መሬቴን ለምን ትወስዳላችሁ? የት ልትወስዱኝ ነው? ያሸተውን በቆሎዬን መነጠሩት። ምን ላደርግ እችላለሁ። መሳሪያ የያዙ ወታደሮች ከበውኛል፣ ጠዋት ስነሳ ማሳዬ ባዶ ሆኖ አገኘሁት … ” ይህ ሁሉ የበደል ሰቆቃ ነው። በምስል ተደግፎ የቀረበ ህሊናን የሚሰብር መረጃዎች አሉ።
anuak man
(Photo: IC magazine)
አንድ የአካባቢው ነዋሪ “ሰላማዊ ህዝብ፣ በቅጡ የሚለብሰው እንኳን የሌለውን ህዝብ፣ አሮጊቶችን፣ አዛውንቶችንና ህጻናትን ሲገድሉና ሲያሰቃዩ የቆዩት ለዚህ ነው? ለዚህ ኢንቨስትመንት ነው ያ ሁሉ የተፈጥሮ ደን ወድሞ ከሰል እንዲሁን የተደረገው? ገንዘብ ሳይሆን የከሰል ጆንያ ይዘው ክልሉን እንዲቀራመቱ የሚፈቅዱት ክፍሎች ስለጊዜና ስለዘመን ለምን አያስቡም?” ሲል ይጠይቃል። በማያያዝም “70 ከመቶ የሚሆኑት ባለሃብቶች የትግራይ ሰዎች መሆናቸውን እናውቃለን። መረጃውም አለን። እባካችሁ የተጨቆናችሁ የትግራይ ወንድምና እህቶች እባካችሁን በስማችሁ እየተፈጸመብን ያለውን በደል ተቃወሙ” ሲል ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ አስረድቷል።
አዛውንቱ ጸሐይ ለመሞቅ ታዛ ስር ቁጭ ባሉበት (በፎቶው የሚታዩት አይደሉም) ከሙሉ ቤተሰባቸው ጋር የጥይት ራት የተደረጉበት ኢንቨስትመንት አስቀድሞ የተገለጸ ቢሆንም መጨረሻው ሌብነት እንደሆነ ኢህአዴግና ራሱ ድርጅቱ ማመናቸው ተሰማ። አቶ መለስ ሲጀነኑበት የነበረው ኢንቨስትመንት አውላላ ሜዳ ላይ የተደፋ ስለመሆኑ የተጠየቁት አቶ ኦባንግ ሜቶ “እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልተሸጠው መሬት ነው” በማለት አቶ መለስ የተናገሩትን በማስታወስ “ህዝብን የማይሰማ ድርጅት ዞሮ ዞሮ ከውርደት አይድንም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሰሙት ዜና የሚጠበቅ እንደሆነ ያመለከቱት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ “ሚዲያዎች በነካ እጃቸው ስለ ሰለባዎቹም ይተንፍሱ” ሲሉ ጠይቀዋል።
ኦገስት 31/ 2013 የታተመው የጎልጉል ዜና “የኢትዮጵያን ለም መሬት ከተቀራመቱት ኢንቨስተሮች መካካል አንዱ የሆነው የህንዱ ካሩቱሪ ከኢትዮጵያ ለቅቆ የሚወጣበት ጊዜ መቃረቡን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታወቁ። አበዳሪዎችና ባለ አክሲዮኖች ፊታቸውን እንዳዞሩበትም ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ባዶ ዋይታ የሚያሰማው ኢህአዴግ የያዘው አዲስ አቋም ድርጅቱንና ከድርጅቱ ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው የሚባሉትን ሃሳብ ላይ ጥሏል” ሲል መዘገቡ ይታወሳል።
በዚሁ ዘገባ ላይ በቦታው ኢህአዴግና ጭፍሮቹ መካከል ሆነው የተካሄደባቸውን የመሬት ነጠቃ በመቃወምና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ጀብድ ለሰሩት “… በቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም። ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችኋልና ክብር ይሁንላችሁ” ሲሉ አቶ አባንግ ያስተላለፉት መልክትም ከዜናው ጋር ተካትቶ ነበር።
“በእውቀት ላይ የተመረኮዘ፣ በእቅድ የተያዘ ትግል እያካሄድን እንደሆነ በገለጽኩበት ወቅት ካሩቱሪ በኪሳራ ከኢትዮጵያ ምድር እንደሚወጣ ተናግሬ ነበር። አሁን ጉዳዩ ያለው የኢትዮጵያን ድንግል መሬት በሳንቲም የቸበቸቡትና ያስቸበቸቡት የጥቅም ተጋሪዎችና ደላሎችን ለይቶ ለፍርድ የሚቀርቡበትን ስራ መስራቱ ላይ ነው። በህንድ ጥሪያችንን ሰምተው ትግላችንን የተቀላቀሉ ፍትህ ወዳድ እህትና ወንድሞች፣ ምስጋና ይገባቸዋል” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ስለ ካሩቱሪ የተሰማውን ዜና አስመልክተው ተናግረዋል።
ሰንደቅ የተሰኘው ጋዜጣ ዜና ባለስልጣኖችንና የካሩቱሪን ሃላፊ አነጋግሮ ይፋ ያደረገው ዜና ኢህአዴግን የሚያሳፍር ከመሆኑም በላይ ከዝርፊያው በስተጀርባ ያሉትን በሙሉ ያስደነገጠ ሆኗል። የጎልጉል ምንጭ እንደሚሉት የጋምቤላ ድንግል መሬት በሳንቲም ሲቸበቸብ ከጀርባ ሆነው ኮሚሽን የተቀበሉና የሚቀበሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ደላሎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የአገሪቱን ሃብት በዓይነት፣ ገንዘቧን በብድር፣ ወገኖቻቸውን በጥይት እያስደበደቡ ለባዕድ በመስጠት የፈጸሙት ወንጀል መጨረሻ በራሳቸው አንደበት ይፋ ተደርጓል።
የአክሲዮን ሽያጩና የብድር ምንጩ የደረቀበት ካሩቱሪ ንብረቱ ለሃራጅ እንዲቀርብ በዝግጅት ላይ ነው። ሰንደቅ ባይገልጸውም ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ሳዑዲ ስታር በሚባለው የግብርና ተቋማቸው ሰፊ መጠን ያለው መሬት በመውሰድ ህዝብ እንዲፈናቀል ካደረጉት ጋር እንደሚደመሩ በተለያየ ጊዜ የሚጠቆም ነው።
የሰንደቅ ዜና እንዲህ ይነበባል፡-

የህንድ ካራቱሪ ኩባንያ 62 ሚሊዮን ብር የንግድ ባንክን ዕዳን መክፈል አልቻለም

  • ኩባንያው የሠራተኞች ግብር፣ ጡረታ እንዲሁም የክልሉን የመሬት ግብር አልከፈለም
  • ከቀረጥ ነጻ ያስገባቸውን ማሽነሪዎች በማከራየትና በመሸጥ እየተከሰሰ ነው።
  • ከተረከበው 300 ሺ ሔክታር ያለማው 800 ሔክታር ብቻ ነው።
መሠረቱን በጋምቤላ ክልል ያደረገው የህንድ ካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክት ኀ/የተ/የግ/ማህበር በተሰጠው መሬት ላይ የልማት ሥራ ማከናወን አለመቻሉን እንዲሁም የባንክ ብድርና የግብር ግዴታዎቹን እየተወጣ አለመሆኑ ተገለፀ።
አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ የቢዝነስ ዴቭሎፕመንት የስራ ሒደት ባለቤት ስለጉዳዩ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንዳስረዱት “ካራቱሪ ከባንኩ እ.ኤ.አ በዲሴምበር 2011 ወደ 62 ሚሊየን ብር ብድር መውሰዱን አስታውሰው ነገር ግን መክፈል በሚገባው ጊዜ ሊከፍል አለመቻሉን፣ ብድሩንም ለማስታመም የተደረጉ ተጨማሪ ጥረቶች ባለመሳካታቸው ጉዳዩ ወደህግ ክፍል መመራቱን አስታውቀዋል። ባንኩ በአሁኑ ወቅት ይህ ብድር የተበላሸ ወይንም መመለስ የማይችል ነው በሚል ጉዳዩን ይዞት ለማስመለስ ወደ ሕጋዊ እርምጃ መግባቱን” ተናግረዋል።
በተያያዘም በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ከአራት ዓመት በፊት በጋምቤላ ክልል 300ሺ ሄክታር መሬት ለማልማት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር ተዋውሎ የገባው የህንዱ ኩባንያ ካራቱሪ ባለው ደካማ ማኔጅመንት ምክንያት ሥራውን ማከናወን ባለመቻሉ በአሁኑ ወቅት ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።
አቶ አለምሰገድ አያሌው የኩባንያው የምርት መሳሪዎች ዋና ክፍል ኃላፊና የሠራተኞች ተወካይ ለሰንደቅ ጋዜጣ በስልክ እንደገለጹት ኩባንያው 300ሺ ሄክታር ለማልማት ከግብርና ሚኒስቴር መሬት ተረክቦ የነበረ ቢሆንም ባለፉት አምስት አመታት ከ800 ሄክታር በላይ ለማልማት አልቻለም።
ግብርና ሚኒስቴር ይህንኑ ደካማ አፈጻጸም በማየት ከአንድ ዓመት በፊት 200ሺ ሄክታር መሬት የነጠቃቸው መሆኑን አቶ አለምሰገድ አስታውሰው ይህንንም ማልማት ባለመቻላቸው በአሁኑ ወቅት በእጃቸው የሚገኘው መሬት 10ሺ ሄክታር ብቻ ነው ብለዋል። ይህም ሆኖ በአሁኑ ወቅት በበቆሎ ሰብል የተሸፈነው 800 ሄክታር ገደማ ብቻ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
ድርጅቱ 150 ያህል ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዳሉት ያስታወሱት አቶ አለምሰገድ የሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ እስከ 45 ቀናት እንደሚዘገይ፣ ለጡረታና ለግብር ከሰራተኛው የሚሰበሰበው ክፍያ በአግባቡ ለሚመለከተው አካል እንደማይገባ ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል።
የኩባንያው አመራሮች በውጪ ምንዛሪ የሚያስገቡዋቸውን ዘርና ማዳበሪያ በአገር ውስጥ እንደሚሸጡ፣ ከቀረጥ ነጻ ያስገቡዋቸውን ማሽነሪዎች በማከራየትና ለሶስተኛ ወገን በመሸጥ ያልተገባ ጥቅም እንደሚያጋብሱ ተናግረዋል።
ይህንኑ አቤቱታቸውን ለጋምቤላ ክልል የሚመለከታቸው መ/ቤቶች በተደጋጋሚ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።
የጋምቤላ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ጆን ሾል ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው የካራቱሪ የስራ አፈጻጸም እጅግ ደካማ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኩባንያው በተጨማሪም ለወረዳ መክፈል ያለበትን የመሬት ግብር ጭምር እንዳልከፈለ የጠቆሙት አቶ ጆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክም የተበደረውን ባለመክፈሉ ባንኩ በመያዥነት የያዛቸውን ንብረቶች ወደማስከበር ስራ ፊቱን ማዞሩን ጠቁመዋል።
በቅርቡ ከፌዴራል መንግስት ባለሙያዎች ወደቦታው መጥተው ችግሩን አጥንተው መመለሳቸውን ጠቁመው በቅርቡ ኩባንያውን በተመለከተ የመጨረሻ መፍትሔ ሊገኝ እንደሚችል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክት ኃ.የተ.የግ.ማኅበር (ጋምቤላ ኤሊያ አካባቢ) የሥራ ኃላፊዎችን በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

onsdag 2. oktober 2013

Democracy, Tolerance, and G7’s position towards Eritrea

September 27, 2013

by Kirubeal Bekele
On Sunday September 22, 2013, the Ginbot 7 leadership had a very revealing and open discussion in Washington DC meeting like it has never had before. As you know, the issue of working with Eritrea has been a bone in the throat for G7 as well as for its supporters around the world. Many have argued against using Eritrea as a spring board to wage an armed struggle against TPLF.Ginbot 7 leadership had a very revealing and open discussion in Washington DC
Opponents claim that Eritrea cannot be trusted based on their experience with Isayas Afeworki so far and his public rhetoric as it relates to Ethiopia. They may have a point. But the problem is that they don’t practice the position they defend or argue for. They don’t provide an alternative and actually implement that alternative. For example, they don’t answer to the question of where to wage an armed struggle and show us the way by an example. They don’t. Why don’t they find a place within Ethiopia and wage an armed struggle and show us the way? Why don’t they go and practice what they preach like G7 Popular Force instead of simply analyzing and arguing from the comfort of their homes in the West? What they do is simply disagree and sometimes with bitterness and even animosity against G7’s position towards Eritrea.
Instead of making an honest and logical attempt to convince and win support, those who oppose G7′s position in Eritrea use intimidation, name callings, insults, put downs and innuendos to impose their opinion on G7 and its supporters. But the irony is that these forces claim to believe and fight for democracy in Ethiopia and yet they forcefully impose their position on others. G7 has repeatedly expressed the right of any political entity to follow a path it believes in without imposing its policy or belief on any one else except asking their support. G7 has often made clear that it does not oppose other political parties who pursue a political path different than its own. It is interesting whether we know how to win support with a clean and convincing argument backed by results on the ground instead of using endless spurious arguments and worse innuendos and name callings.
Those who oppose G7 are not all in the same wave length. One group is of course the enemy. Pro-TPLF mercenaries like Awramba Times editor and TPLF dogs are barking against G7 simply to accomplish their paid assignments. It is their duty. There is no surprise there. They are part of the package. There is a second group that questions and suspects a multi-national political force like G7 for fear of revenge by TPLF victims in the form of genocide or a lesser nationwide violence. This group has a legitimate fear.
But opposing such a political force like G7, or any other multi-national force for that matter, is not a solution to their fear. On the contrary, a force such as G7 that has created an alliance with Tigray People Democratic Movement (TPDM), if strengthened, may help stabilize the country by preventing a possible chaos and ethnic violence in Ethiopia when TPLF collapses. But there are some in this group who may have their own ax to grind who dream to preserve the ethnic hegemony of the status quo by reforming TPLF one way or another. And they strongly oppose the emergence of a formidable multi-national party or organization like G7 or any other multi-national party or group. They support and are comfortable working with a passive resistance movement(s) and if possible lead it (them) or high jack its (their) leadership. They infiltrate these types of do-nothing organizations and use them as their handy tool to wage their smear campaign and propaganda against G7 and anything related to it.
There is a third group. These are political organizations that are contemplating and competing for power in Ethiopia after TPLF. They believe that if they don’t cook the dish, it will never taste good. They want power at any cost and by any means. They are ego-driven and uncompromising, full of intrigues and back stabbing. Nothing satisfies them until they are in charge. They oppose everything any opponent does. They deliberately or honestly believe that truth is on their side. Compromise or giving a chance to others wounds their ego. If something is successful and they are not a part of it, by chance or by design, they want no part of it. And they will oppose it. That is why we see people and even organizations that have the audacity to oppose ESAT some openly and a few in silence. This hurts their ambitions and their life long political journey for fame and fortune extinguishing their chances to positions of power in Ethiopia. And they don’t like it a bit.
There is one final group which I consider innocent but suspicious. This is the vast majority that is mostly patriotic that should be handled with care. They have no ax to grind except to see Ethiopia free. It is critical that they should be convinced to make a difference. Our story with Eritrea is full of suspicions and actual heart-breaking experiences due to the war waged between Ethiopia and Eritrea for over 40 years now. This group doesn’t trust anything related to Eritrea no matter who said what including God. It has a legitimate concern but suspicion should not tie our hands and prevent us from doing what needs to be done. Our situation today is desperate. TPLF has done and still doing all it can to destroy our people and country.
This suspicious group should know that there are times in life when you have to do what you got to do to get out of a rock and hard place by swallowing our pride and controlling our suspicion. There is a saying in our country,”ቀን እስኪአልፍልህ የአባትህ ባርያ ይግዛህ” that sums it up. This group has to be convinced that there is no alternative except to give the policy of using Eritrea as staging platform to deal with TPLF. This is the group Ato Andargachew Tsige specifically addressed asking them to give G7 a chance while holding its suspicions.
We have been spinning our wheels for over 22 years while TPLF is in power. We have left no stone unturned in this struggle for freedom and democracy in Ethiopia. We have been there and we have done that all we can. Nothing happened. Zilch. Twenty two years is too long for doing the same thing for the same problem over and over again. It is time to take a risk or two and test a different path. TPLF has been working hard to negotiate with Eritrea for years. It has tried 37 times to get a deal from Isayas. And not so long ago, TPLF has even offered free electricity to Eritrea when the ‘dream’ Dam is completed. Three weeks ago, Ethiopia’s outgoing president said he wants to go to Eritrea and negotiate on an individual bases without representing his government. All these furious activities by TPLF should ring a bell in our brains. They know Eritrea is the only option left for the opposition to launch a meaningful offensive against it. Not exploring to use the Eritrean option, despite its problems, is very troublesome to say the least, especially when no alternative has been found for the last 22 years.
At this point, all of us have one universal enemy. And we have to focus on it. And that is TPLF. And it is wise to postpone and talk about our differences after we free Ethiopia from TPLF at any cost and by any means necessary. Now, we don’t have the privilege or the time to go against each other’s throat. We simply can’t afford it.
The G7 leadership has directly presented the question in a ‘take it or leave it’ manner to the audience and to the Diaspora watching on ESAT. Ato Andargachew Tsige, secretary of G7, has explained in detail about the Eritrean question during the meeting. It may be hard to tell if everybody is convinced. With all their suspicions remaining, there is no doubt many may be considering to give G7′s policy on Eritrea a chance, if it has any possibility of working, given the dire and critical circumstances Ethiopia has found itself at this time.
There is no sure thing in life as well as in struggle. You take chances and you take risks. Not a blind risk but a pragmatic one based on the circumstances you found yourself boxed in. Not taking that risk, no matter how difficult, is committing suicide. You put all your options on the table. And you pick the one with the least risk. And then you move on. And if not, the choice is to get stuck in some meaningless and fruitless activity and continue to waste time, money and even lives for nothing and finally give up and be forgotten. G7 seems to have made a decision to take the least risky option, according to Ato Andargachew Tsige, and is pursuing it with resolve.
We should permit and even provide whatever support we can to G7 while we are trying our own. If we can’t do this, then the easiest and smartest thing to do is to get the hell out of the way. G7 or any other organization doesn’t need the approval or the blessing of others to pursue its objective. Every organization has its own organizational independence. Unless we are supporting it financially as well as in other ways, we are in no position to force it change its policy. Let G7 pay for its own destiny even if the result along the way confirms our suspicions. Democracy includes the right of an individual or any organizational entity to make its own mistakes and hopefully learn from them. G7 has that right. So does every other organization.
And for those of us with an opposing view, let us do what we believe in without encroaching our position on G7 and its policy towards Eritrea. According to Ato Andargachew Tsige, G7 is not forcing its position upon any person or political entity. He said they don’t oppose the positions other political organizations are taking when it comes to Eritrea.
The take home message is that, we in the opposition camp should all follow our individual political choices in our quest to remove TPLF from power. There is no need to vehemently be involved in slash and burn campaign against a position we don’t agree on. No one party or person has the monopoly on the truth of what works best to bring TPLF down. The only way to establish that truth will be based on the results of a given policy on the ground. And let us all give G7 a chance, with patience and a grain of salt, to see what works with our suspicions still intact. As long as G7 is an anti-TPLF force, we should tolerate the alternative path it is taking at its own risk even if we don’t agree to it. In the final analysis, the vast majority of Ethiopians are patriotic at heart and are dreaming day and night for TPLF to go away, once and for all, out of their lives and out of their beloved country at any cost and by any means necessary. Now!